ዐፄ ቴዎድሮስ እና የኢትዮጵያ አንድነት PDF

Summary

This document is an excerpt from a historical analysis of Emperor Theodore II's reign and the historical period known as the Zemene Mesafint in Ethiopia. It details the emperor's role in uniting the nation and his efforts to resist foreign powers and achieve national unity. This excerpt highlights the historical context and challenges of the period, including internal conflicts and external threats.

Full Transcript

# ዐፄ ቴዎድሮስ እና የኢትዮጵያ አንድነት ## ተክለ ጻድቅ መኵሪያ ### ማስተዋወቂያ ዐፄ ቴዎድሮስ የተነሡበት የታሪክ ወቅት ለቅርቡ ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ ቁልፍ የሆነ መነሻነት አለው። በአንድ በኩል በአፍሪካና በእስያ ሕዝቦች ላይ ኃያል ተጽዕኖ ለማድረግ በዘመናዊ ኢንዱስትሪና ድርጅት ታጥቆ የተነሣውን የምዕራብ አውሮፓን የቅኝ አገዛዝ ኃይል በብቸኝነት መክቶና ተቋቁሞ የኢትዮጵያን ነጻነት ለማቆዬት የተቻለበት ረዥም ፥ መሪርና አኩሪ ታሪካችን መመዝገብ የጀመረው ቀደም...

# ዐፄ ቴዎድሮስ እና የኢትዮጵያ አንድነት ## ተክለ ጻድቅ መኵሪያ ### ማስተዋወቂያ ዐፄ ቴዎድሮስ የተነሡበት የታሪክ ወቅት ለቅርቡ ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ ቁልፍ የሆነ መነሻነት አለው። በአንድ በኩል በአፍሪካና በእስያ ሕዝቦች ላይ ኃያል ተጽዕኖ ለማድረግ በዘመናዊ ኢንዱስትሪና ድርጅት ታጥቆ የተነሣውን የምዕራብ አውሮፓን የቅኝ አገዛዝ ኃይል በብቸኝነት መክቶና ተቋቁሞ የኢትዮጵያን ነጻነት ለማቆዬት የተቻለበት ረዥም ፥ መሪርና አኩሪ ታሪካችን መመዝገብ የጀመረው ቀደም ባሉት ዘመናትም ቢሆን ፥ በተለይ ጐልቶ የወጣው በቴዎድሮስ ዘመን ነው። የቴዎድሮስ የአንድነትና የነጻነት ተጋድሎ ፥ የመቅደላው መሥዋዕትነት ፥ በአጠቃላይ የጀግንነት አርአያነት በነጻነት ተጋዳይነት ታሪካችን ውስጥ ዘላለማዊና አንጸባራቂ ሥፍራ ይዞ የሚኖር ፥ የተከታታይ ትውልድ ጥልቅ አክብሮት ሊለየው የማይገባ እጅግ አኩሪ ቅርስ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ፥ አገሪቱ በረዥም ዘመን ፊውዳላዊ የታሪክ ሂደት ውስጥ ከወደቀችበት ኋላቀርነትና ፥ በተለይም ከቴዎድሮስ በፊት በነበረው የአንድ መቶ ዓመት ዕድሜ ከደረሰ ባት አስከፊ ሁከትና መከፋፈል እንድትወጣ ፥ ጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥት ተመሥርቶ አስተዳደር እንዲስተካከል፥ቀደምት ዓላማ ይዘው የተነሡት ቴዎድሮስ ናቸው። ### የዐፄ ቴዎድሮስ ዘመን ባሕርያት የዐፄ ቴዎድሮስ ዘመን ሁለት ባሕርያትን ያጣመረ ነው። አንደኛው ገጽታው ፥ ከአንድ የታሪክ ዘመን ወደ ሌላ የታሪክ ዘመን ሽግግር የተደረገበት ድልድይ መሆኑ ነው። ከቴዎድሮስ በፊት በነበሩት ሁለት መቶ ዓመታት ፥ ነገሥታቱ በቅርብ ይቆጣጠሯቸው በነበሩት የመሐል አገር ፥ የሰሜን ግዛቶችና አውራጃዎች ውስጥ ልዩ ሁኔታ ተከስቷል። ይኸውም የዘውዱ ሥልጣን መዳከምና በየአውራጃው የነበሩት መሳፍንት በየፊናቸው አምባገነን እየሆኑ ፥ የፈላጭቆራጭነት ሥልጣናቸው እየጐላ መምጣቱና ለነገሥታቱም አንገብርም ፥ አንታዘዝም እያሉ አሻፈረኝ ማለታቸው ነው። በተለይም ጐንደር ፥ የነገሥታቱ ቋሚ መኖሪያና ከተማ ሆና በ17ኛው ምዕት ዓመት መጀመሪያ ላይ መቆርቆሯ ፥ ለዚህ ሂደት ዐይነተኛ ምክንያትና መነሻ ሆኗል። ነገሥታቱ ቀደም ሲል አገር ያስተዳድሩ የነበረው፥ የጦር ሠፈራቸውን ከአውራጃ ወደ አውራጃ በማዘዋወርና ፥ በየጊዜው ሹም ሽር እያደረጉ ለዘውዱ ታማኝ የሆኑ መሳፍንትን በማስቀመጥና ሥልጣናቸውን በማሳየት ነበር። ጐንደር ከተቆረቆረች በኋላ ግን ፥ ተቀማጭነታቸው በአንድ ቦታ በመወሰኑ በአንዳንድ አካባቢ ሥልጣናቸው እስከ መረሳት ደርሶ ፥ በእነሱ ፋንታ መሳፍንቱ ይበልጥ ሥልጣንና ኃይል እያገኙ መጡ። በጐንደር ቤተ መንግሥት የሚታየው የተድላና የደስታ ኑሮ ፥ ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ድልወት እያመዘነ በመሔዱ ፥ የዙፋኑን መዳከምና የመሳፍንቱን ማንአለብኝ ባይነት ይበልጥ እንዲባባስና እንዲፋጠን አድርጐታል። በመጨረሻም፥ ከየአውራጃው የተነሡት መሳፍንት ፥ አንዱ ሌሎቹን አሸንፎ የበላይ ለመሆን በሚያደርገው የርስ በርስ ጦርነትና ፉክክር ዘመኑ የጥፋትና የእልቂት ሆነ። የመሳፍንቱ ዓላማ ፥ አንዱ በሌሎቹ ላይ ኃያልነትን አግኝቶ ፥ በጐንደር ነገሥታት ዘውድ ሥር ሌላውን ለመቈጣጠርና ዋና እንደራሴ ሆኖ ለመግዛት ነበር። ከ1761 አንሥቶ ፥ ቴዎድሮስ እስከ ነገሡ ድረስ የቆየውና ፥ በታሪክም «ዘመነ መሳፍንት» ተብሎ የሚታወቀው