Grade 6 Environmental Science 3 PDF

Document Details

LustrousSavanna6540

Uploaded by LustrousSavanna6540

Abiyot Primary School

Tags

environmental science east african geography natural resources climate

Summary

This document is a chapter on the natural environment of East Africa, focusing on climate regions, natural resources, and their usage. It covers topics like temperature variations, rainfall patterns, and natural resource management.

Full Transcript

Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ  ተማሪዎች ይህን የትምህርት ይዘት ተምራችሁ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፡-  በምሥራቅ አፍሪካ በተለያዩ ቦታዎች ያለውን ወቅታዊ የሙቀት መጠን ልዩነት ትገልጻላችሁ፡፡  በምሥራቅ...

Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ  ተማሪዎች ይህን የትምህርት ይዘት ተምራችሁ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፡-  በምሥራቅ አፍሪካ በተለያዩ ቦታዎች ያለውን ወቅታዊ የሙቀት መጠን ልዩነት ትገልጻላችሁ፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ የሚኖረውን ወቅታዊ የዝናብ ሥርጭት ታወዳድራላችሁ፡፡  የምሥራቅ አፍሪካ የአየር ንብረት ክልሎች ትለያላችሁ፡፡  ምሥራቅ አፍሪካን ዋና ዋና የተፈጥሮ ሀብት ትለያላችሁ፡፡  የምሥራቅ አፍሪካን ውጤታማ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ትገልጻላችሁ፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙ የተለያዩ ማዕድናትን በመግለጽ ታወዳድራላችሁ፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙ የተለያዩ ማዕድናትን ምጣኔ ሀብታዊና ባህላዊ እሴቶችን ትገልጻላችሁ፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ የማዕድናት አጠቃቀም ተግዳሮቶችን ታብራራላችሁ፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች መካከል ያለውን የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ዘዴዎችን ታወዳድራላችሁ፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ የሚበቅሉ የዕፅዋት ዓይነቶችን ትከፍላላችሁ፡፡  የምሥራቅ አፍሪካን የተለያዩ የውሃ ሀብት (ወንዞችና ሐይቆች) በመግለጽ ታወዳድራላችሁ፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙ የውሃ ሀብትን አጠቃቀም ተግዳሮት ታብራራላችሁ፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል በሚገኙ ወንዞች የሚታዩ የአጠቃቀም ተግዳሮትን ታብራራላችሁ፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ በብዛት ሊገኙ የሚችሉ ማዕድናትን ትዘረዝራላችሁ፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች የሚገኙ ማዕድናትን ታወዳድራላችሁ፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ የሚታየውን የደን ጭፍጨፋ መጠን ታብራራላችሁ፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች መካከል የደን ጭፍጨፋን ለመከላከል የሚወስዱ መፍትሔዎችን ታብራራላችሁ፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ የማዕድናት መመናመንን የሚያባብሱ ሁኔታዎችን ትዘረዝራላችሁ፡፡ 69 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ የምዕራፉ ዋና ዋና ይዘቶች 3.1 የምሥራቅ አፍሪካ የአየር ንብረት ክልሎች 3.2 የምሥራቅ አፍሪካ የተፈጥሮ ሀብት 3.3 የምሥራቅ አፍሪካ ዋና ዋና የአፈር ዓይነቶች 3.4 የምሥራቅ አፍሪካ የውሃ ሀብት 3.1 የምሥራቅ አፍሪካ የአየር ንብረት ክልሎች ከንዑስ ርዕሱ የሚጠበቁ አጥጋቢ የመማር ብቃቶች፡- ተማሪዎች ይህን ንዑስ ርዕስ ትምህርት ተምራችሁ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፡-  በምሥራቅ አፍሪካ በተለያዩ ቦታዎች ያለውን ወቅታዊ የሙቀት መጠን ልዩነት ትገልጻላችሁ፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ የሚኖረውን ወቅታዊ የዝናብ ሥርጭት ታወዳድራላችሁ፡፡  የምሥራቅ አፍሪካ የአየር ንብረት ክልሎች ትለያላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት አየር የአየር ሁኔታ የአየር ንብረት ክልል የአየር ንብረት ተቆጣጣሪዎች የማነቃቂያ ጥያቄዎች የአየር ሁኔታ ማለት ምን ማለት ነው? የአየር ንብረትስ? የአየር ሁኔታና አየር ንብረት ልዩነት ምንድን ነው? አንድነታቸውስ? የአየር ሁኔታ በተወሰነ አካባቢ እና ለአጭር ጊዜ የሚከሰት ዕለታዊ የአየር ፀባይ መቀያየር ሲሆን የአየር ንብረት ደግሞ በአንድ በተወሰነ አካባቢ ለረዥም ጊዜ የሚከሰት የአየር ሁኔታ ድምር ውጤት ነው፡፡ የአየር ሁኔታና የአየር ንብረት ልዩነታቸው የጊዜ ርዝመት ሲሆን አንድነታቸው ደግሞ በይዘታቸው ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ማለትም ሁለቱም የአየር ግፊት፣ የሙቀት መጠን፣ የዝናብ ሥርጭትና የመሳሰሉትን ያካትታሉ፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ የተለያየ መልክአ ምድር በመኖሩ ምክንያት የተለያየ የአየር ንብረት እንዲኖር አስችሎታል፡፡ 70 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ የምሥራቅ አፍሪካ የአየር ንብረት ልዩነቶች የምሥራቅ አፍሪካ ከፍተኛ ቦታዎች የሚባሉት ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ታንዛንያ ዝቅተኛ ሙቀት አላቸው፡፡ በነዚህ ሀገራት ባሉ ከፍተኛ ቦታዎች ዓመታዊ አማካይ የሙቀት መጠን እስከ 60ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ይደርሳል፡፡ በተቃራኒው ዝቅተኛ ቦታዎች/ lowlands/ እና ረበዳማ ሥፍራዎች /depressions/ እስከ 260 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ የሚደርስ ዓመታዊ አማካይ የሙቀት መጠን ያስመዘግባሉ፡፡ ከዝናብ ሥርጭት አንጻር ሲታይ አብዛኛው የምሥራቅ አፍሪካ ክፍል ደረቅ ነው:: በኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታዎች፣ በተወሰነ የኬንያ ክፍል፣ በታንዛንያ፣ በዩጋንዳ፣ በሩዋንዳ እና በቡሩንዲ አካባቢ ለግብርና ሥራ በቂ የሚሆን የዝናብ መጠን ይታያል፡፡ ምሥራቅ አፍሪካ በሚገኙ ሀገራት የሚታየው የዝናብ ሥርጭትና የዝናብ ወቅት ተመሳሳይ አይደለም፡፡ ስለዚህም የቀጠናው የዝናብ ወቅትን በሚከተለው መልክ በሦስት ከፍሎ መመልከት ይቻላል፡፡ 1. በምሥራቅ አፍሪካ ሰሜናዊ ክፍል የሚገኙ ብዙ አካባቢዎች ዝናብ የሚያገኙት ከሰኔ እስከ መስከረም ባለው የዝናብ ወቅት ነው፡፡ 2. ከምድር ወገብ በስተ ደቡብ የሚገኙት የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ዝናብ የሚያገኙት ከታኅሣሥ እስከ የካቲት ባሉት ወራት ነው፡፡ 3. በምድር ወገብ አካባቢ ያሉ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ዝናብ የሚያገኙት ደግሞ በጥቅምት እና ሚያዝያ ወር ነው፡፡ ምስል 3.1 የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ወቅታዊ የሙቀት ሥርጭት 71 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ መፍቻ ዓመታዊ የዝናብ መጠን በሚሊሜትር ምስል 3.2 የምሥራቅ አፍሪካ አመታዊ የዝናብ መጠን የቡድን ውይይት 3.1 ዓላማ፡ በምሥረቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን የዝናብና የሙቀት መጠን ስርጭትን መለየት መመሪያ፡ ተማሪዎች በቡድን በመሆን በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ በመወያየት መልሶቻችሁን ለመምህራችሁ ግለጹ፡፡ 1. ከላይ በምስል 3.2 ያለውን የዝናብ መጠንን የሚያሳይ ካርታ በመመልከት የምሥራቅ አፍሪካን ከፍተኛና ዝቅተኛ የዝናብ መጠን ያላቸውን አካባቢዎች አሳዩ፡፡ 2. ስለ ምሥራቅ አፍሪካ አጠቃላይ የአየር ንብረት ተወያዩ፡፡ 3. ከላይ በምስል 3.1 ያለውን የሙቀት መጠንን የሚሳይ ካርታን በመመልከት ከፍተኛና ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ያላቸውን የምሥራቅ አፍሪካ አካባቢዎች አሳዩ፡፡ 72 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ የአየር ንብረት ይዘቶች ዋና ዋና የአየር ንብረት ይዘቶች የሚባሉት እነማን ናቸው? የአየር ንብረት በአንድ ሥፍራ ለረዥም ጊዜ የሚከሰት የአየር ጠባይ ሲሆን የየዕለቱ የአየር ሁኔታ አማካይ ውጤት ለረዥም ጊዜ ቢያንስ ለ 30 ዓመት እና ከዚያ በላይ በማጥናት የሚታወቅ ነው፡፡ የአየር ንብረት፡- የውሃ፣ የእፅዋት እና የእንስሳት ሥርጭት እና የአፈር ዓይነትን በመቆጣጠር ከፍተኛ ተጽዕኖ ይፈጥራል፡፡ የአየር ሁኔታ በደቂቃ፣ በሰዓት፣ በቀናት እንዲሁም በየወቅቱ በተወሰነ ቦታ የሚታይ ዕለታዊ የአየር ለውጥ ነው፡፡ የአየር ለውጥ ማለት የሙቀት መጠን ሥርጭትን፣ የእርጥበት ሁኔታን፣ የአየር ግፊትን እና የንፋስ እንቅስቃሴና አቅጣጫን ያጠቃልላል፡፡ ዋና ዋና የአየር ንብረት ይዘቶች የሚባሉት ሙቀትና ቅዝቃዜ፣ እርጥበት፣ የአየር ግፊት እና ንፋስ ናቸው፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ የአየር ሁኔታና የአየር ንብረት ባሕርያት