ደቀ መዝሙርነት እና ግቡ PDF
Document Details
Uploaded by ExquisiteBanshee
Tags
Summary
ይህ ሰነድ ስለ ደቀ መዝሙርነት እና ግቡ በአማርኛ ይገልፃል። በተጨማሪም ስለ ቅድስና እና ስለ ደቀ መዝሙርነት በመጽሐፍ ቅዱሳዊ አተያይ ይገልፃል። እንዲሁም በአምላክ እና በሰዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ያጎላል።
Full Transcript
ደቀ መዝሙርነት እና ግቡ በአስቻለው ኮራ ለናዝሬት አማኑኤል አገልጋዮች ሰኔ 22/2016 ዓ.ም 1. የማሰላሰያ ጥያቄዎች አንዴ በክርስቶስ ስለ ጸደቅን ዳግም ስለ ደቀ መዝሙርነት መማር አለብን ወይ? መቀደስስ ያስፈልጋል ወይ? ጸጋ ስለበዛልን ምንም ዓይነት ኃጢአት ብንሰራ እንጠየቃለን ወይ? ካልሆነ ደቀ መዝሙር መሆን ምን ጥቅም አለው? በክርስቶስ ከጸደቅን ስለ ደቀ መዝሙርነት መማርና ማስተማር ሕግን ማ...
ደቀ መዝሙርነት እና ግቡ በአስቻለው ኮራ ለናዝሬት አማኑኤል አገልጋዮች ሰኔ 22/2016 ዓ.ም 1. የማሰላሰያ ጥያቄዎች አንዴ በክርስቶስ ስለ ጸደቅን ዳግም ስለ ደቀ መዝሙርነት መማር አለብን ወይ? መቀደስስ ያስፈልጋል ወይ? ጸጋ ስለበዛልን ምንም ዓይነት ኃጢአት ብንሰራ እንጠየቃለን ወይ? ካልሆነ ደቀ መዝሙር መሆን ምን ጥቅም አለው? በክርስቶስ ከጸደቅን ስለ ደቀ መዝሙርነት መማርና ማስተማር ሕግን ማስተማር ነው ወይ? ደቀ መዝሙርነት ለአማኝ ያለው ጥቅም ምንድነው?- በምድር እና በሰማይ የኃጢአት አስፈሪነት እና አደጋው በአማኝ ሕይወት ምንድ ነው? የኃጢአት መንገድ አስፋፊ ትምህርቶች ምንድ ናቸው የኃጢአት ማሸነፊያ መጽሀፍ ቅዱሳዊ መንገዶች ምንድናቸው? የቅድስና ሽልማቶች/ብድራቶች ምንድናቸው? 2. ደቀ መዝሙርነት ማለት 3. መከተል 4. ታላቁ ተልዕኮ “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።” ማት 28፡19-20 4.1. የታላቁ ተልዕኮ ይዘቶች 1. ሰዎች እንዲድኑ- ሂዱ 2. ክርስቲያናዊ ኑሮ እንዲኖሩ- ደቀ መዛሙርት አድርጉአቸው። 4.2. ትርጓሜ ደቀ መዝሙር፡ተማሪ፤ መምህሩ ወደሚመራው ሁሉ ምንም ዋጋ ቢያስከትልም ወዶ የሚከተል ማለት ነው። “ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል።” ዮሀ 15፡8 ደቀ መዝሙርነት 1. የደቀ መዝመሪነት ጥሪ “እርሱም፦ በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው።” ማት 4፡19 2. ደቀ መዝሙርነት የሚያስከፍለን ዋጋ “እነርሱም፦ እንችላለን አሉት። ኢየሱስም፦ እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ፥ እኔ የምጠመቀውንም ጥምቀት ትጠመቃላችሁ፤” ማር 10፡39 3. የደቀ መዝሙርነት ብድራት/ክፍያ “ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።” ዮሀ 10፡10 የደቀ መዝሙርነት ግብ 1. ክርስቶስን መምሰል 2. የክርስቶስን መንግስትና አገዛዝ በምድር ላይ መግለጥ- ፍቅሩን ለሰው ሁሉ ማዳረስ 3. ሌሎች ደቀ መዛሙርትን ማፍራት 4. ታላቁን ተልዕኮ እና የተፈጠርንብትን ዓላማ መፈጸም “እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሠጽን ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው፤” ቆላ 1፡29 ማነው ደቀ መዝሙር አድራጊ? 1. በእግዚአብሄር ጸጋ የሚደገፍ ማንም ትሁት ክርስቲያን ደቀ መዝሙር ማፍራት ይችላል። 