Grade 6 Environmental Science 12 PDF

Document Details

LustrousSavanna6540

Uploaded by LustrousSavanna6540

Abiyot Primary School

Tags

environmental science east africa geography african geography education

Summary

This document covers the location of East Africa, highlighting geographical features and discussing relative and absolute locations based on latitude and longitude using maps. It also touches upon geographic elements within the region including mountains, rivers, and lakes. It includes questions and activities to reinforce learning about the region.

Full Transcript

Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ ከምዕራፉ ትምህርት አጠቃላይ የሚጠበቁ ውጤቶች ተማሪዎች የዚህን ምዕራፍ ይዘቶች ተምራችሁ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፡-  አቅጣጫ የመለየት ክህሎትን ታዳብራላችሁ፡፡  መልክአ ምድራዊ አቀማመጥን፣ ጎግል የካርታ መፈለጊያ መተግ...

Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ ከምዕራፉ ትምህርት አጠቃላይ የሚጠበቁ ውጤቶች ተማሪዎች የዚህን ምዕራፍ ይዘቶች ተምራችሁ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፡-  አቅጣጫ የመለየት ክህሎትን ታዳብራላችሁ፡፡  መልክአ ምድራዊ አቀማመጥን፣ ጎግል የካርታ መፈለጊያ መተግበሪያንና ጎግል ኧርዝ (GPS, Google map and Google earth) በመጠቀም የቦታ አቀማመጥን የመለካትና የመመዝገብ ክህሎት ታዳብራላችሁ፡፡  ካርታን በማንበብ እና በመጠቀም ከሰዎች መረጃ ትለዋወጣላችሁ፡፡  ኬክሮስንና ኬንትሮስን በመጠቀም የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን በአፍሪካ ካርታ ላይ ታሳያላችሁ፡፡  በአፍሪካ ካርታ ላይ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን አንጻራዊና ፍጹማዊ መገኛን ታሳያላችሁ፡፡  የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን አንጻራዊ መገኛ የሚያመለክት ንድፍ ካርታ ትሠራላችሁ፡፡  የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን አጎራባች ሀገራት ትዘረዝራላችሁ፡፡ 1 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ የምዕራፉ ዋና ዋና ይዘቶች 1.1 የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ 1.2 በካርታ ላይ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ ከአጎራባች የአፍሪካ ሀገራትና ውሃማ አካላት አንጻር 1.3 የካርታ መፈለጊያ መተግበሪያንና ጎግል ኧርዝ (GPS, Google map and Google earth) በመጠቀም የተለያዩ ቦታዎችን መለየት መግቢያ አፍሪካ ከሰባቱ ክፍለ ዓለማት አንዱ አህጉር ነው፡፡ ይህ አህጉር በአምስት ቀጠናዎች ይከፈላል፡፡ እነዚህም፡- ምሥራቃዊ አፍሪካ፣ መካከለኛው አፍሪካ፣ ሰሜናዊ አፍሪካ፣ ደቡባዊ አፍሪካ እና ምዕራባዊ አፍሪካ ተብለው ይጠራሉ፡፡ አምስቱ ቀጠናዎች የተከለሉት ባህልን፣ ማኅበራዊ ትስሥርን እና መልክአ ምድራዊ አቀማመጥን መሠረት በማድረግ ነው፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ ከአምስቱ የአፍሪካ ቀጠናዎች በስፋቱ በሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ከአጠቃላይ የአፍሪካ መልክአ ምድር ይዘትም 21 በመቶ ይሸፍናል፡፡ ይህ ቀጠና በውስጡ 19 ሀገራትን ይይዛል፡፡ ከመልክአ ምድር አቀማመጥ አንጻር ሲታይ ምሥራቅ አፍሪካ በውስጡ የተለያየ የመሬት አቀማመጥ አለው፡፡ በቀጠናው በእሳተ ገሞራ የተፈጠሩ ትላልቅ ተራሮች፣ ዝቅተኛ ሥፍራዎች፣ ወንዞችና ሐይቆች ይገኛሉ፡፡ 2 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ 1.1 የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ ተማሪዎች ይህንን ንዑስ ርዕስ ተምራችሁ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፡-  አቅጣጫ የመለየት ክህሎትን ታዳብራላችሁ፡፡  ካርታን በማንበብ እና በመጠቀም ከሰዎች ጋር መረጃ ትለዋወጣላችሁ፡፡  በአፍሪካ ካርታ ላይ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን አንጻራዊና ፍጹማዊ መገኛን ታሳያላችሁ፡፡  የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን አንጻራዊ መገኛ የሚያመለክት ንድፍ ካርታ ትሠራላችሁ፡፡  ኬክሮስንና ኬንትሮስን በመጠቀም የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን በአፍሪካ ካርታ ላይ ታሳያላችሁ፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ አንጻራዊ መገኛ ቁልፍ ቃላት መገኛ ቋሚ መስመር ፍጹማዊ መገኛ አግዳሚ መስመር አንጻራዊ መገኛ የማነቃቂያ ጥያቄዎች ምሥራቅ አፍሪካ የት ይገኛል? አንጻራዊ መገኛ ማለት ምን ማለት ነው? የአፍሪካ ቀንድ ሀገራትን ዘርዝሩ፡፡ የምሥራቅ አፍሪካን አንጻራዊ መገኛ ግለጹ፡፡ 3 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ ምስል1.1 የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት የቡድን ውይይት 1.1ሀ ዓላማ፡ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን በካርታ ላይ መለየት መመሪያ፡ አምስት አምስት በመሆን ቡድን መሥርታችሁ ምስል1.1 ያለውን ካርታ በመመልከት በሚከተሉትን ጥያቄዎች ላይ ተወያይታችሁ ለመምህራችሁና ለክፍል ጓደኞቻችሁ አቅርቡ፡፡ 1. በምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ ስንት ሀገሮች አሉ? 2. የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን ዘርዝሩ፡፡ 3. የምሥራቅ አፍሪካን የሚያዋስኑ የአፍሪካ ሀገራት ዘርዝሩ፡፡ 4. በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኘው የአፍሪካ ትልቁ ደሴት ማን ይባላል? 4 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ ባለፉት የክፍል ደረጃዎች ስለ መገኛ ምንነት፣ ስለ አንጻራዊና ፍጹማዊ መገኛ ተምራችኋል፡፡ በዚህ የክፍል ደረጃ ደግሞ ስለ ምሥራቅ አፍሪካ አንጻራዊና ፍጹማዊ መገኛ ትማራላችሁ፡፡ መገኛ ማለት አንድን አካባቢ ወይም ሀገር በመሬት አካል ላይ የሚገኝበትን ቦታ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም መናገር ነው፡፡ መገኛን ለማወቅ የሚረዱ ሁለት መንገዶች አሉ:: እነዚህም አንጻራዊ መገኛ እና ፍጹማዊ መገኛ ይባላሉ፡፡ ሀ. አንጻራዊ መገኛ፡- የአንድን ሀገር መገኛ በልዩ ልዩ አቅጣጫ ከሚያዋስኑ ነገሮች ጋር በማነጻጸር የሚነገርበት መንገድ ነው፡፡ አንድን ቦታ የሚያዋስኑት ተራራዎች፣ በአካባቢው የሚገኙ ሌሎች ሀገሮች፣ የውሃ አካላትና የመሳሰሉት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አንጻራዊ መገኛን ለመግለፅ የአካባቢ ታዋቂ ቦታዎችን ስም እና ዓራቱ መሠረታዊ አቅጣጫዎችን (ሰሜን፣ ደቡብ፣ ምሥራቅ እና ምዕራብ) መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ ምስሌ፡ 1.2 የምሥራቅ አፍሪካ አንጻራዊ መገኛ ተግባር 1.1 ሀ የግልሥራ ዓላማ፡ የምሥራቅ አፍሪካን አንጻራዊ መገኛ መግለጽ፡፡ መመሪያ፡ ከላይ በምስል 1.2 ያለውን ካርታ በመመልከት የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሱ፡፡ 1. ቀይ ባህር ምሥራቅ አፍሪካን በየት በኩል ያዋስናል? 2. ምሥራቅ አፍሪካን የሚያዋስነው ትልቁ ውሃማ አካል ማን ነው? 3. ምሥራቅ አፍሪካን በምዕራብ በኩል የሚያዋስኑ የአፍሪካ ሀገራት እነማን ናቸው? በደቡብ አቅጣጫስ? 