የማነቃቂያ ጥያቄ የአየር ንብረት ክልል ምንድን ነው? የአየር ንብረት ክልል በአንድ አካባቢ የሚገኝ ተመሳሳይ የአየር ንብረት የሚታይበት የመሬት ገጽ ነው፡፡ የአየር ንብረት ክልል በተለይ የሙቀትና የዝናብ መጠንን መሠረት በማድረግ ይገለጻል፡፡ ምሥራቅ አፍሪካ የሚከተሉት አራት ዋና ዋና የአየር ንብረት ክልሎችን ይይዛል፡፡ 1. የሣር ምድር ሞቃታማ የአየር ንብረት ክልል 2. የበረሃ አየር ንብረት ክልል 3. የሐሩር ሞቃታማ የባሕር ዳርቻዎች 4. የደጋ የአየር ንብረት ክልልን ያጠቃልላል፡፡ በመቀጠል የእያንዳንዱን የአየር ንብረት ክልል መገለጫዎች እንመልከት፡፡ 73 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ 1. የሣር ምድር ሞቃታማ የአየር ንብረት ክልል ይህ የአየር ንብረት ክልል በአፍሪካ በከፍተኛ እርጥበት እና በደረቅ የአየር ንብረት ክልሎች መካከል ላይ ከ 50 እስከ 150 ሰሜን እና ደቡብ ንፍቀ ክበብ ይገኛል፡፡ የሣር ምድር የአየር ንብረት ክልል በሞቃትና እርጥብ የሐሩር የአየር ንብረት ክልል እና በበረሃ የአየር ንብረት ክልል መካከል ስለሚገኝ የሽግግር ቀጠና በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ የአየር ንብረት ክልል በስፋት የሚገኘው በምሥራቅ አፍሪካ በሚገኘው የማዳጋስካር ደሴት ምዕራባዊ ክፍል ነው፡፡ 2. የበረሃ አየር ንብረት ክልል ይህ የአየር ንብረት የሚገኘው በሶማሊያ፣ በኤርትራ እና በሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ ዝቅተኛ ሥፍራ በሚገኙ አካባቢዎች ነው፡፡ ዓመታዊ አማካይ የዝናብ መጠናቸው ከ250 ሚ.ሜ በታች የሆኑ ቦታዎች በረሃ ተብለው ይጠራሉ፡፡ የበረሃ የአየር ንብረት በሚታይበት አካባቢ የደመና ሽፋን ባለመኖሩ ምክንያት ቀን ቀን በጣም ሲሞቅ ሌሊት ሌሊት ደግሞ ይቀዘቅዛል፡፡ ስለዚህም ዕለታዊ የሙቀት ልዩነቱ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ በበረሃ አካባቢ የሚዘንብ ድንገተኛ ዝናብ ወደ አፈር ውስጥ ሳይዘልቅ በአካባቢው ባለው ከፍተኛ የሙቀት መጠን አማካኝነት ወደ ትነት ይቀየራል:: ስለዚህም አካባቢው ዘወትር ደረቅ ነው፡፡ 3. የሐሩር ሞቃታማ የባሕር ዳርቻዎች የሐሩር ሞቃታማ የባሕር ዳርቻ የአየር ንብረት ክልል የሚገኘው በአፍሪካ አህጉር ደቡባዊ ንፍቀ ክበብ (southern hemisphere) ብቻ ነው፡፡ በተለይ እንደ ታንዛንያ እና ማዳጋስካር ባሉ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት በስፋት ይገኛል፡፡ በሞዛምቢክ ሞቃታማ የውቅያኖስ ሞገድ ተፅዕኖ ምክንያት ይህ አካባቢ ዓመቱን ሙሉ ከፍተኛ ሙቀት እና የዝናብ መጠን አለው፡፡ 4. የደጋ የአየር ንብረት ክልል የደጋ የአየር ንብረት ክልል በአብዛኛው የሚገኘው በኢትዮጵያ፣ በኬንያ እና በታንዛንያ ከፍተኛ ቦታዎች ባሉ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ነው፡፡ በዓለም ላይ ካለው የደጋ የአየር ንብረት ክልል ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ ይህ የአየር ንብረት በዝቅተኛ ሙቀት የተነሣ የኪሊማንጃሮ እና የኬንያ ተራራ ጫፎች በበረዶ ይሸፈናሉ፡፡ በዚህ አካባቢ በተራራ ተጽእኖ የሚፈጠረው የዝናብ ዓይነት ጉባገብ ዝናብ (orgraphic / relief) ይባላል፡፡ ይህ የዝናብ ዓይነት ከፍታ ሲጨምር የዝናብ መጠኑም እየጨመረ ይሄዳል፡፡ 74 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ ምስል 3.3 የምሥራቅ አፍሪካ የአየር ንብረት ክልሎች የአየር ንብረት ተቆጣጣሪዎች የማነቃቂያ ጥያቄዎች 1. የአየር ሁኔታ እና የአየር ንብረት ተቆጣጣሪ ማለት ምን ማለት ነው? 2. የአየር ንብረት ተቆጣጣሪዎች የሚባሉት ማን ማን ይባላሉ? 3. የምሥራቅ አፍሪካን ዋና ዋና የአየር ንብረት ተቆጣጣሪዎች ላይ ተወያይታችሁ መልሱን ለመምህራችሁ ግለጹ፡፡ በመሬት ላይ የሙቀት፣ የነፋስ፣ የዝናብ እና የአየር ግፊት ሥርጭት እኩል እንዳይሆን የሚያደርጉ ተፈጥሮአዊ ምክንያቶች የአየር ንብረት ተቆጣጣሪዎች ይባላሉ፡፡ ዋና ዋና የአየር ንብረት ተቆጣጣሪ የሚባሉት አራት ናቸው፡፡ እነርሱም ከምድር ወገብ ያለዉ ርቀት፣ ከፍታ፣ ከባሕር ያለው ርቀትና የውቅያኖስ ሞገድ ናቸው፡፡ በመቀጠል እያንዳንዱ የአየር ንብረት ተቆጣጣሪ የሚኖረውን ተጽዕኖ በአጭሩ እንመልከት፡፡ 75 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ 1.ከምድር ወገብ ያለው ርቀት፡- አንድ ቦታ ከምድር ወገብ የሚኖረው ርቀት በአየር ንብረቱ ላይ ተጽእኖ ያደርግበታል:: ከምድር ወገብ የሚኖር ርቀት በመሬት ላይ የሚያርፈውን የፀሐይ ጨረር ማዕዘን ይወስናል፡፡ ከምድር ወገብ እስከ 23 ½ ዲግሪ ሰሜንና ደቡብ ንፍቀ ክበብ በሚገኙ ቦታዎች ላይ የፀሐይ ጨረር በቀጥታ ያርፋል፡፡ ጨረሩ የሚሸፍነው የቦታ መጠን አነስተኛ በመሆኑ በአካባቢው የሚከሰተው የሙቀት መጠን ከፍተኛ ይሆናል፡፡ ይህ ፀሐይ በቀጥታ የምታርፍበትና ከፍተኛ ሙቀት የሚመዘገብበት የምድር ወገብ አካባቢ ሞቃት የሐሩር የአየር ንብረት ክልል ይባላል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ከምድር ወገብ በርቀት በሚገኙ ቦታዎች የፀሐይ ጨረር የሚያርፈው አግድም (በሰያፍ) በመሆኑ ጨረሩ ሰፊ አካባቢ ይሸፍናል፡፡ ስለዚህም ጨረሩ የሚፈጥረው የሙቀት መጠን አነስተኛ ይሆናል፡፡ በዚህ የተነሣ ከምድር ወገብ በቅርብ ርቀት የሚገኙ ቦታዎች ከፍተኛ የሙቀት መጠን እንዲሁም በተቀራኒው ከምድር ወገብ ርቀው በሚገኙ አካባቢዎች ዝቅተኛ ሙቀት ይኖራቸዋል፡፡ ቀጥተኛ የፀሐይ ጨረር የሚያርፍባቸው ከምድር ወገብ 23½ ሰሜንና ደቡብ መካከል ያሉ አካባቢዎች ከፍተኛ ሙቀትና ከፍተኛ ዝናብ እንዲሁም ዝቅተኛ የአየር ግፊት ይኖራቸዋል፡፡ በአካባቢው በሚመዘገብ ከፍተኛ የሙቀት መጠን የተነሣ ይህ አካባቢ ሞቃታማ የሐሩር የአየር ንብረት ክልል ተብሎ ይጠራል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ በዋልታዎች የሚገኙ አካባቢዎች የፀሐይ ጨረር በሰያፍ ስለሚያርፍባቸው አነስተኛ ሙቀትና ዝናብ እንዲሁም ከፍተኛ የአየር ግፊት ይኖራቸዋል፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት በሐሩር ሞቃታማ የአየር ንብረት ክልል ስለሚገኙ ከፍተኛ ሙቀትና ከፍተኛ ዝናብ እንዲሁም ዝቅተኛ የአየር ግፊት ይኖራቸዋል፡፡ 2. ከፍታ ከፍታ ሲጨምር የአየር ሙቀት ይቀንሳል፡፡ ስለዚህም ከፍታ የአንድን ቦታ የአየር ንብረት ወሳኝ ተቆጣጣሪ ነው፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ በሐሩር ሞቃታማ የአየር ንብረት ክልል የሚገኙ እንደ ኢትዮጵያና ኬንያ የመሳሰሉት ሀገራት በከፍተኛ ተራራዎችና አምባ ምድሮች ላይ ይገኛሉ፡፡ ሀገራቱ በሚገኙበት ከፍተኛ መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ የተነሣ ሞቃት የአየር ንብረት የላቸውም፡፡ በዝቅተኛ መልክአ ምድር ላይ የሚገኙ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ግን ከፍተኛ ሙቀት ያለው የአየር ንብረት አላቸው፡፡ በዚህም ከምድር ወገብ በተመሳሳይ ርቀት ላይ ቦታዎች በሚገኙበት የከፍታ መጠን የተነሣ የተለያየ የአየር ንብረት ሊኖራቸው እንደሚችል መገንዘብ ይገባል፡፡ 3. ከባሕር ያለው ርቀት ሁለት የተለያዩ ሥፍራዎች ከምድር ወገብ ተመሳሳይ ርቀት ቢኖራቸው እንዲሁም ተመሳሳይ ከፍታ ባለው መልክአ ምድር ላይ ቢገኙም ከባሕር በሚኖራቸው ርቀት 76 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ ምክንያት የተለያየ የአየር ንብረት ሙቀት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ይህም ማለት ቦታዎቹ ለባሕር ጠረፍ በሚኖራቸው ቅርበትና ርቀት መጠን የተለያየ የሙቀትና የቅዝቃዜ መጠን ሊኖራቸው ይችላል፡፡ በዚህም መሠረት በባሕር ጠረፍ አካባቢ የሚገኙ ሀገራት በክረምትና በበጋ ወቅት ጉልህ የሙቀት ልዩነት አይታይባቸውም፡፡ በተቃራኒው ከባሕር ጠረፍ የራቁ አካባቢዎች በክረምት ላይ በጣም ሞቃት በበጋ ደግሞ በጣም ቀዝቃዛ የአየር ንብረት ይኖራቸዋል፡፡ 4. የውቅያኖስ ሞገድ በነፋስ ኃይል በመገፋት ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚያደርግ የውቅያኖስ ውሃ የውቅያኖስ ሞገድ ይባላል፡፡ ከሞቃት አካባቢ የሚነሣ የውቅያኖስ ሞገድ አካባቢውን ስለሚያሞቅ በአካባቢው የሚገኙ ሀገራት ሞቃት የአየር ንብረት ይኖራቸዋል፡፡ በተቃራኒው ከቀዝቃዛ አካባቢ የሚነሣ የውቅያኖስ ሞገድ ደግሞ በአካባቢው ቀዝቃዛ የአየር ንብረት እንዲፈጠር ተጽዕኖ ያደርጋል፡፡ ለምሳሌ በምሥራቅ አፍሪካ ዳርቻ የሚገኘው የሞዛቢክ ሞቃታማ ሞገድ በሞዛቢክና በማዳጋስካር ሞቃታማ የአየር ንብረት እንዲኖር አድርጓል፡፡ መልመጃ 3.1 ሀ. የሚከተሉትን ዐረፍተ ነገሮች አንብባችሁ ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል ካልሆኑ ደግሞ ሐሰት በማለት መልሱ፡፡ 1. የምሥራቅ አፍሪካ ሰሜናዊ ክፍል ያሉ ሀገራት ከፍተኛ ዝናብ የሚያገኙት ከታኅሳስ እስከ የካቲት ባሉት ወራት ነው፡፡ 2. የአየር ንብረት ለረዥም ጊዜ የሚከሰት አማካይ የአየር ፀባይ ድምር ውጤት ነው፡፡ 3. በምድር ወገብ አካባቢ ያሉ ሀገራት ሰያፍ የፀሐይ ጨረር ያገኛሉ፡፡ 4. የውቅያኖስ ሞገድ የአየር ንብረት ተቆጣጣሪ ነው፡፡ ለ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ከተሰጡት አማራጮች ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡ 1. ከሚከተሉት ውስጥ የአየር ንብረት ተቆጣጣሪ ያልሆነው ትኛው ነው? ሀ) ከፍታ ለ) የውቅያኖስ ሞገድ ሐ) ከምድር ወገብ ያለው ርቀት መ) የሙቀት መጠን 2. በደቂቃዎችና በሰዓታት የሚቀያየር የአየር ፀባይ ------- ይባላል፡፡ ሀ) የአየር ንብረት ለ) የአየር ግፈት ሐ) የአየር ሁኔታ መ) ሁሉም 77 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ 3. የኢትዮጵያና የኬንያ ከፍተኛ ቦታዎች የሚያገኙት የዝናብ ዓይነት ምን ይባላል? ሀ. ጉባገብ ሐ. ስግረት ዝናብ ለ. ግንባር ዝናብ መ. ሳይክሎኒክ ዝናብ 4. በሰሜንና በደቡብ ዋልታ የሚገኙ አካባቢዎች ዝቅተኛ የሙቀት መጠን እንዲኖራቸው ያደረገው ምክንያት ምንድን ነው? ሀ. ከባሕር ባላቸው ርቀት ለ. ከምድር ወገብ ባላቸው ርቀት ሐ. በውቅያኖስ ሞገድ መ. በከፍታ 5. በኤርትራ እና በሶማሊያ በስፋት ያለው የአየር ንብረት ክልል የትኛው ነው? ሀ) የደጋ አየር ንብረት ክልል ለ) የሣር ምድር አየር ንብረት ክልል ሐ) የሐሩር ጥቅጥቅ ደን አየር ንብረት ክልል መ) የበረሃ አየር ንብረት ክልል 3.2 የምሥራቅ አፍሪካ የተፈጥሮ ሀብት ከንዑስ ርዕሱ የሚጠበቁ አጥጋቢ የመማር ብቃቶች ተማሪዎች ይህን ንዑስ ርዕስ ትምህርት ተምራችሁ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፡-  የምሥራቅ አፍሪካን ዋና ዋና የተፈጥሮ ሀብት ትለያላችሁ፡፡  የምሥራቅ አፍሪካን ውጤታማ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ትገልጻላችሁ፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙ የተለያዩ ማዕድናትን በመግለጽ ታወዳድራላችሁ፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙ የተለያዩ ማዕድናትን ምጣኔ ሀብታዊና ባህላዊ እሴቶችን ትገልጻላችሁ፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ የማዕድናት አጠቃቀም ተግዳሮቶችን ታብራራላችሁ፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች መካከል ያለውን የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ዘዴዎችን ታወዳድራላችሁ፡፡ 78 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ  በምሥራቅ አፍሪካ የሚበቅሉ የዕፅዋት ዓይነቶችን ትከፍላላችሁ፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል በሚገኙ ወንዞች የሚታዩ የአጠቃቀም ተግዳሮትን ታብራራላችሁ፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ በብዛት ሊገኙ የሚችሉ ማዕድናትን ትዘረዝራላችሁ፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች የሚገኙ ማዕድናትን ታወዳድራላችሁ፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ የሚታየውን የደን ጭፍጨፋ መጠን ትመረምራላችሁ፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች መካከል የደን ጭፍጨፋን ለመከላከል የሚወስዱ  መፍትሔዎችን ታብራራላችሁ፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ የማዕድናት መመናመንን የሚያባብሱ ሁኔታዎችን ትዘረዝራላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት ማዕድን የተፈጥሮ ሀብት የማነቃቂያ ጥያቄዎች 1. የተፈጥሮ ሀብት ምንድን ነው? 2. ሁሉም የተፈጥሮ ሀብት በሁሉም አካባቢዎች ይገኛሉ? ካልተገኙ ምክንያቱ ምንድን ነው? የተፈጥሮ ሀብት የሚባሉት በተፈጥሮ የሚገኙና ለሰው ልጆች ኑሮ አስፈላጊ ሀብት ናቸው፡፡ የሰው ልጅ መሠረታዊ ነገሮች የሚያገኘው ከተፈጥሮ ሀብት ነው፡፡ ሁሉም የተፈጥሮ ሀብት በሁሉም አካባቢ በወጥነት አይገኙም፡፡ ምክንያቱም የተፈጥሮ ሀብት ለመፈጠር ምቹ ተፈጥሮአዊ ሁኔታን ስለሚፈልጉ ነው፡፡ የአየር ንብረት መለያየት ለተፈጥሮ ሀብት አቅርቦት መለያየት ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡ ለምሳሌ በቂ ዝናብ ባላቸው አካባቢዎች የተለያዩ ዕፅዋት፣ የዱር እንስሳትና የግብርና ምርት በስፋት ይገኛል፡፡ በዚህ ምክንያት አንዳንድ ሀገራት የተትረፈረፈ የተፈጥሮ ሀብት ሲኖራቸው ሌሎች ደግሞ ውስን የተፈጥሮ ሀብት አላቸው፡፡ በቂ ተፈጥሮ ሀብት የሌላቸው ሀገራት የሚፈለጉትን ምርት ለማግኘት በጥሬ ዕቃነት የሚያስፈልጋቸውን የተፈጥሮ ሀብት ከሌላ ሀገር ያስመጣሉ፡፡ 79 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ የምሥራቅ አፍሪካ ዋና ዋና የተፈጥሮ ሀብት የማነቃቂያ ጥያቄዎች 1. በአካባቢያችሁ ምን ምን ዓይነት የተፈጥሮ ሀብት ይገኛሉ? 2. የምሥራቅ አፍሪካ ዋና ዋና የተፈጥሮ ሀብትን ዘርዝሩ፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ የተለያዩ ተራሮች፣ አምባ ምድሮች እንዲሁም ዝቅተኛ ሥፍራዎች በመኖራቸው ምክንያት ቀጠናው የተለያዩ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት እንዲሆን አስችሎታል፡፡ ከምሥራቅ አፍሪካ የተፈጥሮ ሀብቶች መካከል ለግብርና ተስማሚ አፈር፣ ውሃ፣ ለኑሮ ተስማሚ አየር፣ ማዕድናት፣ የዱር እንስሳት እና ዕፅዋቶችን ያጠቃልላል፡፡ በመቀጠል ዋና ዋና የምሥራቅ አፍሪካ የተፈጠሮ ሀብቶችን በአጭሩ እንመልከት፡፡ ማዕድን የማነቃቂያ ጥያቄዎች 1. ማዕድን ምንድን ነው? 2. የማዕድንን ጠቀሜታ ዘርዝሩ፡፡ በተፈጥሮ የሚገኙ የተለያዩ ብረትአስተኔ፣ ኢ-ብረት አስተኔና የነዳጅ ሀብት ማዕድናት ይባላሉ፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ብዙ ቁጥር ያላቸው የማዕድን ዓይነቶች ይገኛሉ:: ነገር ግን ሁሉም ማዕድናት ከመሬት ውስጥ ወጥተው አገልግሎት ላይ አልዋሉም፡፡ ዋና ዋናዎቹ የማዕድናት ወርቅ፣ መዳብ፣ የድንጋይ ከሰል፣ የኖራ ድንጋይ፣ ብረት፣ የተፈጥሮ ጋዝ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ የማዕድን ሀብት የቡድን ውይይት 3.2.ሀ 1. የምታውቋቸውን የማዕድን ዓይነቶች ዘርዝሩ፡፡ 2. በምሥራቅ አፍሪካ በብዛት ሊገኙ የሚችሉ ማዕድናትን ዘርዝሩ፡፡ 3. በምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች የሚገኙ ማዕድናትን አወዳድሩ፡፡ 80 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ ማዕድናት የተለያየ ምጣኔ ሀብታዊ እና ማኅበራዊ ጠቀሜታ አላቸው፡፡ ለምሳሌ ማዕድናት፡- በገቢ ምንጭነት፤ በውጭ ምንዛሪ ምንጭነት፤ በሥራ ዕድል ፈጣሪነት፤ የተለያዩ መሠረተ-ልማቶችን (ውሃ፣ መንገድ እና መብራት) ለማስፋፋት፤ የተለያዩ ማኅበራዊ አገልግሎቶች (ጤና እና ትምህርት) በስፋት ለማዳረስ እና የገበያ ትሥሥር ለማሳደግ ይጠቅማል፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና በተፈጥሮ ሀብት የበለፀገ ነው፡፡ ቀጥሎ በቀረበው ሰንጠረዥ ውስጥ በተለያየ ማዕድን የሚታወቁ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን ተመልከቱ፡፡ ሰንጠረዥ 3.1 የምሥራቅ አፍሪካ ዋናዋና የማዕድን ዓይነቶች ሀገር የማዕድን ዓይነት ኢትዮጵያ ወርቅ፣ ብር፣ ብረት፣ የድንጋይ ከሰል፣ ጨው፣ እምነ-በረድ፣ ሶዳ አሽ፣ ሸክላ አፈር ሶማሊያ የተፈጥሮ ነዳጅ፣ ወርቅ ኬንያ መዳብ፣ ወርቅ፣ ብረት፣ኒኬል፣ ዚርኮን ታንዛንያ ወርቅ፣ ብረት፣ ኒኬል፣ ብር፣ አልማዝ፣ የድንጋይ ከሰል፣ ዩራኒየም ዩጋንዳ ግራፋይት፣ ጀሶ፣ የኖራ ድንጋይ፣ ጨው፣ እምነ-በረድ፣ ማይካ ሩዋንዳ ወርቅ፣ የተፈጥሮ ነዳጅ፣ ቆርቆሮ ቡሩንዲ ወርቅ፣ ቆርቆሮ ሞዛምቢክ አልሙኒየም፣ ወርቅ፣ ሸክላአፈር፣ የድንጋይ ከሰል፣ የተፈጥሮ ነዳጅ፣ እምነ-በረድ፣ የኖራ ድንጋይ የምሥራቅ አፍሪካ የማዕድናት አጠቃቀም ተግዳሮት የማዕድን ሀብት በምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ ለሚኖሩ ዜጎች በርካታ ምጣኔ ሀብታዊ እና ማኅበራዊ ጠቀሜታ አለው፡፡ ለምሳሌ የሥራ ዕድል ፈጠራና የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን በማሟላትና በመሳሰሉት ጥቅም ይሰጣል፡፡ ምሥራቅ አፍሪካ ጥቅም ላይ ያልዋሉ ብዙ የማዕድናት ዓይነቶች ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ማዕድናት በስፋት ቢገኙም በተለያየ ምክንያት አውጥቶ ጥቅም ላይ ለማዋል የተለያዩ ማነቆዎች አሉ፡፡ በቀጠናው ማዕድናትን አውጥቶ ለመጠቀም ዐበይት ተግዳሮት የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው፡፡ ማዕድናትን ከከርሰ ምድር ለማውጣት የሚያግዝ በቂ የመሠረተ-ልማት አለመኖር፣ ማዕድናትን ለማውጣት በሞያው የሠለጠነ የሰው ኃይል እጥረት፣ በማዕድን ቁፋሮ የቴክኖሎጂ እጥረት አነስተኛ የሀገር ውስጥ ፍላጎት እና የመሳሰሉት በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ 81 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ የምሥራቅ አፍሪካ ተገቢ ያልሆነ የማዕድናት አጠቃቀም እና የሚያስከትለው አሉታዊ ተጽዕኖ ማዕድናት በባህላዊ መንገድ እንዴት ከመሬት ውስጥ እንደሚወጡ ታውቃላችሁ? ማዕድናትን በትክክል ከተጠቀምናቸው ለሀገራት ዕድገት ወሳኝ ሚና አላቸው፡፡ ነገር ግን የማዕድን ማውጣቱ ሂደት የሚያስከትላቸው ዘርፈ ብዙ የአካባቢ ጉዳቶች አሉት:: ለምሳሌ ለማዕድን አገልግሎት የዋለ ቦታ፡- ለአፈር እና ውሃ ጥበቃ ያስቸግራል፣ በአካባቢው ያሉ የዱር እንስሳት ይሰደዳሉ፣ በአፈር ውስጥ ያሉ ጥቃቅን ዘ-አካላት ይሞታሉ፣ የመሬት አቀማመጥን ያበላሻል፣ የአየርና የውሃ መበከል ያስከትላል፣ የአየር ፀባይ እንዲቀየር ያደርጋል፣ የግብርና ምርት እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ የቡድን ውይይት 3.2.