Grade 5 Environmental Science 12 PDF
Document Details
Uploaded by LustrousSavanna6540
Abiyot Primary School
Tags
Summary
This Ethiopian environmental science document, chapter 1, introduces the concepts of geographic location. It covers relative and absolute location, using maps to identify key places in Ethiopia. It includes exercises.
Full Transcript
Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የኢትዮጵያ መገኛ ምዕራፍ አንድ የኢትዮጵያ መገኛ ከምዕራፉ የሚጠበቁ አጥጋቢ የመማር ውጤቶች፡- ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡- ካርታን በመጠቀም መረጃ ለመለዋወጥ ፈቃደኝነትን ታሳያላችሁ፡፡ የአንጻራዊ እና ፍጹማዊ መገኛ ምንነትን ታብራራላችሁ፡፡ ...
Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የኢትዮጵያ መገኛ ምዕራፍ አንድ የኢትዮጵያ መገኛ ከምዕራፉ የሚጠበቁ አጥጋቢ የመማር ውጤቶች፡- ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡- ካርታን በመጠቀም መረጃ ለመለዋወጥ ፈቃደኝነትን ታሳያላችሁ፡፡ የአንጻራዊ እና ፍጹማዊ መገኛ ምንነትን ታብራራላችሁ፡፡ የኢትዮጵያን አንጻራዊና ፍፁማዊ መገኛ በካርታ ላይ ታመለክታላችሁ፡፡ ኬክሮስንና ኬንትሮስን በመጠቀም በኢትዮጵያ የሚገኙ ዋና ዋና ቦታዎችን እና አቅጣጫዎችን በካርታ ላይ ታሳያላችሁ፡፡ ንድፍ ካርታ በመሥራት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ብሔራዊ ክልሎችን አንጻራዊ መገኛ ታመለክታላችሁ። መልክአ ምድራዊ አቀማመጥን፣ ጎግል የካርታ መፈለጊያ መተግበሪያንና ጎግል ኧርዝ (GPS, Google map and Google earth) በመጠቀም የቦታ አቀማመጥን የመለካትና የመመዝገብ ክህሎት ታዳብራላችሁ። 1 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የኢትዮጵያ መገኛ የምዕራፉ ዋና ዋና ይዘቶች 1.1 የቦታ መገኛ በካርታ ላይ 1.2 የኢትዮጵያ አንጻራዊና ፍጹማዊ መገኛ 1.3 በካርታ ላይ የኢትዮጵያ መገኛ ከአጎራባች ሀገራት አንጻር 1.4 በኢትዮጵያ የሚገኙ ታዋቂ ቦታዎች መገኛና አቅጣጫ 1.5 በኢትዮጵያ የሚገኙ ታዋቂ ቦታዎችን ለመጠቆም የተለያዩ ካርታዎች መሥራት 1.6 የካርታ መፈለጊያ መተግበሪያንና ጎግል ኧርዝ (GPS, Google map and Google earth) በመጠቀም የተለያዩ ቦታዎችን መለየት መግቢያ ተማሪዎች በ4ኛ ክፍል የአካባቢ ሳይንስ ምዕራፍ አንድ ትምህርታችሁ የካርታን፣ የአንጻራዊና የፍጹማዊ መገኛ ምንነትን፣ ኬክሮስንና ኬንትሮስን በመጠቀም የከተማችሁን መገኛ ማሳየት እንዲሁም የከተማችሁን አጎራባች አካባቢዎች ተምራችኋል፡፡ በዚህ ክፍል የቦታ መገኛ በካርታ ላይ፣ የኢትዮጵያን አንጻራዊና ፍጹማዊ መገኛ፣ በኢትዮጵያ የሚገኙ ታዋቂ ቦታዎች መገኛና አቅጣጫ እና የካርታ መፈለጊያ መተግበሪያንና ጎግል ኧርዝ (GPS, Google map and Google earth) በመጠቀም የተለያዩ ቦታዎችን እንዴት መለየት እና ማሳየት እንደሚቻል ትማራላችሁ፡፡ 2 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የኢትዮጵያ መገኛ 1.1 የቦታ መገኛ በካርታ ላይ የመማር ብቃት ተማሪዎች ይህን ትምህርት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ ፡- ካርታን በመጠቀም መረጃ ለመለዋወጥ ፈቃደኝነትን ታሳያላችሁ፡፡ የአንጻራዊ እና ፍጹማዊ መገኛ ምንነትን ታብራራላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት ካርታ መገኛ ፍጹማዊ መገኛ አንጻራዊ መገኛ የማነቃቂያ ጥያቄ ስለ ካርታ ምንነት የሚታውቁትን ለመምህራችሁ ተናገሩ፡፡ መገኛ አንድ ቦታ የሚገለፅበት ወይም የሚገኝበት ስፍራ ነው፡፡ ካርታ ደግሞ በይዘት ቀለል የተደረገ፣ መጠኑ ያነሰ እና በዝርግ ወረቀት ላይ ከላይ ወደታች በምድር ላይ ያሉ ቦታዎችን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የምናሳይበት መሣሪያ ነው፡፡ መገኛ ሳይንሳዊ በሆነ አግባብ አንድን ቦታ በካርታ ላይ የሚናሳይበት ዘዴ ነው፡፡ ስለዚህ ካርታን በመጠቀም የአንድን ቦታ መገኛ እና አቅጣጫ ማሳየት ይቻላል፡፡ የመገኛ ዓይነቶች በካርታ ላይ የአንድን ቦታ መገኛ በአንጻራዊ እና ፍጹማዊ የመገኛ ዓይነቶች ማሳየት ይቻላል፡ 1.አንጻራዊ መገኛ አንጻራዊ መገኛ በአካባቢ ከሚገኙ ተፈጥሮአዊ ወይም ሰው ሰራሽ ነገሮች ጋር በማነፃፀር የሚገለፅ የአንድ ነገር መገኛ ነው፡፡ አንድ ቦታ ከየብስ ወይም ከውሀ ክፍሎች አንፃር 3 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የኢትዮጵያ መገኛ የሚገኝበትን ቦታ ማሳያ ነው፡፡ ለምሳሌ- ኢትዮጵያ ከኤርትራ በስተደቡብ ትገኛለች፡፡ 2.ፍጹማዊ መገኛ ፍፁማዊ መገኛ አንድ ቦታ ከኬክሮስ እና ከኬንትሮስ አንጻር የሚገኝበትን ቦታ ማሳያ ነው፡፡ ፍጹማዊ መገኛ የአንድን ቦታ መገኛ በአሃዝ ልኬት ለመግለፅ የሚያስችል መንገድ ነው፡፡ የቡድን ውይይት 1.1 ዓላማ- የአንጻራዊ እና ፍጹማዊ መገኛ ምንነትን መግለፅ መመሪያ- ከ3-5 ቡድን መስራታችሁ የአንጻራዊ እና ፍጹማዊ መገኛ ምንነትን ተወያይታችሁ በተወካዮቻችሁ አማካኝነት ለክፍል ጓደኞቻችሁ አቅርቡ፡፡ መልመጃ 1.1 ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ፡፡ 1. አንጻራዊ መገኛ ምንድን ነው? 2. ካርታ እንዴት የአንድን ቦታ መገኛ ያሳያል ? 3. ፍጹማዊ መገኛ ምንድን ነው ? 