5 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ የምሥራቅ አፍሪካ ፍጹማዊ መገኛ ቁልፍ ቃላት  ፍጹማዊ መገኛ  ቋሚ መስመር  አግዳሚ መስመር ፍጹማዊ መገኛ ማለት ምን ማለት ነው? የምሥራቅ አፍሪካን ፍጹማዊ መገኛ አሳዩ፡፡ ለ. ፍጹማዊ መገኛ፡- ማለት አግድምና ቋሚ መስመሮችን በመጠቀም የአንድን አካባቢ ወይም ሀገር መገኛ የዲግሪ ልኬትን በመጠቀም ያመለክታል፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ ፍጹማዊ መገኛ በአፍሪካ ካርታ ላይ ከ180ሰሜን እስከ 270 ደቡብ ኬክሮስ፣ እንዲሁም ከ22 ምሥራቅ እስከ 510 28’ ምሥራቅ ኬንትሮስ ነው፡፡ የኬክሮስና የኬንትሮስ ማዕዘናዊ መለኪያዎች የኬክሮስና ኬንትሮስ መለኪያዎች ምንድን ናቸው? የኬክሮስ መለኪያዎች ከኬንትሮስ መለኪያዎች በምን ይለያሉ? ቋሚ መስመሮች (Meridians) እና ትይዩ መስመሮች (latitudes) በሉል እና በካርታ ላይ ብቻ የሚገኙ ቋሚ እና አግዳሚ መስመሮች ናቸው፡፡ ስለሆነም በመሬት ላይ ልናያቸው አንችልም፡፡ ኬክሮስ (latitudes) እና ኬንትሮስ (longitudes) ማዕዘናዊ ርቀትን (angular distances) ለመለካት ያገለግላሉ፡፡ በአግድም እና ቋሚ መስመሮች መካከል ያለው ርቀት በዲግሪ ይለካል፡፡ አግድም (ትይዩ) መስመሮች (parallels) አግድም መስመሮች ምንድን ናቸው? የአግድም መስመሮች ጠቀሜታ ምንድን ነዉ? አግድም መስመሮች በካርታ ወይም በሉል ላይ ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ ወይም ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ የተሰመሩ የሐሳብ መስመሮች ናቸው፡፡ የአግድም መስመሮች መነሻ በዜሮ ዲግሪ ላይ ይገኛል፡፡ ይህ መነሻ ቦታም የምድር ወገብ (Equator) ይባላል:: የምድር ወገብ መሬትን በሰሜንና በደቡብ ንፍቀ ክበብ በእኩል ቦታ ይከፍላል፡፡ ከዚህ 6 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ መስመር በስተሰሜን 90 ትይዩ መስመሮች ሲኖሩ፣ በስተደቡብም ይህንኑ ያሀል ቁጥር ያላቸው መስመሮች አሉ፡፡ በአጠቃላይ በሁለቱ ንፍቀ ክበባት 180 የአግድም መስመሮች ይገኛሉ፡፡ በእያንዳንዳቸው መስመሮች መካከል የአንድ ዲግሪ ልዩነት አለ:: በተጨማሪም ሁሉም መስመሮች ትይዩ ናቸው፡፡ በካርታ ወይም በሉል ላይ የሚታዩ አምስት ዐብይ ትይዩ መስመሮች አሉ፡፡ እነዚህም፡ - የምድር ወገብ (00) ፣ የካንሰር መስመር (23 ½0 ሰሜን) ፣ የካፕሪኮርን መስመር (23 ½0 ደቡብ) ፣ የአርክቲክ ክበብ (66 ½0 ሰሜን) እና የአንታርክቲክ ክበብ (66 ½0 ደቡብ) ናቸው፡፡ ምስል 1.3 (ሀ) ትይዩ መስመሮች ምስል 1.3 (ለ) ዋና ዋና ትይዩ መስመሮች ቋሚ (የማገር) መስመሮች (Meridians) ቋሚ መስመሮች ምንድን ናቸዉ? ቋሚ መስመሮች ከየት ወደ የት የተሰመሩ ናቸው? የቋሚ መስመሮች ጠቀሜታ ምንድን ነዉ? ቋሚ መስመሮች በካርታ ወይም በሉል ላይ ከሰሜን ወደ ደቡብ ወይም ከደቡብ ወደ ሰሜን ተሰምረው ይገኛሉ፡፡ አጠቃላይ ብዛታቸውም 360 ነው፡፡ በመካከላቸው ያለው ርቀት በዲግሪ ይለካል፡፡ ሁሉም ቋሚ መስመሮች በሰሜንና በደቡብ ዋልታ አካባቢ ይገናኛሉ፡፡ የቋሚ መስመሮች መነሻ ዜሮ ዲግሪ (00) ነው፡፡ ይህ መነሻ ትልቁ ሜሪዲያን ወይም ግሪንዊች ሜሪዲያን ተብሎ ይጠራል፡፡ ከዚህ መስመር በስተምሥራቅ 180 ቋሚ መስመሮች ሲኖሩ በስተምዕራብ ተመሳሳይ ብዛት ያላቸው ቋሚ መስመሮች ይገኛሉ፡፡ በቋሚ መስመሮች መካከል ያለው ማዕዘናዊ ርቀት መለኪያ ኬንትሮስ 7 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ ይባላል፡፡ ቋሚ መስመሮች መሬትን በምሥራቅና በምዕራብ ንፍቀ ክበባት ይከፍላሉ፡፡ ቋሚ መስመሮች የአንድን ቦታ ፍጹማዊ መገኛን ለማመልከት ይጠቅማሉ፡፡ ምስል1.4 ቋሚ መስመሮች ተግባር1.1 ለ የቡድን ሥራ ዓላማ፡ ቋሚ እና አግዳሚ መስመሮችን መረዳት መመሪያ፡ ተማሪዎች ቡድን በመመሥረት የሚከተሉትን ጥያቄዎች ሠርታችሁ ለመምህራችሁ አቅርቡ፡፡ 1. እኩል የሆኑ ሁለት ብርቱካኖች በመውሰድ አንዱን አግድም እኩል ቦታዎች ላይ በማርከር በማስመር ዐበይት አግድም መስመሮችን አመልክቱ፡፡ በሁለተኛው ላይ ደግሞ ከላይ ወደ ታች እኩል ርቀት በማስመር ቋሚ መስመሮችን አመልክቱ፡፡ በመቀጠል የማይገናኙ መስመሮች ያሉት የትኛው ብርቱካን መሆኑን በመለየት ምንን እንደሚያመለክት ተናገሩ፡፡ 2. በትልቅ ወረቀት ላይ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን አንጻራዊ መገኛ የሚያመለክት ንድፍ ካርታ ሠርታችሁ ለመምህራችሁ አሳዩ፡፡ 3. የምሥራቅ አፍሪካን ፍጹማዊ መገኛ በወረቀት ላይ ስላችሁ ለመምህራችሁ አሳዩ፡፡ 4. በጥንድ ወይንም በቡድን በመሆን የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን አንጻራዊ መገኛን በካርታ ላይ አመልክቱ፡፡ 8 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ መልመጃ 1.1 ሀ)የሚከተሉትን ጥያቄዎች ከጠሰጡት አማራጮች ውሰጥ ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ሆሄ በመምረጥ መልሱ፡፡ 1. የዐብይ ቋሚ መስመር ስንት ድግሪ ላይ ይገኛል? ሀ) 90 ለ) 60 ሐ) 0 መ)180 2. የቋሚ መስመሮች አጠቃላይ ብዛት ስንት ነው? ሀ) 360 ለ) 180 ሐ) 90 መ) 60 3. የአርክቲክ ክበብ የሚገኘው ሀ) ሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ ለ) ደቡባዊ ንፍቀ ክበብ ሐ) ምዕራባዊ ንፍቀ ክበብ መ) ምሥራቃዊ ንፍቀ ክበብ 4. የካንሰር መስመር የሚገኘው በስንት ዲግሪ ላይ ነው? ሀ) 23 ½ ሰሜን ለ) 23 ½ ደቡብ ሐ) 66 ½ ሰሜን መ) 66 ½ ደቡብ 5. የሚከተሉትን አግዳሚና ቋሚ መስመሮችን በመመልከት ከፊደል (ሀ- ሠ) የተመለከቱትን ቦታዎች ፍጹማዊ መገኛ በዲግሪ አስቀምጡ፡፡ ለ. ከተራ ቁጥር 5—8 ያሉትን ጥያቄዎች በምስሌ 1.5 መሠረት መልሱ፡፡ ምስል 1.5 አግዳሚና ቋሚ መስመሮች ሀ. ____________ መ.____________ ለ. ____________ ሠ. ____________ ሐ.____________ 9 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ 6. ለምድር ወገብ በጣም ቅርብ የሆነውን ቦታ የሚያሳየው ፊደል የትኛው ነው? 7. በምሥራቅ ንፍቀ ክበብ የሚገኙ ቦታዎች (ነጥቦች) የትኞቹ ናቸው? 8. በምዕራብ ንፍቀ ክበብ የሚገኙ ቦታዎች (ነጥቦች) የትኞቹ ናቸው? 9. ከታች የተሰጠውን የአፍሪካ ካርታ በመመልከት የሚከተሉትን የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት አንጻራዊና ፍጹማዊ መገኛ በቀረበው ሰንጠረዥ አሟልታችሁ ለመምህራችሁ አሳዩ፡፡ ምስል 1.6 ቋሚና አግዳሚ መስመሮችን የሚያሳይ የአፍሪካ ካርታ 10 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ ሀገር ፍጹማዊ ኢትዮጵያ 3°ሰ - 15° ሰ ኬክሮስ 33° ምሥራቅ - 48° ምሥራቅ ኬንትሮስ ኤርትራ ሶማሊያ ኬንያ ጅቡቲ ታንዛኒያ ዩጋንዳ ሩዋንዳ ማላዊ ምሥራቅ አፍሪካ መገኛ ጥቅምና ጉዳት የቡድን ውይይት1.1ለ ዓላማ፡ ስለ ምሥራቅ አፍሪካ መገኛ ጥቅምና ጉዳት መለየት መመሪያ፡ በቡድን በመሆን ቀጥለው በቀረቡት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩና መልሳችሁን ለመምህራችሁ አቅርቡ፡፡ 1. የምሥራቅ አፍሪካ መገኛን ተጨማሪ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅምና ጉዳት ዘርዝሩ፡፡ 2. የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ በአየር ንብረት ለውጥ ያለውን ተጽዕኖ አብራሩ፡፡ ምሥራቅ አፍሪካ ጂኦግራፊያዊ(ተፈጥሮአዊ) አቀማመጥን ስንመለከት አብዛኛው የቀጠናው ሀገራት በትልልቅ ውሃማ አካላት የተከበቡ በመሆናቸው ይህም የራሱ የሆነ ምጣኔ ሀብታዊና ፖለቲካዊ ጥቅምና ጉዳት አለው፡፡ ከምጣኔ ሀብታዊ አንጻር ስንመለከት ቀጠናው በቀላሉ ከውጭ ሀገራትጋር ባላቸው የወደብ አገልግሎት ጠንካራ የንግድ ትስስር እንዲኖራቸው አድርጓል፡፡ ለምሳሌ ጅቡቲና ኬንያ የተሻለ የወደብ ተጠቃሚ ናቸው፡፡ በተጨማሪም የባህር በር የሌላቸው የቀጠናው ሀገራት ለከፍተኛ የየብስ ትራንስፖርት ወጭ ይዳረጋሉ፡፡ ፖለቲካዊ ተጽኖውን ስንመለከት የቀጠናው ሀገራት በትልልቅ ውሃማ አካላት የተከበቡ መሆናቸው በቀላሉ በቅኝ ገዥዎች እንዲወረሩ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ 11 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ 1.2 የምሥራቅ አፍሪካ አጎራባች ሀገራትና ውሃማ አካላት የንዑስ ርዕሱ አጥጋቢ የመማር ብቃቶች ተማሪዎች ይህንን ንዑስ ርዕስ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፡- የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን አጎራባች ሀገራት ትዘረዝራላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት  አጎራባች ውሃማ አካላት  ሐይቅ ባሕር  ውቅያኖስ የማነቃቂያ ጥያቄዎች ሀ  የምሥራቅ አፍሪካን የሚያዋስኑ የአፍሪካ ሀገራት ስንት ናቸው? ስማቸውን ዘርዝሩ፡፡  ምሥራቅ አፍሪካን ከሚያዋስኑ ውሃማ አካላት መካከል ትልቁ ማን ይባላል? የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት መገኛና አቅጣጫ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት የሚገኙት ከአፍሪካ አህጉር በስተምሥራቅ በኩል ባለው ክፍል ነው፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ በአፍሪካ አህጉር ከሚገኙ አምስቱ ክልሎች አንዱ ነው:: ምሥራቅ አፍሪካን የሚከተሉት አካላት ያዋስናሉ፡፡ ሀ) አጎራባች ሀገራት፡- ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ አንጎላ፣ ቦትስዋና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ስዋዚላንድ ናቸው፡፡ ለ) ምሥራቅ አፍሪካን የሚያዋስኑት ውሃማ አካላት፡- ቀይ ባሕር፣ የኤደን ባሕረ-ስላጤ እና የሕንድ ውቅያኖስ ናቸው፡፡ ምሥራቅ አፍሪካን ከሚያዋስኑ ውሃማ አካላት መካከል ትልቁ የሕንድ ውቅያኖስ ነው፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ ክልል በሦስት ንዑሳን ክፍሎች