Grade 6 Environmental Science Questions PDF
Document Details
![LustrousSavanna6540](https://quizgecko.com/images/avatars/avatar-3.webp)
Uploaded by LustrousSavanna6540
Abiyot Primary School
Tags
Summary
This document presents questions related to the topic of East Africa geography. The questions cover various concepts including location, maps, and geographical features.
Full Transcript
አካባቢ ሳይንስ ፮ኛ ክፍል ጥያቄዎች ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ ከምዕራፉ ትምህርት አጠቃላይ የሚጠበቁ ውጤቶች ተማሪዎች የዚህን ምዕራፍ ይዘቶች ተምራችሁ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፡- አቅጣጫ የመለየት ክህሎትን ታዳብራላችሁ፡፡ መልክአ ምድራዊ አቀማመጥን፣ ጎግል የካርታ መፈለጊያ መተግበሪያንና ጎግል ኧርዝ (GPS,...
አካባቢ ሳይንስ ፮ኛ ክፍል ጥያቄዎች ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ ከምዕራፉ ትምህርት አጠቃላይ የሚጠበቁ ውጤቶች ተማሪዎች የዚህን ምዕራፍ ይዘቶች ተምራችሁ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፡- አቅጣጫ የመለየት ክህሎትን ታዳብራላችሁ፡፡ መልክአ ምድራዊ አቀማመጥን፣ ጎግል የካርታ መፈለጊያ መተግበሪያንና ጎግል ኧርዝ (GPS, Google map and Google earth) በመጠቀም የቦታ አቀማመጥን የመለካትና የመመዝገብ ክህሎት ታዳብራላችሁ፡፡ ካርታን በማንበብ እና በመጠቀም ከሰዎች መረጃ ትለዋወጣላችሁ፡፡ ኬክሮስንና ኬንትሮስን በመጠቀም የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን በአፍሪካ ካርታ ላይ ታሳያላችሁ፡፡ በአፍሪካ ካርታ ላይ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን አንጻራዊና ፍጹማዊ መገኛን ታሳያላችሁ፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን አንጻራዊ መገኛ የሚያመለክት ንድፍ ካርታ ትሠራላችሁ፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን አጎራባች ሀገራት ትዘረዝራላችሁ፡፡ ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ የመግቢያ ጥያቄዎች የሚከተሉትን ጥያቄዎች ካነበብክ በሗላ ትክክለኛውን መልስ በመልስ መስጫ ወረቀቱ ላይ አጥቁር፡፡ 1. የአፍሪካ አህጉር በአምስት ቀጠናዎች ይከፈላል፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 2. የአፍሪካ አህጉር ቀጠናዎች ባህልን፣ ማኅበራዊ ትስሥርን እና መልክአ ምድራዊ አቀማመጥን መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 3. የአፍሪካ ቀጠናዎች ምሥራቃዊ አፍሪካ፣ ሰሜናዊ አፍሪካ፣ ደቡባዊ አፍሪካ እና ምዕራባዊ አፍሪካ ብቻ ተብለው ይጠራሉ፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 4. በአለም ስንት አህጉር ወይም ክፍለ ዓለማት አ ሉ ? ሀ) 7 ለ) 5 ሐ) 3 መ) 4 5. ምሥራቅ አፍሪካ ከአምስቱ የአፍሪካ ቀጠናዎች በስፋቱ ስንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል? ሀ) 1 ለ) 2 ሐ) 3 መ) 4 6. ምሥራቅ አፍሪካ ከአጠቃላይ የአፍሪካ መልክአ ምድር ምን ያህል ይሸፍናል? ሀ) 21% ለ) 30% ሐ) 15 በመቶ መ) 40 በመቶ 7. በምስራቃዊ አፍሪካ ውስጥ ስንት ሀገራት ይገኛሉ? ሀ) 20 ለ) 19 ሐ) 12 መ) 11 8. ከመልክአ ምድር አቀማመጥ አንጻር ሲታይ ምሥራቅ አፍሪካ በውስጡ የተለያየ የመሬት አቀማመጥ አለው፡፡ በቀጠናው በእሳተ ገሞራ የተፈጠሩ ትላልቅ ተራሮች፣ ዝቅተኛ ሥፍራዎች፣ ወንዞችና ሐይቆች ይገኛሉ፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ 1.1 የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት 9. ማዳጋስካር በስንተኛ ቁጥር ላይ ይገኛል? ሀ) 8 ለ) 10 ሐ) 7 መ) መልሱ የለም 10. ሶላሚያ በስንተኛ ቁጥር ላይ ይገኛል? ሀ) 1 ለ) 4 ሐ) 13 መ) መልሱ የለም 11. በተራ ቁጥር 14 የተመለከተው ሃገር ማን ነው? ሀ) ዛምቢያ ለ) ሩዋንዳ ሐ) ዚምባብዌ መ) ኤርትራ 12. የአንድን ሀገር መገኛ በልዩ ልዩ አቅጣጫ ከሚያዋስኑ ነገሮች እ ን ደ አግዳሚ መስመርጋር በማነጻጸር የሚነገርበት መገኛ ምን ይባላል? ሀ) ፍጹማዊ መገኛ ለ) አንጻራዊ መገኛ ሐ) ቋሚ መስመር መ) አግዳሚ መስመር ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ 13. የአንድን ሀገር መገኛ አግድምና ቋሚ መስመሮችን በመጠቀም ወይም የዲግሪ ልኬትን በመጠቀም የሚነገርበት መገኛ ምን ይባላል? ሀ) ፍጹማዊ መገኛ ለ) አንጻራዊ መገኛ ሐ) ቋሚ መስመር መ) አግዳሚ መስመር 14. ቀይ ባህር ምሥራቅ አፍሪካን በየት በኩል ያዋስናል? ሀ) በሰሜን ለ) ምስራቅ ሐ) ሰሜን መስራቅ መ) ደቡብ ምእራብ 15. ምሥራቅ አፍሪካን የሚያዋስነው ትልቁ ውሃማ አካል ማን ነው? ሀ) አትላንቲክ ውቅያኖስ ለ) ቀይ ባህር ሐ) ህንድ ውቅያኖስ መ) የናይል ውንዝ 16. የምሥራቅ አፍሪካ ፍጹማዊ መገኛ በአፍሪካ ካርታ ላይ የት ነው? ሀ) ከ180ሰሜን እስከ 270 ደቡብ ኬክሮስ፣ እንዲሁም ከ22 ምሥራቅ እስከ 510 28’ ምሥራቅ ኬንትሮስ ነው፡፡ ለ) ከ270ሰሜን እስከ 180 ደቡብ ኬክሮስ፣ እንዲሁም ከ22 ምሥራቅ እስከ 510 28’ ምሥራቅ ኬንትሮስ ነው፡፡ ሐ) ከ180ሰሜን እስከ 270 ደቡብ ኬክሮስ፣ እንዲሁም ከ510 28’ ምሥራቅ እስከ 2 2 0 ምሥራቅ ኬንትሮስ ነው፡፡ መ) መልሱ የለም 17. በካርታ ወይም በሉል ላይ ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ ወይም ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ የተሰመሩ የሐሳብ ምን ይባላሉ፡፡ ሀ) ኬክሮስ (latitudes) ለ ) ኬንትሮስ (longitudes) ሐ) የምድር ወገብ (Equator) መ) ቋሚ መስመሮች (Meridians) 18. በካርታ ወይም በሉል ላይ ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ ወይም ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ የተሰመሩ የሐሳብ ምን ይባላሉ፡፡ ሀ) ኬክሮስ (latitudes) ለ ) ኬንትሮስ (longitudes) ሐ) የምድር ወገብ (Equator) መ) ቋሚ መስመሮች (Meridians) 19. የአግድም መስመሮች መነሻ በዜሮ ዲግሪ ላይ ይገኛል፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 20. ቋሚ መስመሮች (Meridians) እና ትይዩ መስመሮች (latitudes) በመሬት ላይ ተሰምረው እናያቸዋለን፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ 21. ትልቁ የአግድም መስመር የምድር ወገብ (Equator) ይባላል:: የምድር ወገብ መሬትን በምስራቅና በምእራብ ንፍቀ ክበብ በእኩል ቦታ ይከፍላል፡፡የሚያዋስነው ትልቁ ውሃማ አካል ማን ነው? ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 22. በመሬት ላይ በአጠቃላይ 180 የአግድም መስመሮች ይገኛሉ፡፡ በእያንዳንዳቸው መስመሮች መካከል የአንድ ዲግሪ ልዩነት አለ:: በተጨማሪም ሁሉም መስመሮች ትይዩ ናቸው፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 23. ከሚከተሉት ስህተት የሆነው የትኛው ነው? ሀ) በካርታ ወይም በሉል ላይ የሚታዩ አምስት ዐብይ ትይዩ መስመሮች አሉ፡፡ ለ) የካንሰር መስመር በ 23 ½0 ሰሜን ይገኛል፡፡ ሐ) የካፕሪኮርን መስመር 66 ½0 ደቡብ ይገኛል፡፡ መ) የአንታርክቲክ ክበብ በ66 ½0 ደቡብ ይገኛል፡፡ 24. የዐብይ ቋሚ መስመር ስንት ድግሪ ላይ ይገኛል? ሀ) 90 ለ) 60 ሐ) 0 መ)180 25. የቋሚ መስመሮች አጠቃላይ ብዛት ስንት ነው? ሀ) 360 ለ) 180 ሐ) 90 መ) 60 26. የአርክቲክ ክበብ የሚገኘው ሀ) ሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ ለ) ደቡባዊ ንፍቀ ክበብ ሐ) ምዕራባዊ ንፍቀ ክበብ መ) ምሥራቃዊ ንፍቀ ክበብ 27. የካንሰር መስመር የሚገኘው በስንት ዲግሪ ላይ ነው? ሀ) 23 ½ ሰሜን ለ) 23 ½ ደቡብ ሐ) 66 ½ ሰሜን መ) 66 ½ ደቡብ ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ የሚከተሉትን አግዳሚና ቋሚ መስመሮችን በመመልከት ከተራ ቁጥር 2 8 — 31 ያሉትን ጥያቄዎች መልስ፡፡ 28. ለምድር ወገብ በጣም ቅርብ የሆነውን ቦታ የሚያሳየው ፊደል የትኛው ነው? ሀ) ሀ ለ) ለ ሐ) መ መ) ሁሉም መልስ ናቸው 29. በምሥራቅ ንፍቀ ክበብ የሚገኙ ቦታዎች (ነጥቦች) የትኞቹ ናቸው? ሀ) ሀ እና ለ ለ) ለ እና መ ሐ) ሐ እና ሠ መ) መ ብቻ 30. በምዕራብ ንፍቀ ክበብ የሚገኙ ቦታዎች (ነጥቦች) የትኞቹ ናቸው? ሀ) ሀ እና መ ለ) ለ እና መ ሐ) ሐ እና ሠ መ) መልሱ የለም 31. የ መ ነጥብ ፍጹማዊ መገኛ _ _ _ _ _ _ _ _ _ ነ ው ፡ ፡ ሀ) 300 ሰሜን እና 100 ምእራብ ለ) 300 ደቡብ እና 100 ምእራብ ሐ) 300 ምስራቅ እና 100 ደቡብ መ) 300 ደቡብ እና 100 ምስራቅ 32. ምሥራቅ አፍሪካ ጂኦግራፊያዊ(ተፈጥሮአዊ) አቀማመጥን ስንመለከት አብዛኛው የቀጠናው ሀገራት በትልልቅ ውሃማ አካላት የተከበቡ በመሆናቸው ይህም የራሱ የሆነ ምጣኔ ሀብታዊና ፖለቲካዊ ጥቅምና ጉዳት አለው፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 33. ፖለቲካዊ ተጽኖውን ስንመለከት የቀጠናው ሀገራት በትልልቅ ውሃማ አካላት የተከበቡ መሆናቸው በቀላሉ በቅኝ ገዥዎች እንዲወረሩ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ 34. የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት በምሥራቅ የሚያዋስኑ ሃገር የቱ ነው? ሀ) ሱዳን እና ዲሞክራቲክ ኮንጎ ለ) አንጎላ እና ቦትስዋና ሐ) ደቡብ አፍሪካ እና ስዋዚላንድ መ) ሁሉም ያዋስናሉ 35. የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት የማያዋስን የውሃ አካል የቱ ነው? ሀ) ቀይ ባሕር ለ) የኤደን ባሕረ-ስላጤ ሐ) የሕንድ ውቅያኖስ መ) የአትላንቲክ ውቅያኖስ 36. የምሥራቅ አፍሪካ ክልል በሦስት ንዑሳን ክፍሎች ይከፈላል፡፡ ከእነዚህ ንዑሳን ክፍሎች ውስጥ የሌለ የቱ ነው? ሀ) የታላላቅ ሐይቆች ክልል ለ) የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች ሐ) የሕንድ ውቅያኖስ ደሴቶች መ) የአትላንቲክ ውቅያኖስ ደሴቶች 37. በምሥራቅ አፍሪካ ንዑሳን ክፍሎች በታላላቅ ሐይቆች ክልል ውስጥ የማይገኝ የቱ ሃገር ነው? ሀ) ዩጋንዳ ለ) ኬንያ ሐ) ኢትዮጵያ መ) ሩዋንዳ 38. በምሥራቅ አፍሪካ ንዑሳን ክፍሎች በአፍሪካ ቀንድ ሃገሮች ክልል ውስጥ የማይገኝ የቱ ሃገር ነው? ሀ) ኤርትራ ለ) ጂቡቲ ሐ) ሶማሊያን መ) ብሩንዲ 39. በምሥራቅ አፍሪካ ንዑሳን ክፍሎች በሕንድ ውቅያኖስ ደሴቶች ክልል ውስጥ የማይገኝ የቱ ሃገር ነው? ሀ) ኮሞሮስ ለ) ሪዩኒየን ሐ) ታንዛኒያ መ) ሞሪሽየስ 40. በምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ ረጂሙ ተራራ ማን ነው? ሀ) ኪሊማንጃሮ ለ) ኬንያ ተራራ ሐ) ራስ ደጀን ተራራ መ) ሩዋንዞሪ 41. ኤልጎን ተራራ በየት ሃገር ይገኛል? ሀ) ታንዛንያ ለ) ኬንያ ሐ) ዩጋናዳ መ) ኢትዮጵያ 42. በምሥራቅ አፍሪካ አካባቢ ወደ ተለያየ አቅጣጫ ከሚፈሱ ወንዞች መካከል የቶቹ ይገኛሉ? ሀ) የዐባይ ወንዝ ለ) የአዋሽ ወንዝ ሐ) የዛምቤዚ ወንዝ መ) ሁሉም መልስ ናቸው ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ 43. በኢትዮጵያ ብዙ የቅሪተ አካላት መገኛ ሥፈራዎች አሉ፡፡ እጅግ ታዋቂ የሆኑ የቅሪተ አካላት መገኛ ሥፍራዎች የሚገኙት ሀ) በአፋር ብሔራዊ ክልል ነው፡፡ ለ) በአማራ ክልል ነው፡፡ ሐ) በኦሮሚያ ክልል ነው፡፡ መ) በትግራይ ክልል ነው፡፡ 44. በኢትዮጵያ ከሚገኙ ታዋቂ ቅሪተ አካላት መካከል አንዱ ሀ) አርዲ እና ሰላም ለ) ኢዳልቱ፣ ሐ) ድንቅነሽ (Lucy) መ) ሁሉም መልስ ናቸው 45. ድንቅነሽ (Lucy) የተገኘችው ሐረር በሚባል ቦታ ነው፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 46. በኬንያ የተለያዩ አካባቢዎች የጥንታዊ ሰው ቅሪተ አካል እና ቅሪተ ቁስ መገኛ ሥፍራዎች አሉ፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 47. በቱርካና (ሩዶልፍ) ሐይቅ ዳርቻ ኮቢ ፎራ በሚባል አካባቢ በርካታ ጥንታዊ ሰው ቅሪተ አካል እና የድንጋይ መሣሪያዎች ተገኝቷል፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 48. በኢትዮጵያ የማይገን የቱሪስት መስህብ የቱ ነው? ሀ) የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ለ) ዳሎል ዝቅተኛ ቦታ ሐ) ማሳይ ማራ ፓርክ መ) የአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ 49. በምሥራቅ አፍሪካ አካባቢ ከህንድ ውቅያኖስ ጋር ረጅም ወሰን ያለው ደሴት ማን ነው? ሀ) ኮሞሮስ ለ) ሪዩኒየን ሐ) ማዳጋስካር መ) ሞሪሽየስ 50. ኬንያ ከዩጋንዳ በየት አቅጣጫ ይገኛል? ሀ) ሰሜን ለ) ደቡብ ሐ) ምስራቅ መ) ምእራብ 51. የአባይ ወንዝ መነሻ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገር ማን ትባላለች? ሀ) ዩጋንዳ ለ) ኬንያ ሐ) ኢትዮጵያ መ) ሩዋንዳ 52. የምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ ከየት ይነሳል ሀ)ዩጋንዳ ለ) ኬንያ ሐ) ኢትዮጵያ መ) ሶርያ 53. የምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ በኢትዮጵያ ወደ ደቡብ አቅጣጫ ይዞራና የት ድረስ ይሄዳል? ሀ) ታንዛንያ ለ) ኬንያ ሐ) ዩጋናዳ መ) ሞዛምቢክ ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ 54. የምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ አጠቃላይ ርዝመቱ ስ ን ት ነ ው ? ሀ ) 7200 ኪ.ሜ ለ ) 5600 ኪ.ሜ ሐ ) 4000 ኪ.ሜ መ) ሁሉም 55. ዩጋንዳ፣ ታንዛኒያና ኬንያ መካከል የሚገኘው ሐይቅ ማን የባላል? ሀ ) ታንጋኒካ ሐይቅ ለ ) የቪክቶርያ ሐይቅ ሐ ) የጣና ሐይቅ ኪ.ሜ መ) ማላዊ ሐይቅ 56. ታንዛንያና ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ መካከል የሚገኘው ሐይቅ ማን የባላል? ሀ ) ታንጋኒካ ሐይቅ ለ ) የቪክቶርያ ሐይቅ ሐ ) የጣና ሐይቅ ኪ.