1.2 የኢትዮጵያ አንፃራዊ እና ፍፁማዊ መገኛ አጥጋቢ የመማር ብቃት ተማሪዎች ይህን ትምህርት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ ፡- ¾ የኢትዮጵያን አንጻራዊ እና ፍጹማዊ መገኛ በካርታ ላይ ታመለክታላችሁ ፡፡ ቁልፍ ቃላት አቅጣጫ ኬክሮስ ኬንትሮስ የማነቃቂያ ጥያቄ የኢትዮጵያን አንጻራዊ መገኛ ለክፍል ጓደኞቻችሁ ግለፁ፡፡ 4 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የኢትዮጵያ መገኛ የኢትዮጵያን መገኛ በሁለት ዘዴ በካርታ ላይ መግለፅ እና ማሳየት ይቻላል፡፡ እነርሱም አንጻራዊ እና ፍፁማዊ መገኛ ዘዴዎች በመባል ይታወቃሉ፡፡ 1.የኢትዮጵያ አንጻራዊ መገኛ ኢትዮጵያ በተለያዩ አቅጣጫዎች በተለያዩ ሀገራት ትዋሰናለች፡፡ በእነዚህ በሚያዋስኗት ሀገራት በመጠቀም የኢትዮጵያን አንጻራዊ መገኛ መግለፅ እና ማሳየት ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያ በሁሉም አቅጣጫዎች በመሬት በመዋሰኗ የባህር በር የላትም፡፡ በሁሉም አቅጣጫ በውሃ ክፍል የተከበበ አካባቢ ደሴት ይባላል፡፡ ስዕል1.1 የኢትዮጲያ አንጸራዊ መገኛ ካርቱም እና ጁባ ከኢትዮጵያ በየትኛው አቅጣጫ ይገኛሉ? ሀገራት አቅጣጫዎች ከኤርትራ በስተ ደቡብ ከኬንያ በስተ ሰሜን ከደቡብ ሱዳን በስተ ደቡብ ምሥራቅ ከጂቡቲ በስተ ምዕራብ ከሱዳን በስተ ሰሜን ምሥራቅ ከሶማሊያ በስተ ደቡብ ምዕራብ ሰንጠረዥ 1.1 የኢትዮጵያ አንጻራዊ መገኛ-ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት አንጻር 5 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የኢትዮጵያ መገኛ የኢትዮጵያ ፍጹማዊ መገኛ የማነቃቂያ ጥያቄ ኬክሮስ እና ኬንትሮስ ምንድን ናቸው ? የኢትዮጵያ ፍጹማዊ መገኛ ከ 3 ዲግሪ ሰሜን እስከ 15 ዲግሪ ሰሜን እንዲሁም ከ 33 ዲግሪ ምሥራቅ እስከ 48 ዲግሪ ምሥራቅ ነው፡፡ ስለዚህ ከሰሜን እስከ ደቡባዊ ጫፍ ድረስ 12 ዲግሪ የኬክሮስ (Latitudes) ርዝመት ከምሥራቃዊ ጫፍ እስከ ምዕራባዊ ጫፍ 15 ዲግሪ የኬንትሮስ (Longitudes) ነው፡፡ ስዕል 1.2. የኢትዮጵያ ፍፁማዊ መገኛ ተግባር 1.1 ስዕል 1.2ን በመመልከት ኬክሮስና ኬንትሮስን በመጠቀም የኢትዮጵያን ፍጹማዊ መገኛ አጠገባችሁ ላለ ጓደኛችሁ አመልክቱ ፡፡ 6 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የኢትዮጵያ መገኛ 1.2. መልመጃ አንድ አጭር መልስ ስጡ፡፡ 1. የኢትዮጵያ ፍፁማዊ መገኛ ከ_____እስከ_______ሰሜን እና ከ___እስከ____ ምሥራቅ ነው :: 2. ኢትዮጵያን በደቡብ አቅጣጫ የሚያዋስናት ሀገር -------- ነው፡፡ 3. ኢትዮጵያ በሰሜን አቅጣጫ የምትዋሰነው ከ------ ጋር ነው፡፡ 4. ከኢትዮጵያ በስተ ደቡብ ምሥራቅ የምትገኝ አገር ----------- ናት፡፡ 1.3 በካርታ ላይ የኢትዮጵያ መገኛ ከአጎራባች ሀገራት አንጻር አጥጋቢ የመማር ብቃት ተማሪዎች ይህን ትምህርት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ ፡- የኢትዮጵያን አጎራባች ሀገራትን ትዘረዝራላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት አጎራባች ሀገራት የማነቃቂያ ጥያቄ የኢትዮጵያን