ለ ዓላማ፡ የምሥራቅ አፍሪካን የማዕድን ሀብት አጠቃቀም መለየት፡፡ መመሪያ፡ ተማሪዎች በቡድን በመሆን በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ከተወያያችሁ በኋላ መልሱን ለመምህራችሁ አቅርቡ፡፡ 1. በምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ያለውን የማዕድን ሀብት አወዳድሩ፡፡ 2. በምሥራቅ አፍሪካ የማዕድን ሀብት አጠቃቀም ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ሁኔታዎችን በመለየት አስረዱ፡፡ 3. በምሥራቅ አፍሪካ የማዕድን ሀብት የሚሰጠውን ምጣኔ ሀብታዊና ባህላዊ ጠቀሜታ የሚያሳዩ ቢያንስ ሦስት መገለጫዎች ግለጹ፡፡ 4. በምሥራቅ አፍሪካ የተሻለ የማዕድን ሀብት ያላቸውን ሀገራት ዘርዝሩ፡፡ 5. ከምሥራቅ አፍሪካ ማዕድናት መካከል ሦስቱን በመውሰድ ጥቅማቸውን ዘርዝሩ፡ 6. የማዕድናት ምጣኔ ሀብታዊ ጠቀሜታዎችን ግለጹ፡፡ 82 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ የምሥራቅ አፍሪካ ውጤታማ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ዘዴዎች የማነቃቂያ ጥያቄዎች 1. ውጤታማ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ምንድን ነው? 2. የአካባቢያችሁ ነዋሪዎች የተፈጥሮ ሀብትን የሚጠቀሙት እንዴት ነው? 3. ለተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ በሚደረገው እንቅስቃሴ ምን ዓይነት ተሳትፎ ሊኖራችሁ ይችላል? በአንድ አካባቢ የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶች በአግባቡ በመጠቀም፣ ለረዥም ጊዜ እንዲቆዩና ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፉ የሚደረግ እንቅስቃሴ ውጤታማ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ይባላል፡፡ ዕፅዋትና የዱር እንስሳት ለሰው ልጆች የተለያዩ ጥቅሞችን ይሰጣሉ፡፡ በተጨማሪም የተፈጥሮ ሚዛን እንዳይዛባ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ በርካታ የተፈጥሮ ሀብቶች ይገኛሉ። እነዚህ የተፈጥሮ ሀብቶች አህጉራዊና ቀጠናዊ ምጣኔ ሀብትን ለማሳደግ ጉልህ ሚና አላቸው። በምሥራቅ አፍሪካ ከሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶች፣ መካከል፣ ደኖች፣ ውሃ፣ የዱር እንስሳቶች፣ ተራራዎች፣ ማዕድናትና የኃይል ምንጮች ዋና ዋናዎቹ ናቸው። በቀጠናው ባለው ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር መጨመርና የግብርና መስፋፋት ምክንያት የተፈጥሮ ሀብቶቹ ለሰው ሠራሽ አደጋዎች የተጋለጡ ናቸው። ለምሳሌ፡- አዲስ የእርሻ መሬት ፍላጎትን ለማሟላት የተፈጥሮ ዕፅዋቶች በከፍተኛ ፍጥነት ይጨፈጨፋሉ:: በመሆኑም የአፈር መሸርሸር በከፍተኛ ፍጥነት ይጨምራል፤ የዱር እንስሳት መጠለያና ምግብ አጥተው ዝርያቸው እንዲጠፋ ወይም እንዲሰደዱ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ የተፈጥሮ ሀብት ቀጣይነት እንዲኖራቸው የሚከተሉትን ተገቢ የሆኑ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ዘዴዎች ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል ዛፍ መትከል፣ በቤት ውስጥ ውሃን በአግባቡ መጠቀም፣ በወንዞች አካባቢ ዕፅዋትን መትከል፣ ከኢንዱስትሪ የሚለቀቁ ቆሻሻ ፍሳሾችን መቀነስና ወደ ውሃማ አካላት ከመለቀቃቸው በፊት ማጣራት፣ ስለ ተፈጥሮ ሀብት አያያዝ የወጡ ሕግና ደንቦችን መተግበር፣ ባዮጋዝን መጠቀም፣ 83 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ በተቆረጡ ዛፎች ምትክ ችግኝ መትከል እንዲሁም ባዶ ቦታዎችን ዕፅዋት መሸፈን፣ በቤት ውስጥ ያገለገሉ ከእንጨት የተሠሩ ዕቃዎችን በማደስ እንደገና መጠቀም፣ ሀገር-በቀል ዕፅዋትና እንስሳት እንዳይጠፉ ልዩ ልዩ እንክብካቤ ማድረግ፣ እንደ ፀሐይና ነፋስ ኃይል የመሳሰሉትን አማራጭ የኃይል ምንጮችን መጠቀም:: የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ዘዴዎች የተፈጥሮ ሀብት ለመንከባከብ የሚያስችሉ የተለያዩ ዘዴዎች አሉ፡፡ የሚከተሉትን ዘዴዎች በምሳሌነት መመልከት ይቻላል፡፡ ሀገር በቀል ዕፅዋቶችን መትከል እና መንከባከብ፡፡ እንደ ፀሐይ ብርሃን ያሉ ታዳሽ የኃይል ምንጮችን መጠቀም፡፡ የሚታደሱ የተፈጥሮ ሀበቶችን በመተካት መጠቀም፡፡ የተፈጥሮ ሀብትን ሳያባክኑ፣ ሳያጠፉ ወይም ሳያበላሹ በሥርዓት መጠቀም የተፈጥሮ ሀብትን ለመንከባከብ የምንጠቀምባቸው ዘዴዎች ናቸው፡፡ ተግባር 3.1 የቡድን ውይይት ዓላማ፡ የተፈጥሮ ሀብት የመንከባከብ ዘዴዎችን መለየት መመሪያ፡ ተማሪዎች በቡድን በመሆን በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ከተወያያችሁ በኋላ መልሱን ለመምህራችሁ አቅርቡ፡፡ 1. የተፈጥሮ ሀብቶች ለተተኪው ትውልድ እንዲተላለፉ ምን መደረግ እንዳለበት አብራሩ፡፡ 2. ለተፈጥሮ ሀብት መመናመን ዋና ዋና ምክንያቶችን ዘርዝሩ፡፡ 3. ዕፅዋትን መንከባከብ የሚያስገኘውን ጥቅም አብራሩ፡፡ 4. የምሥራቅ አፍሪካን ውጤታማ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ግለጹ፡፡ 84 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ መልመጃ 3.2 የሚከተሉትን ጥያቄዎች በማንበብ ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ሆሄ በመምረጥ መልሱ፡፡ 1. የማዕድን ጠቀሜታ ያልሆነው የቱ ነው? ሀ) የገቢ ምንጭ መሆን ለ) የውጭ ምንዛሬን ይጨምራል ሐ) የሥራ አጥ ቁጥርን ይቀንሳል መ) የሀገር ገቢን ይቀንሳል 2. የምሥራቅ አፍሪካ የማዕድናት አጠቃቀም ተግዳሮት ያልሆነው የቱ ነው? ሀ) በቂ የመሠረተ- ልማት አለመኖር ለ) በማዕድን ማውጣት የሰለጠነ ሰው መብዛት ሐ) የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪ አቅም ማነስ መ) የቴክኖሎጂ እጥረት 3. ከሚከተሉት ውስጥ የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ዘዴ የቱ ነው? ሀ) ታዳሽ የሀይል ምንጮችን መጠቀም ለ) ሀገር በቀል ዕፅዋትን መትከል ሐ) የተፈጥሮ ሀብትን በአግባቡ መጠቀም መ) ሁሉም 4. ከሚከተሉት ውሰጥ የተፈጥሮ ሀብት ያልሆነው የቱ ነው? ሀ) ዕፅዋት ለ) አየር ሐ) አፈር መ) ድልድይ 5. በተፈጥሮ የሚገኝ ብረታ ብረትና ኢ-ብረታብረት ምን ይባላል? ሀ) ማዕድን ለ) አፈር ሐ) ውሃ መ) አየር 85 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ 3.3 የምሥራቅ አፍሪካ ዋና ዋና የአፈር ዓይነቶች ቁልፍ ቃላት አፈር እርከን ዳግም ድነና ድነና የማነቃቂያ ጥያቄዎች 1. አፈር ምንድን ነው? 2. አፈር እንዴት ይፈጠራል? 3. በአካባቢያችሁ ያሉ የአፈር ዓይነቶችን ዘርዝሩ፡፡ አፈር ከአለቶች ስብርባሪ፣ ከዕፅዋት እና ከእንስሳት ብስባሽ የሚፈጠር የላይኛው የመሬት አካል ነው፡፡ አፈር ለዕፅዋት እድገት ወሳኝ የሆኑ ውሃ፣ አየርና ማዕድናትን በውስጡ ይይዛል፡፡ አብዛኛው የአፍሪካ ህዝብ በግብርና እንቅስቃሴ የሚተዳደር በመሆኑ አፈር ለምሥራቅ አፍሪካ ዋነኛ የተፈጥሮ ሀብት ነው፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ የሚከተሉት ዋና ዋና የአፈር ዓይነቶች ይገኛሉ፡፡ ሰንጠዥ 3.2 የምሥራቅ አፍሪካ ዋና ዋና የአፈር ዓይነቶችና የሚገኙበት ሀገራት የአፈር ዓይነቶች የሚገኙበት ሀገር አንዶሶል እና ኒቶሶል ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ታንዛንያ ካምቢሶል እና ላቪሶል ኢትዮጵያ ፈራሶል እና አክሪሶል ዛምቢያ፣ ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ እና ማዳጋስካር ቨርቲሶል ኢትዮጵያ ዜሮሶል፣ ሊቶሶል፣ የርሞሶል እና ሶማሊያ እና ኤርትራ ሶላንቻክ 86 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ ምስል3.4 የምሥራቅ አፍሪካ ዋና ዋና የአፈር ዓይነቶች የአፈር መሸርሸር የመሬት የላይኛው ክፍል በውሃ ወይም በነፋስ ተጠርጎ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መወሰድ የአፈር መሸርሸር ይባላል፡፡ የአፈር መሸርሸር በሚከተሉት ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፡፡ የአፈር ዓይነት፣ የመሬት አቀማመጥ (ተራራ፣ ቁልቁለት እና ኮረብታ) ያለው አካባቢ ሲኖር፣ የዕፅዋት ሽፋን መመናመን በጎርፍ የመጠረግ አጋጣሚ ያስከትላል፣ በተዳፋት ቦታ ቁልቁል ማረስ፣ በግጦሽ መሬት ከብቶች ለረዥም ጊዜ ማሰማራት፣ ተራራማ ቦታን ለእርሻ ሥራ ማዋል፣አንድን ቦታ ለረጅም ጊዜ በተከታታይ ማረስ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ 87 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ የበድን ውይይት 3.3ሀ ዓላማ፡ የአፈር መሸርሸር ምክንያቶችንና መፍትሔዎችን መለየት መመሪያ፡ ተማሪዎች በቡድን በመሆን በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ከተወያያችሁ በኋላ መልሱን ለመምህራችሁ አቅርቡ፡፡ 1. የምሥራቅ አፍሪካ የአፈር ዓይነቶችን ዘርዝሩ፡፡ 2. የአፈር መሸርሸር የት አካባቢ ይከሰታል? 3. የአፈር እንክብካቤ ማድረግ ያለበት ማን ነው? 4. የአፈር መሸርሸር ለግብርና ሥራ ትልቅ ችግር የሆነው ለምንድን ነው? 5. የምሥራቅ አፍሪካ የአፈር መሸርሸር መፍትሔዎች አብራሩ፡፡ የአፈር ሀብት አጠባበቅ ዘዴ በአካባቢያችሁ የሚደረጉ የአፈር አጠባበቅ ዘዴዎች ምን ምን ናቸው? በአካባቢያችሁ ችግኞች ለምን ይተከላሉ? አፈር በጥንቃቄ ካልተያዘ ወደ ጠፍነት ይቀየራል ወይም ለምነቱን ያጣል፡፡ የአፈር ለምነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ በሄደ ቁጥር ምርታማነት ይቀንሳል፡፡ ስለዚህ የአፈርን ለምነት ለመጠበቅ በጥንቃቄ ማረስ፣ በየጊዜው በተፈጥሮ ዘዴ ለምነቱ እንዲጠበቅ ማድረግና በተወሰነ ጊዜ ፋታ (እረፍት) እንዲያገኝ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ የአፈርን እርጥበትና ለምነት ለመጠበቅ የሚከተሉት አስፈላጊ ዘዴዎች ናቸው፡፡ ሀ. ዳግም ድነና (Reforestation) በአንድ ወቅት በደን ተሸፍነው የነበሩ አካባቢዎች አግባብ በሌለው የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ምክንያት ደን አልባ ይሆናሉ፡፡ እነዚህን የጠፉ ዛፎች የመተካት ዘዴ ዳግም ድነና ይባላል፡፡ ስለዚህ ዛፎችን በመትከል ደኖቹ እንዲመለሱ ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ለ. ድነና (Afforestation) ደን ባልነበረበት ዛፎችን ማብቀል እንዲሁም ዕጽዋት ባልነበረበት ሥፍራ ችግኞችን የመትከል ተግባር ድነና ይባላል፡፡ ድነና የእፅዋት ሽፋን ባልነበረበት አካበቢ ሊካሄድ ይችላል፡፡ 88 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ ሐ. ጣምራ የደን እርሻ (Agroforestry) ከእርሻ ተግባራት ወይም ከእንስሳት እርባታ ጋር ተቀናጅቶ ዛፎች የሚተከሉበት የግብርና ዘርፍ ጣምራ የደን እርሻ ይባላል፡፡ ጣምራ የደን እርሻ በአንድ አካባቢ ለረጅም ጊዜ የሚካሄድ ወይም ለአጭር ወቅት ሊከናወን ይችላል፡፡ አርሶ አደሮች ለእርሻና ለከብት እርባታ ተግባራቸው ጋር ጎን ለጎን በእርሻ ማሳዎቻቸው ላይ ዛፍ ይተክላሉ፡፡ በማሳ አካባቢ ዛፎችን መትከል የተፈጥሮ አካባቢን ለመጠበቅና ምጣኔ ሀብትን (ገቢን) ለማሳድግ ይረዳል፡፡ መ. የእርከን ሥራ (Terracing) እርከን ማለት መደብ መሰል ሁኖ በከፍተኛ ሥፍራ ላይ የሚሠራና በዝናብ ወቅት አፈር በጎርፍ እንዳይጠረግ የሚረዳ የመከላከያ ዘዴ ነው፡፡ ሠ. በከፍተኛ ሥፍራ አግድም ማረስ (Contour ploughing) አግድም ማረስ የሚተገብረው በከፍተኛ ሥፍራዎች ዳገታማ መሬት ላይ ነው፡፡ ይህ የእርሻ ተግባር ሲካሄድ የሚፈጠሩት መስመሮች ከላይ በዝናብ ወቅት ቁልቁል የሚወርደውን ጎርፍ ፍጥነት ይቀንሳሉ፡፡ ረ. ዘር ማፈራረቅ (Croprotation) ዘር ማፈራረቅ ማለት በአንድ ማሳ ላይ የተለያዩ ዘሮችን የመዝራትና የማብቀል ዘዴ ነው፡፡ የዘር ማፈራርቅ ጥቅሞች መካከል፣ አረምን ለመቆጣጠር፣ የአፈርን ለምነትን ለመጠበቅ፣ በሽታዎችን ለመከላከል፣ የአፈርን መሸርሸር ለማስወገድ፣ ሰው ሠራሽ ማዳበሪያ ፍጆታን ለመቀነስ፣ የሰብል አጥፊ ነፍሳትን (ተህዋስያን) መራባትን ለመቆጣጠር ይጠቅማል፡፡ ሰ. የተፈጥሮ ማዳበሪያ መጠቀም የግብርና ምርትን ለማሻሻል ከምንጠቀምባቸው ግብአቶች መካከል ማዳበሪ አንዱ ነው:: የማዳበሪያ ዓይነቶች ተፈጥሯዊና ሰው ሠራሽ ተብለው ይከፈላሉ፡፡ ሀ. የተፈጥሮ ማዳበሪያ የሚሠራው በተፈጥሮ ከሚገኙ ተረፈ ምርቶች ነው፡፡ ለምሳሌ ከፍግ፣ ከእንስሳትና ዕፅዋት ግብአት ብስባሽ በቀላሉ ይዘጋጃል፡፡ ለ. የአፈርን ምርታማነት ለመጨመር የተለያዩ ኬሚካሎችን በፋብሪካ በማቀነባበር ለእርሻ ሥራ በግብአትነት የሚውል ውሕድ ሰው ሠራሽ ማዳበሪያ ይባላል፡፡ ሰው ሠራሽ ማዳበሪያዎችን ያለአግባብ (ሁልጊዜ) መጠቀም የአካባቢውን ተፈጥሮአዊ ሁኔታ ያዛባል፡፡ ምክንያቱም አፈሩ ለምነቱን ስለሚያጣና ምርት መስጠቱን ስለሚያቆም ነው፡፡ 89 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ የቡድን ውይይት 3.3 ለ ዓላማ፡- የአፈር ሀብት እንክብካቤ ዘዴዎችን መለየት መመሪያ፡- ተማሪዎች በቡድን በመሆን በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ከተወያያችሁ በኋላ መልሱን ለመምህራችሁ አቅርቡ፡፡ 1. የተፈጥሮ ማዳበሪያ ማለት ምን ማለት ነው? ከምንስ ይሠራል? 2. የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ማዳበሪያ ልዩነትን አብራሩ፡፡ ለአፈር ለምነት የተሻለ ጠቀሜታ ያለው የቱ ነው? 3. እርከን መሰራት ያለበት ምን ዓይነት የመሬት አቀማመጥ ላለው ቦታ ነው? መልመጃ 3.3 ሀ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል ካልሆኑ ደግሞ ሐሰት በማለት መልሱ፡፡ 1. አፈር ማለት ከአለቶች የተሠራ የውስጠኛው የመሬት ክፍል ነው፡፡ 2. የአፈር ዓይነት ለአፈር መሸርሸር ያጋልጣል፡፡ 3. ዕፅዋት በመትከል የአፈር ለምነትን መንከባከብ ይቻላል፡፡ 4. የተፈጥሮ እና ሰው ሠራሽ ማዳበሪያዎች ልዩነት የላቸውም፡፡ 5. አፈር በጥንቃቄ ካልተያዘ ወደ ለምነቱን ይቀንሳል፡፡ ለ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች በማንበብ ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ሆሄ በመምረጥ መልሱ፡፡ 1. ከሚከተሉት ለአፈር ሀብት እንክብካቤ ጠቀሜታ የሌለው የቱ ነው? ሀ. እርከን መስራት ሐ. ዕፅዋትን መቁረጥ ለ. ዕፅዋትን መትከል መ. አግድም ማረስ 2. ደን ባልነበረበት ቦታ ዕፅዋትን መትከል ምን ይባላል? ሀ. ድነና ሐ. የጣምራ ደን ለ. ዳግም ድነና መ. ዘር ማፈራረቅ 90 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ 3. ከሚከተሉት ውስጥ ለአፈር መሸርሸር ምክንያት የሆነው የቱ ነው? ሀ. አግድም ማረስ ሐ. ቁልቁል ማረስ ለ. የጣምራ ደን እርሻ መ. የዕፅዋትን ሽፋን መጨመር 4. ከሚከተሉት ውስጥ ለአፈር መሸርሸር ምክንያት ያልሆነው የቱ ነው? ሀ. ተራራማ ቦታዎችን ከእንስሳት ንክኪ ነጻ ማድረግ ለ. ለእርሻ ተስማሚ ያልሆኑ ቦታዎችን በዕፅዋት መሸፈን ሐ. ዳግም ድነና መ. ሁሉም 3.4 የምሥራቅ አፍሪካ የውሃ ሀብት የንዑስ ርዕሱ አጥጋቢ የመማር ብቃት  ተማሪዎች ይህን ንዑስ ርዕስ ትምህርት ተምራችሁ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፡-  የምሥራቅ አፍሪካን የተለያዩ የውሃ ሀብት (ወንዞችና ሐይቆች) በመግለጽ ታወዳድራላችሁ፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙ የውሃ ሀብትን አጠቃቀም ተግዳሮት ታብራራላችሁ:: ቁልፍ ቃላት ሐይቅ ውቅያኖስ ወንዝ የዱር እንስሳት እፅዋት የማነቃቂያ ጥያቄዎች 1. በአብዛኛው የመሬት ክፍል በምን የተሸፈነ ነው? 2. ውሃማ አካላት የሚባሉት እነ ማን ናቸው? 91 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ ከአጠቃላይ የመሬት ክፍል ሰባ በመቶ የሚሆነው የመሬት ገጽ በውሃ የተሸፈነ ነው:: ውሃ በውቅያኖስ፣ በባሕር፣ በሐይቆች፣ በወንዞችና በከርሰ ምድር ላይ ይገኛል፡፡ ውሃ ለመጠጥ፣ ምግብ ለማዘጋጀት፣ ለንፅህና፣ ለዕፅዋት እድገት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨትና ለመጓጓዣ ያገለግላል፡፡ መሬትን ሸፍኖ ከሚገኘው ውሃ ዘጠና ሰባት በመቶ በውቅያኖስና በባሕር ውስጥ ይገኛል፡፡ የውቅያኖስ ውሃ በውስጡ ከፍተኛ የጨው መጠን ስላለው ለመጠጥነት አያገለግልም፡፡ መሬትን ከሸፈነው ውሃ ሁለት በመቶ በበረዶ መልክ በሰሜንና ደቡብ ዋልታዎች አከባቢ ተጠራቅሞ ይገኛል፡፡ አንድ በመቶ የሚሆን ንጹህ ውሃ ደግሞ በሐይቆች፣ ወንዞችና ከርሰ ምድር ውስጥ ይገኛል፡፡ ውጤታማ የውሃ ሀብት አጠቃቀም የማነቃቂያ ጥያቄ ውጤታማ የውሃ ሀብት አጠቃቀም ምንድን ነው? በዝናብ የሚገኝ ውሃን በማሰባሰብ እና በማቆር የሚተገበር የተቀናጀ የውሃ ሀብት አጠቃቀም አስፈላጊ ነው፡፡ ውጤታማ የውሃ ሀብት አጠቃቀም የአፈር እርጥበትን ለማሻሻል፣ ለእርሻ እና ለከብት ሀብት ልማት የሚውለው የውሃ መጠን ሳይቀንስና ሳይቋረጥ ለማቅረብ ያስችላል፡፡ በተጨማሪም ምርታማነትን ለማሻሻል፣ አነስተኛ መስኖዎችን ለማጎልበትና የጉድጓድ ውሃን በተገቢው መንገድ ለመጠቀም ያገለግላል:: ስለዚህም ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ለውሃ ሀብት መጠበቅ ከፍተኛ ጠቀሜታ ባላቸው ነገሮች ለምሳሌ ዕፅዋት መትከልና መንከባከብ እንቅስቃሴዎች ላይ መሳተፍ እንዲሁም የተለያዩ የውሃ ሀብቶችን እንዳይባክኑ በአግባቡ መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ የውሃ ሀብት ጠቀሜታ የማነቃቂያ ጥያቄዎች 1. ውሃማ አካላት የሚሰጡትን ጥቅም ተናገሩ፡፡ 2. የዓሣ ሀብትን የሚቀንሱ ዋና ዋና ምክንያቶችን ዘርዝሩ፡፡ ውሃማ አካላት ከመስኖና መጠጥ አገልግሎት በተጨማሪ ለተለያየ ጥቅም ይውላሉ:: ለምሳሌ የሚከተሉትን አገልግሎቶች መመልከት ይቻላል፡፡ ለመጓጓዣ፡- ውቅያኖስ መርከቦች ከባድ ዕቃዎችን ጭነው የሚሄዱበት ግዙፍ ውሃማ አካል ነው፡፡ በወንዞችና በሐይቆች ላይ ጀልባዎች የመጓጓዣ አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡ 92 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ፡- ውሃማ አካላት የመብራት ኃይል ለማመንጨት ያገለግላሉ፡፡ ከከፍተኛ ቦታዎች በፍጥነት ወደ ታች የሚፈሱ ወንዞች የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ምቹ ሁኔታ አላቸው፡፡ ለዓሣ እርባታ፡- ዓሣ ለሰው በምግብ ምንጭነት ያገለግላል፡፡ ስለዚህም ውሃማ አካላት ለዓሣ እርባታ ይጠቅማሉ፡፡ ከዓሣ በፕሮቲን የበለፀገ ምግብ ስለሚገኝ በሰው ሠራሽ ሀይቅ ወይም የተፈጥሮ ውሃማ አካላትን በመጠቀም ማራባት ይቻለል፡፡ ለቱሪዝምና መዝነኛ አገልግሎት፡- ብዙ የምሥራቅ አፍሪካ ወንዞች እና ሐይቆች ጥሩ መዝናኛዎችና የቱሪስት መዳረሻዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ የቪክቶሪያ ፏፏቴ በዛምቤዚ ወንዝ፣ የኬንያ ናኩሩ ሐይቅ፣ የጭስ ዓባይ ፏፏቴ እና የአዋሽ ወንዝ ፏፏቴ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ የውሃ ሀብት አጠቃቀም ተግዳሮት በምሥራቅ አፍሪካ በሚገኙ የውሃ ሀብት ላይ በርካታ ተግዳሮት ይስተዋላል፡፡ ለምሳሌ፡ ከፋብሪካዎች እና ከኢንዱስትሪዎች በሚወጡ ፈሳሾች መበከል፣ ድርቅ እና የአየር ንብረት መለዋወጥ፣ በጋራ የውሃ ተፋሰስ ሀገራት ፍትሐዊ የውሃ ሀብት አጠቃቀም ችግር መኖር፣ በውሃማ አካላት ላይ የሚጨመሩ የፕላስቲክ እና የተበከሉ ኬሚካሎች መብዛትና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ የሐይቅ ዓይነቶች የማነቃቂያ ጥያቄዎች 1. የምሥራቅ አፍሪካ ሐይቆች በስንት ይከፈላሉ? 