ሜ መ) ማላዊ ሐይቅ 57. በምሥራቅ አፍሪካ ከሚገኙ የተለያዩ ታላላቅ ወንዞች መካከል ያልሆነው ማን ነው? ሀ) ዋቢሸበሌ ለ) ገናሌ ሐ) ዛምቤዚ መ) አባይ 58. በዓለማችን ረዥሙ ወንዝ ማን ነው? ሀ) ዋቢሸበሌ ለ) ናይል ሐ) ዛምቤዚ መ) አባይ 59. በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙ ሐይቆች የሚከፈሉት ሀ) የስምጥ ሸለቆ ሐይቆች በመባል ይታወቃሉ:: ለ) ከስምጥ ሸለቆ ውጭ ያሉ ሐይቆች በመባል ይታወቃሉ:: ሐ) ሁለቱም መልስ ናቸው መ) መልሱ የለም 60. በስምጥ ሸለቆ ውስጥ የታንጋኒካ፣ የማላዊ፣ የኪቩ እና በኢትዮጵያ የሚገኙትን የላንጋኖ፣ የዝዋይ፣ የሻላ፣አባያ፣ የሐዋሳና የመሳሰሉት ሐይቆች ይገኛሉ፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 61. በአፍሪካ ትልቁ ሐይቅ ተብሎ የሚታወቀው ማን ነው? ሀ) ቪክቶርያ ሐይቅ ለ) ጣና ሐይቅ ሐ) ዝቋላ ሐይቅ መ) ሁሉም 62. ጎግል ካርታ በቀጥታ ከጎግል በመሬት ላይ የምንፈልገውን አካባቢ ካርታ በተንቀሳቃሽ ስልክ (በሞባይል) ወይም በኮምፒውተር አማካኝነት አንድን ቦታ በቀጥታ ለማመልከት የሚያስችል መተግበሪያ ነው፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 63. ጎግል ካርታ የአንድ ቦታን አቅጣጫ፣ የአካባቢን የገበያ ትስስር እና የመሳሰሉትን ለመፈለግ ይጠቅማል፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ 64. ጎግል ካርታ ሰዎች በቀላሉ ወደ ማያውቁት ቦታ ለመሄድ፣ መልዕክት ለማድረስ፣ ሰዎችን በቀላሉ ለማግኘት ሲፈልጉ የጎግል ካርታ መፈለግያን መጠቀም ይቻላል፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 65. ጂፒኤስ (GPS) በመሬት ዙሪያ የሚሽከረከሩ ሰው ሠራሽ ሳተላይቶችን በመጠቀም የተለያዩ መረጃዎችን ወደ መሬት የሚያቀብሉ መተግሪያዎች ወይም መሳሪያዎች (devices) ናቸው፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ አንድን አካባቢ ወይም አገር በመሬት አካል ላይ የሚገኝበትን ቦታ ለማመልከት የምንጠቀምበት ዘዴ መገኛ ይባላል፡፡ አንድ አካባቢ ወይም አገር የሚገኝበትን ለማወቅ አንጻራዊ መገኛ እና ፍጹማዊ መገኛ እንጠቀማለን፡፡ የኬክሮስ መስመሮች በካርታ ወይም በሉል ላይ ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ ወይም ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ የተሰመሩ የሐሳብ መስመሮች ናቸው፡፡ የኬንትሮስ መስመሮች በካርታ ወይም በሉል ላይ ከሰሜን ወደ ደቡብ ወይም ከደቡብ ወደ ሰሜን ተሰምረው ይገኛሉ፡፡ የኬክሮስ መስመሮች መነሻ በዜሮ ዲግሪ ላይ የሚገኘው የምድር ወገብ (Equa- tor) ይባላል፡፡ የኬንትሮስ መስመሮች መነሻ ዜሮ ዲግሪ ላይ የሚገኘው ፕራይም ሜሪዲያን ወይም ግሪንዊች ሜሪዲያን ተብሎ ይጠራል፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ በሰሜን የሰሜን አፍሪካ አገራት እና ቀይ ባህር፣ በደቡብ አቅጣጫ ደቡብ አፍሪካ፣ በምሥራቅ የኤደን ባህረ-ሰላጤ እና የህንድ ውቅያኖስ እና በምዕራብ ማዕከላዊ አፍሪካ አገሮች ያዋስኑታል፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ ብዙ ታዋቂ ቦታዎች አሉ፡፡ ከነዚህም መካከል ዋና ዋናዎቹ፡- ከፍተኛ ተራሮች፣ አምባ ምድሮች፣ የስምጥ ሸለቆ ፣ ወንዞችና ሐይቆች ይገኛሉ፡፡ ጎግል ማፕን በመጠቀም የአንድን ቦታ አቅጣጫ፣ የአካባቢን የገበያ ትስስር እና የመሳሰሉትን ለመፈለግ ጠቃሚ ነው፡፡ ጂፒኤስ (GPS) በመሬት ዙሪያ የሚሽከረከሩ ሰው ሠራሽ ሳተላይቶችን በመጠቀም የተለያዩ መረጃዎችን ወደ መሬት የሚያቀበሉ መተግሪያዎች ወይም መሳሪያዎች (devices) ናቸው፡፡ ጎግል ኧርዝ ሰው ሰራሽ ሳታላይቶችን በመጠቀም የመሬትን ትክክለኛ ምስል ማሳየት የሚያስችል መተግበሪያ ነው፡፡ ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ የሚከተሉትን ዐረፍተ ነገሮች አንብባችሁ ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል ካልሆኑ ደግሞ ሐሰት በማለት መልሱ፡፡ 66. የኬክሮስ መስመሮች ከሰሜን ወደ ደቡብ የተሰመሩ ናቸው፡፡ 67. የኬክሮስ መሰመሮች ትይዩ ናቸው፡፡ 68. ከፕራይም ሜሪዲያን በስተምሥራቅ 180 የኬንትሮስ መስመሮች አሉ፡፡ 69. የምድር ወገብ የመሬትን ክፍል ምሥራቅና ምዕራብ እኩል ቦታ ይከፍላል፡፡ 70. የኬንትሮስ እና ኬክሮስ መስመሮች በካርታ እና በሉል ላይ ይገኛሉ፡፡ 71. ፍጹማዊ መገኛ ታዋቂ ነገሮችን ምልክት በማድረግ ይገለፃል፡፡ ለ. በ “ሀ” ሥር ያሉትን ማብራሪያዎች በ “ለ” ሥር ካሉት አማራጮች ጋር አዛምዱ፡፡ “ሀ” “ለ” 72. የምሥራቅ አፍሪካ ትልቁ ተራራ ሀ)ታንጋኒካ 73. የኢትዮጵያ ትልቁ ተራራ ለ)ቪክቶርያ 74. የምሥራቅ አፍሪካ ትልቁ ሐይቅ ሐ)ኪሊማንጃሮ 75. የምሥራቅ አፍሪካ የስምጥ ሸለቆ ሐይቅ መ)ራስ ደጀን(ዳሸን) 76. በምሥራቅ አፍሪካ ሁለተኛ ትልቁ ተራራ ሠ) የኬንያ ተራራ ሐ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ከተሰጡት አማራጮች ውስጥ ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ መልሱ፡፡ 77. የምሥራቅ አፍሪካን በስተምሥራቅ በኩል የሚያዋስነው ከሚከተሉት የትኛው ነው? ሀ) የአትላንቲክ ውቅያኖስ ለ) ቀይ ባህር ሐ) የፓሲፊክ ውቅያኖስ መ) የህንድ ውቅያኖስ 78. በካርታ ወይም በሉል ላይ ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ የተሰመሩ መስመሮች ምን ይባላሉ? ሀ) ኬክሮስ ለ) ኬንትሮስ ሐ) ቋሚ መስመሮች መ) ተቋራጭ መስመሮች 79. የአንድን አካባቢ ወይም አገር መገኛ ዲግሪን በመጠቀም ማመልከት ምን ይባላል? ሀ) አካባቢያዊ መገኛ ለ) አንጻራዊ መገኛ ሐ) ፍጹማዊ መገኛ መ) ግምታዊ መገኛ ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ 80. ከሚከተሉት ውስጥ ስለ ምሥራቅ አፍሪካ አንጻራዊ መገኛ ትክክል ያልሆነው የቱ ነው? ሀ) ምሥራቅ አፍሪካ ከማእከላዊ አፍሪካ በስተምዕራብ ይገኛል፡፡ ለ) ምሥራቅ አፍሪካ ከደቡብ አፍሪካ በስተሰሜን ይገኛል፡፡ ሐ) ቀይ ባህር ምሥራቅ አፍሪካን በስተሰሜን ያዋስናል፡፡ መ) ህንድ ውቅያኖስ ምሥራቅ አፍሪካን በስተምሥራቅ ያዋስናል፡፡ 81. ከሚከተሉት ውስጥ ዐብይ የአግዳሚ መስመር ያልሆነው የትኛው ነው? ሀ) የምድር ወገብ ለ) የካንሰር መስመር ሐ) የካፕሪኮርን መስመር መ) ግሪንዊች ሜሪዲያን መ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ፡ 82. ምሥራቅ አፍሪካን በስተምዕራብ አቅጣጫ የሚያዋስነው የአፍሪካ ክፈል _____________________ይባላል፡፡ 83. ስለ ምስራቅ አፍሪካ መገኛ ጥቅምና ጉዳት ዘርዝሩ፡፡ ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ከምዕራፉ የሚጠበቁ አጥጋቢ የመማር ብቃቶች ተማሪዎች ይህን የትምህርት ይዘት ተምራችሁ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፡- ❖ የሰው የደም ዑደትን በመሳል ስያሜዎቹን ታመለክታላችሁ፡፡ ❖ የደም ዓይነቶችንና ጠቀሜታዎች ትገልጻላችሁ፡፡ ❖ የልብን የተለያዩ ክፍሎች እና ጠቀሜታዎች ትገልጻላችሁ፡፡ ❖ በጉርምስና እና በኮረዳነት ወቅት በወንዶችና በልጃገረዶች ላይ የሚታዩ ለውጦችን ትገልጻላችሁ፡፡ ❖ ዋና ዋና የሰው የሥርዐተ ትንፈሳ ክፍሎችንና ተግባሮቻቸውን ትለያላችሁ፡፡ ❖ የድብልቅን ምንነት ትገልጻላችሁ፡፡ ❖ ድብልቅን የመለያ ዘዴዎች ትገልጻላችሁ፡፡ ❖ በአካባቢያችሁ የሚገኙ ድብልቆችን ትለያላችሁ፡፡ ❖ በአካባቢያችሁ የሚገኙ ድብልቆችን ዋህድ-ዘር ድብልቅ እና ልይ-ዘር ድብልቅ በማለት ትመድባላችሁ፡፡ ❖ ተግባራዊ ክንውን በመስራት ድብልቆችን ትለያላችሁ፡፡ ❖ የተለያዩ የጉልበት ምንጮችን መገኛ፣ ጥቅምና ተፅዕኖ ታወዳድራላችሁ፡፡ ❖ ቀሊሌ መኪና ስራን በቀሊለ ለመስራት እንደሚያግዝ ትገሌፃሊችሁ፡ ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ የመግቢያ ጥያቄዎች 1. ደም ፈሳሽ ከሆነ ፕላዝማ እና ከደም ህዋሶች የተሰራ የአካላችን ክፍል ነው፡፡ ፕላዝማ ውሃና አልሚ ምግቦችን የሚይዝ የደም ክፍል ነው፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 2. ሦስት አይነት የደም ህዋሶች አሉ፡፡ እነሱም፡- ቀይ የደም ህዋስ ፣ነጭ የደም ህዋስና ፕሌትሌትስ ናቸው፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 3. ደም በሽታን ለመከላከል፣ አየር ለማስተላለፍ፣ ደም ለማርጋት፣ ምግቦችን ወደ ተለያዩ ህዋሳት ለማሰራጨትና የተቃጠለ አየርን ከሰውነታችን ለማስወገድ ይጠቅማል፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 4. ደም በሰውነታችን ውስጥ የሚጓዘው በደም ስሮች አማካኝነት ነው፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 5. ከሦስት አይነት የደም ስሮች መካከል ያልሆነው የቱ ነው? ሀ) ደም ቅዳ ለ) ደም መልስ ሐ) ቀጫጭን የደም ስሮች መ) መለሱ የለም 6. ልብ በሰውነታችን ውስጥ በደረታችን በቀኝ አከባቢ ትንሽ ዝቅ ብሎ የሚገኝ በጡንቻዎች የተገነባ የውስጥ አካል ክፍል ነው፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 7. ልብ ሶስት ክፍሎች አሉት፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 8. ለብ ቀኝ ተቀባይ ልበገንዳ፣ ቀኝ አቀባይ ልበገንዳ፣ ግራ ተቀባይ ልበገንዳና ግራ አቀባይ ልበገንዳ የሚባሉ ክፍሎች አሉት፡: ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 9. ልብ ደም ለመርጨት፣ ኦክሲጅንና ምግብን ለህብረ ህዋሳት ለማድረስና አላስፈላጊ የሆኑ ቆሻሻዎችን ለምሳሌ ካርበን ዳይ ኦክሳይድን ለማስወገድ ይጠቅማል፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ 10. ጉርምስና እና ኮርዳነት በተወሰነ የዕድሜ ክልል በወንዶችና በሴቶች ላይ የሚታዩ አካላዊና የባህሪ ለውጦች ናቸው፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 11. ሴቶች በኮረዳነት ወቅት የወር አበባ ማየት ይጀምራሉ:: ይህ የወር አበባ በየ 30 ቀናት በማህፀንና በእንቁልጢ ውስጥ የሚካሄድ ተፈጥሮአዊ ክስተት ነው፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 12. አየር የተለያዩ ጋዞች ተዋህደው የሚፈጥሩት ልዩቁስ ነው፡፡ ያለ አየር እንስሳት፣ እፅዋት እና የሰው ልጆች ሊኖሩ አይችሉም፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 13. በሳንባ ውስጥ የሚካሄድ የአየር ልውውጥ ትንፈሳ ይባላል፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 14. ድብልቅ ማለት ሁለትና ከሁለት በላይ የሆኑ ልዩቁሶች አካላዊ በሆነ መንገድ የሚፈጥሩት የቁስ ዓይነት ነው፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 15. ድብልቅን ለመለየት አራት ዘዴዎች አሉ፡፡ እነሱም፡ ጥለያ፣ ቀረራ፣ ንጥረትና ትነት ናቸው፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 16. የሰው ልጅ ስራዎችን ለማከናወን ጉልበት ይጠቀማል፡፡ ያለጉልበት ምንም ስራ መስራት አይቻልም፡፡ ሀይልን ለማጎልበትና ጉልበትን ለመቆጠብ ስራን በፍጥነት ለመስራት የሚያግዝ መሳሪያ ቀላል መኪና ይባላል፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ 2.1 የደም ዑደት 17. ኦክስጂንና አልሚ ምግቦች ለሰውነታችን ህዋሶች የሚሰራጩበት እንዲሁም ካረቦን ዳይኦክሳይድ እና ሌሎች ቆሻሻዎች በደም አማካኝነት የሚሄዱበት ሂደት ምን ይባላል?፡ ሀ) ደም ለ) ትንፈሳ ሐ) የደም ዑደት መ) የደም ህዋስ 18. የደም ፈሳሽ አካል አልሚ ምግቦችን የሚይዝ የደም ክፍል ምን ይባላል? ሀ) ፕላዝማ ለ) ከደም ህዋሶች ሐ) ፈሳሽ ደም መ) መለሱ የለም 19. ከሦስቱ የደም ህዋሶች ያልሁነው የቱ ነው? ሀ) ፕላዝማ ለ) ቀይ የደም ህዋሶች ሐ) ነጭ የደም ህዋሶች መ) ፕሌትሌትስ 20. ቀይ የደም ህዋሶች ሀ) መሀላቸው ላይ ጎድጎድ ያለ እና የዶናት ቅርፅ ያላቸው ናቸው:: ለ) ቀይ የደም ህዋሶች ኦክስጂንን ከሳንባ ተቀብለው በመሸከም ለመላ የሰውነታችን ህዋሶች ያደርሳሉ፡፡ ሐ) ቁጥራቸው ከሌሎች የደም ህዋሶች አንፃር ሲታይ በጣም በርካታ ነው፡፡ መ) ሁሉም መልስ ናቸው 21. ቀይ የደም ህዋሶች መቅኔ ውስጥ የሚመረቱ ሲሆን ዕድሜያቸው ሀ) ከ10 - 20 ቀን ብቻ ነው፡፡ ለ) ከ100 - 120 ቀን ብቻ ነው፡፡ ሐ) ከ90 - 100 ቀን ብቻ ነው፡፡ መ) መልስ የለም 22. ቀይ የደም ህዋሶች ኦክስጂንን ለመሸከም የሚያስችል ምን ሃመልሚል (pigment) አላቸው? ሀ) ፕላዝማ ለ) ቀይ የደም ህዋሶች ሐ) ሄሞግሎቢን መ) ፕሌትሌትስ 23. ነጭ የደም ህዋሶች ተግባር የበሽታ አምጪ ተህዋሲያንን ወይም ጀርሞችን ወደ ሰውነታችን ሲገቡ በማጥቃት እና በመከላከል የሰውነታችንን ጤንነት መጠበቅ ነው፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ 24. ከሚነተሉ አረፍት ነገሮች ሀሰት የሆነው የቱ ነው ሀ) ነጭ የደም ህዋሶች በመቅኔ ውስጥ ይመረታሉ ለ) ቀይ የደም ህዋሶች በመቅኔ ውስጥ ይመረታሉ ሐ) ነጭ የደም ህዋሶች በቁጥራቸው ከቀይ የደም ህዋሶች ያንሳሉ፡፡ መ) ነጭ የደም ህዋሶች ወጥ የሆነ ቅርፅም አላቸው፡፡ 25. ፕሌትሌቶች የደም ህዋሶች ተግባራቸው ሰውነታችን ሲደማ ብዙ ደም እንዳይፈስ ለማርጋት ነው፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 26. ከሚሀተሉት ውስጥ የደም ጥቅም ያልሆነው የቱ ነው? ሀ) ደም እንዲረጋ ማድረግ ለ) ምግቦችን ወደ ተለያዩ የአክል ህዋሶች ለማሰራጨ ሐ) አየርን ማስተላለፍ እና የተቃጠለ አየር ከሰውነት ለማስወገድ ይጠቅማል መ) በሽታን አለመከላከል 27. ደምን ከልብ ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ያሰራጫል፡፡ ደም በከፍተኛ ደረጃ ስለሚረጩ በጣም ወፍራም ግድግዳ አላቸው፡፡ ሀ) ደም ቅዳ (Artery) ለ) ደም መልስ (Vein) ሐ) ቀጫጭን የደም ሥሮች (Capillary) መ) ሁሉም መልስ ናቸው 28. ደምን ከተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ወደ ልብ ይመልሳል፡፡ ሀ) ደም ቅዳ (Artery) ለ) ደም መልስ (Vein) ሐ) ቀጫጭን የደም ሥሮች (Capillary) መ) ሁሉም መልስ ናቸው 29. ለሰውነታችን ህዋሶች በጣም ቅርብ የሆኑ የደም ሥሮች ናቸው፡፡ በጣም ቀጫጭንና ስስ ግድግዳ ያላቸው ሲሆን ደም ቅዳንና ደም መልስን ያገናኛሉ፡፡ ሀ) ደም ቅዳ (Artery) ለ) ደም መልስ (Vein) ሐ) ቀጫጭን የደም ሥሮች (Capillary) መ) ሁሉም መልስ ናቸው 30. ደም ምግብንና አየርን በሰውነታችን ውስጥ ያሰራጫል፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 31. ሁሉም የደም ሥሮች ወፍራም ግድግዳ አላቸው፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 32. ደምን ወደ ልብ የሚመልስ የደም ሥር ደም ቅዳ ነው፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ 33. የደም ሥሮችን በውጫዊ ሰውነታችን ላይ ማየት እንችላለን፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 34. ቀጫጭን የደም ሥሮች ደም ቅዳንና ደም መልስን