ፍፁማዊ መገኛ ጥቀሱ? የኢትዮጵያ አጎራባች ሀገራት ኢትዮጵያ ከስድስት ጎረቤት ሀገራት ጋር ትዋሰናለች፡፡ እነዚህ ሀገራት በተለያዩ አቅጣጫዎች ኢትዮጵያን የሚያዋስኑ ሲሆን የኢትዮጵያን አንጻራዊ መገኛ ለመግለፅም ያገለግላሉ። እነርሱም፡- 1. ኤርትራ 4. ኬንያ 1. ሶማሊያ 5. ጂቡቲ 2. ሱዳን 6. ደቡብ ሱዳን 7 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የኢትዮጵያ መገኛ ስዕል 1.3. የኢትየጵያ አጎራባች ሀገራት ተግባር 1.2 የግል ሥራ 1. የኢትዮጵያ አጎራባች ሀገራትን መገኛ በሥዕል 1.3 ካርታ ላይ አሳዩ፡፡ 2. የኢትዮጵያ አጎራባች ሀገራት ከኢትዮጵያ ያላቸውን ርቀትን ከተለያዩ ምንጮች በመፈለግ በደብተራችሁ ላይ ፅፋችሁ ለመምህራችሁ አሳዩ ፡፡ 8 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የኢትዮጵያ መገኛ 1.4 በኢትዮጵያ የሚገኙ ታዋቂ ቦታዎች መገኛ እና አቅጣጫ አጥጋቢ የመማር ብቃት ተማሪዎች ይህን ትምህርት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ ፡- ኬክሮስንና ኬንትሮስን በመጠቀም በኢትዮጵያ የሚገኙ ቦታዎችን አቅጣጫ በካርታ ላይ ታሳያላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት ታዋቂ ቦታዎች የማነቃቂያ ጥያቄ በአካባቢያችሁ ታዋቂ ቦታዎች አሉ? ካሉ ለጓደኞቻችሁ ተናገሩ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ታዋቂ ቦታዎች የተፈጥሮ እና ሰው-ሠራሽ ሊሆኑ ይችላሉ:: ኢትዮጵያ በተፈጥሮም ሆነ ሰው ሠራሽ በርካታ ታዋቂ ቦታዎች ያላት ሀገር ስትሆን እነዚህ ቦታዎች በተለያዩ አቅጣጫዎች ላይ ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ፡ -የኢትዮጵያ ዋና ዋና ወንዞች፣ ሀይቆች፣ ተራሮች፣ ዋሻዎች፣ ፓርኮች፣ ግድቦች፣ ሐውልቶች፣ የሐይማኖት ቦታዎች፣ እና የመሳሰሉት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ የጥያ ትክል ድንጋይ-80 25’ 58” ሰሜን ኬክሮስ እና-380 36’ 35” ምሥራቅ ኬንትሮስ የአክሱም ሐውልት 140 7’ 47” ሰሜን ኬክሮስ እና-380 43’ 60”ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ይገኛሉ፡፡ ተግባር 1.3 የግል ስራ ኬክሮስ እና ኬንትሮስን በመጠቀም የኢትዮጵያን ታዋቂ ቦታዎች ለመምህራችሁ አሳዩ 9 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የኢትዮጵያ መገኛ 1.5 በኢትዮጵያ የሚገኙ ታዋቂ ቦታዎችን ለመጠቆም የተለያዩ ካርታዎችን መስራት አጥጋቢ የመማር ብቃት ተማሪዎች ይህን ትምህርት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ ፡- ንድፍ ካርታ በመሥራት በኢትዮጵያ የሚገኙ ክልሎችን አንጻራዊ መገኛ ታመለክታላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት ንድፍ ካርታ የማነቃቂያ ጥያቄ በኢትዮጵያ የሚገኙ ክልሎችን ስም ዝርዝር ጥቀሱ፡፡ ንድፍ ካርታ ምንድን ነው? ንድፍ- ካርታ ንድፍ-ካርታ መረጃ በመሰብሰብ እና መስፈርት በመወሰን በዝርግ ወረቀት ላይ በግለሰብ የሚሰራ የአንድ አካባቢ ንድፍ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በመስፈርት መሰረት በተሰበሰበ መረጃ አማካኝነት የተሳለ የአንድ ስፍራ ማሳያ ነው፡፡ ንድፍ-ካርታ በአጭር ጊዜ የሚሳል፣ በቀላሉ የሚለይ እና የአንድን ቦታ ገፅታ በቀላሉ ለማስቀመጥ ስለሚያስችል ለመስራት አስቸጋሪ አይደለም፡፡ ንድፍ ካርታ ለመስራት የሚያስችሉ መመሪያዎች 1. ካርታዎቻቸው የሚዘጋጁ ቦታዎችን መለየት 2. የቦታዎችን መነሻ ማስቀመጥ 3. የቦታውን ንድፍ ካርታ በሀሳብ ማስቀመጥ 4. የሚሳለውን ካርታ ድንበር መወሰን 5. የድንበሩን መስመሮች በመክፈል በአራት ማዕዘን ቦታውን ማስቀመጥ 6. በተዘጋጀው ካርታ ላይ ወሳኝ መረጃዎችን መፃፍ ናቸው፡፡ 10 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የኢትዮጵያ መገኛ ተግባር 1.4 የግል ስራ 1. በኢትዮጵያ የሚገኙ ክልሎችን ንድፍ ካርታ በወረቀት ላይ በመስራት ከአዲስ አበባ ያላቸውን አንጻራዊ መገኛ ለመምህራችሁ አሳዩ፡፡ 2. በኢትዮጵያ የሚገኙ ታዋቂ ቦታዎችን ንድፍ ካርታ በመስራት ለክፍል ጓደኞቻችሁ አሳዩ፡፡ በካርታ ላይ የአንድን ቦታ መገኛ ነጥብ በባለ አራት ወይንም ስድስት አኀዝ ፍርግርግ የማጣቀሻ ሥርዓት (four/six digit grid reference system) ማመልከት ይቻላል:: በባለ አራት ወይንም ስድስት አኃዝ ፍርግርግ የማጣቀሻ ሥርዓት ስንጠቀም የሚከተሉትን መመሪያዎችን ደረጃ በደረጃ መተግበር ያስፈልጋል፡፡ 1. ማሳየት ከፈለግነው ነጥብ በታች ያለውን ቀጥ ያለ መስመር እና ቁጥር ማየት 2. ማሳየት ከፈለግነው ነጥብ በስተግራ ያለውን ቀጥ ያለ መስመር በማየት በ 10 መክፈልና የነጥቡን ንባብ መውሰድ 3. ማሳየት ከፈለግነው ነጥብ በታች ያለውን የጎን መስመር መመልከት እና ቁጥር ማየት 4. ማሳየት ከፈለግነው ነጥብ በስተግራ ያለውን የጎን መስመር በማየት በ 10 መክፈልና የነጥቡን ምንባብ መውሰድ ናቸው፡፡ ሰንጠረዥ 1.2 ፍርግርግ የማጣቀሻ ሥርዓት.ሐ ሀ..ለ ሰንጠረዥ፡- 1.2 ባለ ዐራት ወይንም ስድስት አኀዝ ፍርግርግ የማጣቀሻ ሥርዓት ለምሳሌ- የነጥብ ሀ መገኛ በባለ አራት አኀዝ ፍርግርግ የማጣቀሻ ሥርዓት - 2728 ነው፡፡ ተግባር 1.5 የግል ስራ ከላይ የተቀመጠውን መመሪያ መሰረት በማድረግ የነጥብ ለ እና ሐ ን መገኛ አመልክቱ፡፡ 11 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የኢትዮጵያ መገኛ 1.6 የካርታ መፈለጊያ መተግበሪያን ጎግል ኧርዝ (GPS, Google map and Google earth) በመጠቀም የተለያዩ ቦታዎችን መለየት አጥጋቢ የመማር ብቃት ተማሪዎች ይህን ትምህርት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ ፡- መልክአ ምድራዊ አቀማመጥን፣ ጎግል የካርታ መፈለጊያ መተግበሪያንና ጎግል ኧርዝ (GPS, Google map and Google e arth) በመጠቀም የቦታ አቀማመጥን የመለካትና የመመዝገብ ክህሎት ታዳብራላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት ጂ ፒ ኤስ ጎግል ካርታ ጎግል ኧርዝ የማነቃቂያ ጥያቄ የካርታ መፈለጊያ መተግበሪያን ጎግል ኧርዝ (GPS, Google map and Google earth) ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? ምንነታቸውን ለክፍል ጓደኞቻችሁ ተናገሩ፡፡ የቦታ እና አቅጣጫ ማሳያ (Global Positioning System-GPS) ማለት በሳተላይቶች አማካኝነት ዓለማቀፋዊ በሆነ ሁኔታ ቦታዎችን የምናሳይበት ዘዴ ነው፡፡ የቦታ እና አቅጣጫ ማሳያ -የGPS ጥቅሞች 1. ተጓዦች በአየር፣ በባህር እና በመሬት ያሉበትን እና የሚሄዱበትን ቦታ ይለዩበታል:: 2. አንድ ቦታ ከሌላ ቦታ የሚገኝበትን ርቀት ለማወቅ ያስችላል፡፡ 3. የሰዎችን እንቅስቃሴ ለማወቅ ይረዳል፡፡ 4. የተለያዩ ካርታዎችን ለማዘጋጀት ይረዳል፡፡ 12 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የኢትዮጵያ መገኛ ጉግል ካርታ (Google map) ጉግል ካርታ በጉግል የሚቀርብ የድር ካርታ መድረክ እና የሸማቾች መተግበርያ ነው፡፡ እነዚህ ካርታዎች የሳተላይት ምስሎችን፣ የአየር ላይ ፎቶግራፎችን፣ የጎዳና ካርታዎችን ያካትታል፡፡ ጉግል ኧርዝ (Google earth)- ጉግል ኧርዝ እጅግ በጣም የታወቀ እና በስፋት ጥቅም ላይ የዋለ ጂኦግራፊያዊ የመረጃ ስርዓት መተግበርያ ነው፡፡ ይህ መተግበርያ ካርታ አዘጋጆችን ከቦታ ጋር ስለሚገናኝ መረጃን እንዲፈጥሩ፣ እንዲያከማቹ፣ እንዲመለከቱ እና መስተጋብር እንዲፈጥሩ ያስችላቸዋል፡፡ ተግባር 1.6 የቡድን ስራ ትምህርት ቤታችሁ ያለውን ኮምፒዩተር ማዕከል በመጠቀም ፡- 1. በጉግል ካርታ እና በጉግል-ኧርዝ የኢትዮጵያን መገኛ አሳዩ፡፡ 2. የጉግል ካርታ፣ ጂ ፒ ኤስ እና ጉግል ኧርዝ አገልግሎት ካነበባችሁ በኋላ ተወያዩበት፡፡ 13 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የኢትዮጵያ መገኛ የምዕራፉ ማጠቃለያ የተለያዩ አካባቢዎች የተለያየ መገኛ ቦታ አላቸው፡፡ መገኛ ማለት አንድ ቦታ የሚገኝበት ስፍራ ሲሆን በካርታ ላይ ማሳየት ይቻላል፡፡ ሁለት አይነት የቦታ መገኛዎች አሉ፤እነርሱም አንጻራዊ እና ፍጹማዊ መገኛ በመባል ይታወቃሉ፡፡አንጻራዊ መገኛ በየብስ ወይም በውሃ ክፍል የሚገለፅ ሲሆን ፍጹማዊ መገኛ ደግሞ በኬክሮስ እና ኬንትሮስ ይገለጻል፡፡ የኢትዮጵያን አንጻራዊ እና ፍጹማዊ መገኛ በመጠቀም የተለያዩ ታዋቂ ቦታዎችን በካርታ ላይ ማሳየት ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያ በተለያዩ አቅጣጫዎች በስድስት ሀገራት ትዋሰናለች፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ሰው ሠራሽ እና ተፈጥሯዊ ታዋቂ ቦታዎች ያሉ ሲሆን እነዚህን ቦታዎች በካርታ መለየት እና ማሳየት ይቻላል፡፡ የተለያዩ መተግበራዎችን (GPS, Earth map and Google map) በመጠቀም የተለያዩ ቦታዎችን መገኛ ማሳየት ይቻላል፡፡ 14 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የኢትዮጵያ መገኛ የምዕራፉ ማጠቃያ ጥያቄዎች I.የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል ካልሆኑ ደግሞ ሐሰት በማለት በተሰጣችሁ ባዶ ቦታ ላይ መልሱን ጻፉ፡፡ 1. የአንድ ቦታ አንጻራዊ መገኛ በውሃ ክፍሎች ሊዋሰን ይችላል፡፡ 2. ካርታ አንድን ቦታ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በዝርግ ወረቀት ያሳያል። 3. ኬክሮስ እና ኬንትሮስ የአንድን ቦታ አንፃራዊ መገኛ ይገልጻሉ፡፡ 4. ፍጹማዊ መገኛ የአንድን ቦታ ወይም ክስተት ትክክለኛ መገኛ በአሀዝ ልኬት ያሳያል፡፡ 5. ንድፍ ካርታ ሲነደፍ የኬክሮስ እና ኬንትሮስ መስመሮችን እንጠቀማለን፡፡ II. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ የያዘ ሆሄ መርጣችሁ በተሰጣችሁ ባዶ ቦታ ላይ ፃፉ፡፡ ___1. ከሚከተሉት ሀገራት ውስጥ ኢትዮጵያን የማያዋስነው የቱ ነው? ሀ. ግብፅ ለ. ኤርትራ ሐ. ሱዳን መ. ኬንያ ___2. ታዋቂ ቦታቸውን ለማሳየት የሚያገለግለን ሀ. ኬክሮስ ለ. ኬንትሮስ ሐ. ሀ እና ለ ___3. አንጻራዊ መገኛን ለመግለፅ የማያገለግለው የቱ ነው? ሀ. የውሀ ክፍል ለ. የመሬት ክፍል ሐ. ኬክሮስ መ. ሁሉም III. ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ፡፡ 1. በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የተፈጥሮና ሰው-ሠራሽ ዋና ዋና ቦታዎች ምን ምን ናቸው? 2. የኢትዮጵያ አንጻራዊ መገኛ ከፍጹማዊ መገኛ በምን ይለያል? 3. የካርታ መፈለጊያ መተግበራዎች የሚባሉትን ስማቸውን ጥቀሱ፡፡ ለምንስ ያገለግላሉ? 15 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የኢትዮጵያ መገኛ የኢትዮጵያን ካርታ በመመልከት የኢትዮጵያን አጎራባች ሀገራት እና የሚገኙበትን አቅጣጫ ጻፉ፡፡ ሥዕል 1.13 የኢትዮጵያ ካርታ 1.______________________ 4. ______________________ 2. ______________________ 5. ______________________ 3. ______________________ 6. ______________________ የቁልፍ ቃላት ፍቺ 1. ካርታ- የመረትን ገጽታ ወይም በመሬት ገጽታ ላ አንድ የተለየ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፍል የሚያሳይ ሥዕላዊ መግለጫ 2. አንጻራዊ መገኛ-በአካባቢ ከሚገኙ ነገሮች/አገሮች ጋር በማነጻጸር የሚገለፅ 3. ፍጹማዊ መገኛ- ኬንትሮስን እና ኬክሮስን በመጠቀም የሚገለፅ መገኛ 4. ጂ ፒ ኤስ- የአቅጣጫ ማሳያ መተግበርያ 5. ንድፍ ካርታ-በመስፈርት በተገኘ መረጃ የሚዘጋጅ ንድፍ/ፕላን 