2. የምሥራቅ አፍሪካ ሐይቆችን ዘርዝሩ፡፡ ሐይቆች በአፈጣጠራቸው ተፈጥሮአዊና ሰው ሠራሽ ተብለው በሁለት ይከፈላሉ፡፡ የተፈጥሮ ሐይቆች በመሬት ተፈጥሯዊ አቀማመጥ፣ በእሳተ ገሞራ እና በሽርሸራ በተስተካከለ መሬት ላይ ይፈጠራሉ፡፡ የተፈጥሮ ሐይቆች በመገኛቸው በሁለት ይከፈላሉ:: እነዚህም የስምጥ ሸለቆ ሐይቆች እና ከስምጥ ሸለቆ ውጭ ያሉ ሐይቆች በመባል ይታወቃሉ፡፡ 93 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ የስምጥ ሸለቆ ሐይቆች፡- እነዚህ ሐይቆች በታላቁ የምሥራቅ አፍሪካ የስምጥ ሸለቆ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ እነዚህም ቱርካና፣ ታንጋኒካ፣ ኪቩ፣ አልበርት፣ ማላዊ፣ ኢድዋርድ እና የኢትዮጵያ የስምጥ ሸለቆ ሐይቆችን ያጠቃልላል፡፡ ታንጋኒካ በጥልቀቱ የአፍሪካ ትልቁ ሐይቅ ሲሆን በዓለም ደግሞ ሁለተኛ ነው፡፡ ከስምጥ ሸለቆ ውጭ ያሉ ሐይቆች፡- በምሥራቅ አፍሪካ ከስምጥ ሸለቆ ውጭ ያሉ ሐይቆች ከሚባሉት ዋና ዋናዎቹ ቪክቶሪያና ጣና ይገኙበታል፡፡ ቪክቶሪያ በሥፋቱ የአፍሪካ ትልቁ ሐይቅ ነው፡፡ ሰንጠረዥ 3.3 የምሥራቅ አፍሪካ የተፈጥሮ ሐይቆች ሐይቅ ስፋት (በካሬ ኪ.ሜ) ጥልቀት (በሜትር) ዓይነት ቪክቶሪያ 83,000 92 ከስምጥ ሸለቆ ውጭ ታንጋኒካ 32,890 1435 የስምጥ ሸለቆ ሐይቅ ማላዊ 30,800 706 የስምጥ ሸለቆ ሐይቅ ቱርካና 8,660 72 የስምጥ ሸለቆ ሐይቅ አልበርት 5,500 17 የስምጥ ሸለቆ ሐይቅ ሜሩ 4,920 27 የስምጥ ሸለቆ ሐይቅ ጣና 3,600 9 ከስምጥ ሸለቆ ውጭ ኢድዋርድ 3,550 112 የስምጥ ሸለቆ ሐይቅ ኪቩ 2,650 475 የስምጥ ሸለቆ ሐይቅ ሰው ሠራሽ ሐይቆች ሰው ሠራሽ ሐይቆች የሚባሉት ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ወይም ለሌሎች ጥቅሞች ከወንዞች የተገደቡ ሐይቆችን ያጠቃልላል፡፡ ሰንጠረዥ 3.4 በምሥራቅ አፍሪካ ከሚገኙ ሰው ሠራሽ ሐይቆች ሐይቅ ስፋት (በካሬ ኪ.ሜ) ዓይነት ቆቃ 250 ሰው ሠራሽ ሐይቅ ካሪባ 5400 ሰው ሠራሽ ሐይቅ ካቦራባሳ 2739 ሰው ሠራሽ ሐይቅ ተከዜ - ሰው ሠራሽ ሐይቅ 94 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ ምስል 3.4 የምሥራቅ አፍሪካ ሐይቆችን የሚያሳይ ካርታ የምሥራቅ አፍሪካ ሐይቆች ምጣኔ ሀብታዊ ጠቀሜታ የሐይቆችን ጠቀሜታ ዘርዝሩ፡፡ መጓጓዣ፡- የሕንድ ውቅያኖስ ለሚያዋስናቸው የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ትልቅ የመጓጓዣ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ እንደ ታንዛንያ፣ ኬንያና ሶማሊያ በሕንድ ውቅያኖስ ላይ ወደብ አላቸው፡፡ እነዚህን ወደቦች በመጠቀም ከውጭ አገሮች ጋር የንግድ ልውውጥ ያካሂዳሉ፡፡ የኬንያ ሞምባሳ ወደብ ከኬንያ አልፎ ለኡጋንዳ፣ ቡሩንዲና ሩዋንዳ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ኬንያ ከዚህ ወደብ ከፍተኛ ጥቅም ታገኛለች፡፡ ከቀይ ባሕርና ከኤደን ባህረ ሰላጤ ጋር የሚዋሰኑ ሀገሮችም በተመሳሳይ ሁኔታ የየራሳቸውን ወደብ በመጠቀም ላይ ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ የኤርትራና ጂቡቲ ወደቦች ከፍተኛ ምጣኔ ሀብታዊ ጠቀሜታ አላቸው፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ ትላልቅ ሐይቆች እንደ ቪክቶሪያ፣ ታንጋኒካ፣ ማላዊና አልበርት ላይ ትልልቅ ጀልባዎች የመጓጓዣ አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡ በኢትዮጵያ ትንንሽ ጀልባዎች በጣና፣ ዝዋይ እና አባያ ሐይቆች ላይ የመጓጓዣ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ ለዓሣ እርባታ፡- የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ዓሣ ለማርባት ከፍተኛ ዕድል አላቸው:: በምሥራቅ አፍሪካ አካባቢ የውሃማ አካላት ውስጥ የተለያዩ የዓሣ ዝርያዎች ይገኛሉ:: ዓሣ ለሰው ልጅ ከሚያስፈልጉ የተመጣጠኑ ምግቦች አንዱ ነው፡፡ የባሕርና ውቅያኖስ ዳርቻ ሕዝቦች ምግባቸው በአብዛኛው በዓሣ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ዓሣ ለምግብነት ብቻ ሳይሆን የገቢ ምንጭ በመሆን ያገለግላል፡፡ ዓሣን በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ሐይቆች ውስጥ ማርባት ይቻላል፡፡ 95 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ የምሥራቅ አፍሪካ ሐይቆች ባህላዊ ጠቀሜታ ተግባር 3.2 ሐይቆች በአካባቢው ላሉ ማኅበረሰቦች የሚሰጡትን ባህላዊ ጠቀሜታ የሚገልጽ አጭር ጽሑፍ አዘጋጅታችሁ አቅርቡ፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ ወንዞች በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙ ወንዞችን ዘርዝሩ፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ አካባቢ ወደ ተለያየ አቅጣጫ የሚፈሱ ወንዞች አሉት፡፡ እነሱም ይየሚከተሉት ናቸው። ናይል ወንዝ፡- ነጭ ዓባይ ከቪክቶሪያ ሐይቅ እንዲሁም ጥቁር ዓባይ (Blue Nile) ደግሞ ከኢትዮጵያ በመነሳት በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ተቀላቅለው ናይል የሚባል ወንዝ ይፈጥራሉ፡፡ ከዚያም የናይል ወንዝ ወደ ግብፅ በመፍሰስ በመጨረሻ ሜዲትራኒያን ባሕር ይገባል፡፡ ይህ ወንዝ 6650 ኪ.ሜ ርቀት ይጓዛል፡፡ ናይል በርዝመቱ የዓለማችን ትልቁ ወንዝ ነው፡፡ የአዋሽ ወንዝ፡- የአዋሽ ወንዝ በኢትዮጵያ ከሚገኙና በከፍተኛ ጥቅም ላይ ከዋሉ ወንዞች አንዱ ነው፡፡ ይህ ወንዝ ከምዕራብ ሸዋ ደንዲ ወረዳ በመነሣት የደቡብ ምዕራብና ምሥራቅ ሸዋ ዞኖችን አቋርጦ አፋር ክልል አቤ ሐይቅ ይገባል፡፡ የአዋሽ ወንዝ 1200 ኪ.ሜ ርቀት በመጓዝ ከአገር ውስጥ ሳይወጣ በአቤ ሐይቅ ውስጥ ይቀራል፡፡ የዋቢ ሽበሌ ወንዝ፡- ከምዕራብ አርሲ ተራሮች በመነሣት ወደ ደቡብ ምሥራቅ አቅጣጫ ይፈሳል፡፡ ሶማሊያ ከደረሰ በኋላ ሕንድ ውቅያኖስ ሳይደርስ ሶማሌ አሸዋ ውስጥ ሰምጦ ይቀራል፡፡ የዋቢ ሸበሌ ወንዝ ርዝመት ወደ 2000 ኪ.ሜ ይገመታል፡፡ የገናሌ ወንዝ፡- ከደቡብ - ምሥራቅ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታዎች ይነሣል፡፡ በደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ቆላማ አካባቢዎችን በማቋረጥ በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ ድንበር የተወሰነ ርቀት ከተጓዘ በኋላ ሶማሊያን አቋርጦ ወደ ሕንድ ውቅያኖስ ይገባል፡፡ ይህ ወንዝ 1660 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ሲሆን ከኢትዮጵያ ከወጣ በኋላ ጁባ በመባል ይታወቃል፡፡ የዛምቤዚ ወንዝ፡- ከሰሜን ምዕራብ ዛምቢያ ተነሥቶ 2750 ኪ.ሜ ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ በመጓዝ ሕንድ ውቅያኖስ ይገባል፡፡ በውስጡ የአፍሪካ ትልቁ ፏፏቴ ቪክቶርያ ፏፏቴ እና ሁለት ሰው ሠራሽ ግድቦች ካሪባን (ዛምቢያና ዚምባቡየ) እና ካቦራባሳ (ሞዛምቢክ) ይገኙበታል፡፡ 96 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ ታና ወንዝ፡- ይህ ወንዝ የኬንያ ትልቁና በጣም ጠቃሚ ወንዝ ሲሆን ከደቡብ ምዕራብ ኬንያ በመነሣት 708 ኪ.ሜ በመጓዝ ወደ ህንድ ውቅያኖስ ይገባል፡፡ የሩፉጂ ወንዝ፡-በታንዛንያ ውስጥ ይገኛል፡፡ ይህ ወንዝ ከደቡብ ታንዚንያ ከፍታኛ ቦታ ተነሥቶ ወደ ሕንድ ውቅያኖስ ይፈሳል፡፡ የዚህ ወንዝ ርዝመት 600 ኪ.ሜ ይሆናል፡፡ ሩቩማ ወንዝ፡- የታንዛንያና ሞዚምቢክ ድንበር በመሆን ያገለግላል፡፡ በታንዛንያና በሞዚምቢክ ለሚፈሱ ገባር ወንዞች የውሃውን መጠን ያሳድጋል፡፡ ይህ ወንዝ 800 ኪ.ሜ.ርቀት ከተጓዘ በኋላ ወደ ሕንድ ውቅያኖስ ይገባል፡፡ ሰንጠረዥ 3.5 ዋናዋና የምሥራቅ አፍሪካ ወንዞች ተ.ቁ የወንዝ ስም መገኛ መድረሻ ርዝመት በኪ.ሜ 1 ናይል ኢትዮጵያ ሜዲትራንያን ባሕር 6650 2 አዋሽ ኢትዮጵያ አቤ ሐይቅ 1200 3 ዋቢሸበሌ ኢትዮጵያ ሶማሊያ አሸዋ 2000 4 የገናሌ ኢትዮጵያ ሕንድ ውቅያኖስ 1660 5 ዛምቤዚ ዛምቢያና ዚምባቡዌ ሕንድ ውቅያኖስ 2750 6 ታና ኬንያ ሕንድ ውቅያኖስ 708 7 ሩፉጂ በታንዛንያ ሕንድ ውቅያኖስ 600 8 ሩቩማ በታንዛንያና ሞዚምቢክ ሕንድ ውቅያኖስ 800 97 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ ምስል 3.6 የምሥራቅ አፍሪካ ወንዞች የቡድን ውይይት 3.4ሀ ዓላማ፡- የምሥራቅ አፍሪካ ወንዞችን መለየት መመሪያ፡- በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ከተወያያችሁ በኋላ መልሱን ለመምህራችሁ አቅርቡ፡፡ 1. የምሥራቅ አፍሪካ ወንዞችን በርዝመታቸው በቅደም ተከተል በማሥቀመጥ አሣዩ፡፡ 2. የናይል ወንዝ የሚያቋርጣቸውን የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ዘርዝሩ 3. ወደ ሕንድ ውቅያኖስ የሚገቡ የምሥራቅ አፍሪካ ወንዞችን ዘርዝሩ 98 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ የምሥራቅ አፍሪካ ወንዞች ጠቀሜታ ወንዞች ለምን ለምን ያገለግላሉ? በምሥራቅ አፍሪካ በርካታ ወንዞች ይገኛሉ። እነዚህ ወንዞች ለአከባቢው ማኅበረሰብ ከፍተኛ ግልጋሎት ይሰጣሉ። ከምሥራቅ አፍሪካ ወንዞች ጠቀሜታ መካከል ዋና ዋናዎቹ፡- 1. ለመስኖ እርሻ ወንዝ የዝናብ እጥረት ባለበት አካባቢ ለመስኖ እርሻ ትልቅ ሚና አለው። ይህም ሀገሮች ራሳቸውን ከምግብ ዕጥረት እንዲከላከሉ ያግዛቸዋል። ለምሳሌ የታችኛው የአዋሽ ወንዝ ሸለቆ በኢትዮጵያ በአትክልትና ፍራፍሬ ምርት ይታወቃል፡፡ 2. ለመዝናኛና ለቱሪዝም የወንዝ ዳርቻዎች ማራኪ ተፈጥሮ ስላላቸው ለመዝናኛና ለቱሪዝም ምቹ ሁኔታን ይፈጥራሉ። ይህም ለምጣኔ ሀብት ዕድገት ጉልህ ፋይዳ አላቸው፡፡ 3. ለዓሣ እርባታ ወንዞች የተለያዩ የዓሣ ዝርያዎች መኖሪያ ናቸው። ይህም በቀጠናው የሥራ ዕድልን በመፍጠር የዕለት ገቢን ለማሳደግ ይጠቅማል። 4. ለንጹሕ መጠጥ ውሃ አቅርቦት በምሥራቅ አፍሪካ አብዛኛው የንጹሕ መጠጥ ውሃ ምንጭ ወንዝ ነው። ለምሳሌ የገፈርሳና የለገዳዲ ግድቦች በኢትዮጵያ ለዚህ ጥሩ ማሳያዎች ናቸው። 