2. ሌሎችን ደቀ መዛሙርት ለማድረግ በአንድ እርምጃ ቀዳሚ የሆነ ሁሉ ተከታዩን ደቀ መዝሙር ማድረግ ይችላል 3. ደቀመዝሙር ለመሆን፦ ታማኝ መሆን፤ ለጌታ የሚገኝ እንዲሁም ለመማር የተዘጋጀ ልብ ካለ በቂ ነው የደቀ መዝሙር አድራጊ ባህሪያት I. የሚያበረታታ VI. አብልጦ የሚያፈቅር II. የሚገነባ VII. በሰላም የሚኖር III. የሚያደንቅ VIII. የሚገስጽ IV. የሚተጋ IX. የሚደግፍ V. መመሪያ የሚሰጥ “ስለዚህ እናንተ ደግሞ እንደምታደርጉ፥ እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ አንዱም አንዱም ሌላውን ያንጸው። ወንድሞች ሆይ፥ በመካከላችሁ የሚደክሙትን በጌታም የሚገዙአችሁን የሚገሥጹአችሁንም ታውቁ ዘንድ፥ ስለ ሥራቸውም በፍቅር ከመጠን ይልቅ ታከብሩአቸው ዘንድ እንለምናችኋለን። እርስ በርሳችሁ በሰላም ሁኑ። ወንድሞች ሆይ፥ እንመክራችኋለን፤ ያለ ሥርዓት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤ ድፍረት የሌላቸውን አጽኑአቸው፤ ለደካሞች ትጉላቸው፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ።” 1ተሴ 5፡11-14 የቀደ መዝሙርነት ደረጃዎች የዘመናችን የደቀ መዝሙርነት ፈተናዎች የሰው ሕይወት ተኮር ያልሆኑ ስነ-መለኮታዊ ክርክሮች ውስብስብና ብሮክራቲክ የሆኑ የቤተ ክርስቲያን ፕሮግራሞች እና ፕሮጀክቶች በጣም የበዙ እና የሰፉ የቤተ ክርስቲያን መዋቅር የራሱ ላባ እንደከበደው ንስር መብረር አለመቻል የሸማችነት(አማራጭነ) ዝንባለ ፈተና፡ ቤተክርስቲያንን ስብከት፤ አምልኮ ዘይቤ መሰረት በማድረግ እንደ ሸቀጥ መምረጥ ፡የኃይማኖተ ነጻነት የተሳሰተ የጸጋ ትምህርት (ይሁ 1፡4) የተሳሰተ የሰው ማንነት ትምህርት (1 ዮሀ 4፡1-4) የተሳሳተ ትምሀርት ስለ ሙታን ትንሳዔ (2ጢሞ 2፡15-19) የተሳሳተ የፍልስፍና ትምህርት (ሐዋ 17፡17-19) የተሳሳተ የድኅነት ትምህርት (ራዕ 2፡12-17) የደቀ መዝሙርነት አምዶች በእምነት ማደግ በማንበብ እና የፍቅር ተነሳሽነት በመሰጠት ማደግ በአስተሳሰብ ማደግ ባለ አደራነት በአምልኮ እና በግንኙነት ማደግ በጸሎት ጽናት በአገልግሎት ማደግ ጊዜን በአግባቡ መጠቀም (2ጴጥ 1፡2-11፤ 1ጢሞ 6፡12-16፤ማት 16፡24-27) የደቀ መዝሙርነት መሰረታዊያን 1. የእግዚአብሄር ቃል - መማር፤ ማሰብ 2. የመንፈስ ቅዱስ አሰራር በሕይወታችን 3. መስቀል መሸከም 4. ጸሎት 5. የእግዚአብሄር ፍቅር እግዚአብሄርን መምሰል “ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤” ሮሜ 8፡27 ስለ ቅድስና እና ስለ ደቀ መዝሙርነት የእግዚአብሄር ቃል ምን ይላል? ተቀደሱ “ዳሩ ግን፦ እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።” 1ጴጥ 1፡15-16 ተግባራዊ የሆነ የህይወት ለውጥ ማምጣትና በቃሉ መሰረት ተለይቶ መኖር ተቀደሱ “የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።” 1 ተሰ 5፡23 “አሁን ግን ከኃጢአት አርነት ወጥታችሁ ለእግዚአብሔርም ተገዝታችሁ፥ልትቀደሱ ፍሬ አላችሁ፤ መጨረሻውም የዘላለም ሕይወት ነው።” ሮሜ 6፡22 ተቀደሱ “ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና።” ዕብ 12፡14 “ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና፤” 1ተሰ 4፡3 ተቀደሱ “ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።ይህን በሙሉ ሥልጣን ተናገርና ምከር ገሥጽም፤ ማንም አይናቅህ።” ቲቶ 2፡11-14 ተቀደሱ “በዚያም ጐዳናና መንገድ ይሆናል እርሱም የተቀደሰ መንገድ ይባላል፤ ንጹሐንም ያልሆኑ አያልፉበትም፥ ለንጹሐን ግን ይሆናል፤ ተላላፊዎችና ሰነፎች እንኳ አይስቱበትም።