ጊዜ ይህ ነው። የቴዎድሮስ ጊዜ፥ከአንድ የታሪክ ዘመን ወደሌላ የታሪክ ዘመን ሽግግር የተደረገበት ድልድይ ነው የምንለውም ፥ እርሳቸው ይህን ሁከትና ውዝግብ ለማቆምና ጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥት ተመሥርቶ የአገሪቱን አንድነት መልሶ የመገንባቱን ተግባር ቀደምት ዓላማቸው አድርገው በመነሣታቸው ነው። ዐፄ ቴዎድሮስ ፥ ይህን ዓላማቸውን ዕውን ለማድረግ ሲሉ የተለሟቸው የአስተዳደር ዘዴዎች፥ ከፊሎቹ ከጊዜው የቀደሙ ስለ ነበሩ፥ አገሪቱ የነበረችበት ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሁኔታ ፥ እንዲሁም ሰፍኖ የነበረው የፖለቲካ ባህል ሊቀበላቸው አልቻለም። በየአውራጃው የነበሩትን ገዥዎች የመንግሥት ተቀጣሪና ደመወዝተኛ ለማድረግ ሞክረዋል። የመሳፍንቱ ወታደሮች በባላገሩ ላይ የሚያደርሱትን ዘረፋና ቅሚያ ለማቆም ሲሉ ቋሚ ጦር ተመልምሎ እንዲሠለጥንና በደመወዝ እንዲተዳደር ጽኑ ሐሳባቸው ነበር። ከዚህም በተረፈ ፥ የመሬትን ሥሪት ለመለወጥ ፥ የቤተ ክህነትን የፖለቲካ ተጽዕኖ ለማስወገድና ሰፊ የኢኮኖሚ ይዞታውን ለማስለቀቅ ፥ በአጠቃላይ ፥ ዘመናዊ የአስተዳደርና የኢኮኖሚ ሥልጣኔ አገር ውስጥ እንዲገባላቸው ያለፋታ ደክመዋል። እዚህ ላይ ቁምነገሩ ፥ ቴዎድሮስ በሕይወት ዘመናቸው የወጠኑትን ሁሉ ሊፈጽሙ ቻሉ ወይስ አልቻሉም? የሚለው ጥያቄ አይደለም። የዘመኑ ታሪክ እንደሚመሰክረው አብዛኛው ዕቅዳቸው አልተሳካላቸውም። የመሳፍንቱና የቤተ ክህነት ጥላቻና ተቃውሞ ፥ የዘረጉትን የአስተዳደር ሥርዓት እያደናቀፈ አስቀርቶባቸዋል። እሳቸውም ምኞታቸው በራቀ መጠን ፥ ቁጣቸውና እልኻቸው እየገነፈለ ፥ በግለሰቦችም ሆነ በአውራጃዎች ላይ የሚያሳርፉት ቅጣት የከፋ ሊሆን ችሏል። ይሁን እንጂ ፥ እስከ ርሳቸው ዘመን ድረስ ያለ ምንም ገደብ በሕዝቡ ላይ ሲወርድ የነበረውን ጥፋትና እልቂት ለማቆምና ፥ ጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥት ለመትከል ቆርጠው መነሣታቸው ፥ ለዘመነ መሳፍንት ፍጻሜ ምክንያት መሆናቸውን ታሪክ ይመሰክራል። ከርሳቸው በኋላ የመጡት ነገሥታት ፥ ጠንካራ የፊውዳል ማዕከላዊ መንግሥት ለማቆምና ፥ ተበታትነው የነበሩትን የአገሪቱን ክፍሎች በአንድ አስተዳደር ሥር ለማሰባሰብ የቻሉት ፥ ርሳቸው በከፈቱት ጐዳና ተጉዘው ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚከሰተውና ' ለቴዎድሮስ የታሪክ ዘመን ሌላውንና ሁለተኛውን ገጽታ የሚያጐናጽፈው ባሕርይ ፥ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ መሠረት የተጣለው ፥ በዚሁ በርሳቸው ዘመን መሆኑ ነው። እስከ 16ኛው ምዕት ዓመት ድረስ የነበረው የማዕከላዊው ዘመን ረዥም ታሪካችን ፥ በመሐልና በሰሜን አውራጃዎች ብቻ የተወሰነ ሳይሆን፥ መላውን የዛሬይቱን ኢትዮጵያ ቆዳና ከዚያም ባሻገር የነበሩ ክፍሎችን በአንድ የታሪክ ሒደት ያስተሳሰረና ያወራረሰ ነው። ለዚህ ዘመን ታሪክ፥ ወሳኝነት ከነበራቸው ክስተቶች መካከል አንዱ ፥ በክርስትናና በእስልምና ሃይማኖት ሽፋን የተካሔደው የሥልጣን ትግልና የርስ በርስ ጦርነት ነው። ነገሥታቱ በምሥራቅና በደቡብ ምሥራቅ አውራጃዎች ላይ ሲዘምቱ ፥ ሕዝቡን ክርስትና ሲያጠምቁና መስጊዶችን ሲያቃጥሉ ፥ በአንጻሩ ደግሞ ፥ በተለይ በ16ኛው ምዕት ዓመት በአህመድ ግራኝ መሪነት እነዚህ አውራጃዎች ኃይል አግኝተው ፥ በልብነ ድንግል ላይ ካመፁ በኋላ ፥ መሐሉንና ሰሜኑን አገር እየወጉ ሕዝቡ እስልምናን እንዲቀበል ሲያስገድዱና ቤተ ክርስቲያኖችን ሲያቃጥሉ የምናየው የርስ በርስ የጦርነት ታሪክ ፥ የሃይማኖት ጦርነት እየሆነ ሲቀርብ ኖሯል። ሆኖም ፥ ሃይማኖት ሽፋን እንጂ መሠረታዊ የውጊያ መነሻ ሆኖ አያወቅም። ይህ ቢሆን ኖሮ ክርስቲያን ከክርስቲያን ፥ እስላምም ከእስላም ባልተዋጋ ነበር። ሁልጊዜም አንዱ ሌላውን ለማስገበር ፥ ለመሬት ወይም የንግድ መሥመርን ተቆጣጥሮ የኢኮኖሚ ኃይል ለማግኘትና የፖለቲካ የበላይነትን ለመያዝ ነው። በኢትዮጵያ የማዕከላዊ ዘመን (ከ13ኛው ምዕት ዓመት ሁለተኛ አጋማሽ እስከ 16ኛው አጋማሽ) ታሪክ ከዐምደ ጽዮን እስከ ልብነ ድንግል ተደጋግሞ የምናየው ይህንኑ ነው። ሌላው ለኢትዮጵያ ታሪክ ፥ ለሕዝቧ ዕድግትና ባሕርይ ወሳኝነት ያለው የሕዝብ ፍልሰት ነው። ከዚህም አንዱና ዋንኛው ፥ ከ16ኛው ምዕት ዓመት ጀምሮ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ልዩ ዘርፎች ፥ በመላው የአገሪቱ ክፍሎች መስፋፋትና ፥ ይህም ያስከተለው መሠረታዊ ሒደት ነው። ፍልሰቱ የጀመረበት ወቅት ፥ በኢትዮጵያ ውስጥ የነገሥታቱም ሆነ የአውራጃዎች ሥልጣን የተዳከመበት ወቅት ነበር። በተለይ ከላይ በተመለከትነው ሁኔታ ፥ በአህመድ ግራኝ መሪነት በተቀጣጠለው ጦርነት ፥ የመሐልና የሰሜኑም ሆነ ፥ የምሥራቅና የደቡብ ምሥራቁ የሀገሪቱ ኃይል ፥ ክፉኛ የተዳከመበት ነበር። በዚህ መሐል ፥ በጐሣና በገዳ ተደራጅቶ የተነሣው የኦሮሞ ብሔረሰብ ፍልሰት ፥ በጣም አጭር በሆነ ጊዜ ውስጥ የአገሪቱን መሠረታዊ ሒደት ፥ ለኢትዮጵያ ታሪክና ሕዝቧም ዛሬ ላለው ማኅበራዊ ዕውነታ አንዱ ወሳኝ ገጽታ ሆኗል። የብሔረሰቡ ልዩ ልዩ ዘርፎች እንደየሔዱበት አካባቢ ሁኔታ ፥ የተለያየ ሒደት እንዲከሰት አድርገዋል። እስልምና ተስፋፍቶ በነበረበት አውራጃ እስልምናን ፥ ክርስትና ባለበት ክርስትናን የተቀበሉ አሉ። በቁጥርም ሆነ በድርጅት አይለው ፥ ቀድሞ የነበረውን ሕዝብ እንዲዋጥ በማድረግ ፥ የበላይነትን የያዙባቸው አካባቢዎችም በተለያዩ ክፍሎች ይገኛሉ። ### ቴዎድሮስ ፣ ዘመነ መሳፍንት እና አዲሱ ኢትዮጵያ በቴዎድሮስ ዘመን የነበረውን ሁኔታ ፥ ቀድሞ ከነበረው ጋር ስናነጻጽር በጉልህ የሚታየን አንድ ነጥብ አለ። ይኸውም፥ ከኢትዮጵያ የዛሬ ድንበሮች ውጭ ጭምር ፥ ቀድሞ በአንድ የታሪክ ሒደት ተሳስረው የነበሩት ክፍሎች ከ17ኛው እስከ19ኛው ምዕት ዓመት በየፊናቸው ተከፋፍለውና ተለያይተው መገኘታቸው ነው። ይህም ሊሆን የበቃው ከላይ እንደ ተመለከትነው ፥ በርስ በርስ ጦርነት በደረሰው መዳከምና፥ ቀድሞ በአንድ ታሪክ የተሳሰረውን ክልል መልሶ ለማያያዝ የሚችል ኃይል ሊፈጠር ባለመቻሉ ነው። ቴዎድሮስ የተነሡበት የዘመነ መሳፍንት መድረክ፥ ከሰሜኑና ከመሐሉ አገር የኢትዮጵያ ክልል ያለፈ አልነበረም። የርሳቸው ሥልጣን ከፍተኛውን ደረጃ በያዘበት ወቅት እንኳን ክልላቸው በሰሜን ከቦጐስ (ዛሬ ከረን) በደቡብ ደግሞ ከሸዋ አልዘለለም። ይሁን እንጂ ፥ ቴዎድሮስ ዘመነ መሳፍንት እንዲያከትም ከማድረጋቸውም በላይ ፥ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ መሠረትም የተጣለው በዚሁ በርሳቸው ዘመን ነው ስንል ፥ ያለ ምክንያት አይደለም። ቀድሞ በአንድ የታሪክ ክልል ውስጥ የነበረውን ክፍል ሁሉ ፥ ከረዥም ጊዜ በኋላ በ19ኛው ምዕት ዓመት አጋማሽ እንደገና ለማያያዝ ዓላማ ይዘው የተነሡት እርሳቸው በመሆናቸው ነው። በተለይም ቅኝ ንዥ ኃይሎች በአፍሪካና በእስያ ሕዝቦች ላይ የገዥነት ዓላማ ይዘው በተነሡበት ዘመን፥ ይህን አደጋ በቅድሚያ መገንዘባቸውና ከውስጥ የነበረውን መከፋፈልና ድክመት አስወግደው ፥ አገሪቱን መልሶ የአንድ ታሪክ ባለቤት ለማድረግ መነሣታቸው ለዚህ ክብር ያበቃቸዋል። ### ክፍል አንድ ## የዐፄ ቴዎድሮስ የወጣትነትና የሽፍትነት ዘመን ### ምዕራፍ አንድ #### የደምቢያና የወሎ መሳፍንት ፍልሚያ በጐንደር መንግሥት ውስጥ የኢትዮጵያን መከፋፈል ለማስቀረትና አገሪቱን