5) ለውሃ ኃይል የኤሌክትሪክ ጉልበት ማመንጫ ወንዞች ከከፍተኛ ሥፍራ ወደ ዝቅተኛ ሥፍራ ስለሚፈሱ የኤሌክትሪክ ጉልበት በማመንጨት ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣሉ። ለምሳሌ የዓባይ ወንዝ (በኢትዮጵያ)፣ ኦዌን ፏፏቴ (በዩጋንዳ) 6) ለመጓጓዣ በምሥራቅ አፍሪካ አንዳንድ ወንዞች ለመጓጓዣነት ያገለግላሉ። ለምሳሌ የባሮ ወንዝ (በኢትዮጵያ)፣ የታና ወንዝ (በኬንያ)፡፡ በአጠቃላይ በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙ ወንዞች በርካታ ምጣኔሀብታዊ ፋይዳቸው የጎላ ነው። 99 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ በምሥራቅ አፍሪካ የሐይቆች አጠቃቀም ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ሁኔታዎች የድርቅ መከሰት እና የሐይቆች መጥፋት(መድረቅ)፣ የደኖች መመንጠር እና የእርሻ ማሳ መስፋፋት፣ የሐይቆች በደለል መሞላት፣ የኢንዱስትሪዎችና ከተሞች መስፋፋትን ተከትሎ ወደ ሐይቆች የሚገቡ የተለያዩ በካይ ፈሳሾች እና ፕላስቲኮች መብዛት፣ የተለያዩ መጤ ዕፅዋት መከሰት ለምሳሌ የእምቦጭ አረም በጣና ሐይቅ የቡድን ውይይት 3.4ለ ዓላማ፡- የምሥራቅ አፍሪካን የውሃ ሀብት አጠቃቀም መለየት፡፡ መመሪያ፡- ተማሪዎች በቡድን በመሆን ስለ ምሥራቅ አፍሪካ የውሃ ሀብት ከተወያያችሁ በኋላ የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ ሰርታችሁ ለመምህራችሁ አቅርቡ፡፡ 1. የሐይቆችና ወንዞች ማኅበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ጠቀሜታን ዘርዝሩ፡፡ 2. በወንዞች አጠቃቀም ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ምክንያቶችን ዘርዝሩ፡፡ 3. በምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ያሉ ወንዞችና በሐይቆች አጠቃቀም ዙሪያ የሚያጋጥሙ ችግሮችን እንዴት መፍታት እንደሚቻል የሚገልጹ መረጃዎችን በማሰባሰብ ዘገባ አቅርቡ፡፡ መልመጃ 3.4 ሀ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል ካልሆኑ ደግሞ ሐሰት በማለት መልሱ፡፡ 1. ሁሉም የምሥራቅ አፍሪካ ሐይቆች በተፈጥሮ የተገኙ ናቸው፡፡ 2. የመሬት የውሃ ሀብት 97 በመቶ የሚሆነው የውቅያኖስ ውሃ ነው፡፡ 3. ቆቃ ከሰው ሠራሽ ሐይቆች ውስጥ ይመደባል፡፡ 100 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ ለ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ሆሄ ምረጡ፡፡ 1. ከሚከተሉት አማራጮች የወንዝ ጥቅም የሆነው የቱ ነው? ሀ. ለቱሪዝም ለ. ለዓሣ ምርት ሐ. ለመጓጓዣ መ. ሁሉም 2. ከሚከተተሉት ውስጥ ሰው ሠራሽ ሐይቅ የሆነው የቱ ነው? ሀ. ካሪባ ለ. ሜሩ ሐ. ቱርካና መ. ሁሉም 3. በርዝመቱ የአፍሪካ ትልቁ ወንዝ ማን ይባላል? ሀ. ናይል ለ. ዋቢ ሸበሌ ሐ. ዛምቤዚ መ. ሩቩማ 4. በኢትዮጵያ በሥፋት ጥቅም ላይ የዋለው ወንዝ የትኛው ነው? ሀ. ገናሌ ለ. ዋቢ ሸበሌ ሐ. ዛምቤዚ መ. አዋሽ በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙ የዱር እንስሳት ዓይነቶች የቡድን ውይይት 3.4ሐ 1. በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙ የዱር እንስሳት ዓይነቶችን ዘርዝሩ፡፡ 2. በምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት በዱር እንስሳት ሥርጭትና ብዝኀነት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ዋና ዋና ሁኔታዎች ግለጹ፡፡ የዱር እንስሳት ለማዳ ያልሆኑና በማንኛውም የተፈጥሮ አካባቢ የሚገኙ እንስሳት ናቸው፡፡ የዱር እንስሳት ስንል ከጥቃቅን እስከ ትላልቅ እንስሳት ያሉትን አጥቢዎች፣ የአእዋፍ ዝርያዎች፣ ዓሣዎች፣ ተሳቢዎችና የተለያዩ ነፍሳትን ያጠቃልላል፡፡ የዱር እንስሳት ከአካባቢያቸው ጋር እንዴት ተስማምተው እንደሚኖሩ ለማሳየት በሦስት የምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች ላይ የተደረገውን ጥናት መመልከት ተገቢ ነው፡፡ የደንከል በረሃ በኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የተለያዩ የተፈጥሮ አካባቢዎች አሏት፡፡ ከብዙ ጥቂቱን ለማንሳት ከፊል በረሃማ እና የበረሃ ሥነ- ምኅዳር መጥቀስ ይቻላል፡፡ የደንከል በረሃ በበረሃማ ሥነ-ምኅዳር ይገኛል:: ይህ አካባቢ በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ እና በጂቡቲ መካከል በሚገኝ ባለሦስት ማዕዘን ወሰን ላይ ይገኛል፡፡ በአፍሪካ ከሚገኙ ዝቅተኛ ሥፍራዎች አንዱ ሲሆን በኢትዮጵያ በአፋር ብሔራዊ ክልል ይገኛል፡፡ ይህ ቦታ የሚገኘው ከባሕር ጠለል በታች 120 ሜትር ላይ ነው፡፡ በዚህ አካባቢ ዓመታዊ የዝናብ መጠን በጣም አነስተኛ በመሆኑ የተነሣ ጥቂት 101 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ የዕፅዋት ሽፋን አለው፡፡ እነዚህ ዕፅዋት ቁጥቋጦዎችንና ጥቅጥቅ ብለው የበቀሉ የሣር ዝርያዎችን ያጠቃልላል፡፡ በደንከል በረሃ በተወሰኑ አካባቢዎች ላይ የዱር አህያ፣ ገመሬ ዝንጀሮና የመሳሰሉት ይገኛሉ፡፡ ምስል 3.7 የደንከል በረሃ የዱር እንስሳት የሣር ምድር በኬንያ (ማሳይ ማራ) ማሳይ ማራ በኬንያ በስተደቡብ በኩል ከታንዛኒያ ጋር በምትገናኝበት ወሰን ላይ የሚገኝ ሥፍራ ነው። ይህ ምኅዳር በአካባቢው ከቦታ ወደ ቦታ በሚዘዋወሩ የዱር እንስሳት ይታወቃል:: በየዓመቱ ዝናብ ከኅዳር እስከ ግንቦት ባለው ወቅት በሚጥለው ዝናብ አማካኝነት ለግጦሽ የሚሆን ሣር በበቂ ሁኔታ ይበቅላል፡፡ በዚህ የተነሳ በሴሬንጌቲ ፓርክ በርካታ የዱር እንስሳት ይገኛሉ፡፡ የዝናቡ ወቅት ሲያልፍ አካባቢውን የሸፈነው ሣር ወዲያውኑ ይደርቃል፡፡ ይህም በመሆኑ የዱር እንስሳት የሴሬንጌቲን ፓርክ ለቀው ማሳይ ማራ ፓርክ ይገባሉ:: እንስሳቱ ከቦታ ወደ ቦታ የሚዘዋወሩት የዝናቡን ወቅት በመከተልና ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚበቅለውን ሣር በመፈለግ ነው፡፡ እንቅስቃሴያቸው በግልጽ የሚታየው ከሚያዚያ እስከ ነሐሴ ባለው ወቅት ነው፡፡ በዚህ ሥፍራ የሚገኙ ሣር በል እንስሳት ለሥጋ በል እንስሳት ለምግብነት ያገለግላሉ፡፡ በማሳይ ማራ ፓርከ አንበሳ፣ አቦሸማኔ፣ የሜዳ አህያ፣ ነብር፣ ጅብ፣ ዝሆን፣ ጎሽና የመሳሰሉት የዱር እንስሳት ይገኛሉ፡፡ ምስል 3.8 በማሳይ ማራና በሴሬንጌቲ ፓርክ የሚገኙ አንስሳቶች የዱር እንስሳት 102 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ የተራራ ደን በዩጋንዳ በዩጋንዳ በሚገኝ የተራራ ደን ላይ ቁጥራቸው በመቀነሱ ለመጥፋት የተቃረቡ እንስሳት ይገኛሉ፡፡ በቫሩንጋ ሰንሰለታማ ተራራ ደን ላይ በዓለም የተመዘገቡ የተለያዩ የተፈጥሮ ዕፅዋት ይገኛሉ፡፡ በደን ውስጥ ቁጥራቸው በመቀነስ ላይ የሚገኙ ጎሬላዎች አሉ:: በቫሩንጋ ተራራ ደን ውስጥ ደግሞ ቺምፓዚዎች፣ ጉሬዛዎች፣ዝንጀሮዎች እና ግራጫ ጉንጮች ያላቸው ትላልቅ የአፍሪካ ዝንጀሮዎች ይገኛሉ፡፡ ምስል 3.9 በዩጋንዳ ተራራ ደን የሚገኙ አጥቢ እንስሳት የቡድን ውይይት 3.4መ በቡድን በመሆን በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ከተወያያችሁ በኋላ መልሶቻችሁን ለመምህራችሁ አቅርቡ፡፡ 1. በአንድ አካባቢ የሚገኙ ሥጋ በል እና ሣር በል እንስሳትን በተመለከተ አጭር ማብራሪያ ጻፉ፡፡ 2. ስለ ደንከል በረሃ የተረዳችሁትን ፅንሰ-ሀሳብ በጽሁፍ አብራሩ፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት በዱር እንስሳት ሥርጭትና ብዝኀነት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ዋና ዋና ሁኔታዎች የአየር ንብረት መለዋወጥ፣ የደን መጨፍጨፍ፣ ሕገ ወጥ አደን፣ የአፈር ለምነት መቀነስ፣ የግጦሽ ሣር ማጣት፣ የከተሞች መስፋፋት፣ ፈጣን የቱሪዝም ዕድገት፣ የሕዝብ ቁጥር መጨመር እና የመሳሰሉት በምሥራቅ አፍሪካ በእንስሳት እና በብዝሃ ሕይወት ሥርጭት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸው:: 103 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ የምሥራቅ አፍሪካ ዋና ዋና ዕፅዋት የማነቃቂያ ጥያቄዎች 1. በምሥራቅ አፍሪካ የሚበቅሉ የዕፅዋት ዓይነቶችን ዘርዝሩ፡፡ 2. በምሥራቅ አፍሪካ የዕጽዋት ሥርጭት እና የደን መጨፍጨፍን ለመከላከል መወሰድ የሚገባቸውን እርምጃዎች አብራሩ፡፡ የተፈጥሮ ዕፅዋት የተለያዩ የአፈር ዓይነቶች፣ ተስማሚ የአየር ንብረት እና ከፍታ ባሉበት አካባቢዎች ይገኛሉ፡፡ የዕጽዋቱ ዓይነት፣ በአየር ንብረቱና በከፍታው መለያየት ምክንያት ይለያያሉ፡፡ ስለዚህ በአንድ አካባቢ ጥቅጥቅ ያለ የዕፅዋት አበቃቀል እና ሥርጭት ሊኖር የሚችለው በአካባቢው ለም አፈር እና ከፍተኛ ዝናብ ነው፡፡ የአካባቢው መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ መካከለኛ ከፍታ ሲኖረው ነው:: የምሥራቅ አፍሪካ ዋና ዋና ዕፅዋት በ6 ምድብ ሊከፈሉ ይችላሉ እነርሱም፡- ምስል 3.10 የምሥራቅ አፍሪካ የደን ሽፋን 1. የቅጠለ ሰፋፊ ዛፎች ደን ቅጠላቸው ሰፋፊና ለምለም አረንጓዴ ቅጠሎች አሉት፡፡ እነዚህ ደኖች የሚበቅሉት ከፍተኛ የዝናብ መጠን በሚያገኙ አካባቢዎች ውስጥ ነው፡፡ ይህ ዓይነት ደን የሚበቅልበት ከፍታ ከ1500-1800 ሜትር ይሆናል፡፡ በዚህ አካባቢ የሚበቅሉ ዛፎች ረጃጅም ናቸው:: ለምሳሌ የዋንዛ፣ የጥቁር እንጨት፣ የወይራ፣ የቀረሮና የዶቅማ ዛፎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ 2. ቅጠላቸውን የሚያራግፉ ዛፎች ደን ይህ ደን በብዛት የሚገኘው በሞቃታማ አየር ክልል አካባቢ ነው፡፡ የዚህ አካባቢ ዛፎች ውሃ በትነት እንዳይወጣ በበጋ ወራት ቅጠላቸውን ያራግፋሉ፡፡ ለምሳሌ፡- ሾላ፣ ዋርካ፣ዋንዛን መመልከት ይቻላል፡፡ 104 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ 3. የዝግባ ዛፎች ደን በዚህ አካባቢ የሚበቅሉ ዛፎች በመካከለኛ ሙቀት የአየር ንብረት የሚገኙ ዕፅዋት የሚበቅሉበት አካባቢ ነው፡፡ በዚህ አካባቢ የሚገኝ ዋናው ዛፍ ዝግባ ነው፡፡ 4. የውርጭ አካባቢ ደን ዛፎች ይህ ደን የባሕር ጠለል ከፍታቸው ከ2000 