አንበሳም አይኖርበትም፥ ነጣቂ አውሬም አይወጣበትም፥ ከዚያም አይገኙም፤ የዳኑት ግን በዚያ ይሄዳሉ፤ እግዚአብሔርም የተቤዣቸው ይመለሳሉ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይመጣሉ፤ የዘላለም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ሐሤትንና ደስታን ያገኛሉ፥ ኀዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።” ኢሳ 35፡8-10 ተቀደሱ “ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆችዋም ወደ ከተማይቱም እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብዘዓን ናቸው።ውሻዎችና አስማተኞች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትንም የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።” ራዕ 22፡14-15 ቅድስና- የክብር መንገድ የጸደቀ ወደ ጌታ ይቀርባል (ኤፌ 2፡13) ወደ ጌታ የቀረበ ይቀደሳል (ሮሜ 5፡10) የተቀደሰ ይከብራል (2ቆሮ 3፡18) “አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው።” ሮሜ 8፡20 ቅድስና በዚህ ዓለምም በሚመጣ ዓለምም ይጠቅማል “ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።”1ጢሞ 4፡8 የቅድስና ዓይነቶችና ደረጃዎች ዓይነት ትርጉም አፈጻጸም ጥቅስ መጽደቅ የተቆጠረልን ቅድስና ወዲያው በድነት ጊዜ የሚፈጸም ሮሜ 5፡9-10 (Justification) (Imputed Righteouseness) (Positional Holiness) ኤፌ 2፡1-8 ዮሀ 1፡12 መቅረብ በጽድቅ ምክንያት ራስን ወደ ጌታ በፈቃድኝነት የዳነ ሰው በሂደት ሮሜ 6፡13 (Consecration) እና ወደ ጸጋው ዙፋን ማቅረብ የሚፈጽሜው ሮሜ 12፡1-2፡ ዕብ 4፡14- (Consecratative Holiness) (Presentational Holiness) 16 መቀደስ የተካፈልነው ሕይወት በኑሮ ስገለጥ በሕይወትመንፈስ ሕግ 2ጴጥ 1፡2-8 ሮሜ 8፡1-8 (Sanctification) (Imparted Righteousness) በመመላለስ በሂደት የሚፈጸም ገላ 5፡16 (Progressive Holiness) መክበር የቅድስና ሕይወት ውጤት በቅድስና ስንመላለስ በሂደት ሮሜ 8፡28 (Glorification) (Godliness) የሚገኝ ውጤት 2ቆሮ 3፡18 (Progressive Result of መዝ 19፡1-4 Holiness) መጽደቅ- የአቆጣጠር ቅድስና- መጽደቅ/ከወንጀል ፍርድ ነጻ መሆን/ከክስ ነጻ መሆን(Justification/Righteousness/Right Stand With God) ማለት ፦ ቅዱስ/እንከን አልባ በሆነው በእግዚአብሄር ፊት ከሕጉ አንጻር (የሕልና ይሁን የተጻፈ ሕግ) ጥፋተኛ የሆነ ሰው የጥፋቱ ቅጣት/ካሳ/ቤዛ ከፍሎ ወይም ተከፍሎለት፤ ዕዳው በመነሳቱ/በመከፈሉ ምክንያት ጥፋተኛ የሆነው አካል ነጻ/ወንጀል አልባ ተብሎ ሲቆጠር/ሲጠራ ያ ሂደት መጽደቅ፤ ሰውየው ጻድቅ ፤ ተግባሩ ጽድቅ ተብሎ ይጠራል በመጽደቅ ውስጥ ያሉት ሂደቶች 1. ልክነትን የሚዳኝ ሕግ መኖር አለበት (ሮሜ 5፡12) 2. ዳኛ መኖር (ኢሳ 33፡22) 3. ሕግ አድራጊ/ጠባቂ መኖር (ዘጸ 19፡4-6) 4. ሕግ ከተጠበቀ- ጽድቅ ይሆናል 5. ሕግ ከተጣሰ- ኃጢአት ይሆናል 6. የኃጢአት ዕዳው/ቤዛ ከተከፈለ ጽድቅ እንደገና ይገባል/ይቆጠራል። በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ 1. ልክነትን የሚዳኝ ሕግ መኖር- የጌታ ቃል 2. ዳኛ መኖር- ጌታ እራሱ 3. ሕግ አድራጊ/ጠባቂ መኖር- የሰው ልጆች 4. ሕግ ከተጠበቀ- ጽድቅ ይሆናል- በቃሉ ይፈረዳል 5. ሕግ ከተጣሰ- ኃጢአት ይሆናል- በቃሉ ይፈረዳል 6. የኃጢአት ዕዳው/በዛ ከተከፈለ ጽድቅ እንደገና ይገባል/ይቆጠራል። -በኢየሱስ ደም ቤዛነት ዳግም ጽደቅ ተሰራልን በመሆኑም 1. ጌታ ለሰው ልጆች ሁሉ የሕልና ፤ ለእስራኤል የተጻፈ ሕግ ሰጥቷል። “ያለ ሕግ ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ ያለ ሕግ ደግሞ ይጠፋሉና፤ ሕግም ሳላቸው ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ በሕግ ይፈረድባቸዋል፤... ሕግ የሌላቸው አሕዛብ ከባሕርያቸው የሕግን ትእዛዝ ሲያደርጉ፥ እነዚያ ሕግ ባይኖራቸው እንኳ ለራሳቸው ሕግ ናቸውና፤ እነርሱም ሕሊናቸው ሲመሰክርላቸው፥ አሳባቸውም እርስ በርሳቸው ሲካሰስ ወይም ሲያመካኝ በልባቸው የተጻፈውን የሕግ ሥራ ያሳያሉ።” ሮሜ 2፡12-15 በመሆኑም 2. በሕጉ መሰረት ሁሉም ኃጢአተኛ ሆነው ተገኝተዋል “ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤ ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና።... ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤” ሮሜ 3፡20- 23 “እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦ ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ፤ አስተዋይም የለም፤ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ የለም፤ ሁሉ ተሳስተዋል፥በአንድነትም የማይጠቅሙ ሆነዋል፤ ቸርነት የሚያደርግ የለም፥ አንድ ስንኳ የለም።” ሮሜ 3፡ 10-12 በመሆኑም 3. በኃጢአት ምክንያት የእግዚአብሄር ፍርድ፤ ቁጣ በላችን ላይ ሆነ። “በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ ሁላችን ደግሞ፥ የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን፥ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን እንደ ሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን።” ኤፌ 2፡2 “እውነትን በዓመፃ በሚከለክሉ ሰዎች በኃጢአተኝነታቸውና በዓመፃቸው ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቍጣ ከሰማይ ይገለጣልና፤” ሮሜ 1፡18 በመሆኑም 4. ከመካከላችን ቤዛ ሆኖ የሚያድነን አንድም አልተገኘም። “ተመለከትሁ፥ የሚረዳም አልተገኘም፤ የሚያግዝም አልነበረምና ተደነቅሁ፤ ስለዚህ የገዛ ክንዴ መድኃኒት አመጣልኝ፥ ቍጣዬም እርሱ አገዘኝ።” ኢሳ 63፡5 “ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፥ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፤” 1ጢሞ 2፡6 “እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።” ዮሀ 1፡29 በመሆኑም 5. እግዚአብሄር ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛችን አድርጎ ላከልን። “ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤” ገላ 4፡4 “እኛም አይተናል አባትም ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን እንደ ላከው እንመሰክራለን።” 