አንድ ለማድረግ ፥ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉትን የዐፄ ቴዎድሮስን አነሣሥና አወዳደቅ ከመመልከታችን በፊት ፥ የርሳቸው ወገኖች የሆኑትን ፥ የቋረኞችን ሁኔታ አስቀድሞ መመልከቱ የታሪኩን አመጣጥ ለመገንዘብ ይጠቅማል። ቴዎድሮስ ከመንገሣቸው በፊት ፥ ማንም እንደሚያውቀው ፥ መጠሪያ ስማቸው ካሣ ነበር። ከሌላ ጋር በሞግሼነት እንዳያደናግር ፥ በትውልድ ወረዳቸው በቋራ ፥ “ቋረኛው ካሣ” እየተባሉ ይጠሩ ነበር። ቋራ የሚገኘው ፥ በቤጌምድር አውራጃ በደምቢያ ውስጥ ነው። የዚህ ክፍል ተወላጆች “ቋረኞች” እየተባሉ በጐንደር መንግሥት ከዐፄ በካፋ ሞት ወዲህ ብዙ ሚና ተጫውተዋል። አጭር ታሪኩ ከዚህ እንደሚከተለው ነው። * በካፋ በ1686 ዓ.ም. ተወልደው ፥ በ1713 ዓ.ም. ስመ መንግሥታቸው “መሢህ ሰገድ” ተብሎ ከነገሡ በኋላ ፥ በ1715 ዓ.ም. ከቋራ ባላባቶች ከደጃች መንበርና ከወይዘሮ እንኮዬ የሚወለዱትን ፥ ቁንዥናቸውን እነጄምስ ብሩስ ያደነቁትን ወይዘሮ ምንትዋብን አገቡ። ከዚሁ ጋብቻ ፥ ስመ መንግሥታቸው “ብርሃን ሰገድ” የተባለው ዳግማዊ ኢያሱ ፥ በ1715 በሰኔ 12 ቀን ተወለዱ። በካፋና ምንትዋብ 8 ዓመት ያህል አብረው እንደተቀመጡ ፥ በመስከረም 11 ቀን 1723 ዓ.ም. ባልዮው ዐፄ በካፋ ስለ ሞቱ ፥ የስምንቱ ዓመት ወጣት ኢያሱ ነገሡ። ምንም ለስሙ ኢያሱ ቢነግሡ ፥ እናትዬዋ እቴጌ ምንትዋብ በመልክ ውበት ብቻ ሳይሆን በማስተዳደር ዕውቀትም ችሎታም አሟልተው የያዙ በመሆናቸው በልጃቸው ጐን ሆነው ፥ ንግሥት ተብለው የጐንደርን መንግሥት ይመሩ ዠመር። (¹) * ከእቴጌነታቸው በላይ በንግሥትነት በነገሠበት ቀን ምንትዋብ የወርቅ አክሊል ደፍተው ፥ የወርቅ ጫማ ተጫምተው ፥ በደንብ ተጊያጊጠው ፥ ጎማ በተባለው በቅሏቸው ላይ ሆነው በአደባባይ ሲያልፉ ፥ በዘመኑ ያማርኛ አገጣጠም ፥ “አሁን ወጻች ዠምበር ፥ ተሸሽጋ ነበር። አሁን ወጻች ጨረቃ የምትለን en ENAU Hoog: hァクチ * ይብቃ ደስ ይበልህ ባለጌ (*)• ከነገሠች ይተጌ ደስ ይበልህ ጐንደር ' ቀድሞ ከፍቶህ ነበር” እያለ ወንዱም ሴቱም ሲዘፍን ፥ ካህናቱም በበኩላቸው ፥ “መንክር ግርማ ፥ መንክር ግርማ ወልደ ልዑል ጸለላ መንክር ግርማ” እያሉ በወረብ አሸብሽበዋል ▪ (') * ኢያሱ በዕድሜ ከፍ ብለው ሥልጣን በጨበጡብትም ጊዜ ፥ እናትና ልጁ በሥልጣን ሽሚያ ሰምና እሳት ሳይሆኑ ፥ ሰምና ወርቅ ሆነው ፥ በፍቅር በስምምነት ፥ በኅብረት አብረው ሲገዙ ቆዩ። በሴትዬዋ ምክንያት ፥ ገና ቀደም ብለው በበካፋ ዘመን የሴትዬዋ ዘመድ አዝማዶች ከቋራ እየመጡ በየሥልጣኑ ገብተው ፥ ኒቆላዎስ የራስነት ማዕረግ ተጨምሮ የስሜን ገዥ ሆነው ከቆዩ በኋላ ፥ ቢትወደድነት ጨምረው እንደራሴ ሆኑ። (¹) ወንድም “RAGA OAR ADA I HUS* १०८ १९ *OAR ADA ጸለላ” እያሉ ስሙን የጠቀሱት ፥ ለእኅትዬዋ መንግሥት ጣራም ግድግዳም ሆኖ ፥ ከሹመት ወደ ሹመት ሲዘዋወር ቆይቶ ፥ በመጨረሻ ከራስ ኒቆላዎስ ሞት በኋላ ፥ ራስ ተብሎ የእንደራሴነቱን ሥፍራ የያዘ ነው። (') እነ ራስ ኤልያስ ፥ እነ ማሞ ተንሤ ሸፍተው ፥ ባለጌ ማለት ባላገር ማለት ነው ፥ ይተጌ ማለትም በዛሬ አነጋገር እቴጌ ማለት ነው። * ሕዝቅያስ የሚባል የነጋሢነት ዘር ያለውን ከወህኒ አምባ አውጥተው ፥ በኢያሱ ፋንታ ለማንገሥ ቤተ መንግሥቱን ከበው ውጊያው በከበደበት ሰዓት ለመሸሽያቆበቆበውን ወታደር ፥ «ባለህ ቁም ጐልማሳ! እኔ የወንዶች ወንድ መሆኔን ከተማው ያውቃል» ብሎ በፉከራው ያረጋጋ ፥ ራሱም «ለምድር ቃል ይሁን ፥ አንቺ ካልሸሸሽ እኔ እንዳልሸሽ» ብሎ ፥ በመፎከር ለውጊያ ከቆመባት መሬት ጋር ቃል ኪዳን የተጋባ ፥ ታላቅ የዤግና ወንድም ነው ▪ (') * ከዚህ ድል በኋላ ፥ የኢያሱና የንግሥት ምንትዋብ መንግሥት ጸና። ወልደ ልዑልም ከዚህ በኋላ ነው—ቢቶደድ ሲባል ቆይቶ ራስ ተብሎ የመንግሥቱ እንደራሴ የሆነው። የግዕዙ ዜና መዋዕል ይኸን ሰው አንድ ጊዜ “መልአከ ምክር ' ' ሌላ ጊዜ “መልአከ ሠራዊት” ይለዋል *(3) * ከራስ ወልደ ልዑል በቀር ፥ የንግሥት ምንትዋብ ዘመድ አዝማድ የራስ ኒቆላዎስ ወንድም አዛዥ ደኔ ፥ የአዛዥ ዶኔ ልጅ ደጃች ማሞ ፥ የአያታቸው የወይዘሮ ዮልያና እኅት የወይዘሮ ሰብሌና የአቤቶ መርቆርዮስ ልጆች ደጃች አውሳብዮስ ፥ ደጃች አዮ ፥ ደጃች እሸቴ( ) *የንግሥት ምንትዋብ አክስት የወይዘሮ ማሚት ልጆች ፥ ደጃች አደሩና አዛዥ ልዑለ ቃል ፥ አሳላፊ ቀጸላ ሌሎችም በጐንደር ቤተ መንግሥት በየሥልጣኑ በብዛት ማስተዳደር ስለያዙ ፥ መንግሥቱ ራሱ ማቋረኞች መንግሥት እየተባለ ይጠራ ዠመር ▪ ነገር ግን ፥ ምንም እንኳን አብዛኛውን ያስተዳደር ቦታ ቢይዙም ፥ በአገው ምድርና በዳሞት ደጃች ወሬኛ ፥ በአማራ አገር ራስ ወዳጆ ፥ በቤጌምድር ደጃች የማርያም ባሪያ ፥ በትግሬ ደጃች ስሑል ሚካኤል ፥ በጐጃም ደጃች ዮሴዴቅ ጣልቃ እየገቡ ፥ በጋርዮሽ በየክፍለ አገራቸው እየተሾሙ ማስተዳደራቸው አል

Use Quizgecko on...
Browser
Browser