ይከፈላል፡፡ እነሱም፡- 12 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ  የታላላቅ ሐይቆች ክልል፡- ዩጋንዳ፣ ኬንያ፣ ታንዛንያ፣ ሩዋንዳ እና ቡሩንዲ ናቸው፡፡  የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች፡ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ጂቡቲ እና ሶማሊያን ያካትታል፡፡  የሕንድ ውቅያኖስ ደሴቶች፡- ኮሞሮስ፣ ሪዩኒየን፣ ሲሸልስ፣ ሞሪሽየስ እና ማዳጋስካር የመሳሰሉትን ያጠቃልላል፡፡ ምስል 1.7 የምሥራቅ አፍሪካ አጎራባች የአፍሪካ ሀገራት፣ ውሃማ አካላትና ደሴቶች የቡድን ውይይት 1.2 ዓላማ፡ የምሥራቅ አፍሪካን አጎራባች ሀገራት እና የሚያዋስኑትን ውሃማ አካላት መለየት፡፡ መመሪያ፡ በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ቡድን መስርታችሁ ከተወያያችሁ በኋላ አንድ ሰው በመወከል ለመምህራችሁ አቅርቡ፡፡ ምሥራቅ አፍሪካን የሚያዋስኑ ውሃማ አካላትን ዘርዝሩ፡፡ ምሥራቅ አፍሪካን የሚያዋስኑ ውሃማ አካላት በየት በኩል ይገኛሉ? የምሥራቅ አፍሪካን ካርታ በመመልከት የባሕር በር ያላቸውንና የሌላቸውን ሀገራት ስም ዘርዝሩ፡፡ የባሕር በር ጥቅም ምንድን ነው? በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙ ደሴቶችን ዘርዝሩ፡፡ 13 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙ ታዋቂ ቦታዎች የማነቃቂያ ጥያቄዎች ለ በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙ ታዋቂ ወንዞችንና ሐይቆችን ጥቀሱ፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙ የከፍተኛ ተራሮች መገኛ ሀገራትን ተናገሩ፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ ብዙ ታዋቂ ቦታዎች አሉ፡፡ ከነዚህም መካከል ዋና ዋናዎቹ፡- ከፍተኛ ተራሮች፣ አምባ ምድሮች፣ የስምጥ ሸለቆዎች ፣ ወንዞችና ሐይቆች ይገኛሉ:: በተለይም ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ታንዛኒያ ብዛት ያላቸው ከፍተኛ ቦታዎች ይገኛሉ:: ከሩዋንዝሪ ተራራ በስተቀር በምሥራቅ አፍሪካ አካባቢ የሚገኙ ከፍተኛ ተራሮች የተፈጠሩት በእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ነው፡፡ ሰንጠዥ 1.1 ሀ የምሥራቅ አፍሪካ ተራሮች የታዋቂ ተራሮች ስም የከፍታ መጠን የሚገኝበት ሀገር በሜትር ኪሊማንጃሮ ተራራ ታንዛኒያ 5,895 የኬንያ ተራራ ኬንያ 5,200 ራስ ደጀን ተራራ ኢትዮጵያ 4,620 ሩዋንዞሪ ኡጋንዳና ኮንጎ ድንበር ላይ ይገኛል፡፡ 5,110 ራስ ዳሸን ኢትዮጵያ 4,620 ሜሩ ተራራ ታንዛንያ 4,565 ኤልጎን ዩጋናዳ 4,321 14 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ ምስል 1.8 የምሥራቅ አፍሪካ ታዋቂ ቦታዎች (ሥምጥ ሸለቆ፣ ወንዞችና ሐይቆች) በምሥራቅ አፍሪካ አካባቢ ወደ ተለያየ አቅጣጫ የሚፈሱ ብዙ ወንዞች አሉ፡፡ ዋና ዋናዎቹ፡- የዐባይ ወንዝ፣ የአዋሽ ወንዝ፣ የዋቢሸበሌ ወንዝ፣ ገናሌ ወንዝ፣ የዛምቤዚ ወንዝ፣ የሩቩማ ወንዝ ይገኙበታል፡፡ ሰንጠዥ 1.1 ለ ሰንጠረዥ ታዋቂ ወንዞች የታዋቂ ወንዞች ስም የሚገኝበት ሀገር የዐባይ ወንዝ ኢትዮጵያ የዛምቤዚ ወንዝ ዛምብያ፣ ዝምባብዌና ሞዛምቢክ የዋቢሸበሌ ወንዝ ኢትዮጵያ የገናሌ ወንዝ ኢትዮጵያ የሩቩማ ወንዝ ታንዛኒያና ሞዛምቢክ ድንበር 15 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ ምስል 1.9 የምሥራቅ አፍሪካ ታዋቂ ወንዞች ምሥራቅ አፍሪካ የጥንታዊ ሰው ቅሪተ አካላት ተቆፍሮ የተገኘበት ሥፍራ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ብዙ የቅሪተ አካላት መገኛ ሥፈራዎች አሉ፡፡ እጅግ ታዋቂ የሆኑ የቅሪተ አካላት መገኛ ሥፍራዎች የሚገኙት በሰሜን መሥራቅ ኢትዮጵያ በአፋር ብሔራዊ ክልል ነው፡፡ ከእነዚህም ታዋቂ ቅሪተ አካላት መካከል አርዲ፣ ኢዳልቱ፣ ድንቅነሽ (Lucy) እና ሰላም ይገኙበታል፡፡ ድንቅነሽ (Lucy) የተገኘችው ሐዳር በሚባል ቦታ ነው፡፡ በኬንያ የተለያዩ አካባቢዎች የጥንታዊ ሰው ቅሪተ አካል እና ቅሪተ ቁስ መገኛ ሥፍራዎች አሉ፡፡ በቱርካና (ሩዶልፍ) ሐይቅ ዳርቻ ኮቢ ፎራ በሚባል አካባቢ በርካታ ጥንታዊ ሰው ቅሪተ አካል እና የድንጋይ መሣሪያዎች ተገኝቷል፡፡ 16 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ ምስል 1.10 የምሥራቅ አፍሪካ ታዋቂ ቅሪተ አካላት የተገኙባቸው ሥፍራዎች ሰንጠዥ 1.1 ሐ ሰንጠረዥ ታዋቂ የቱሪስት መስህቦች የታዋቂ ቦታ ስም የሚገኝበት ሀገር የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ኢትዮጵያ ዳሎል ዝቅተኛ ቦታ ኢትዮጵያ የኤርታሌ እሳተ ገሞራ ኢትዮጵያ የዩጋንዳ የተራራ ደን ዩጋንዳ ማሳይ ማራ ፓርክ ኬንያ የአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ኢትዮጵያ ብዊንዲ ጥቅጥቅ ደን ዩጋንዳ 17 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ መልመጃ 1.2 ሀ ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ፡- 1. በምሥራቅ አፍሪካ አካባቢ ከህንድ ውቅያኖስ ጋር ረጅም ወሰን ያለው ደሴት ማን ነው? 2. ኬንያ ከዩጋንዳ በየት አቅጣጫ ይገኛል? 3. የአባይ ወንዝ መነሻ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገር ማን ትባላለች? 4. የምሥራቅ አፍሪካ ትልቁ ተራራ የት ሀገር ይገኛል? መጠሪያውስ? 5. በምሥራቅ አፍሪካ ከሚገኙት ታላላቅ ተራራዎች መካከል ሦስቱን ባላቸው ከፍታ ከትልቅ ወደ ትንሽ ዘርዝሩ፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ፡- ይህ ታላቅ ስምጥ ሸለቆ በእስያ አህጉር ሶሪያ ከምትባል አገር ይነሣል፡፡ በመጀመሪያ ወደ ደቡብ ምሥራቅ አቅጣጫ ገብቶ በኢትዮጵያ ወደ ደቡብ አቅጣጫ ይዞራል፡፡ ከዚያም እስከ ሞዛምቢክ ይዘልቃል፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ አጠቃላይ ርዝመቱ 7200 ኪ.ሜ ሲሆን በአፍሪካ ብቻ 5600 ኪ.ሜ ይሸፍናል፡፡ የምሥራቅ አፍሪካን መሬት በመከፋፈል አልፎ የተለያየ መልከኣ ምድር ፈጥሯል፡፡ ለምሳሌ ይህ ሸለቆ በሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ አፋር አካባቢ የሦስት ጎን ቅርፅ ያለው መልክአ ምድር ፈጥሯል፡፡ ቀይ ባሕ ር የኢትዮጵያ ሦስት ማዕዘን ስምጥ ሸለቆ ቅርጽ ያለው የአፋር ስምጥ ሸለቆ የስምጥ ሸለቆ ምዕራባዊ ቅርንጫፍ የስምጥ ሸለቆ ምሥራቃዊ ቅርንጫፍ ምስል 1.11 የምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ 18 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ ወንዞችና ሐይቆች በምሥራቅ አፍሪካ የተለያዩ ታላላቅ ወንዞች ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል ናይል፣ ዋቢሸበሌ፣ ገናሌ እና ዛምቤዚ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ የናይል ወንዝ በዓለማችን ረዥሙ ወንዝ ነው፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙ ሐይቆች በሁለት ይከፈላሉ፡፡ እነሱም፡- የስምጥ ሸለቆ ሐይቆች እና ከስምጥ ሸለቆ ውጭ ያሉ ሐይቆች በመባል ይታወቃሉ:: በስምጥ ሸለቆ ውስጥ የታንጋኒካ፣ የማላዊ፣ የኪቩ እና በኢትዮጵያ የሚገኙትን የላንጋኖ፣ የዝዋይ፣ የሻላ፣አባያ፣ የሐዋሳና የመሳሰሉት ሐይቆች ይገኛሉ፡፡ በአፍሪካ ትልቁ ሐይቅ ተብሎ የሚታወቀው ቪክቶርያ ሐይቅ እንዲሁም ጣና እና ዝቋላ የመሳሰሉት ሐይቆች ከስምጥ ሸለቆ ውጭ ይገኛሉ፡፡ ሰንጠረዥ 1.2 ታዋቂ ሐይቆች የታዋቂ ቦታ ስም የሚገኝበት ሀገር የቪክቶርያ ሐይቅ ዩጋንዳ፣ ታንዛኒያና ኬንያ መካከል የጣና ሐይቅ ኢትዮጵያ ታንጋኒካ ሐይቅ ታንዛንያና ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ማላዊ ሐይቅ ማላዊ የግል ሥራ የሚከተለውን ካርታን በማንበብ እና በመጠቀም የምሥራቅ አፍሪካ ታዋቂ ሐይቆችን ለመምህራችሁ እየተነሳችሁ አመልክቱ፡፡ ምስል1.12 የምሥራቅ አፍሪካ ታዋቂ ሐይቆች 19 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ መልመጃ 1.2 ለ 1. ስምጥ ሸለቆ ውጭ የሚገኙ ሁለት የምስራቅ አፍሪካ አካባቢ ትላልቅ ሐይቆች ስም ጻፉ፡፡ 2. የሚከተለውን ምስል በመመልከት ቀጥለው የተዘረዘሩት ሐይቆች የሚያዋስኑ ሀገራትን ስም ዘርዝሩ፡፡ ሀ. የቪክቶርያ ሐይቅ__________________________________ ለ. ታንጋኒካ ሐይቅ __________________________________ ሐ. ማላዊ ሐይቅ ________________________________ 20 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ 1.3 የካርታ መፈለጊያ መተግበሪያንና ጎግል ኧርዝ (GPS, Google map and Google earth) በመጠቀም የተለያዩ ቦታዎችን መለየት ከንዑስ ርዕሱ የሚጠበቁ አጥጋቢ የመማር ብቃቶች፡ ተማሪዎች ይህንን ንዑስ ርዕስ ካጠነናቀቃችሁ በኋላ፡- መልክአ ምድራዊ አቀማመጥን፣ ጎግል የካርታ መፈለጊያ መተግበሪያንና ጎግል ኧርዝ (GPS, Google map and Google earth) በመጠቀም የቦታ አቀማመጥን የመለካትና የመመዝገብ ክህሎት ታዳብራላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት ጎግል የካርታ ጎግል ኧርዝ ጂፒ ኤስ የካርታ መፈልጊያና መተግበሪያ የማነቃቂያ ጥያቄዎች የመሬትን ትክክለኛ ምስል ለማየት የሚያስችለው መተግበርያ ምን ይባላል? ጎግል ካርታ (Google map) እና ጂፒኤስ(GPS) ምንድን ናቸው? ጥቅማቸውስ? ጎግል ካርታ (Google map) ጎግል ካርታ በቀጥታ ከጎግል በመሬት ላይ የምንፈልገውን አካባቢ ካርታ በተንቀሳቃሽ ስልክ (በሞባይል) ወይም በኮምፒውተር አማካኝነት አንድን ቦታ በቀጥታ ለማመልከት የሚያስችል መተግበሪያ ነው፡፡ ይህ መተግበሪያ የአንድ ቦታን አቅጣጫ፣ የአካባቢን የገበያ ትስስር እና የመሳሰሉትን ለመፈለግ ይጠቅማል፡፡ ስለዚህም ሰዎች በቀላሉ ወደ ማያውቁት ቦታ ለመሄድ፣ መልዕክት ለማድረስ፣ ሰዎችን በቀላሉ ለማግኘት ሲፈልጉ የጎግል ካርታ መፈለግያን መጠቀም ይቻላል፡፡ ምስል1.13 ጎግል ካርታ (Google map) 21 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ ጎግል ኧርዝ (Google earth) በሕዋ ላይ በተቀመጡና በመሬት ዙሪያ በሚሽከረከሩ ሰው ሰራሽ ሳተላይቶች አማካኝነት የመሬትን ትክክለኛ ገጽታ ለማሳየት የሚገለግል መተግበሪያ ነው፡፡ ተመራማሪዎች ጎግል ኧርዝን በመጠቀም ሩቅ ያሉ ቦታዎችን ለማየት እና ለመመርመር፣ ስለተለያዩ በሽታዎች መከሰት ትንበያ ለመስጠት እንዲሁም የተፈጥሮ ሀብቶችን ለመፈለግ፣ ለማየት እና ለመንከባከብ የሚያስችል ተግባራትን ያከናውናል፡፡ ምስል1.14 (ሀ) ጎግል ኧርዝ ምስል 1.14 (ለ) የመሬት ሳተላይት ምስል በጎግል ኧርዝ ጂፒኤስ (GPS) በመሬት ዙሪያ የሚሽከረከሩ ሰው ሠራሽ ሳተላይቶችን በመጠቀም የተለያዩ መረጃዎችን ወደ መሬት የሚያቀብሉ መተግሪያዎች ወይም መሳሪያዎች (devices) ናቸው፡፡ የጂፒኤስ መሣሪያዎች አቅጣጫን ያሳያሉ፡፡ በተጨማሪም በየብስ፣ በመኪናና በአየር ላይ የሚንቀሳቀሱ አካላትን አቅጣጫ ለመጠቆም እንዲሁም ፍጥነታቸውን ለመቆጣጠር ያግዛሉ፡፡ ምስል1.15 (ሀ) ጂፒኤስ (GPS) ምስል 1.15 (ለ) የጂፒኤስ ሳተላይቶች መሬትን ሲዞሩ 22 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ የቡድን ስራ 1.3 ዓላማ፡ የካርታ መፈለጊያ መተግበሪያንና ጎግል ኧርዝ (GPS, Google map and Google earth) በመጠቀም የተለያዩ ቦታዎችን መለየት መመሪያ፡ አምስት አምስት በመሆን በትምህርት ቤት የኤይሲቲ (ICT) ክፍል ባለው ኮምፒውተር በመጠቀም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ሠርታችሁ ለመምህራቹ አሳዩ፡፡ 1. የካርታ መፈለጊያ መተግበሪያን በመጠቀም ሀ. የት/ቤታችሁን አቀማመጥ፣ ለ. በአዲስ አበባ ውስጥ(መስቀል አደባባይን፣ መርካቶንና የኢትዮጵያን አየር መንገድ) መገኛ እና አቀማመጥ አመልክቱ፡፡ ሐ. የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን መገኛ አሳዩ፡፡ 2. ጎግል ኧርዝን በመጠቀም የምትኖሩበትን አካባቢ ፈልጋችሁ አሳዩ፡፡ 3. የጎግል ካርታ መፈለጊያ እና ጎግል ኧርዝን በመጠቀም የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን መገኛ አቅጣጫ እና ስፋታቸውን አወዳድሩ፡፡ 4. የጎግል ካርታ መፈለጊያ መተግበሪያን በመጠቀም የምሥራቅ አፍሪካ ታዋቂ ቦታዎችን መገኛ መዝግባችሁ ለመምህራችሁ አሳዩ፡፡ 23 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ የምዕራፉ ማጠቃለያ  አንድን አካባቢ ወይም አገር በመሬት አካል ላይ የሚገኝበትን ቦታ ለማመልከት የምንጠቀምበት ዘዴ መገኛ ይባላል፡፡  አንድ አካባቢ ወይም አገር የሚገኝበትን ለማወቅ አንጻራዊ መገኛ እና ፍጹማዊ መገኛ እንጠቀማለን፡፡  የኬክሮስ መስመሮች በካርታ ወይም በሉል ላይ ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ ወይም ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ የተሰመሩ የሐሳብ መስመሮች ናቸው፡፡  የኬንትሮስ መስመሮች በካርታ ወይም በሉል ላይ ከሰሜን ወደ ደቡብ ወይም ከደቡብ ወደ ሰሜን ተሰምረው ይገኛሉ፡፡  የኬክሮስ መስመሮች መነሻ በዜሮ ዲግሪ ላይ የሚገኘው የምድር ወገብ (Equa- tor) ይባላል፡፡  የኬንትሮስ መስመሮች መነሻ ዜሮ ዲግሪ ላይ የሚገኘው ፕራይም ሜሪዲያን ወይም ግሪንዊች ሜሪዲያን ተብሎ ይጠራል፡፡  የምሥራቅ አፍሪካ በሰሜን የሰሜን አፍሪካ አገራት እና ቀይ ባህር፣ በደቡብ አቅጣጫ ደቡብ አፍሪካ፣ በምሥራቅ የኤደን ባህረ-ሰላጤ እና የህንድ ውቅያኖስ እና በምዕራብ ማዕከላዊ አፍሪካ አገሮች ያዋስኑታል፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ ብዙ ታዋቂ ቦታዎች አሉ፡፡ ከነዚህም መካከል ዋና ዋናዎቹ፡- ከፍተኛ ተራሮች፣ አምባ ምድሮች፣ የስምጥ ሸለቆ ፣ ወንዞችና ሐይቆች ይገኛሉ፡፡  ጎግል ማፕን በመጠቀም የአንድን ቦታ አቅጣጫ፣ የአካባቢን የገበያ ትስስር እና የመሳሰሉትን ለመፈለግ ጠቃሚ ነው፡፡  ጂፒኤስ (GPS) በመሬት ዙሪያ የሚሽከረከሩ ሰው ሠራሽ ሳተላይቶችን በመጠቀም የተለያዩ መረጃዎችን ወደ መሬት የሚያቀበሉ መተግሪያዎች ወይም መሳሪያዎች (devices) ናቸው፡፡  ጎግል ኧርዝ ሰው ሰራሽ ሳታላይቶችን በመጠቀም የመሬትን ትክክለኛ ምስል ማሳየት የሚያስችል መተግበሪያ ነው፡፡ 24 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ የምዕራፉ ማጠቃለያ ጥያቄዎች ሀ. የሚከተሉትን ዐረፍተ ነገሮች አንብባችሁ ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል ካልሆኑ ደግሞ ሐሰት በማለት መልሱ፡፡ 1. የኬክሮስ መስመሮች ከሰሜን ወደ ደቡብ የተሰመሩ ናቸው፡፡ 2. የኬክሮስ መሰመሮች ትይዩ ናቸው፡፡ 3. ከፕራይም ሜሪዲያን በስተምሥራቅ 180 የኬንትሮስ መስመሮች አሉ፡፡ 4. የምድር ወገብ የመሬትን ክፍል ምሥራቅና ምዕራብ እኩል ቦታ ይከፍላል፡፡ 5. የኬንትሮስ እና ኬክሮስ መስመሮች በካርታ እና በሉል ላይ ይገኛሉ፡፡ 6. ፍጹማዊ መገኛ ታዋቂ ነገሮችን ምልክት በማድረግ ይገለፃል፡፡ ለ. በ “ሀ” ሥር ያሉትን ማብራሪያዎች በ “ለ” ሥር ካሉት አማራጮች ጋር አዛምዱ፡፡ “ሀ” “ለ” 1. የምሥራቅ አፍሪካ ትልቁ ተራራ ሀ)ታንጋኒካ 2. የኢትዮጵያ ትልቁ ተራራ ለ)ቪክቶርያ 3. የምሥራቅ አፍሪካ ትልቁ ሐይቅ ሐ)ኪሊማንጃሮ 4. የምሥራቅ አፍሪካ የስምጥ ሸለቆ ሐይቅ መ)ራስ ደጀን(ዳሸን) 5. በምሥራቅ አፍሪካ ሁለተኛ ትልቁ ተራራ ሠ) የኬንያ ተራራ ሐ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ከተሰጡት አማራጮች ውስጥ ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ መልሱ፡፡ 1. የምሥራቅ አፍሪካን በስተምሥራቅ በኩል የሚያዋስነው ከሚከተሉት የትኛው ነው? ሀ) የአትላንቲክ ውቅያኖስ ለ) ቀይ ባህር ሐ) የፓሲፊክ ውቅያኖስ መ) የህንድ ውቅያኖስ 2. በካርታ ወይም በሉል ላይ ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ የተሰመሩ መስመሮች ምን ይባላሉ? ሀ) ኬክሮስ ለ) ኬንትሮስ ሐ) ቋሚ መስመሮች መ) ተቋራጭ መስመሮች 25 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ 3. የአንድን አካባቢ ወይም አገር መገኛ ዲግሪን በመጠቀም ማመልከት ምን ይባላል? ሀ) አካባቢያዊ መገኛ ለ) አንጻራዊ መገኛ ሐ) ፍጹማዊ መገኛ መ) ግምታዊ መገኛ 4. ከሚከተሉት ውስጥ ስለ ምሥራቅ አፍሪካ አንጻራዊ መገኛ ትክክል ያልሆነው የቱ ነው? ሀ) ምሥራቅ አፍሪካ ከማእከላዊ አፍሪካ በስተምዕራብ ይገኛል፡፡ ለ) ምሥራቅ አፍሪካ ከደቡብ አፍሪካ በስተሰሜን ይገኛል፡፡ ሐ) ቀይ ባህር ምሥራቅ አፍሪካን በስተሰሜን ያዋስናል፡፡ መ) ህንድ ውቅያኖስ ምሥራቅ አፍሪካን በስተምሥራቅ ያዋስናል፡፡ 5. ከሚከተሉት ውስጥ ዐብይ የአግዳሚ መስመር ያልሆነው የትኛው ነው? ሀ) የምድር ወገብ ለ) የካንሰር መስመር ሐ) የካፕሪኮርን መስመር መ) ግሪንዊች ሜሪዲያን መ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ፡፡ 1. ምሥራቅ አፍሪካን በስተምዕራብ አቅጣጫ የሚያዋስነው የአፍሪካ ክፍል___________ ይባላል፡፡ 2. ስለ ምሥራቅ አፍሪካ መገኛ ጥቅምና ጉዳት ዘርዝሩ፡፡ 26 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የምሥራቅ አፍሪካ መገኛ ፍተሻ ልታከናውኗቸው የምትችሏቸውን ተግባራት የ() ምልክት በሣጥኖች ውስጥ በማኖር አመልክቱ፡፡ 1. አቅጣጫ የመለየት ክህሎትን አዳብራለሁ፡፡ 2. መልክአ ምድራዊ አቀማመጥን፣ ጎግል የካርታ መፈለጊያ መተግበሪያንና ጎግል ኧርዝ (GPS, Google map and Google earth) በመጠቀም የቦታ አቀማመጥን የመለካትና የመመዝገብ ክህሎት አዳብራለሁ፡፡ 3. ካርታን በማንበብ በመጠቀም ከሰዎች መረጃ እለዋወጣለሁ፡፡ 4. ኬክሮስንና ኬንትሮስን በመጠቀም የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን በአፍሪካ ካርታ ላይ አሳያለሁ፡፡ 5. በአፍሪካ ካርታ ላይ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን አንጻራዊና ፍጹማዊ መገኛን አሳያለሁ፡፡ 6. የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን አንጻራዊ መገኛ የሚያመለክት ንድፍ ካርታ እሠራለሁ፡፡ 7. የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን አጎራባች ሀገራት እዘርዝራለሁ፡፡ 27 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ከምዕራፉ የሚጠበቁ አጥጋቢ የመማር ብቃቶች ተማሪዎች ይህን የትምህርት ይዘት ተምራችሁ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፡-  የሰው የደም ዑደትን በመሳል ስያሜዎቹን ታመለክታላችሁ፡፡  የደም ዓይነቶችንና ጠቀሜታዎች ትገልጻላችሁ፡፡  የልብን የተለያዩ ክፍሎች እና ጠቀሜታዎች ትገልጻላችሁ፡፡  በጉርምስና እና በኮረዳነት ወቅት በወንዶችና በልጃገረዶች ላይ የሚታዩ ለውጦችን ትገልጻላችሁ፡፡  ዋና ዋና የሰው የሥርዐተ ትንፈሳ ክፍሎችንና ተግባሮቻቸውን ትለያላችሁ፡፡  የድብልቅን ምንነት ትገልጻላችሁ፡፡  ድብልቅን የመለያ ዘዴዎች ትገልጻላችሁ፡፡  በአካባቢያችሁ የሚገኙ ድብልቆችን ትለያላችሁ፡፡  በአካባቢያችሁ የሚገኙ ድብልቆችን ዋህድ-ዘር ድብልቅ እና ልይ-ዘር ድብልቅ በማለት ትመድባላችሁ፡፡  ተግባራዊ ክንውን በመስራት ድብልቆችን ትለያላችሁ፡፡  የተለያዩ የጉልበት ምንጮችን መገኛ፣ ጥቅምና ተፅዕኖ ታወዳድራላችሁ፡፡  ቀሊሌ መኪና ስራን በቀሊለ ለመስራት እንደሚያግዝ ትገሌፃሊችሁ፡ የምዕራፉ ዋና ዋና ይዘቶች፡- 2.1 የደም ዑደት 2.2 ጉርምስና እና ኮረዳነት 2.3 የሰው ሥርዓተ ትንፈሳ ክፍሎች 2.4 ድብልቅ 2.5 ጉልበትና ጠቀሜታው 2.6 ቀላል መኪና (Simple machine) 28 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ መግቢያ ደም ፈሳሽ ከሆነ ፕላዝማ እና ከደም ህዋሶች የተሰራ የአካላችን ክፍል ነው፡፡ ፕላዝማ ውሃና አልሚ ምግቦችን የሚይዝ የደም ክፍል ነው፡፡ ሦስት አይነት የደም ህዋሶች አሉ፡፡ እነሱም፡- ቀይ የደም ህዋስ ፣ነጭ የደም ህዋስና ፕሌትሌትስ ናቸው፡፡ ደም በሽታን ለመከላከል፣ አየር ለማስተላለፍ፣ ደም ለማርጋት፣ ምግቦችን ወደ ተለያዩ ህዋሳት ለማሰራጨትና የተቃጠለ አየርን ከሰውነታችን ለማስወገድ ይጠቅማል፡፡ ደም በሰውነታችን ውስጥ የሚጓዘው በደም ስሮች አማካኝነት ነው፡፡ ሦስት አይነት የደም ስሮች አሉ፡፡ እነሱም፡- ደም ቅዳ፣ ደም መልስ እና ቀጫጭን የደም ስሮች ናቸው፡፡ ልብ በሰውነታችን ውስጥ በደረታችን አከባቢ ትንሽ ዝቅ ብሎ የሚገኝ በጡንቻዎች የተገነባ የውስጥ አካል ክፍል ነው፡፡ በደረታችን ውስጥ የሚሰማን እንቅስቃሴ የልብ ምት ወይም ትርታ ይባላል፡፡ ልብ አራት ክፍሎች አሉት፡፡ እነርሱም፡- ቀኝ ተቀባይ ልበገንዳ፣ ቀኝ አቀባይ ልበገንዳ፣ ግራ ተቀባይ ልበገንዳና ግራ አቀባይ ልበገንዳ ናቸው:: ልብ ደም ለመርጨት፣ ኦክሲጅንና ምግብን ለህብረ ህዋሳት ለማድረስና አላስፈላጊ የሆኑ ቆሻሻዎችን ለምሳሌ ካርበን ዳይ ኦክሳይድን ለማስወገድ ይጠቅማል፡፡ ጉርምስና እና ኮርዳነት በተወሰነ የዕድሜ ክልል በወንዶችና በሴቶች ላይ የሚታዩ አካላዊና የባህሪ ለውጦች ናቸው፡፡ ሴቶች በኮረዳነት ወቅት የወር አበባ ማየት ይጀምራሉ:: ይህ የወር አበባ በየ 28 ቀናት በማህፀንና በእንቁልጢ ውስጥ የሚካሄድ ተፈጥሮአዊ ክስተት ነው፡፡ አየር የተለያዩ ጋዞች ተዋህደው የሚፈጥሩት ልዩቁስ ነው፡፡ ያለ አየር እንስሳት፣ እፅዋት እና የሰው ልጆች ሊኖሩ አይችሉም፡፡ በሳንባ ውስጥ የሚካሄድ የአየር ልውውጥ ትንፈሳ ይባላል፡፡ ድብልቅ ማለት ሁለትና ከሁለት በላይ የሆኑ ልዩቁሶች አካላዊ በሆነ መንገድ የሚፈጥሩት የቁስ ዓይነት ነው፡፡ ድብልቅን ለመለየት አራት ዘዴዎች አሉ፡፡ እነሱም፡ -ጥለያ፣ ቀረራ፣ ንጥረትና ትነት ናቸው፡፡ የሰው ልጅ ስራዎችን ለማከናወን ጉልበት ይጠቀማል፡፡ ያለጉልበት ምንም ስራ መስራት አይቻልም፡፡ ሀይልን ለማጎልበትና ጉልበትን ለመቆጠብ ስራን በፍጥነት ለመስራት የሚያግዝ መሳሪያ ቀላል መኪና ይባላል፡፡ 29 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ 2.1 የደም ዑደት ከንዑስ ርዕሱ የሚጠበቁ አጥጋቢ የመማር ብቃቶች ተማሪዎች ይህንን ንዑስ ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ፡-  የሰው የደም ዑደትን በመሳል ስያሜዎቹን ታመለክታላችሁ፡፡  የደም ዓይነቶችንና ጠቀሜታዎች ትገልጻላችሁ፡፡  የልብን የተለያዩ ክፍሎች እና ጠቀሜታዎች ትገልጻላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት ዑደት የደም ሥር ደም ደም መልስ ልብ ደም ቅዳ የቡድን ውይይት 2.1ሀ ዓላማ፡ የደም ዑደትን መግለጽ መመሪያ፡ ተማሪዎች የሚከተለውን ጥያቄ ከ3 እስከ 5 አባላት ያለው ቡድን መሥርታችሁ ከተወያያችሁ በኋላ መልሱን ተራ በተራ ለመምህራችሁ እና ለክፍል ጓደኞቻችሁ አብራሩ፡፡ የደም ዑደት ማለት ምን ማለት ነው? የደም ዑደት ማለት ኦክስጂንና አልሚ ምግቦች ለሰውነታችን ህዋሶች የሚሰራጩበት እንዲሁም ካረቦን ዳይኦክሳይድ እና ሌሎች ቆሻሻዎች በደም አማካኝነት የሚሄዱበት ሂደት ነው፡፡ ሀ. ደም የማነቃቂያ ጥያቄዎች ደም ምንድን ነው? የደም ህዋሶችን ዘርዝሩ፡፡ የደም ጥቅም ምንድን ነው? 30 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ደም ፈሳሽ ከሆነ ፕላዝማ እና ከደም ህዋሶች የተሰራ የአካላችን ክፍል ነው፡፡ ፕላዝማ ውሃና አልሚ ምግቦችን የሚይዝ የደም ክፍል ነው፡፡ ሦስት አይነት የደም ህዋሶች አሉ፡፡ እነርሱም፡- 1. ቀይ የደም ህዋሶች 2. ነጭ የደም ህዋሶች እና 3. ፕሌትሌትስ ናቸው፡፡ ቀይ የደም ህዋሶች እነዚህ የደም ህዋሶች መሀላቸው ላይ ጎድጎድ ያለ እና የዶናት ቅርፅ ያላቸው ናቸው:: ቁጥራቸው ከሌሎች የደም ህዋሶች አንፃር ሲታይ በጣም በርካታ ነው፡፡ ቀይ የደም ህዋሶች ኦክስጂንን ከሳንባ ተቀብለው በመሸከም ለመላ የሰውነታችን ህዋሶች ያደርሳሉ፡፡ ኦክስጂንን ለመሸከም የሚያስችል ሄሞግሎቢን (Haemoglobin) የሚባል ሃመልሚል (pigment) አላቸው፡፡ ቀይ የደም ህዋሶች መቅኔ ውስጥ የሚመረቱ ሲሆን ዕድሜያቸውም ከ100 - 120 ቀን ብቻ ነው፡፡ ምስል 2.1 ቀይ የደም ህዋሶች ነጭ የደም ህዋሶች ነጭ የደም ህዋሶች በቅርፅ እና በአገልግሎታቸው ከቀይ የደም ህዋሶች ይለያሉ፡፡ ነጭ የደም ህዋሶች ተግባር የበሽታ አምጪ ተህዋሲያንን ወይም ጀርሞችን ወደ ሰውነታችን ሲገቡ በማጥቃት እና በመከላከል የሰውነታችንን ጤንነት መጠበቅ ነው፡፡ ነጭ የደም ህዋሶች እንደ ቀይ የደም ህዋሶች በመቅኔ ውስጥ የሚመረቱ ሲሆን በቁጥራቸው ከቀይ የደም ህዋሶች ያንሳሉ፡፡ ወጥ የሆነ ቅርፅም የላቸውም፡፡ 31 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ምስል 2.2 ነጭ የደም ህዋሶች ፕሌትሌቶች ፕሌትሌቶች ከቀይ እና ከነጭ የደም ህዋሶች በመጠናቸው በጣም ትንንሽ የሆኑና ክብ ቅርፅ ያላቸው ናቸው፡፡ ተግባራቸውም ሰውነታችን ሲደማ ብዙ ደም እንዳይፈስ ለማርጋት ይጠቅማሉ፡፡ ምስል 2.3 ፕሌትሌቶች ለ. የደም ጠቀሜታዎች ደም በሰውነታችን ውስጥ ብዙ ጥቅሞች አሉት፡፡ እነዚህም፡- ከበሽታ ለመከላከል፣ አየርን ለማስተላለፍ፣ ደም እንዲረጋ ለማድረግ፣ ምግቦችን ወደ ተለያዩ የአክል ህዋሶች ለማሰራጨት እና የተቃጠለ አየር ከሰውነት ለማስወገድ ይጠቅማል፡፡ 32 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ መልመጃ 2.1.ሀ የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሱ፡፡ 1. ደም ለምን ይጠቅማል? 2. የደም ህዋሶች ስንት ናቸው? 3. በሰው የደም ዑደት ሥርዓት አካል የሆኑትን ዘርዝሩ? ሐ. የደም ሥሮች የቡድን ውይይት 2.1ለ ዓላማ፡- የደም ስሮችን መግለፅ ተግባር፡- በቡድናችሁ ከተወያያችሁ በኋላ መልሳችሁን ለመምህራችሁና ለክፍል ጓደኞቻችሁ አብራሩ፡፡ የመወያያ ጥያቄዎች 1. ደም በሰውነታችን ውስጥ በምን ይጓዛል? 2. ጥንድ ጥንድ በመሆን አንዳችሁ የአንዳችሁን ዓይን በትኩረት ተመልከቱ በነጩ የዓይን ክፍል ላይ የተሰመሩ መስመሮች ልትመለከቱ ትችላላችሁ፡፡ እነዚህ መስመሮች ምንድን ናቸው? ጥቅማቸውን አብራሩ፡፡ ደም በሰውነታችን ውስጥ የሚጓዘው በደም ሥሮች ውስጥ ነው፡፡ የደም ሥሮች ደምን ከልብ ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ያሰራጫሉ፡፡እንዲሁም ከተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ወደ ልብ ይመልሳሉ፡፡ በሰውነታችን ውስጥ ሦስት ዋና ዋና የደም ሥር አይነቶች አሉ፡፡ እነሱም፡- ደም-ቅዳ፣ ደም መልስ እና ቀጫጭን የደም ስር ናቸው፡፡ ደም ቅዳ (Artery)፡- ደምን ከልብ ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ያሰራጫል፡፡ ደም በከፍተኛ ደረጃ ስለሚረጩ በጣም ወፍራም ግድግዳ አላቸው፡፡ ደም መልስ (Vein)፡- ደምን ከተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ወደ ልብ ይመልሳል፡፡ ቀጫጭን የደም ሥሮች (Capillary)፡- ለሰውነታችን ህዋሶች በጣም ቅርብ የሆኑ የደም ሥሮች ናቸው፡፡ በጣም ቀጫጭንና ስስ ግድግዳ ያላቸው ሲሆን ደም ቅዳንና ደም መልስን ያገናኛሉ፡፡ 33 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ምስል 2.4 ሦስቱ የደም ስር አይነቶች መልመጃ 2.1 ለ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል ካልሆኑ ሐሰት በማለት መልሱ፡፡ 1. ደም ምግብንና አየርን በሰውነታችን ውስጥ ያሰራጫል፡፡ 2. ሁሉም የደም ሥሮች ወፍራም ግድግዳ አላቸው፡፡ 3. ደምን ወደ ልብ የሚመልስ የደም ሥር ደም ቅዳ ነው፡፡ 4. የደም ሥሮችን በውጫዊ ሰውነታችን ላይ ማየት እንችላለን፡፡ 5. ቀጫጭን የደም ሥሮች ደም ቅዳንና ደም መልስን ያገናኛሉ፡፡ መ. ልብ የማነቃቂያ ጥያቄዎች፡- የልብን የተለያዩ ክፍሎች ዘርዝሩ፡፡ የልብ ክፍሎች ጠቀሜታዎች ግለፁ፡፡ 34 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ምስል2.5 ዋና ዋና የልብ ክፍሎች ልብ በሰውነታችን ውስጥ በስተግራ ደረታችን አካባቢ ትንሽ ዝቅ ብሎ የሚገኝ በጡንቻዎች የተገነባ የውስጥ አካላችን ነው፡፡ በደርታችን ውስጥ የሚሰማን እንቅስቃሴ ወይም ድምፅ የልብ ትርታ ይባላል፡፡ የልብ ትርታን የምናዳምጥበት መሳሪያ ስቴቶስኮፕ ተብሎ ይጠራል፡፡ ልባችን አራት ዋና ዋና ክፍሎች ወይም ልበ ገንዳዎች አሉት፡፡ እነሱም እንደሚከተለው ተገልፀዋል፡፡ 1. ቀኝ ተቀባይ ልበ ገንዳ (Right auricle)፡- በኦክስጂን ያልበለፀገ ደም ከትልቁ ደም መልስ ተቀብሎ ወደ ቀኝ አቀባይ ልበ ገንዳ ይልካል፡፡ 2. ቀኝ አቀባይ ልበ ገንዳ(Right ventricle)፡- ከቀኝ ተቀባይ ልበ ገንዳ የተቀበለውን ደም በፑልሞናሪ አርተሪ (Pulmonary artery) ወደ ሳንባ ይረጫል፡፡ 3. ግራ ተቀባይ ልበ ገንዳ (Left auricle)፡- ከሳንባ በኦክስጂን የበለፀገ ደም በፑልሞናሪ ቨይን (Pulmonary vein) ተቀበሎ ወደ ግራ አቀባይ ልበ ገንዳ ይልካል፡፡ 4. ግራ አቀባይ ልበ ገንዳ (Left ventricle) ፡- ከግራ ተቀባይ ልበ ገንዳ የተቀበለውን ደም በአኦርታ (ትልቁ ደም ቅዳ) ውስጥ ወደ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ይረጫል፡፡ 35 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ የልብ ጠቀሜታ ልብ የተለያዩ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ እነርሱም፡- ደም መርጨት፣ አክስጂንና ምግብን ለሕብረ ሕዋሳት ማድረስ፣ ካርቦን ዳይኦክሳይድንና ቆሻሻን ከሰውነታችን ውስጥ ማስወገድ ነው፡፡ ምስል2. 6 የደም ዑደት ከልብ ወደ ሳንባ እና ከልብ ወደ የተለያዩ አካላት ከላይ በምስል እደሚታየው ደም ኦክስጂን ለመቀበል ወደ ሳንባችን ይሄዳል፡፡ ከዚያም ደግሞ በኦክስጂን የበለፀገውን ደም ልብ ተቀብሎ ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ይረጫል፡፡ ደም ካርቦን ዳይኦክሳይድንና ሌሎች የሚወገዱ አላስፈላጊ ቆሻሻዎችን ጭምር በመሸከም ወደ ልብ ተመልሶ ሳንባ ድረስ ይሄዳል፡፡ የደም ዑደት እንደሚከተለው ይከናወናል፡፡ በኦክስጂን የበለፀገ ደም ከሳንባፑልሞናሪ ቬይንግራ ተቀባይ ልበ ገንዳግራ አቀባይ ልበ ገንዳትልቁ ደም ቅዳወደ ሰውነት አካል ይሰራጫል፡፡ በኦክስጂን ያልበለፀገው ደም ደግሞ ከሰውነትትልቁ ደም መልስቀኝ ተቀባይ ልበ ገንዳቀኝ አቀባይ ልበ ገንዳፑልሞናሪ አርተሪወደ ሳንባ ይመለሳል፡፡ ምስል 2.7 ስቴቶስኮፕ 36 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ መልመጃ 2.1 ሐ ስዕሉን መሠረት በማድረግ የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሱ፡፡ 1. ቀኝ ተቀባይ ልበ ገንዳን የሚያመለክተው ፊደል የቱ ነው? 2. ቀኝ አቀባይ ልበ ገንዳን የሚያመለክተው ፊደል የቱ ነው? 3. ግራ ተቀባይ ልበ ገንዳን የሚያመለክተው ፊደል የቱ ነው? 4. ግራ አቀባይ ልበ ገንዳን የሚያመለክተው ፊደል የቱ ነው? 5. በኦክስጂን የበለፀገውን ደም የሚሸከሙት ፊደላት እነማን ናቸው? 6. በኦክስጂን ያልበለፀገውን ደም የሚሸከሙት ፊደላት እነማንናቸው? 7. የደም ዑደት ጠቀሜታ ምንድን ነው? 2.2 ጉርምስና እና ኮረዳነት ከንዑስ ርዕሱ የሚጠበቁ አጥጋቢ የመማር ብቃቶች፡- ተማሪዎች ይህንን ንዑስ ርዕስ ተምራችሁ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፡- በጉርምስና እና በኮረዳነት ወቅት በወንዶችና በልጃገረዶች ላይ የሚታዩ ለውጦችን ትዘረዝራላችሁ፡፡ የወር አበባ ዑደትንና ንፅህናን ታብራራላችሁ፡፡ ጾታዊ ጥቃት ምን እንደሆነ ትገልፃላችሀ፡፡ ቁልፍ ቃላት ጉርምስና የወር አበባ ኮረዳነት ፆታዊ ጥቃት 37 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ የማነቃቂያ ጥያቄዎች ጉርምስና ማለት ምን ማለት ነው? ኮረዳነትስ? በጉርምስና በኮረዳነት ወቅት የሚታዩ ለውጦችን ግለጹ፡፡ ጉርምስና እና ኮረዳነት ማለት በተወሰነ የዕድሜ ክልል ውስጥ በወንዶችና በሴቶች ላይ የሚከሰት የአካል እና የባህሪ ለውጥ ነው፡፡ በጉርምስናና በኮረዳነት ወቅት የሚታዩት አካላዊና የባህሪ ለውጦች ስነ ሕይወታዊ ለውጦች ይባላሉ፡፡ ጉርምስና እና ኮረዳነት በዕድገት የሚመጣ ጤናማ የሆነ የአካልና የባህሪ ለውጥ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት በወንዶች እና በሴቶች ላይ የሚታዩት የአካል እና የባህሪ ለውጥ የተለያዩ ናቸው፡፡ በጉርምስና ወቅት በወንዶች ላይ የሚታዩ ዋና ዋና ስነ-ሕይወታዊ ለውጦች ወንዶች ልጆች ላይ አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ለውጦች መታየት የሚጀምሩት 12-14 ዓመት ባሉት የእድሜ ክልሎች ውስጥ ነው፡፡ በጉረምስና ወቅት የሚታዩት ዋና ዋና ስነሕወታዊ ለውጦች የሚከተሉት ናቸው፡፡ እነርሱም፡- የድምፅ መጎርነን ይታያል፤ ትከሻ እና ደረት ይሰፋል፤ ጡንቻዎች ይዳብራሉ፤ በፊት ላይ፣ በብብት ስር እና በብልት አካባቢ ፀጉር ይበቅላል፤ የወንድ ዘርፈ ፈሳሽ መመንጨት ይጀምራል፤ ፈጣን የሆነ የክብደት እና የቁመት መጨመር ይታያል፡፡ በከረዳነት ወቅት በሴቶች ላይ የሚታዩ ዋና ዋና ስነ- ሕይወታዊ ለውጦች ሴቶች ልጆች ላይ አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ለውጦች መታየት የሚጀምሩት 11-13 ዓመት ባሉት የእድሜ ክልሎች ውስጥ ነው፡፡ በኮረዳነት ወቅት የሚታዩት ዋና ዋና ስነሕወታዊ ለውጦች የሚከተሉት ናቸው፡፡ የጡት ማጎጥጎጥ (ማደግ) ይጀምራል፤የወር አበባ መታየት ይጀምራል፤የዳሌ መስፋት ይታያል፤ ድምፅ ይቀጥናል፤ በብብት ስር እና በብልት አካባቢ ፀጉር ይበቅላል፤ ፈጣን የሆነ የክብደት እና የቁመት መጨመር ይታያል፡፡ 38 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ መልመጃ 2.2.ሀ የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሱ፡፡ 1. በጉርምስና ወቅት በወንዶች ላይ ብቻ የሚከሰቱ ነገር ግን በሴቶች ላይ የማይከሰቱ ስነ-ሕይወታዊ ለውጦችን ዘርዝሩ፡፡ 2. በኮረዳነት ወቅት በሴቶች ላይ ብቻ የሚከሰቱ ነገር ግን በወንዶች ላይ የማይከሰቱ ስነ-ሕይወታዊ ለውጦችን ዘርዝሩ፡፡ 3. በጉርምስና ወቅት በወንዶችና በልጃገረዶች ላይ የሚታዩ ለውጦችን ጥቀሱ፡፡ የወር አበባ ንጽሕና አጠባበቅ የማነቃቂያ ጥያቄዎች የወር አበባ በድንገት ቢመጣ በአከባቢያችን በሚገኙ ቁሳቁስ ንጽህናን መጠበቅ ይቻላልን? በምን በምን? ጾታዊ ጥቃት ምንድን ነው? የወር አበባ ንፅህና ማለት ሴቶች አላስፈላጊ የሆኑ የደም ቆሻሻዎችን የሚያስወግዱበት ተፈጥሮአዊ ክስተት ነው፡፡ የወር አበባ በአማካኝ በየ28 ቀናት በማህፀንና በእንቁልጢ ውስጥ የሚካሄድ ወርሃዊ ዑደት ነው፡፡ የወር አበባ ዑደት አንዲት ልጃገረድ ለአቅመ ሔዋን በደረሰችበት ጊዜ ማለትም ከ12- 14 ዓመት ዕድሜ ይጀምራል፡፡ ይህ ዕድሜ ኮረዳዋ ልጅ መውለድ የምትችልበትና የምትጀምርበት የዕድሜ ክልል ነው፡፡ ይህ ወርሃዊ ዑደት የእንቁላል በእንቁልጢ መፈጠርንና እንቁላሉ ወደ ማህፀን ቦይ መግባትን ወይም ውፃትን ተከትሎ የሚከሰት ነው፡፡ በወር አበባ ጊዜ የሚከሰቱ ዋና ዋና ሂደቶች፡- የማህፀን ግድግዳ በደም ስሮች እና ሽፋን ሕብረ-ሕዋሳት መደራጀት፡፡ እንቁላል ከእንቁልጢ መውጣት እና ወደ ማህፀን ቦይ መግባት፡፡ ፅንስ ባለመከናወኑ የማህፀን ግድግዳ መፈራረስ፡፡ የፈራረሰው የማህፀን ግድግዳ በትንሽ ደም መልክ በከረቤዛ በኩል መወገድ፡፡ የወር አበባ ዑደት ከ12 - 55 ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ ባሉት ሴቶች ላይ የሚታይ ጤናማ ተፈጥሯዊ ሂደት ነው፡፡ የወር አበባ በሚመጣበት ጊዜ ሴቶች እና ልጃገረዶች ንፁህ ጨርቅ ወይም ሞዴስ በማዘጋጀት ንፅህናቸውን ይጠብቃሉ፡፡ የወር አበባ እንቁላል በእንቁልጢ ውስጥ መመረትንና መውጣትን የሚያሳይ ዑደት ነው፡፡ 39 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ጾታዊ ጥቃት ሰዎች ለግል ፍላጎታቸው እና ጥቅማቸው ብለው በሌሎች ሰዎች ላይ ፆታን መሠረት ያደረገ ትንኮሳና አስገድዶ መድፈር ጾታዊ ጥቃት ይባላል፡፡ መልመጃ 2.2.ለ ሀ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል ካልሆኑ ደግሞ ሀሰት በማለት መልሱ፡፡ 1. የወር አበባ ማለት በየ28 ቀናት የሚመጣ ስነ-ሕይወታዊ ዑደት ነው፡፡ 2. ጉርምስና ማለት በሴቶች ላይ የሚከሰት አካላዊ ለውጥ ብቻ ነው፡፡ 3. የድምፅ መቅጠንና የዳሌ መስፋት በወንዶች ላይ የሚታዩ አካላዊ ለውጦች ናቸው፡፡ 4. እንቁላል ከእንቁልጢ መውጣት ውፃት ይባላል፡፡ ለ.ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ፡፡ 1. የወር አበባ ንፅህናን በምን በምን መጠበቅ ይቻላል? 2. ጾታዊ ጥቃት ማለት ምን ማለት ነው? 40 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ 2.3 የሰው ሥርዓተ ትንፈሳ ክፍሎች ከንዑስ ርዕሱ የሚጠበቁ አጥጋቢ የመማር ብቃቶች፡- ተማሪዎች ይህንን ንዑስ ርዕስ ከተማራችሁ በኋላ፡-  ዋና ዋና የሰው የሥርዐተ ትንፈሳ ክፍሎችንና ተግባሮቻቸውን ትለያላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት አየር ትንከረት ትንቧ ድህረ አፍ አፈወና ትንፈሳ የማነቃቂያ ጥያቄዎች ትንፈሳ ማለት ምን ማለት ነው? የመተንፈሻ አካላትን ዘርዝሩ፡፡ የሥርዓተ ትንፈሳ ክፍሎች ትንፈሳ ማለት ኦክሲጅን ወደ ሰውነታችን ውስጥ የማስገባትና ካርበን ዳይኦክሳይድን ወደ ውጭ የማስወጣት ሂደት ነው፡፡ አየር ወደ ውስጥ ስንምግ (ስናስገባ) ሳንባችን በአየር ይሞላል፡ ፡ ወደ ውጭ ስንተነፍስ ደግሞ አየር ከሳንባችን ይወጣል፡፡ ሰው ሁለት ሳንባዎች አሉት፡፡ ሁለቱ ሳንባዎቻችን በደረታችን ውስጥ የሚገኙ ትልልቅ ስፖንጅ መሰል አካላት ሲሆኑ ለትንፈሳ የምንገለገልባቸው ክፍሎች ናቸው፡፡ ምስል 2.8 የሰው ሥርዓተ ትንፈሳ ክፍሎች 41 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ የሥርዓተ ትንፈሳ ክፍሎች እና ተግባራት ሥርዓተ ትንፈሳ ክፍሎች እና ተግባራቸውን በሚከተለው ሰንጠረዥ ተመልከቱ፡፡ የማነቃቂያ ጥያቄዎች የመተንፈሻ አካላትን ዘርዝሩ፡፡ ኦክስጂንና ካርቦን ዳይኦክሳይድ የሚለዋወጡበት የመተንፈሻ አካል ምን ተብሎ ይጠራል? ሰንጠረዥ 2.1፡ የመተንፈሻ አካላት እና ተግባራት የመተንፈሻ አካላት ተግባራት የአፍንጫ ቀዳዳ(Nasal የአየር መግቢያና መውጫ ነው፡፡ cavity) አፍ(Mouth) የአየር መግቢያና መውጫ ነው፡፡ ሰርን(Nostril) አየር ያሞቃል፣ ቆሻሻንና ጀርምን ያጣራል፡፡ ድህረ-አፍ ወደ ዐብይ ትንቧ ለሚገባውና ለሚወጣው አየር (pharynx) መተላለፊያ ነው፡፡ ዐብይ ትንቧ ወደ ባላትንቧ ለሚገባውና ለሚወጣው አየር መተላለፊያ (trachea) በመሆን ያገለግላል፡፡ ባላ ትንቧ(ተገንጣይ ከዐብይ ትንቧ ወደ ሳንባ ለሚገባውና ለሚወጣው አየር የአየር ቧንቧ) (bronchi) መተላለፊያ የመተንፈሻ አካል ነው፡፡ ደቂቅ ትንቧ አየር ወደ አየር ትንከረት(አየር ከረጢት) መግቢያና (bronchiole) መውጫ በመሆን ይጠቅማል፡፡ ትንከረት(የአየር ለኦክስጂንና ለካረቦን ዳይኦክሳይድ ወደ ደም ውስጥ ከረጢት) (alveoli) መግቢያ እና መውጫ ሆኖ ያገለግላል፡፡ 42 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ የሰውነታችን ሥርዓተ ትንፈሳ ሂደት ወደ ውስጥ ስንተነፍስ አየር ወደ ሳንባችን ለመድረስ የሚያልፍባቸው የመተንፈሻ አካላት በቅደም ተከተል ሲቀመጡ፡- የአፍንጫ ቀዳዳ  ሰርን  ድህረ-አፍ  ዐብይ የአየር ቧንቧ  ተገንጣይ የአየር ቧንቧ  ደቂቅ ትንቧ  የአየር ከረጢት ናቸው፡፡ ሳንባዎቻችን በሰውነታችን ደረት ወና በሚባል ትልቅ ክፍት ቦታ ውስጥ ይገኛል። አንደኛው ሳንባችን በደረት ወና ውስጥ በስተቀኝ በኩል ሲገኝ ሁለተኛው ደግሞ በስተግራ በኩል ይገኛል፡፡ የደረት ወና ግድግዳ ከወፍራም ጡንቻዎች እና የጎድን አጥንቶች የተሰራ ነው፡፡ ወደ ውስጥ እና ወደ ውጭ በምንተነፍስበት ጊዜ ጡንቻዎቹ ግድግዳዎቹን ወደ ውጭ እና ወደ ውስጥ እንዲንቀሳቀሱ ያደርጓቸዋል፡፡ ይህ ሂደት ደግሞ ሳንባዎቻችን በአየር የተሞሉ ያደርጋል፡፡ ጡንቻዎች እና የጎድን አጥንቶች ሳንባዎቻችንን እንደ አጥር ከበው ከጉዳት ይጠብቃሉ፡፡ ድህረ-አፍ አፍንጫንና አፍን ከትንቧ እና ከጉሮሮ ጋር ያገናኛል፡፡ ድህረ-አፍ አየር እና ምግብ በጋራ የሚተላለፍበት መንገድ ነው፡፡ ባላትንቧዎች ልክ የተዘቀዘቀ የዛፍ ቅርንጫፎችን ይመስላሉ፡፡ በሳንባ ውስጥ የሚገኙ ትንንሽ ቅርንጫፎች ደቂቅ ባላትንቧዎች ይባላሉ፡፡ በአፍ ከመተንፈስ ይልቅ በአፍንጫ መተንፈስ ይመረጣል፡፡ ምክንያቱም ከአየር ጋር ተቀላቅለው የሚገቡትን ጀርሞችንና ቆሻሻዎችን በሰርን ወና ውስጥ በሚገኙ ጥቃቅን ፀጉሮች አማካኝነት ተጣርተው ወደ አየር ከረጢት ይደርሳሉ፡፡ ድልሺ ወደ ታች ሲወርድ የደረት ወና ስለሚሰፋ የአየር ግፊት ይቀንሳል፡፡ ስለዚህ ወደ ውስጥ እንተነፍሳለን፡፡ ድልሺ ወደ ቦታው ሲመለስ ደግሞ የአየር ግፊት ስለሚጨምር ወደ ውጭ እንተነፍሳለን፡፡ የሥርዓተ ትንፈሳ ጠቀሜታዎች የማነቃቂያ ጥያቄ  ሥርዓተ ትንፈሳ ጠቀሜታው ምንድን ነው? ሥርዓተ ትንፈሳ ብዙ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ እነርሱም፡- ለማውራት እና ለማሽተት፣ ኦክስጂንን ለሕዋሶቻችን ማሰራጨት፣ ቆሻሻ ነገሮችን(ካርቦን ዳይኦክሳይድ) ማስወገድ፣ በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የሙቀትና የቅዝቃዜ መጠን ተመጣጣኝ እንዲሆን ማድረግ እና የአየር መተላለፍያ መንገዶችን ከጉዳት መከላከል ናቸው፡፡ 43 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ተግባር 2.1 ተግባራዊ ክንውን ርዕስ፡ የአየር ንጽህና አጠባበቅ አላማ፡ የመማሪያ ክፍልን የአየር ንጽህና አጠባበቅ ዘዴዎችን በተግባር ማሳየት መመሪያ፡ ከ3-5 አባላት ያለውን ቡድን በመመሥረት በትምህረት ቤታችሁ የሚገኙ ልዩ ልዩ የመማሪያ ክፍሎችን በመንቀሳቀስ ጎብኙ፡፡ በጉብኝታችሁ ወቅት የሚከተሉትን መሞላታቸውንና አለመሞላታቸውን አረጋግጡ::  በቂ መስኮቶች መኖራቸውን፣  መስኮቶች ክፍት መሆናቸውን፣  በተማሪዎች መቀመጫ መካከል በቂ ክፍት ቦታ መኖራቸውን፣  ከተለያዩ ቆሻሻዎች የጸዱ መሆናቸውንና  የትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ማራኪ እና ሳቢ መሆኑን እዩ፡፡ ከላይ በቀረቡት ጉዳዮች ላይ ምልከታ ካደረጋችሁ በኋላ ለአየር ብክለት እና ሥርዓተ ትንፈሳን የሚያውኩ ነገሮች መኖራቸውንና አለመኖራቸውን አረጋግጣችሁ ለክፍል ጓደኞቻችሁ በዘገባ መልክ አቅርቡ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ችግሮችን ከተመለከታችሁ የመፍትሄ ሀሳብ በቡድን መሪያችሁ አማካኝነት ለትምህርት ቤት ምክትል ርዕሰ መምህር እንዲደርስ አድርጉ:: መልመጃ 2.3.ሀ የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሱ፡፡ 1. አየር ወደ ውስጥ በምንተነፍስበት ጊዜ የሚያልፍባቸውን የመተንፈሻ አካላት በቅደም ተከተል አስቀምጡ፡፡ 2. ድልሺ ምንድን ነው? በሥርዓተ ትንፈሳ ውስጥ የድልሺ ተግባር ፃፉ፡፡ 3. ሳንባ በሰውነታችን ውስጥ የት ይገኛል? 44 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ስዕሉን መሠረት በማድረግ ከተራ ቁጥር 4 እስከ 10 ያሉትን ጥያቄዎች መልሱ፡፡ 4. ምግብና አየር በጋራ የሚተላለፍበት የአካል ክፍል የሚያመለክተው ቁጥር ስንት ነው? 5. ግራ ሳንባ እና ቀኝ ሳንባን በቅደም ተከተል የሚያመለክቱት ቁጥሮች ስንትና ስንት ናቸው? 6. ወደ ሳንባ ለሚገባው እና ከሳንባ ለሚወጣው አየር መተላለፊያ ሁኖ የሚያገለግለው ቁጥር ስንት ነው? 7. ከአየር ጋር የገቡትን ቆሻሻዎችን በማጣራት ንጹህ አየር የሚሰጠን የአካላችን ክፍል የሚያመለክተው ቁጥር ስንት ነው? 8. የአየር ልውውጥ የሚደረግበትን ቦታ የሚያመለክተው ቁጥር ስንት ነው? ስሙን ጥቀሱ፡፡ 9. ካርቦን ዳይኦክሳይድ ለመወገድ የሚያልፍባቸውን የሥርዓተ ትንፈሳ አካላት የሚያመለክቱትን ቁጥሮች በቅደም ተከተል አስቀምጡ፡፡ ስማቸውንም ፃፉ፡፡ 10. አየር ወደ አየር ከረጢት እንዲገባና እንዲወጣ የሚያደርገውን የሚያመለክተው ቁጥር ስንት ነው? የምጋት እና የኢምጋት የአየር ምንዝሮች አየርን ወደ ሰውነታችን የምናስገባበት ሂደት ምጋት ይባላል፡፡ አየርን ከሰውነታችን ወደ ውጭ የምናስወጣበት ሂደት ደግሞ ኢምጋት ይባላል፡፡ ወደ ሳንባችን የምናስገባው አየር ኦክሲጅን ሲባል የምናስወጣው ደግሞ ካረበን ዳይኦክሳይድ ይባላል፡፡ 45 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ሰንጠረዥ 2.2፡ የምጋት እና የኢምጋት የአየር ምንዝሮች በመቶኛ ሲቀመጡ የአየር ምንዝሮች ምጋት(%) ኢምጋት(%) ኦክሲጅን 21 16 ካረቦን ክልቶኦክሳይድ 0.03 4 ናይትሮጂን 78 78 የውሃ ትነት ዝቅተኛ ከፍተኛ ሙቀት ዝቅተኛ ከፍተኛ ምስል 2.11፡ የድልሺ ቅርፅ በምጋትና በኢምጋት 46 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ የቡድን ውይይት 2.3 ዓላማ፡ የአየር ምንዝሮችን በምጋትና በኢምጋት ማወዳደር መመሪያ፡ የሚከተሉትን ጥያቄዎች በቡድን ተወያይታችሁ ከሰራችሁ በኋላ ለመምህራችሁና ለክፍል ጓደኞቻችሁ ተራ በተራ እየተነሳችሁ አብራሩ፡፡ 1. ከላይ በሰንጠረዡ ላይ እንደተመለከታችሁት የአየር ምንዝሮች ውስጥ የኦክሲጅን መጠን በኢምጋት ጊዜ ለምን ቀነሰ? 2. የናይትሮጂን መጠን በምጋት እና በኢምጋት ጊዜ መጠኑ ለምን ለውጥ አላመጣም? 3. የካርበን ክልቶኦክሳይድ መጠን በኢምጋት ጊዜ ለምን ጨመረ? መልመጃ 2.3.