ያገናኛሉ፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 35. ልባችን ስንት ዋና ዋና ልበ ገንዳዎች አሉት? ሀ) 1 ለ) 2 ሐ) 3 መ) 4 36. ከግራ የተቀበለውን ደም በአኦርታ (ትልቁ ደም ቅዳ) ውስጥ ወደ ክፍሎች ይረጫል፡፡ ሀ) ግራ አቀባይ ልበ ገንዳ (Left ventricle) ለ) ቀኝ ተቀባይ ልበ ገንዳ (Right auricle) ሐ) ግራ ተቀባይ ልበ ገንዳ (Left auricle) መ) ቀኝ አቀባይ ልበ ገንዳ(Right ventricle) 37. በኦክስጂን ያልበለፀገ ደም ከትልቁ ደም መልስ ተቀብሎ ወደ ቀኝ አቀባይ ልበ ገንዳ ይልካል፡፡ ሀ) ግራ አቀባይ ልበ ገንዳ (Left ventricle) ለ) ቀኝ ተቀባይ ልበ ገንዳ (Right auricle) ሐ) ግራ ተቀባይ ልበ ገንዳ (Left auricle) መ) ቀኝ አቀባይ ልበ ገንዳ(Right ventricle) 38. ከሳንባ በኦክስጂን የበለፀገ ደም በፑልሞናሪ ቨይን (Pulmonary vein) ተቀበሎ ወደ ግራ አቀባይ ልበ ገንዳ ይልካል፡፡ ሀ) ግራ አቀባይ ልበ ገንዳ (Left ventricle) ለ) ቀኝ ተቀባይ ልበ ገንዳ (Right auricle) ሐ) ግራ ተቀባይ ልበ ገንዳ (Left auricle) መ) ቀኝ አቀባይ ልበ ገንዳ(Right ventricle) ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ 39. ከቀኝ ተቀባይ ልበ ገንዳ የተቀበለውን ደም በፑልሞናሪ አርተሪ (Pulmonary artery) ወደ ሳንባ ይረጫል፡፡ ሀ) ግራ አቀባይ ልበ ገንዳ (Left ventricle) ለ) ቀኝ ተቀባይ ልበ ገንዳ (Right auricle) ሐ) ግራ ተቀባይ ልበ ገንዳ (Left auricle) መ) ቀኝ አቀባይ ልበ ገንዳ(Right ventricle) 40. የልብ ጠቀሜታ ሀ) ደም መርጨት ለ) አክስጂንና ምግብን ለሕብረ ሕዋሳት ማድረስ ሐ) ካርቦን ዳይኦክሳይድንና ቆሻሻን ከሰውነታችን ውስጥ ማስወገድ መ) ሁሉም መልስ ናቸው 41. በኦክስጂን የበለፀገ ደም ከሳንባ→ፑልሞናሪ ቬይን→ግራ ተቀባይ ልበ ገንዳ→ግራ አቀባይ ልበ ገንዳ→ትልቁ ደም ቅዳ→ወደ ሰውነት አካል ይሰራጫል፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 42. በኦክስጂን ያልበለፀገው ደም ደግሞ ከሰውነት→ትልቁ ደም መልስ→ቀኝ ተቀባይ ልበ ገንዳ→ቀኝ አቀባይ ልበ ገንዳ→ፑልሞናሪ አርተሪ→ ወደ ሳንባ ይመለሳል፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 43. የልብ ትርታ መለኪያ መሳሪያ ምን የባላል ሀ) ኪሎ ግራም ለ) ስቴቶስኮፕ ሐ) ቴርሞ ሜትር መ) አኒሞ ሜትር ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ የሚከተለውን ስዕል መሠረት በማድረግ ከተራ ቁጥር 4 4 —49 ያሉትን ጥያቄዎች መልስ፡፡ 44. ቀኝ ተቀባይ ልበ ገንዳን የሚያመለክተው ፊደል የቱ ነው? ሀ) ሀ ለ) ለ ሐ) ሐ መ) መ 45. ቀኝ አቀባይ ልበ ገንዳን የሚያመለክተው ፊደል የቱ ነው? ሀ) ሀ ለ) ለ ሐ) ሐ መ) መ 46. ግራ ተቀባይ ልበ ገንዳን የሚያመለክተው ፊደል የቱ ነው? ሀ) ሀ ለ) ለ ሐ) ሐ መ) መ 47. ግራ አቀባይ ልበ ገንዳን የሚያመለክተው ፊደል የቱ ነው? ሀ) ሀ ለ) ለ ሐ) ሐ መ) መ 48. በኦክስጂን የበለፀገውን ደም የሚሸከሙት ፊደላት እነማን ናቸው? ሀ) ሀ እና ለ ለ) ለ እና ሐ ሐ) ሐ እና መ መ) መ እና ሀ 49. በኦክስጂን ያልበለፀገውን ደም የሚሸከሙት ፊደላት እነማንናቸው? ሀ) ሀ እና ለ ለ) ለ እና ሐ ሐ) ሐ እና መ መ) መ እና ሀ ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ 2.2 ጉርምስናና ኮረዳነት 50. በጉርምስናና በኮረዳነት ወቅት የሚታዩት አካላዊና የባህሪ ለውጦች ሀ) ስነ ሕይወታዊ ለውጦች ይባላሉ ለ) በዕድገት የሚመጣ ጤናማ የሆነ የአካልና የባህሪ ለውጥ ነው፡፡ ሐ) በወንዶች እና በሴቶች ላይ የሚታዩት የአካል እና የባህሪ ለውጥ የተለያዩ ናቸው፡፡ መ) ሁሉም መልስ ናቸው 51. ወንዶች ልጆች ላይ አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ለውጦች መታየት የሚጀምሩት በስንት ዓመት ባሉት የእድሜ ክልሎች ውስጥ ነው፡፡ ሀ) 10-12 ለ) 12-14 ሐ) 14-16 መ) 16-18 52. በጉረምስና ወቅት የሚታይ ስነሕወታዊ ለውጥ አይደለም ሀ) የድምፅ መጎርነን ለ) ትከሻ እና ደረት ይሰፋል ሐ) ጡንቻዎች መዳበር መ) መልሱ የለም 53. በጉረምስና ወቅት የሚታይ ስነሕወታዊ ለውጥ ሀ) በፊት ላይ፣ በብብት ስር እና በብልት አካባቢ ፀጉር ይበቅላል ለ) የወንድ ዘርፈ ፈሳሽ መመንጨት ይጀምራል ሐ) የሆነ የክብደት እና የቁመት መጨመር ይታያል መ) ሁሉም መልስ ናቸው 54. በሴት ልጆች ላይ አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ለውጦች መታየት የሚጀምሩት በስንት ዓመት ባሉት የእድሜ ክልሎች ውስጥ ነው፡፡ ሀ) 10-12 ለ) 11-13 ሐ) 13-15 መ) 15-18 55. በኮረዳነት ወቅት የሚታይ ስነሕወታዊ ለውጥ አይደለም ሀ) በብብት ስር እና በብልት አካባቢ ፀጉር ይበቅላል ለ) የዳሌ መስፋት ይታያል ሐ) ድምፅ ይቀጥናል፤ በብብት ስር እና በብልት አካባቢ ፀጉር ይበቅላል መ) መልሱ የለም 56. በኮረዳነት ወቅት የሚታይ ስነሕወታዊ ለውጥ ሀ) የጡት ማጎጥጎጥ (ማደግ) ይጀምራል ለ) የወር አበባ መታየት ይጀምራል ሐ) የሆነ የክብደት እና የቁመት መጨመር ይታያል መ) ሁሉም መልስ ናቸው ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ 57. የወር አበባ ንፅህና ማለት ሴቶች አላስፈላጊ የሆኑ የደም ቆሻሻዎችን የሚያስወግዱበት ተፈጥሮአዊ ክስተት ነው፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 58. የወር አበባ በአማካኝ በየ28 ቀናት በማህፀንና በእንቁልጢ ውስጥ የሚካሄድ ወርሃዊ ዑደት ነው፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 59. አንዲት ልጃገረድ ለአቅመ ሔዋን በደረሰችበት ልጅ መውለድ የምትችልበትና የምትጀምርበት የዕድሜ ክልል ነው፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 60. በወር አበባ ጊዜ የማይከሰት ሂደት ሀ) የማህፀን ግድግዳ በደም ስሮች እና ሽፋን ሕብረ-ሕዋሳት መደራጀት፡፡ ለ) እንቁላል ከእንቁልጢ መውጣት እና ወደ ማህፀን ቦይ መግባት፡፡ ሐ) ፅንስ ባለመከናወኑ የማህፀን ግድግዳ መፈራረስ፡፡ መ) ደም በከረቤዛ በኩል አይወገድም 61. የወር አበባ ዑደት የሚታይበት ዕድሜ ክልል ሀ) ከ12 - 55 ዓመት ለ) ከ25 - 60 ዓመት ሀ) ከ18 - 45 ዓመት ለ) ከ12 - 35 ዓመት 62. ጾታዊ ጥቃት የሚባለው ሰዎች ለግል ፍላጎታቸው እና ጥቅማቸው ብለው በሌሎች ሰዎች ላይ ፆታን መሠረት ያደረገ ትንኮሳና አስገድዶ መድፈር ነው፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ 2.3 የሰው ሥርዓተ ትንፈሳ ክፍሎች 63. ትንፈሳ ማለት ኦክሲጅን ወደ ሰውነታችን ውስጥ የማስገባትና ካርበን ዳይኦክሳይድን ወደ ውጭ የማስወጣት ሂደት ነው፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 64. አየር ወደ ውስጥ ስንምግ (ስናስገባ) ሀ) ሳንባችን በአየር ይሞላል ለ) አየር ከሳንባችን ይወጣል ሐ) ደረታችን ይቀንሳል መ) ሁለቱ መልስ ናቸው 65. ከሚከተሉት ሀሰት የቱ ነው? ሀ) ሁለቱ ሳንባዎቻችን በደረታችን ውስጥ አሉ ለ) ሳንባዎቻችን ትልልቅ ስፖንጅ መሰል አካላት ናቸው ሐ) ሳንባዎቻችን በጡንቻ የተከበበ ነው መ) ሳንባዎቻችን ለትንፈሳ የምንገለገልበት አካል ነው 66. አየር ያሞቃል፣ ቆሻሻንና ጀርምን ያጣራል፡፡ ሀ) የአፍንጫ ቀዳዳ(Nasal cavity) ለ) አፍ(Mouth) ሐ) ሰርን(Nostril) መ) ድህረ-አፍ (pharynx) 67. ወደ ዐብይ ትንቧ ለሚገባውና ለሚወጣው አየር መተላለፊያ ነው፡፡ ሀ) የአፍንጫ ቀዳዳ(Nasal cavity) ለ) አፍ(Mouth) ሐ) ሰርን(Nostril) መ) ድህረ-አፍ (pharynx) 68. ወደ ባላትንቧ ለሚገባውና ለሚወጣው አየር መተላለፊያ በመሆን ያገለግላል፡፡ ሀ) ዐብይ ትንቧ (trachea) ለ) ባላ ትንቧ(ተገንጣይ የአየር ቧንቧ) (bronchi) ሐ) ደቂቅ ትንቧ (bronchiole) መ) ትንከረት(የአየር ከረጢት) (alveoli) 69. ከዐብይ ትንቧ ወደ ሳንባ ለሚገባውና ለሚወጣው አየር መተላለፊያ የመተንፈሻ አካል ነው፡፡ ሀ) ዐብይ ትንቧ (trachea) ለ) ባላ ትንቧ(ተገንጣይ የአየር ቧንቧ) (bronchi) ሐ) ደቂቅ ትንቧ (bronchiole) መ) ትንከረት(የአየር ከረጢት) (alveoli) ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ 70. አየር ወደ አየር ትንከረት(አየር ከረጢት) መግቢያና መውጫ በመሆን ይጠቅማል፡፡፡፡ ሀ) ዐብይ ትንቧ (trachea) ለ) ባላ ትንቧ(ተገንጣይ የአየር ቧንቧ) (bronchi) ሐ) ደቂቅ ትንቧ (bronchiole) መ) ትንከረት(የአየር ከረጢት) (alveoli) 71. ለኦክስጂንና ለካረቦን ዳይኦክሳይድ ወደ ደም ውስጥ መግቢያ እና መውጫ ሆኖ ያገለግላል፡፡፡ ሀ) ዐብይ ትንቧ (trachea) ለ) ባላ ትንቧ(ተገንጣይ የአየር ቧንቧ) (bronchi) ሐ) ደቂቅ ትንቧ (bronchiole) መ) ትንከረት(የአየር ከረጢት) (alveoli) 72. ወደ ውስጥ ስንተነፍስ አየር ወደ ሳንባችን ለመድረስ የሚያልፍባቸው የመተንፈሻ አካላት በቅደም ተከተል ሲቀመጡ፡- ሀ) የአፍንጫ ቀዳዳ -> ድህረ-አፍ -> ዐብይ የአየር ቧንቧ -> ተገንጣይ የአየር ቧንቧ -> ሰርን -> ደቂቅ ትንቧ - > የአየር ከረጢት ናቸው፡፡ ለ) የአፍንጫ ቀዳዳ -> ሰርን -> ተገንጣይ የአየር ቧንቧ -> ደቂቅ ትንቧ - > የአየር ከረጢት -> ድህረ-አፍ -> ዐብይ የአየር ቧንቧ ናቸው፡፡ ሐ) የአፍንጫ ቀዳዳ -> ሰርን -> ድህረ-አፍ -> ዐብይ የአየር ቧንቧ -> ደቂቅ ትንቧ - > ተገንጣይ የአየር ቧንቧ - > የአየር ከረጢት ናቸው፡፡ መ) የአፍንጫ ቀዳዳ -> ሰርን -> ድህረ-አፍ -> ዐብይ የአየር ቧንቧ -> ተገንጣይ የአየር ቧንቧ -> ደቂቅ ትንቧ - > የአየር ከረጢት ናቸው፡፡ 73. ሁለቱ ሳንባዎቻችን በሰውነታችን ደረት ወና በሚባል ትልቅ ክፍት ቦታ ውስጥ ከወፍራም ጡንቻዎች እና የጎድን አጥንቶች እንደ አጥር ከበው ከጉዳት በሚጠብቁት ቦታዎች ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 74. በአፍ ከመተንፈስ ይልቅ በአፍንጫ መተንፈስ ይመረጣል ምክንያቱም ከአየር ጋር ተቀላቅለው የሚገቡትን ጀርሞችንና ቆሻሻዎችን በሰርን ወና ውስጥ በሚገኙ ጥቃቅን ፀጉሮች አማካኝነት ተጣርተው ወደ አየር ከረጢት ይደርሳሉ፡፡ ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 75. __________ ወደ ታች ሲወርድ የደረት ወና ስለሚሰፋ የአየር ግፊት ይቀንሳል፡፡ ወደ ቦታው ሲመለስ ደግሞ የአየር ግፊት ስለሚጨምር ወደ ውጭ እንተነፍሳለን፡፡ ሀ) ድልሺ ለ) ሰርን ሐ) ድህረ-አፍ መ) ሳንባ ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ 76. ሥርዓተ ትንፈሳ ለምን ይጠቅማል? ሀ) ለማውራት እና ለማሽተት፣ ለ) ኦክስጂንን ለሕዋሶቻችን ማሰራጨት እና ቆሻሻ ነገሮችን (ካርቦን ዳይኦክሳይድ) ማስወገድ ሐ) በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የሙቀትና የቅዝቃዜ መጠን ተመጣጣኝ እንዲሆን ማድረግ እና የአየር መተላለፍያ መንገዶችን ከጉዳት መከላከል መ) ሁሉም መልስ ናቸው የሚከተለውን ስዕል መሠረት በማድረግ ከተራ ቁጥር 4 4 —49 ያሉትን ጥያቄዎች መልስ፡፡ ፡፡ 77. ምግብና አየር በጋራ የሚተላለፍበት የአካል ክፍል የሚያመለክተው ቁጥር ስንት ነው? ሀ) 2 ለ) 3 ሐ) 7 መ) 8 78. ግራ ሳንባ እና ቀኝ ሳንባን በቅደም ተከተል የሚያመለክቱት ቁጥሮች ስንትና ስንት ናቸው? ሀ) 10 እና 5 ለ) 13 እና 4 ሐ) 5 እና 9 መ) 11 እና 6 79. ወደ ሳንባ ለሚገባው እና ከሳንባ ለሚወጣው አየር መተላለፊያ ሁኖ የሚያገለግለው ቁጥር ስንት ነው? ሀ) 2 ለ) 3 ሐ) 7 መ) 8 ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ 80. ከአየር ጋር የገቡትን ቆሻሻዎችን በማጣራት ንጹህ አየር የሚሰጠን የአካላችን ክፍል የሚያመለክተው ቁጥር ስንት ነው? ሀ) 12 ለ) 1 ሐ) 7 መ) 2 81. የአየር ልውውጥ የሚደረግበትን ቦታ የሚያመለክተው ቁጥር ስንት ነው? ስሙን ጥቀሱ፡፡ ሀ) 10 ለ) 11 ሐ) 4 መ) 9 82. ካርቦን ዳይኦክሳይድ ለመወገድ የሚያልፍባቸውን የሥርዓተ ትንፈሳ አካላት የሚያመለክቱትን ቁጥሮች በቅደም ተከተል አስቀምጥ ሀ) 11 > 10 > 9 > 8 > 7 > 12 > 1 ሀ) 11 > 10 > 9 > 8 > 7 > 12 > 2 ሐ) 1 > 12 > 7 > 8 > 9 > 10 > 11 መ) 10 > 11 > 9 > 8 > 7 > 12 > 1 83. አየር ወደ አየር ከረጢት እንዲገባና እንዲወጣ የሚያደርገውን የሚያመለክተው ቁጥር ስንት ነው? ሀ) 10 ለ) 11 ሐ) 4 መ) 9 84. አየርን ከሰውነታችን ወደ ውጭ የምናስወጣበት ሂደት ደግሞ ምን ይባላል? ሀ) ምጋት ለ) ኢምጋት ሐ) ኦክሲጅን መ) ካረበን ዳይኦክሳይድ 85. አየርን ወደ ሰውነታችን የምናስገባበት ሂደት ምን ይባላል? ሀ) ምጋት ለ) ኢምጋት ሐ) ኦክሲጅን መ) ካረበን ዳይኦክሳይድ 86. ምጋት ጊዜ ምን ያህል ኦክስጂን እና ምን ያህል ካረበን ዳይኦክሳይድ ወደ ሰውነታችን የምናስገባው? ሀ) 21% እና 4 % ለ) 16% እና 0.03 % ሐ) 21% እና 0.03 % መ) 16% እና 4 % 87. ኢምጋት ጊዜ ምን ያህል ኦክስጂን እና ምን ያህል ካረበን ዳይኦክሳይድ ከሰውነታችን ያስወጣል? ሀ) 21% እና 4 % ለ) 16% እና 0.03 % ሐ) 21% እና 0.03 % መ) 16% እና 4 % 88. በምጋት እና ኢምጋት ጊዜ ምን ያህል ናይትሮጂን የምናስገባውና የምናስወጣው? ሀ) 21% ለ) 16% % ሐ) 78% መ) 4 % ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ 89. በምጋት እና ኢምጋት ጊዜ የምናስገባውና የምናስወጣው የውሃ ትነት እና ሙቀት ተመሳሳይ ነው? ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው በ “ሀ” ስር የቀረቡትን ተግባራት “ለ” ስር ከቀረቡት መተንፈሻ አካት ጋር አዛምዱ፡፡ ሀ ለ 90. ወደ አየር ከረጢት መግቢያና መውጫ ሀ) ሰርን 91. አየር መግቢያና መውጫ ለ) ባላትንቧ 92. ኦክስጂን እና ካረቦን ክልቶኦክሳይድ ወደ ደም መግቢያ እና መውጫ ሐ) የአፍንጫ ቀዳዳ 93. ወደ ትንቧ የሚገባና የሚወጣ አየር መተላለፊያ መ) ደቂቅ ትንቧ 94. አየር ያሞቃል፤ ጀርምንና ቆሻሻን ያጣራል ሠ) ድህረ-አፍ 95. ከ ትንቧ ወደ ሳንባ ለሚገባ ረ) የአየር ከረጢት እና ለሚወጣ አየር መተለላለፊያ ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ 2.4 ድብልቅ (mixture) 96. ሁለትና ከሁለት በላይ የሆኑ ልዩ ቁሶች አካላዊ (physical) በሆነ መንገድ በመጣመር የሚፈጥሩት የቁስ አይነት ምንድን ነው? 97. ሀ) ጠጣር ለ) ድብልቅ ሐ) ሙሙት መ) ሁሉም መልስ ናቸው 98. ከሚከተሉት ውስጥ አካላዊ (physical) በሆነ መንገድ የሚደባለቁ እነማን ናቸው? ሀ) የስኳርና የውሃ ድብልቅ ለ) የጨውና የውሃ ድብልቅ ሐ) የስኳርና የአሸዋ ድብልቅ መ) ሁሉም መልስ ናቸው 99. ከሚከተሉት ትክክለኛው የቱ ነው? ሀ) ቁሶች አካላዊ (physical) በሆነ መንገድ በመጣመር የሚፈጥሩት የቁስ አይነት የራሳቸውን ባህሪ አይለውጡም ያልተለመደም ባህሪ አያሳዩም ለ) ቁሶች አካላዊ (physical) በሆነ መንገድ በመጣመር የሚፈጥሩት የቁስ አይነት የራሳቸውን ባህሪ አይለውጡም ያልተለመደም ባህሪ አያሳዩም ሐ) ሀ እና ለ መልስ ናቸው መ) መልሱ የለም 100. በድብልቅ ውስጥ የሚገኙ ምንዝሮችን በ አይን ወይም በአጉሊ መነጸር መለየት የሚቻሉና የማይቻሉ መሆናቸውን መሰረት በማድረግ ድብልቆች ምን ሊባሉ ይችላሉ? ሀ) ዋህድ-ዘር ድብልቆች (Homogeneous mixtures) ለ) ልይ-ዘር ድብልቆች (hetrogeneous mixtures) ሐ) ሀ እና ለ መልስ ናቸው መ) መልሱ የለም 101. ዋህድ-ዘር ድብልቆች (Homogeneous mixtures) ሀ) በአብዛኛው ዋህድ-ዘር ድብልቆች ሙሙት ናቸው ለ) በምንዝሮቻቸውም መካከል ልዩነት የለምና መቀላሉ መለያየት አንችልም፡፡ ሐ) የድብልቁ ይዘት ወጥና ተመሳሳይ ነው፡፡ መ) ሁሉም መልስ ናቸው 102. በድብልቅ ውስጥ ያሉትን ምንዝሮች በዓይን ወይም በአጉሊ መነጸር በመታገዝ ለይተን ማየት የምንችል ከሆነ ድብልቁ ምን ይባላል? ሀ) ዋህድ-ዘር ድብልቆች (Homogeneous mixtures) ለ) ልይ-ዘር ድብልቆች (hetrogeneous mixtures) ሐ) ሀ እና ለ መልስ ናቸው መ) መልሱ የለም ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ 103. ምንዝሮቹን በአካላዊ (ፊዚካዊ) ዘዴ መለያየት ይቻላል፡፡ ድብልቅን ወደ ምንዝሮቻቸው ለመለየት ምን ማንገድ መለየት ይቻላል? ሀ) የድብልቁን አካላዊ ባህሪ ማወቅ ለ) ድብልቁን በመጠን (size) መለየት ሐ) ድብልቁን በነጥበ- ፍሌት (boiling point)፣ በነጥበ- ቅልጠት (melting point) እና በእፍግታ (density) መለየት መ) ሁሉም መልስ ናቸው 104. ጥሊያ (Filtration) ምን ማለት ነው? ሀ) ጥቃቅን ቀዳዳዎች ባሉት እቃ ላይ የፈሳሽና ያልሟሙ የጠጣር ድብልቅን የምንለይበት ዘዴ ነው፡፡ ለ) ካልሟሙ ጠጣሮች ወይም ፈሳሾች የምንለይበት ዘዴ ነው፡፡ ሐ) ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ፈሳሾችን በድብልቅ ውስጥ ባላቸው የነጥበ ፍሌት ልዩነት የምንለይበት ዘዴ ነው፡፡ መ)የሟሙ ጠጣሮችን ከአሟሚው ፈሳሽ የምንለይበት ዘዴ ነው፡፡ 105. ቀረራ (Decanitation) ምን ማለት ነው? ሀ) ጥቃቅን ቀዳዳዎች ባሉት እቃ ላይ የፈሳሽና ያልሟሙ የጠጣር ድብልቅን የምንለይበት ዘዴ ነው፡፡ ለ) ካልሟሙ ጠጣሮች ወይም ፈሳሾች የምንለይበት ዘዴ ነው፡፡ ሐ) ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ፈሳሾችን በድብልቅ ውስጥ ባላቸው የነጥበ ፍሌት ልዩነት የምንለይበት ዘዴ ነው፡፡ መ)የሟሙ ጠጣሮችን ከአሟሚው ፈሳሽ የምንለይበት ዘዴ ነው፡፡ 106. ንጥረት (Distillation) ምን ማለት ነው? ሀ) ጥቃቅን ቀዳዳዎች ባሉት እቃ ላይ የፈሳሽና ያልሟሙ የጠጣር ድብልቅን የምንለይበት ዘዴ ነው፡፡ ለ) ካልሟሙ ጠጣሮች ወይም ፈሳሾች የምንለይበት ዘዴ ነው፡፡ ሐ) ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ፈሳሾችን በድብልቅ ውስጥ ባላቸው የነጥበ ፍሌት ልዩነት የምንለይበት ዘዴ ነው፡፡ መ)የሟሙ ጠጣሮችን ከአሟሚው ፈሳሽ የምንለይበት ዘዴ ነው፡፡ ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ 107. ትነት (Evaporation) ምን ማለት ነው? ሀ) ጥቃቅን ቀዳዳዎች ባሉት እቃ ላይ የፈሳሽና ያልሟሙ የጠጣር ድብልቅን የምንለይበት ዘዴ ነው፡፡ ለ) ካልሟሙ ጠጣሮች ወይም ፈሳሾች የምንለይበት ዘዴ ነው፡፡ ሐ) ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ፈሳሾችን በድብልቅ ውስጥ ባላቸው የነጥበ ፍሌት ልዩነት የምንለይበት ዘዴ ነው፡፡ መ)የሟሙ ጠጣሮችን ከአሟሚው ፈሳሽ የምንለይበት ዘዴ ነው፡፡ 108. ዘይትና የውሃ ድብልቅ፣ ቡናን ማስከን በማድረግ ያልሟሟ ጠጣሩን ልዩ - ቁስ ደግሞ ማጥለያው ላይ እንዲቀር በማድረግ ድብልቅን መለየት የምን ምሳሌ ነው? ሀ) ጥሊያ (Filtration) ለ) ቀረራ (Decanitation) ሐ) ንጥረት (Distillation) መ) ትነት (Evaporation) 109. ድፍድፍ ነዳጅ የሚጣራው እንዲሁም በሀገራችን በኢትዮጵያ የሀበሻ አረቄ የሚወጣው በምን ዘዴ ነው? ሀ) ጥሊያ (Filtration) ለ) ቀረራ (Decanitation) ሐ) ንጥረት (Distillation) መ) ትነት (Evaporation) 110. የጨውና የውሃ ድብልቅን ሙሙት ጨውንና ውሀውን ለመለየት ምን ዘዴን እንጠቀማለን? ሀ) ጥሊያ (Filtration) ለ) ቀረራ (Decanitation) ሐ) ንጥረት (Distillation) መ) ትነት (Evaporation) ሀ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች ከተሰጡት አማራጮች ውስጥ ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ መልሱ፡፡ 111. ሁለት ፈሳሾችን ባላቸው የነጥበ ፍሌት ልዩነት የምንለይበት የመለያ ዘዴ የትኛው ነው? ሀ. ትነት ለ. ቀረራ ሐ. ጥሊያ መ. ንጥረት 112. ናፍጣን ከድፍድፍ ነዳጅ የምንለይበት የመለያ ዘዴ የትኛው ነው? ሀ. ንጥረት ለ. ትነት ሐ. ጥሊያ መ. ቀረራ 113. ሁለት ፈሳሾችን ባላቸው እፍግታ ልዩነት የምንለይበት የመለያ ዘዴ የትኛው ነው? ሀ. ጥሊያ ለ. ቀረራ ሐ. ትነት መ. ንጥረት ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ 2.5 ጉልበትና ጠቀሜታው 114. የሰው ልጅ ዕለት ተዕለት ለሚያከናውናቸው ተግባራት ጉልበት ይጠቀማል። ጉልበት ስራን የመስራት አቅም ነው። ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 115. ጉልበት ከተለያዩ የጉልበት ምንጮች ይገኛል። በዋናነት እነዚህ የጉልበት ምንጮች በሁለት/2/ ይመደባሉ። እነሱም ታዳሽ የጉልበት ምንጮች እና ታዳሽ ያልሆኑ የጉልበት ምንጮች ናቸው። ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 116. በቀላሉ ሊተኩ ወይም ሊታደሱ የሚችሉ የጉልበት ምንጮች ስንጠቀምባቸውም የማያልቁ እንድ የጸሐይ ብርሃን፣ ንፋስና ውሃ ምን ይባላሉ? ሀ) ታዳሽ የጉልበት ምንጮች ለ) ታዳሽ ያልሆኑ የጉልበት ምንጮች ሐ) ሀ እና ለ መልስ ናቸው መ) መልስ የለም 117. በቀላሉ ሊተኩ ወይም ሊታደሱ የማይችሉ የጉልበት ምንጮች እና ስንጠቀምባቸውም የሚያልቁ እንደ የማገዶ እንጨት፣ የድንጋይ ከሰል፣ የባትሪ ድንጋይ፣ የተፈጥሮ ነዳጆች እንደ ቤንዚን፣ናፍጣ፣ነጭ ጋዝ አይነቶች ምን ይባላሉ? ሀ) ታዳሽ የጉልበት ምንጮች ለ) ታዳሽ ያልሆኑ የጉልበት ምንጮች ሐ) ሀ እና ለ መልስ ናቸው መ) መልስ የለም 2.6 ቀላል መኪና (simple machine) 118. ሀይልን በማጎልበት እና ጉልበትን በመቆጠብ ስራን በፍጥነት ለመስራት የሚያግዝ መሳሪያ መኪና(machine) ይባላል። ቀላል መኪና/ simple machine/፦ ማለት ስራን በቀላሉ ለመስራት የሚያስችል መሳሪያ ማለት ነው። ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ 119. አንድ ቀላል መኪና ስራ ሰራ የሚባለው አንድን መጠነቁስ የተወሰነ ከፍታ ሲያነሳ ወይም የተወሰነ ርቀት በሚያንቀሳቅስበት ጊዜ ነው። ሀ) እውነት ለ) ሀሰት ሐ) መልሱ የለም መ) ሁሉም መልስ ናቸው 120. ቀላል መኪናዎች በስንት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላሉ? ሀ) 2 ለ) 4 ሐ) 6 መ) 8 121. __________ማለት የቀላል ማሽን አይነት ሲሆን ክብደት ያላቸውን ነገሮች ለመጫን ይጠቅማል፡፡ ምሳሌ ፎቅ ለመውጣት የምነጠቀምበት ደረጃ ሀ) ዘንባይ ወለል ለ) መፈንቅል ሐ) ሽብልቅ መ) ሽክርክሪትና ዘንግ 122. _________ ረጅም የእንጨት ወይም የብረት ዘንግ ሲሆን ድጋፍ በመጠቀም ድንጋይ ለመፈንቀል ወይም ሚስማርን በመዶሻ ለመንቀል ይጠቅማል፡፡ ሀ) ዘንባይ ወለል ለ) መፈንቅል ሐ) ሽብልቅ መ) ሽክርክሪትና ዘንግ 123. _______ የቀላል ማሽን አይነት ሲሆን አንድን ነገር ለሁለት ለመክፈል የሚረዳ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ቢላዋ፣ መጥረቢያ ሀ) ዘንባይ ወለል ለ) መፈንቅል ሐ) ሽብልቅ መ) ሽክርክሪትና ዘንግ 124. _______ ነገሮችን ለመስቀልና ከጉርጓድ ውሃ ለማውጣት የምንጠቀምበት ቀላል ማሽን ነው፡፡ ሀ) ዘንባይ ወለል ለ) መፈንቅል ሐ) ሽብልቅ መ) ሽክርክሪትና ዘንግ 125. ___________ሁለት የሚሽከረከሩ ክብ ነገሮችን ትልቅና ትንሽ አንድ ላይ የያዘ ሲሆን ትንሹ ላይ ጥረት ሲተገበር ትልቁ ጭነትን ለማንቀሳቀስ የሚጠቅም የቀላል መኪና አይነት ነው፡፡ ሀ) ዘንባይ ወለል ለ) መፈንቅል ሐ) ሽብልቅ መ) ሽክርክሪትና 126. ________________ነገሮችን አጥብቆ ለማሰር ጠንካራ የሆኑ እንደግድግዳ ያሉ ነገሮችን ለመሰርሰር የሚጠቅም ቀላል መኪና አይነት ነው፡፡ ሀ) መፍቻ ለ) መፈንቅል ሐ) ሽብልቅ መ) ሽክርክሪትና ሀ. የሚከተሉትን ቀላል መኪናዎች ከትክክለኛ አገልግሎታቸው ጋር አዛምዱ፡፡ ሀ ለ 127. ሰንደቅ ዓላማ ለማውጣት ሀ) ሽብልቅ 128. ከባድ ዕቃዎችን በመኪና ላይ ለመጫን ለ) ሽክርክሪትና ዘንግ 129. ውሃን ከጉድጓድ ለመቅዳት ሐ) ሽክርክሪት 130. ሚስማር ለመንቀል መ) መፈንቅል 131. አንድን ነገር ለሁለት ለመክፈል ሠ) ዘንባይ ወለል 132. አንድን ነገር አጥብቆ ለማሰር ረ) መፍቻ ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ፡፡ 133. 1) የቀላል መኪናን ምንነት ግለጹ። 134. 2) ቀላል መኪና ስራን በቀላሉ የሚሰራው እንዴት ነው? የደም ዑደት ማለት ኦክስጂንና አልሚ ምግቦች ለሰውነታችን ህዋሶች የማሰራጨት እንዲሁም ካርቦን ዳይኦክሳይድንና ሌሎች ቆሻሻዎች በደም አማካኝነት የሚሄዱበት ሂደት ነው፡፡ ሦስቱ የደማችን ህዋሶች፡- ነጭ የድም ህዋሶች፣ ቀይ የደም ህዋሶች እና ፕሌትሌቶች ናቸው፡፡ ደም በሰውነታች ውስጥ ብዙ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ ለምሳሌ፡- አየር ማስተላለፍ፣ ከበሽታ መከላከል፣ ደም ማርጋትና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ልብ በሰውነታችን ውስጥ በስተግራ ደረታችን አካባቢ ትንሽ ዝቅ ብሎ የሚገኝ በጡንቻዎች የተገነባ የውስጥ አካል ክፍል ነው፡፡ የወር አበባ ማለት በየ28 ቀናት በሴቶች ላይ የሚከሰት ስነ-ህይወታዊ ዑደት ነው፡፡ ሥርዓተ ትንፈሳ ማለት አየር ወደ ውስጥ የማስገባትና የማስወጣት ሄደት ነው። ምጋት ማለት አየር ወደ ሰውነታችን የማስገባት ሂደት ነው፡፡ ኢምጋት ማለት አየር ወደ ውጭ የማስወጣት ሂደት ነው፡፡ አየር የተለያዩ ጋዞች ተደባልቀው የሚፈጥሩት ልዩ-ቁስ ነው፡፡ የአየር ምንዝሮች ቢደባለቁም እንኳን የየራሳቸው ባህሪያት እንደያዙ ይቆያሉ፡፡ የዋህድ- ዘር ድብልቆች ሙሉ በሙሉ ስለሚዋሀዱ ምንዝሮቹን በዓይን ወይም በአጉሊ መነጸር በመታገዝ ለይተን ማየት አይቻልም፡፡ የልይ- ዘር ድብልቅ ምንዝሮች አይዋሀዱም፡፡ ስለዚህ ምንዝሮችን በአይን ወይም በአጉሊ መነጸር በመታገዝ ለይተን ማየት እንችላለን፡፡ የተለያዩ ድብልቆችን ወደ ምንዝሮቻቸው ለመለየት ጥሊያ፣ ቀረራ፣ ንጥረትና ትነት ዘዴዎችን በመጠቀም መለየት ይቻላል፡፡ ጉልበት ስራ የመስራት አቅም ነው። ጉልበት ምግብ ለማብሰል፣ለመጓጓዣ፣ለሙቀት ምንጭነት፣ለቤት ውስጥ ብርሃን፣ ለቴክኖሎጂ፣ለኢንዱስትሪና ለህክምና አገልግሎት ይጠቅማል። ቀላል መኪና ስራን በቀላሉ ለመስራት የሚያስችል መሳሪያ ነው። እንደ አካፋ፣ ዶማ፣ መዶሻ፣ ሚስማር፣ ቢላዋ፣ መቀስ፣ ምላጭ፣ ማንኪያ፣ ፒንሳ የመሳሰሉት መሳሪያዎች ቀላል መኪና ሊባሉ ይችላሉ። በዋናነት ስድስት(6) የቀላል መኪና ዓይነቶች አሉ። እነሱም፦ ዘንባይ ወለል፣ መፈንቅል፣ ሽብልቅ፣ ሽክርክሪትና ዘንግ፣ ሽክርክሪት እና መፍቻ ናቸው። ሀ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች ከተሰጡት አማራጮች ውስጥ ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ መልሱ፡፡ 135. ደም የሚረጨው የሰውነታችን አካል የቱ ነው? ሀ) ሳንባ ለ) አፍ ወና ሐ) ልብ መ) የደም ስር 136. ከሚከተሉት ውስጥ ወፍራሙ የልብ ክፍል የቱ ነው? ሀ) ቀኝ አቀባይ ለ) ግራ ተቀባይ ሐ) ቀኝ ተቀባይ መ) ግራ አቀባይ 137. በወንዶች ላይ የማይታይ አካላዊ ለውጥ የቱ ነው? ሀ) የደረት መስፋት ለ) የዳሌ መስፋት ሐ) የድምፅ መጎርነን መ) በፊት ላይ ፀጉር ማብቀል 138. የአየር ልውውጥ የሚካሄድበት ቦታ የቱ ነው? ሀ) አፍንጫ ለ) ሰርን ሐ) ትንቧ መ) ትንከረት 139. ደም ለማርጋት የሚጠቅመው የደም ህዋስ የቱ ነው? ሀ) ነጭ የደም ህዋስ ለ) ቀይ የደም ህዋስ ሐ) ፕላትሌቶች መ) ደም ቅዳ 140. አየር እና ምግብ በጋራ የሚተላለፍበት አካለችን የቱ ነው? ሀ) አፍ ወና ለ) ድህረ-አፍ ሐ) ባላትንቧ መ) ተገንጣይ ባላትንቧ 141. ከሚከተሉት ድብልቆች አንዱ የዋህድ ዘር ድብልቅ ነው? ሀ) አፈር ለ) ዘይትና ውሃ ሐ) የጨው ሙሙት መ) አሸዋና ውሃ 142. ኮምጣጤ ምን አይነት ድብልቅ ነው? ሀ) የዋህድ- ዘር ድብልቅ ሐ) ሀ ና ለ ለ) የልይ - ዘር ድብልቅ መ) ድብልቅ አይደለም 143. የናፍጣና የ ውሃ ድብልቅ በየትኛው አይነት የመለያ ዘዴ በቀላሉ ይለያሉ? ሀ) በትነት ለ) በቀረራ ሐ) በንጥረት መ) ጥሊያ 144. ከሚከተሉት ውስጥ የትንከረት ተግባር ያልሆነው የቱ ነው? ሀ) ትልቅ ቦታ ይሸፍናል ለ) ቀጭን ግድግዳ አለው ሐ) እርጥባማ ቦታ ነው መ) ዝቅተኛ የደም ክምችት አለው 145. የታችኛው የስርዓተ ትንፈሳ ክፍል የቱነው? ሀ) አፍወና ለ) ድህር አፍ ሐ) ሳንባ መ) የድምጽ ሳጥን 146. 12. የትኛው የስረዓተ ትንፈሳ ክፍል ነው ቅርፁን በመቀያየር ሳንባችን በስረዓት እንድንተነፍስ የሚያስችለው? ሀ) ድልሺ ለ) ሰርን ሐ) ትንከረት መ) አፍወና 147. ሁል ጊዜ ያለማቋረጥ በስራ ላይ የሚገኘው የሰውነታችን ክፍል የቱ ነው? ሀ) ሳንባ ለ) ልብ ሐ) አፍ መ) አይን 148. ነጭ የደም ህዋስ በሽታን እንዴት መከላከል ይችላል? ሀ) ኦክሲጅን ወደ ሰውነታችን ስለሚወስድ ለ) ቆሻሻን ከስረዓተ ትንፈሳ ስለሚያስወግድ ሐ) ሁሉም ደቂቅ ዘኣካላት ወደ ሰውነታችን እንዲገቡ ስለሚፈቅድ መ) ጀርምን መከላከል መቻሉ 149. ትንሹ የስረዓተ ትንፈሳ ክፍል የቱ ነው? ሀ) ሰርን ለ) አፍወና ሐ) ድህረ አፍ መ) ትንከረት 150. የደም ሥሮችን ዘርዝሩ፡፡ 151. ቀይ የደም ህዋስንና ነጭ የደም ህዋስን በቅርፃቸውና በጥቅማቸው አወዳድሩ፡፡ 152. የደም ዑደትን በመሣል ደም ቅዳ፣ ደም መልስ፣ ቀጫጭን የደም ሥሮችንና የልብ ክፍሎችን ሥዕል ሠርታችሁ አሳዩ፡፡ 153. በየትኛው የአካል ክፍል ብትተነፍሱ ይመረጣል? በአፍ ወይም በአፍንጫ? ለምን? 154. በጥሊያ የምንለያቸው ድብልቆች የምን ልዩነት ያላችው ናቸው? 155. በንጥረት የምንለያቸው ድብልቆች የምን ልዩነት ያላችው ናቸው? 156. በቀረራ የምንለያቸው ድብልቆች የምን ልዩነት ያላችው ናቸው? 157. በትነት የምንለያቸው ድብልቆች የምን ልዩነት ያላችው ናቸው? 158. ድብልቅን ወደ ምንዝሮቻቸው ለመለየት የሚያስችል አስተማማኝ የመለያ ዘዴ የትኛው ነው? ለምን? 159. የጉልበት መለኪያ አሀድ ምን ይባላል? 160. አንድን አካል የመግፋት ወይም የመጎተት ሄደት ነው፡፡ 161. በቀላል መኪና ላይ መኪናው ሥራ የሚሠራበት አካል _____________ይባላል፡፡ 162. አንድ አካል በእንቅስቃሴው የተነሳ ሊኖረው የሚችለው ጉልበት______________ይባላል፡፡