1ዮሃ 4፡14 በመሆኑም 6. ሁላችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት የተነሳ ዳግም በጌታ ፊት መጽደቅ ቻልን “ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን። ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤” ሮሜ 5፡9-10 1. የተቆጠረልን ጽድቅ(Imputed Righteousness) ይህ በክርስቶስ ሥራና ደም ያገኘነው ጽድቅ የተቆጠረልን ጽድቅ ነው እንጅ እኛ ለፍተን ያመጣነው ጽድቅ አይደልም። ከክርስቶስ ደም የተነሳ የኃጢአት ስርየት አገኘን ስርየት ስላገኘን አብ ፊት ጻድቅ ሆነን ታየን ስለጸደቅን አብ ፊት ምግባትን አገኘን መቅረብና መግባት ስለቻልን ወደ ጽጋው ዙፋን መድረስ ቻልን ከጸጋው የተነሳ መቀደስም እንችላለን። የተቆጠረልን ጽድቅ “ወይስ ዓመኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል።” 1 ቆሮ 6፡9-11 የተቆጠረልን ጽድቅ የተቆጠረልኝ ጽድቅ በክርስቶስ ያገኘሁትን ቦታዬን ነው የሚናገረው እንጅ ተግባረን አይደልም የሚያሳየው። የተቆጠረልኝ ጽድቅ/ቅድስና ስጦታ ነው እንጅ የልፋት ውጤት አይደለም። “በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል።” ዕብ 10፡10 “በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።” ዮሀ 3፡36 የተቆጠረልን ጽድቅ እግዚአብሄር ስለ እኛ ያለውን አመለካከትና አቆጣጠር ነው የሚቀይረው እንጂ ባህሪያችንን፤ ጸባያችንን እና አካሄዳችንን አይደልም የሚቀይረው። “እንግዲህ ፈጽሞ የእርስ በርስ ሙግት እንዳለባችሁ በእናንተ ጉድለት ነው። ብትበደሉ አይሻልምን? ብትታለሉስ አይሻልምን? ነገር ግን እናንተ ትበድላላችሁ ታታልሉማላችሁ፥ያውም ወንድሞቻችሁን።”1ቆሮ 6፡7-8 ጽድቅ የድነታችን መጀመሪያ እና መግቢያችን ነው የጸደቀ ሁሉ በአዲስ ሕይወት ሊመላለስ ይገባዋል። “ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤” ሮሜ 5፡10 “እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን።” ሮሜ 6፡4 2. ራስን የማቅረብ ቅድስና(Presentational Holiness) “እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።” ሮሜ 12፡1 “ብልቶቻችሁንም የዓመፃ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፥ ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ በሕይወት እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፥ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።” ሮሜ 6፡13 ራስን የማቅረብ ቅድስና በአማኝ በፈቃደኝነት የሚከናወን ተግባር ነው በሂደት ከመጽደቅ እስከ መክበር የሚቀጥል ነው። ምርጫ ነው በእግዚአብሄር ምህረት ላይ የቆሜ ነው በዚህ ደረጃ ራስ ማቅረብ የሚነግረን ስለ ፍላጎታችንና ስለ ፈቃደኝነታችን ነው ። “እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን፥” ዕብ 10፡19-20 መቅረብ “እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።” ዕብ 4፡16 “በእርሱም ዘንድ ባለ እምነታችን በኩል በመታመን ድፍረትና መግባት በእርሱ አለን።”