ሜትር በላይ በሆኑ አካባቢዎች ይበቅላል፡፡ በዚህ ደን በብዛት የሚገኘው ዛፍ ጥድ ነው፡፡ 5. የሣር ምድር የሣር ምድር በጥንት ዘመን በመካከለኛ ደን ተሸፍነው በነበሩ አካባቢዎች ይገኛል፡፡ በሣር ምድር አጫጭር ዛፎችና ረጃጅም ሣሮች አልፎ አልፎ የሚታዩበት አካባቢ ነው:: የሣር ምድር ዕፅዋት በተራሮች አካባቢና ጫፍ ላይም ይገኛሉ፡፡ 6. የሞቃት በረሃ ዕፅዋት፡- የበረሃ ዕፅዋት የሚገኙት የበረሃ አየር ንብረትና በረሃ ነክ አካባቢዎች ውስጥ ነው:: በዚህ አካባቢ የሚበቅሉ ዕፅዋት በቂ የዝናብ መጠን አያገኙም፡፡ የበረሃ ዕፅዋት አጫጭር፣ እሾሃማ ዛፎችና ሣሮች ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- ቁልቋልና ግራርን መጥቀስ ይቻላል:: በተጨማሪም የምሥራቅ አፍሪካ ተራሮችና አምባ ምድሮች በብዛት በዚህ አካባቢ ስለሚገኙ ተመሳሳይ የዕፅዋት ዓይነቶች ይገኙበታል፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ የደን ጭፍጨፋ ሁኔታ ደኖች ለምን ይጨፈጭፋሉ? የደኖች መጨፍጨፍ የሚያስከትለውን ጉዳት ተናገሩ፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ የተከሰተው ፈጣን የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ተጨማሪ የእርሻ መሬት ፍላጎት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል፡፡ በዚህም የተነሣ ሰዎች ወደ ጥብቅ አካባቢዎች በመግባት ደኖችን ይመነጠራሉ፡፡ አብዛኛው የምሥራቅ አፍሪካ ሕዝብ ኑሮው በእርሻ እና በከብት እርባታ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ለከብት እርባታ በቂ የግጦሽ ሥፍራ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን ይህ ሁኔታ ባለመመቻቸቱ በአንድ ቦታ ከብቶች ለረጅም ጊዜ ለግጦሽ እንዲቆዩ ያደርጋል፡፡ 105 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ ምስል 3.11 የደን መጨፍጨፍ በኢትዮጵያና በሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች ለደን ሀብት መመናመን ምክንያት ከሆኑት ጥቂቶቹ እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡ 1.ፈጣን የሕዝብ ቁጥር መጨመር፡- በየጊዜው የሚታየውን የሕዝብ ቁጥር መጨመር ተከትሎ ለእርሻና ለእንስሳት እርባታ የመሬት ፍላጎት ይጨምራል፡፡ 2.ለቤት ግንባታና የማገዶ ፍላጎት መጨመር፡- የሕዝብ ቁጥር መጨመር ለቤት ግንባታ፣ የማገዶና የሌሎች ቁሳቁስ ፍላጎትን ያሳድጋል፡፡ 3.የከተሞች መስፋፋት፡- እንደሌሎች ታዳጊ አገሮች በምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ከከተሞች መስፋፋት ጋር ተያይዞ የማገዶ፣ የቤት ግንባታና ቁሳቁሶች ፍላጎት ይጨምራል፡፡ 4.የዘመናዊ እርሻ መስፋፋት፡- የእርሻ መሬትን ለማስፋፋትና ምርትን ለማሳደግ በአንዳንድ ቦታዎች ደኖች ተመንጥረዋል፡፡ 5.የደን መቃጠል፡- በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች የእርሻ ፍላጎትን ለማሟላትና ሰብል አጥፊ እንስሳትን ለመከላከል ደኖች ይቃጠላሉ፡፡ እነዚህ የእርሻ ምርት የሚያበላሹትን እንደ ዝንጀሮ፣ ከርከሮ፣ ጦጣ፣ አእዋፍ ለመከላከል እንዲሁም የእርሻ መሬት ለማስፋፋትም የተፈጥሮ ዕፅዋት ይቃጠላሉ፡፡ ሰዎች ቤት ለመሥራት፣ የቤት ቁሳቁስ ለመሥራት እንዲሁም ምግባቸውን ለማብሰል የደን ዛፎችን ይቆርጣሉ፡፡ ይህ አላግባብ ደኖችን መጨፍጨፍ የአካባቢውን ሥነምኅዳር ይጎዳል፡፡ የአንድ ሀገር ፈጣን የሕዝብ መጨመር በደን ሀብት፣ በሌሎች የተፈጥሮ ዕፅዋትና እንስሳት ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ይፈጥራል፡፡ 106 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ መልመጃ 3.5 ሀ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል ካልሆኑ ደግሞ ሐሰት በማለት መልሱ፡፡ 1. የደኖች መጨፍጨፍ ምንም አይነት ጉዳት አያስከትልም፡፡ 2. ማዕድናት የሚገኙት በተፈጥሮ ነው፡፡ 3. የጥድ ዛፍ በብዛት የሚገኘው በውርጭ የአየር ንብረት ባላቸው የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ነው፡፡ ለ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች በማንበብ ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ሆሄ በመምረጥ መልሱ፡፡ 1. ከሚከተሉት ውስጥ የተፈጥሮ ሀብት ያልሆነው የቱ ነው? ሀ.ማዕድን ለ. አፈር ሐ. ውሃ መ. መኪና 2. ተገቢ ያልሆነ የማዕድናት አጠቃቀም የሚያስከትለው ተጽዕኖ የቱ ነው? ሀ. የቦታዎችን ተፈጥሮአዊ አቀማመጥ ያበላሻል ለ. የዱር እንስሳት እንዲሰደዱ ያደርጋል ሐ. አየርና ውሃ እንዲበከል ያደርጋል መ. ሁሉም 3. ከሚከተሉት ውስጥ የምሥራቅ አፍሪካ ብሔራዊ ፓርክ ያልሆነው የቱ ነው? ሀ. ማሳይ ማራ ለ. ደንከል በረሃ ሐ. ሴሬንጌቲ መ. ኦላንካ 4. የበረሃ ዕፅዋት የሚባለው የቱ ነው? ሀ. ቁልቋል ለ. ጥድ ሐ. ዋንዛ መ. ዝግባ ሐ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ፡፡ 1. የምሥራቅ አፍሪካን ዋና ዋና ዕፅዋትን ዘረዝሩ፡፡ 2. በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙ የማዕድን ዓይነቶችን ዘረዝሩ፡፡ 3. የዱር እንስሳት ማለት ምን ማለት ነው? 4. የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ዘዴዎችን ጥቀሱ፡፡ 5. ለተፈጥሮ ሀብት አጠባበቅ የሚረዱ ዋና ዋና ዘዴዎችን ግለጹ፡፡ 107 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ የምዕራፉ ማጠቃለያ  በምሥራቅ አፍሪካ የተለያየ መልክአ ምድር በመኖሩ ምክንያት የተለያየ የአየር ንብረት እንዲኖር አስችሎታል፡፡  የአየር ንብረት በአንድ ሥፍራ ለረዥም ጊዜ የሚከሰት የአየር ጠባይ ነው፡፡ ይህም የየዕለቱን የአየር ሁኔታ አማካይ ውጤት ለረዥም ጊዜ ቢያንስ ለ 30 ዓመት እና ከዚያ በላይ በማጥናት የሚታወቅ ነው፡፡  የአየር ንብረት ክልል ማለት በአንድ አካባቢ የሚገኝ ተመሳሳይ የአየር ሁኔታ የሚታይበት የመሬት ገጽ ነው፡፡  የተፈጥሮ ሀብት የሚባሉት በተፈጥሮ የሚገኙና አስፈላጊ ሀብቶች ናቸው፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ የተለያዩ ተራሮች፣ አምባ ምድሮች እንዲሁም ዝቅተኛ ሥፍራዎች በመኖራቸው ምክንያት ቀጠናው የተለያየ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት እንዲሆን አስችሎታል፡፡  ማዕድናት በከርሰ-ምድር ውስጥ በተፈጥሮ የሚገኙ የተለያዩ ብረታብረቶች፣ ኢ-ብረታብረቶችንና የነዳጅ ሀብትን ያጠቃልላል፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ የታወቁ የማዕድን ሀገራት የሚባሉት ዛምቢያ በመዳብ ምርት፣ ኬንያ፣ ታንዛንያ እና ኢትዮጵያ በወርቅ ምርት ናቸው፡፡  አፈር ማለት ከአለቶች ስብርባሪ፣ ከዕፅዋት እና ከእንስሳት ብስባሽ በብዙ ዘመናት ለውጥ ሂደት የሚፈጠር የላይኛው የመሬት አካል ነው፡፡  ውሃ ከመስኖና መጠጥ አገልግሎት በተጨማሪ ለተለያየ ጥቅም ይውላሉ:: ለምሳሌ፣ ለመጓጓዣ አገልግሎት፣ የመብራት ኃይል ለማመንጨትና ለዓሣ እርባታ ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣል፡፡  በምሥራቅ አፍሪካ በርካታ የተፈጥሮ ሀብቶች ይገኛሉ። እነዚህ የተፈጥሮ ሀብቶች አህጉራዊና ቀጠናዊ ኢኮኖሚን ለማሳደግ ጉልህ ሚና አላቸው። በምሥራቅ አፍሪካ ከሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶች መካከል፣ ደኖች፣ ውሃ፣ የዱር እንስሳቶች፣ ተራራዎች፣ ማዕድናትና የኃይል ምንጮች ዋና ዋናዎቹ ናቸው።  የዱር እንስሳት ለማዳ ያልሆኑ በማንኛውም የተፈጥሮ አካባቢ ባለ ሥፍራ የሚገኙ እንስሳት ናቸው፡፡  የተፈጥሮ ዕፅዋት የተለያዩ የአፈር ዓይነቶች፣ ተስማሚ የአየር ንብረት እና ከፍታ ቦታዎች ይገኛሉ፡፡ 108 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥሮ አካባቢ የምዕራፉ ማጠቃለያ ጥያቄዎች ሀ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል ካልሆኑ ደግሞ ሐሰት በማለት መልሱ፡፡ 1. የቪክቶርያ ሐይቅ በምሥራቅ አፍሪካ በስምጥ ሸለቆ ውስጥ ይገኛል፡፡ 2. የምሥራቅ አፍሪካ ከፍተኛ ቦታዎች ያላቸው የዝናብ መጠን ዝቅተኛ ነው፡፡ 3 ከባሕር የራቁ አካባቢዎች በበጋ ወቅት ቀዝቃዛ የአየር ንብረት አላቸው 4. ሁሉም የምሥራቅ አፍካ ሀገራት ተመሳሳይ የአየር ንብረት አላቸው፡፡ 5. የነገውን ሳይሆን የዛሬውን ትውልድ በማሰብ የተፈጥሮ ሀብትን መጠቀም ውጤታማ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ይባላል፡፡ ለ. በ ‘’ሀ’’ ሥር ለሚገኙት የወንዞቹና ሐይቆቹ ማብራሪያ ትክክለኛ መልስ ከ ‘’ለ’’ ሥር ካለው ስማቸው ጋር አዛምዱ፡፡ ሀ ለ 1. የስምጥ ሸለቆ ሐይቅ ሀ) ታና ወንዝ 2. ከስምጥ ሸለቆ ውጭ ያለ ሐይቅ ለ) አዋሽ ወንዝ 3. ከኢትዮጵያ የማይወጣ ወንዝ ሐ) ቪክቶሪያ ሐይቅ 4. በኬንያ ትልቁ ወንዝ መ) ዛምቤዚ ወንዝ 5. በአፍሪካ ትልቅ ፏፏቴ ያለው ወንዝ ሠ) ናይል ወንዝ 6. የዓለማችን ረዥሙ ወንዝ ረ) ቱርካና ሐይቅ ሐ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ሆሄ በመምረጥ መልሱ፡፡ 1. የምድር ወገብ አካባቢ ያሉ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ዝናብ የሚያገኙት መቼ ነው? ሀ) በሚያዝያና መስከረም ለ) በጥቅምትና ሚያዝያ ሐ) ከሰኔ እስከ መስከረም መ) ከታህሳስ እስከ የካቲት 2. የአየር ንብረት ይዘት ያልሆነው የቱ ነው? ሀ) ሙቀት ለ) የአየር ግፊት ሐ) እርጥበት መ) ዕፅዋት 109 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሦስት የተፈጥ

Use Quizgecko on...
Browser
Browser