ለ በ “ሀ” ስር የቀረቡትን ተግባራት “ለ” ስር ከቀረቡት መተንፈሻ አካት ጋር አዛምዱ፡፡ ሀ ለ 1. ወደ አየር ከረጢት መግቢያና መውጫ ሀ) ሰርን 2. አየር መግቢያና መውጫ ለ) ባላትንቧ 3. ኦክስጂን እና ካረቦን ክልቶኦክሳይድ ወደ ደም መግቢያ እና መውጫ ሐ) የአፍንጫ ቀዳዳ 4. ወደ ትንቧ የሚገባና የሚወጣ አየር መተላለፊያ መ) ደቂቅ ትንቧ 5. አየር ያሞቃል፤ ጀርምንና ቆሻሻን ያጣራል ሠ) ድህረ-አፍ 6. ከ ትንቧ ወደ ሳንባ ለሚገባ እና ለሚወጣ ረ) የአየር ከረጢት አየር መተለላለፊያ 47 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ 2.4 ድብልቅ (mixture) ከንዑስ ርዕሱ የሚጠበቁ አጥጋቢ የመማር ብቃቶች ተማሪዎች ይህንን ንዑስ ርዕስ ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡-  የድብልቅን ምንነት ትገልጻላችሁ፡፡  በአካባቢያችሁ የሚገኙ ድብልቆችን ትለያላችሁ፡፡  በአካባቢያችሁ የሚገኙ ድብልቆችን ዋህድ-ዘር ድብልቅ እና ልይ-ዘር ድብልቅ በማለት ትመድባላችሁ፡፡  የድብልቅን መለያ ዘዴዎች ትገልጻላችሁ፡፡  ተግባራዊ ክንውን በመስራት ድብልቆችን ትለያላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት ድብልቅ ትነት ጥሊያ ልይ-ዘር ድብልቅ ቀረራ ዋህድ -ዘር ድብልቅ ንጥረት ድብልቅ ድብልቅ ማለት ሁለትና ከሁለት በላይ የሆኑ ልዩ ቁሶች አካላዊ (physical) በሆነ መንገድ በመጣመር የሚፈጥሩት የቁስ አይነት ነው፡፡ ይህም ማለት ድብልቁን የሠሩት ልዩ ቁሶች ከመቀላቀላቸው በፊትና በኋላ ያላቸውን ማንነትና ባህሪይ ሳይቀይሩ እንደያዙ በመጣመር የሚፈጥሩት የቁስ አይነት ነው፡፡ ነገር ግን ድብልቅ ኬሚካዊ (chemical) በሆነ መንገድ ስላልተጣመሩ ምንዝሮቹ የራሳቸውን ባህሪ አይለውጡም ያልተለመደም ባህሪ አያሳዩም፡፡ ለምሳሌ የስኳርና የውሃ ድብልቅ፣ የጨውና የውሃ ድብልቅና የስኳርና የአሸዋ ድብልቅና የመሳሰሉት ድብልቆች የያዙዋቸውን የልዩ ቁሱን ባህሪያት ነው፡፡ ይህም ማለት ድብልቁ ሊኖረው የሚችለው ባህሪ በልይ ቁሱ ባህሪ ይወሰናል ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ የጨው ሙሙት የተሠራው ከጨውና ከውሃ ነው። የሚይዘውም የጨውና የውሃን ባህሪ ነው፡፡ የድብልቅ ዓይነቶች በድብልቁ ውስጥ የሚገኙ ምንዝሮችን በ አይን ወይም በአጉሊ መነጸር መለየት የሚቻሉና የማይቻሉ መሆናቸውን መሰረት በማድረግ ድብልቆች በሁለት ይከፈላሉ፡፡ 48 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ 1. ዋህድ-ዘር ድብልቆች (Homogeneous mixtures) 2. ልይ-ዘር ድብልቆች (hetrogeneous mixtures) 1.ዋህድ- ዘር ድብልቆች (Homogeneous mixtures) የማነቃቂያ ጥያቄዎች ዋህድ-ዘር ድብልቅ ምን ማለት ነው? አየር ዋህድ-ዘር ድብልቅ ይመስላችኋል? ለምን? ዋህድ- ዘር ድብልቅ የድብልቅ ዓይነት ሲሆን በድብልቁ ውስጥ ያሉትን ምንዝሮች በአይን ወይም በአጉሊ መነጸር በመታገዝ ለይተን ማየት የማንችል ከሆነ ድብልቁ ዋህድ- ዘር ድብልቅ ይባላል፡፡ በአብዛኛው ዋህድ-ዘር ድብልቆች ሙሙት ናቸው:: በምንዝሮቻቸውም መካከል ልዩነት የለም፡፡ ስለዚህ ምንዝሮቹን በቀላሉ መለየት አንችልም፡፡ የድብልቁ ይዘት ወጥና ተመሳሳይ ነው፡፡ ለምሳሌ የጨው ሙሙት፣የስኳር ሙሙት፣ የአልኮልና የውሃ ድብልቅ፣ አየርና የመሳሰሉት የዋህድ- ዘር ድብልቆች ናቸው፡፡ የአየር ምንዝሮች የምንላቸው ናይትሮጂን፣ ኦክስጅን፣ አርጎን፣ ካርቦን ዳይኦክሳይድና ከሌሎች ምንዝሮች የተሰራ ነው፡፡ እነዚህን ምንዝሮች ዋህድ ዘር ድብልቅ ስለሆኑ በአይንና በአጉሊ መነጸር መለየት አይቻልም፡፡ ምሥል 2.12 የጨው ሙሙት 2. ልይ-ዘር ድብልቆች (Hetrogeneous mixtures) የማነቃቂያ ጥያቄዎች ልይ- ዘር ድብልቅ ምንድን ነው? ደም ልይ-ዘር ድብልቅ ይመስላችኋል? ለምን? ልይ-ዘር ድብልቅ በድብልቁ ውስጥ ያሉትን ምንዝሮች በዓይን ወይም በአጉሊ መነጸር በመታገዝ ለይተን ማየት የምንችል ከሆነ ድብልቁ ልይ- ዘር ድብልቅ ይባላል፡፡ 49 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ በልይ- ዘር ድብልቅ ውስጥ ያሉ ምንዝሮች መካከል ልዩነት ስላለ ምንዝሮቹን በቀላሉ በዓይናችን ወይም በአጉሊ መነጸር መለየት እንችላለን፡፡ የድብልቁ ይዘትም ወጥና ተመሳሳይ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ደም፣ ወተት፣ የአሸዋና የውሃ ድብልቅ፤ የበቆሎና የስንዴ ድብልቅና የመሳሰሉት የልይ- ዘር ድብልቆች ናቸው፡፡ ደም በውስጡ ጠጣር የደም ህዋስና ውሀን በመያዙ ልይ- ዘር ድብልቅ ውስጥ ይመደባል፡፡ ተግባር 2.4 ተግባራዊ ክንውን ርዕስ፡-ልይ - ዘር ድብልቅ ዓላማ፡-የልይ - ዘር ድብልቅ ማዘጋጀትና ምንዝሮችን በአይነት በመመልከት ማየት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች፡-ሁለት እፍኝ ሽምብራ፣ ሁለት እፍኝ ገብስ፣ ዝርግ ሰሃን የአሰራር ቅደም ተከተል፡- 1. ከ 3-5 በመሆን ቡድን መስርቱ 2. በዝርግ ሰሃኑ ላይ የሽምብራውንና የገብሱን ፍሬ ጨምሩ በመቀጠልም በእጅ ጣቶቻችሁ አደባልቁ፡፡ ሙከራውን መሰረት በማድረግ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ላይ በቡድናችሁ ተወያዩና ለክፍል ጓደኞቻችሁ አቅርቡ ፡፡ 1. ያዘጋጃችሁት ድብልቅ ስንት ምንዝሮች አሉት? ስማቸውስ? 2. ያዘጋጃችሁትን ድብልቅ በአይን ለይታችሁ ማየት ችላችኋል? 3. ያዘጋጃችሁትን ድብልቅ የሚመስሉ ሌሎች የድብልቅ አይነቶችን ዘርዝሩ:: 50 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ መልመጃ 2.4 ሀ ተማሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ድብልቆች ዋህድ- ዘርና ልይ- ዘር ድብልቅ በማለት ከመደባችሁ በኋላ በቀረበው ሰንጠርዥ ሞልታችሁ መልሱን ለመምህራችሁ አሳዩ? የድብልቅ አይነት ዋህድ-ዘር ድብልቅ ልይ-ዘር ድብልቅ 1. ለስላሳ መጠጦች 2. የፍራፍሬ ጭማቂ 3. ጠጠርና የሎሚ ፍሬ 4. የስኳርናማር ድብልቅ 5. የስኳር ሙሙት 6. የሙዝና የቅቤ ድብልቅ 7. አሸዋና በቆሎ 8. የባቄላና የስንዴ ድብልቅ 9. የጨውና የስኳር ድብልቅ 10. የወተትና የቡና ድብልቅ የድብልቆች ልየታ የድብልቅ ምንዝሮች ኬሚካዊ ትስስር እንደሌላቸው ከዚህ በፈት ተምራችኋል፡፡ ስለዚህ ምንዝሮቹን በአካላዊ (ፊዚካዊ) ዘዴ መለያየት ይቻላል፡፡ ድብልቅን ወደ ምንዝሮቻቸው ለመለየት የሚከተሉትን ነጥቦች ማጤን ያስፈልጋል፡፡ ሀ. የድብልቁን አካላዊ ባህሪ ማወቅ ለምሳሌ፡- ሟሚነት በድብልቁ ውሰጥ አንዱ ምንዝር ወይም ልዩ- ቁስ በውሃ ውስጥ ሟሚ ቢሆንና ሌላኛው ምንዝር ደግሞ በውሃ ውስጥ ላይሟማ ይችላል ስለዚህ በቀላሉ እንለያቸዋለን ማለት ነው፡፡ 51 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ለ. ድብልቁን በመጠን መለየት ድብልቁን የሰሩት ምንዝሮች ወይም ልዩ-ቁሶች በመጠን ትንሽና ትልቅ ከሆኑ፤ ትልቁን ምንዝር በቀላሉ መለየት ይቻላል፡፡ ሐ. ድብልቁን በነጥበ- ፍሌት፣ በነጥበ- ቅልጠት እና በእፍግታ መለየት በድብልቁ ውስጥ ያሉት ምንዝሮች ባላቸው የነጥበ-ፍሌት (boiling point)፣ የነጥበ-ቅልጠት (melting point) ና በእፍግታ (density) ልዩነት በቀላሉ መለየት እንችላለን፡፡ ከላይ በተገለጹት የድብልቅ ልየታ የሚረዱ ነጥቦች (pa- rameters) በማገናዘብ የድብልቅ ልየታ ዘዴዎች በዐራት ከፍለን እናያለ፡፡ ሀ. ጥሊያ (Filtration) ተግባር 2.4 የቡድን ውይይት ተማሪዎች አምስት አምስት በመሆን ቡድን መስርቱና የሚከተሉትን ጥያቄዎች ስሩ መልሶቻችሁንም ለመምህራችሁ ግለጹ? 1. ጥሊያ ምንድን ነው? 2. ተማሪዎች ቤት ውስጥ ሻይ ሲፈላ ከማንቆርቆሪያው ወይም ከሻይ ጀበና ውስጥ በኩል ትንንሽ ቀዳዳዎችን አይታችሁ ታውቃላችሁ? የነዚህ ትንንሽ ቀዳዳዎች ጠቀሜታ ምን ይመስላችኋል? ጥሊያ ማለት ጥቃቅን ቀዳዳዎች ባሉት እቃ ላይ የፈሳሽና ያልሟሙ የጠጣር ድብልቅን የምንለይበት ዘዴ ነው፡፡ ድብልቁን በማጥለያ ላይ በማንቆርቆር ፈሳሹን ብቻ በቀዳዳዎቹ እንዲያልፍ በማድረግ ያልሟሟ ጠጣሩን ልዩ - ቁስ ደግሞ ማጥለያው ላይ እንዲቀር በማድረግ ይለያሉ፡፡ የማጥለያ እቃው ከጨርቅ፣ ከፕላስቲክ፣ ከብረትና ከወረቀት ሊሰራ ይችላል፡፡ ተግባር 2.4 የቤተ- ሙከራ ተግባራዊ ክንውን ርዕስ፡- የጠመኔ ዱቄትንና የውሃን ድብልቅ የመለየት ዘዴ ዓላማ፡- ጥሊያን በመጠቀም የጠመኔ ዱቄትንና የውሃን ድብልቅ መለየት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች፡- የጠመኔ ዱቄት፣ ውሃ፣ቅል አንገት (Funnel)፣ የማጣሪያ ወረቀት (Filter paper)፣ ቅምብብ ፋሽኮ (Conical flask) የአሰራር ቅደም ተከተል፡- 1. የማጣሪያ ወረቀቱን በትክክል በማጠፍና መሀሉን በመክፈት ቅል አንገቱ ውስጥ ክተቱት፡፡ 52 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ምሥል ‘ሀ’፣ ‘ለ’፣ እና ‘ሐ’ ተመልከቱ፡፡ ምሥል 2.13 የጠመኔ ዱቄትና የውሃ ድብልቅ ልየታ 2. የቅምብብ ፋሽኮ አፍ ላይ የማጣሪያ ወረቀት የያዘውን ቅል አንገት አስቀምጡ፡፡ ለአሰራሩ ምሥል 2.13 ተመልከቱ፡፡ 3. የጠመኔ ዱቄቱን ከውሃው ጋር አደባልቁና ድብልቁን በተዘጋጀው የቅምብብ ፋሽኮ አፍ ላይ በዝግታ አንቆርቁሩ፡፡ 4. ለትንሽ ደቂቃ ድብልቁ እስኪለይ ጠብቁ፡፡ ሙከራውን መሰረት በማድረግ በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ በቡድናችሁ ተወያዩና ለክፍል ጎደኞቻችሁ አቅርቡ፡፡ 1. የማጣሪያ ወረቀቱ ላይ ተለጥፎ የቀረው የጠመኔ ዱቄት ነው ወይስ ውሃው? አብራሩ፡፡ 2. ከተግባሩ ምን ተገነዘባችሁ? 3. የማጣሪያ ወረቀቱ ጥቅም ምንድን ነው? ለ. ቀረራ (Decanitation) ተግባር 2.5 የቡድን ውይይት ተማሪዎች አምስት አምስት በመሆን ቡድን መስርቱና የሚከተሉትን ጥያቄዎች ስሩ መልሶቻችሁንም ለመምህራችሁ ግለጹ? 1. ቀረራ ምን ማለት ነው? 2. በቀረራ መለየት የሚቻለው ምን አይነት ድብልቆችን ይመስላችኋል? 3. የቀረራ ጠቀሜታ ምን ይመስላችኋል? 53 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ በድብልቅ ውስጥ የሚገኝ ፈሳሽ ምንዝርን በዝግታ በማንቆርቆር (በመቅዳት) ከሌላኛው ካልሟሙ ጠጣሮች ወይም ፈሳሾች የምንለይበት ዘዴ ነው፡፡ ለምሳሌ ዘይትና የውሃ ድብልቅ፣

Use Quizgecko on...
Browser
Browser