ኤፌ 3፡12 “ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።” ዕብ 7፡25 3. መቀደስ (Sanctification)- የተካፈልነው ቅድስና/Imparted Righteousness መቀደስ ማለት፦ በአዲስ ሕይወት መመላለስ (ሮሜ 6፡4)/ እግዚአብሄር መምሰል(1ጢሞ 4፡8)/ በመንፈስ መመላለስ (ሮሜ 8፡1-2)/ ተግባራዊ የህይወት ለውጥ እና አካሄድ (ኤፌ 4፡17-32) ማለት ነው። የለውጡ መነሻ ከተካፈልነው አዲስ ሕይወት የሚጀምር (2ጴጥ 1፡2-3) ነው እንጅ ከሰው ጥረት እና ልፋት የሚጀምር አይደልም። መቀደስ “የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን።” 2 ጴጥ 1፡2-4 2 ጴጥ 1፡2-4 ስብራራ 1. የተጠራነው በመለኮት ኃይሉ፤ በጌታ የገዛ ክብሩ እና በበጎነቱ ነው።(ኤፌ 2፡4) 2. ከጠራን በኋላ ለሕይወትና እግዚአብሄርን ለመምሰል የሚሆነን ነገር ሁሉ ሰጥቶናል፤ ከመለኮት ባህሪ ተካፋዮችም አድርጎናል። 3. በዳግም ልደት ሁሉን ከተቀበልን በኋላ በጌታ ጸጋ እና ዕውቀት ማደግ ይጠበቅብናል። 4. ውጤቱም በዓለም ካለው ጥፋት ማምለጥ፡ እጅግ የከበረ ተስፋ መውረስ ነው። በቅደስና ሕይወት ውስጥ የጌታ እና የእኛ ድርሻ 1. የጌታ ድርሻ፡ እና በክርስቶስ ሞት ዳግም መፍጠር፤ አዲስ ሕይወት ማካፈል፤ የእግዚአብሄር ልጆች እኛን ማድረግ።(ያዕ 1፡18፤ 2ቆሮ 5፡17፤ ዮሀ 10፡10) 2. የእኛ ድርሻ፡- ትጋትን ሁሉ እያሳየን በቃሉ፤ በመንፈሱ እና በደሙ የተካፈልነው ሕይወት ክብር/ውበት መግለጥ (2ጴጥ 1፡5፡9፤1ጢሞ 4፡8) በመሆኑም ከተካፈልነው መለኮታዊ ባህሪ በመነሳት፤ በሕይወት እየበዛን (ዮሀ 10፡10)፤ እግዚአብሄርን እየመሰልን (1ጢሞ 3፡14-16፤ 4፡8፤ 2ጴጥ 1፡6-7) መኖር፤ መመላለስ ይጠበቅብናል። ይህም ከእኛ በምጠበቅ ትጋት የሚከተሉትን የህይወት ለውጦች ማግኘት እንችላለን። የቅድስና ሕይወት መገለጫዎች እምነት መጽናት በጎነት እግዚአብሄር መምሰል ዕውቀት የወንድማማች መዋደድ ራስ መግዛት ፍቅር ውጤቱም ሥራ ፈት አንሆንም ፍሬ ቢስ አንሆንም የተጠራነው፦ ሠራተኛ ለመሆንና ፍሬ ለማፍረት ነውና (ማት 20፡1-2፤ ዮሀ 15፡16) ካልተቀደስን ውጤቱ ዕውርነት- ርስታችንና ክብራችንን ማየት አለመቻል የቅርቡ ብቻ ተመለረካች- ምድራዊ ሕይወት ተኮር የቀደመው ሐጢአት ለምን ይቅር እንደተባለልን ያልገባን፤ በመንገድ የምንቀር ነን። ያልተፈጸመ ድኅነት ይሆናል። “ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤” ፊል 2፡12 እና ምን እናድርግ “ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና።” 2ጴጥ 1፡10 ውጤቱ “እንዲሁ ወደ ዘላለሙ ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችኋልና።” 2ጴጥ 1፡11 የቅድስና ጎዳና 1. የቅድስና ኑሮን ከሥጋ /ከራስ ጥረት አትጀምር፤ በራስ ጥረት የጌታን ሕግ ለመጠበቅ እና ለመፈጸም አትምክር (ሮሜ 7፡15-24) 2. አዲስ ኑሮ ለመኖር ከአዲሱ ሕይወታችን፤ ከተካፈለነው ሕይወት ለመኖር እንጀምር (ሮሜ 8፡ 1- 4፡ ኤፈ 4፡16-20፤ ገላ 5፡16-20) 3. የሕይወት ለውጥ የምኞች ወይም የሰው ጥረት ውጤት ሳይሆን የሚገዛን መንፈሳዊ ሕግ ውጤት እንደሆነ መረዳት (ሮሜ 8፡1-2፤ አስ 8፡3-8) የቅድስና ጎዳና 4. ሁለት መንፈሳዊ ሕጎች - የሕይወት መንፈስ ሕግና የሞትና የሐጢአት ሕግ በእኛ ውስጥ እንደሚሰራ መረዳት (ሮሜ 7፡23-24፤ 8፡1-2 ) 5. ሁለቱ ሕጎች የሚንቀሳቀሱበትን አሰራር መረዳት (ሮሜ 8፡4-8) 6. የህይወት መንፈስ ሕግ የሚሰራባቸው፤ የሚንቀሳቀስባቸው መንገዶችን መረዳት እና ማሰራት/ማንቀሳቀስ (ሮሜ 8፡1-39) የሕይወት መንፈስ ሕግ አስራር 1. ሀሳብ፡ የጌታን ቃል ማሰብ(ሮሜ 8፡4-8፤ፊል4፡8-9፤ ኢያ 1፡9-10) 2. መንፈስ ቅዱስ (በእኛ ዘንድ፤ በእኛ ውስጥ፤ የትንሳዔ መንፈስ፤ የልጅነት መንፈስ) (ሮሜ 8፡9- 16) 3. ከክርስቶስ ጋር በመከራው መካፈል (ሮሜ 8፡17-25) 4. በጸሎት (ሮሜ 8፡26-27) 5. የጌታን ፍቅር መረዳት እና ጌታን በመውደድ (ሮሜ 8፤28-39) የደቀመዝሙርነት ፈተናዎች 1. የኃጢአት ምኞች/ፈተና (Temeptation) “ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።” 1ቆሮ 10፡13 የኃጢአት ፈተና “ማንም ሲፈተን፦ በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም። ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል።ከዚህ በኋላ ምኞት ንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች፤ ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።” ያዕ 1፡13-15 የኃጢአት ፈተና አደገኛነት 1. ኃጢአት ጊዜያው ደስታ / እርካታ አለው “ከግብፅም ብዙ ገንዘብ ይልቅ ስለ ክርስቶስ መነቀፍ እጅግ የሚበልጥ ባለ ጠግነት እንዲሆን አስቦአልና ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ፤ ብድራቱን ትኵር ብሎ ተመልክቶአልና።” ዕብ 11፡25 ውጤቱ 2. ሞት ነው “የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።” ሮሜ 6፡23 ድሮም ዛሬም ወደ ፊትም የኃጢአት ደመዎዝ ሞት ነው!!!!!! የኃጢአት ፈተና ምንጭ ምንጩ ከውስጥ በሆነ ክፉ ምኞት/ሀሳብ ነው “ማንም ሲፈተን፦ በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም።” ያዕ 1፡13 “በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በብልቶቻችሁ ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን?” ያዕ 4፡1 የኃጢአት ፈተና ደረጃዎች እና መፊትሄዎች ሀሳብ/ፍላጎት - ቃሉን በጉዳዩ ላይ ማሰብ፤መጸለይ ዕድል/አጋጣም -በቃሉ ክፉን ሀሳብ መቃወም/መሻር መሳብ- መሸሽ፤ መጸለይ ክፉ ምኞትን መጸነስ- መሸሽ፤ ፥መቃወም፡ መጸለይ የምኞት በተግባር መወለድ- መሸሽ፤ በንስሀ መመለስ የተግባር ማደግ/ባህሪያችን መሆን- በንስሀ መመለስ፤ መተው፤ ተግባር መቀየር/መተው ሞት- ንስሀ፤ መመለስ፤ መተው የቅድስና ብድራቶች 1. ለበጉ ሰርግ ብቁ ሆኖ ለመገኘት (ማት 22፡1-14፤ ራዕ 19፡7-9፤ ራዕ 3፡1-6፤ ኤፌ 5፡26) 2. ወደ እግዚአብሄር መንግስት በሙላት መግባት (2 ጴጥ 1፡11፤ ማት 16፡24-27፤ 1ቆሮ 15፡35-42፤ 1ቆሮ 3፡10-15)\ 3. የልጅነት እና የዘላለም ክብራችንን በሙላት ለመግለጥ (2ጢሞ 2፡10፤ መዝ 19፡1-4፤ ማት 5፡13-16፤) 4. ከኃጢአት ባርነት ነጻ ሆኖ በምድር ላይ ለመኖር (ቲቶ 2፡11-14) የኃጢአት እና የኃጢአተኝነት ውጤቶች 1. እፍረት (ዘፍ 3፡10፤ኢሳ 59፡8) 2. ጥፋት/መጎዳት (ምሳ 11፡3፤ 13፡13፤ ) 3. በሽታ፤ ደዌ፤ ድካም (ምሳ 14፡30፤ ዘዳ 28፡15-68) 4. የሰላም እጦት (2ዜና 15፡3-6፤ ) 5. ሞት (ሮሜ 6፡23፤ ኤፌ 2፡1-4) መደምደሚያ የኃጢአት ደመዎዝ ሁል ጊዜ ሞት ነው! “ወይስ ዓመኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ፤ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።” 1ቆሮ 6፡9-10