6. አቅጣጫ- የአንድ ሰው ወይም ነገር ፍሰት ነው፡፡ 16 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አንድ የኢትዮጵያ መገኛ ፍተሻ ልታከናውኗቸው የምትችሏቸውን ተግባራት ለመግለፅ ይህን ()ምልክት በሳጥኖቹ ውስጥ በማኖር አመልክቱ፡፡ 1. ካርታን በመጠቀም መረጃ ለመለዋወጥ ፈቃደኝነትን አሳያለሁ፡፡ 2. የአንጻራዊና የፍጹማዊ መገኛን ምንነት አብራራለሁ፡፡ 3. የኢትዮጵያን አንጻራዊ መገኛ አመለክታለሁ፡፡ 4. የኢትዮጵያን ፍጹማዊ መገኛ አመለክታለሁ፡፡ 5. ኬክሮስንና ኬንትሮስን በመጠቀም የኢትዮጵያን መገኛ በካርታ ላይ አሳያለሁ፡፡ 6. ኬክሮስንና ኬንትሮስን በመጠቀም በኢትዮጵያ የሚገኙ ቦታዎችን አቅጣጫ በካርታ ላይ አሳያለሁ፡፡ 7. መልክአ ምድራዊ አቀማመጥን፣ ጎግል የካርታ መፈለጊያ መተግበሪያንና ጎግል ኧርዝ (GPS, Google map and Google earth) በመጠቀም የቦታ አቀማመጥን የመለካትና የመመዝገብ ክህሎት አዳብራለሁ፡፡ 8. ንድፍ ካርታ በመሥራት በኢትዮጵያ የሚገኙ ክልሎችን አንጻራዊ መገኛ አመለክታለሁ፡፡ 17 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ የምዕራፉ የመማር ውጤቶች ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡- ዋና ዋና የሥርዓተ ልመት አካላትንና ተግባራትን ትገልጻላችሁ፡፡ የሥርዓተ ልመት አካላት ጠቀሜታ ትለያላችሁ፡፡ የቁስ አካልን ምንነት ትገልጻላችሁ፡፡ ድብልቅ ያልሆኑ ልዩ ቁሶችን ምንነት ትገልጻላችሁ፡፡ የውህድን ምንነት ትገልጻላችሁ፡፡ የኦክሳይዶችን፣ አሲዶችን፣ ቤዞችን እና ጨዎችን ምንነት ትገልጻላችሁ፡፡ መጠነ ቁስን፣ ርዝመትን፣ ይዘትን፣ ጊዜን እና የመሳሰሉትን ትለካላችሁ፡፡ ለእንቅስቃሴና ለውጥ ለማምጣት አስፈላጊ የጉልበት ምንጮችን (ምግብ፣ ነዳጅ፣ የፀሐይ ብርሃን) ትገልጻላችሁ፡፡ የድምጽን ምንነት በመግለጽ ድምጽ የሚተላለፍባቸውን ቁሶች ትገልጻላችሁ፡፡ 18 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ የምዕራፉ ይዘቶች 2.1 ዋና ዋና የሥርዓተ ልመት አካላት 2.2 ቁስ አካል(Matter) 2.3 ልኬት 2.4 የጉልበት ምንጮች 2.5 ድምጽ መግቢያ በአራተኛ ክፍል የአካባቢ ሳይንስ ትምህርታችሁ ስለ ምግብና ጤናማ አኗኗር፣ የምግብና የጤናማ አኗኗር ምንነት፣ የሰው ውስጣዊ አባለ አካላት ተምራችኋል:: በዚህ ክፍል ደግሞ ዋና ዋና የሥርዓተ ልመት አካላትን ፣ ቁስ አካል፣ ልኬትን፣ የጉልበት ምንነት እና የድምጽ ምንነትን በዝርዝር ትማራላችሁ፡፡ ሥርዓተ ልመት ምግብ ሰውነታችን ሊጠቀማቸው ወደሚችሉ የምግብ ንጥረ ነገሮች የሚፈጭበት ሂደት ነው፡፡ ይህ ሂደት በተለያዩ የምግብ መፍጫ አካላት ይከናወናል፡፡ ቁስ አካል ማንኛውም ቦታ የሚይዝና መጠነ-ቁስ(mass) ያለው ነገር ሁሉ ነው፡፡ ልኬት የአንድን ነገር መጠነ ቁስ፣ ርዝመት፣ ስፋት፣ ይዘት እና የመሳሰሉትን ለማወቅ የሚደረግ ሂደት ነው፡፡ በውስጡ የቁሱ መጠን እና መለኪያ አሐድን የያዘ ነው፡፡ ጉልበት የአንድን ቁስ ፍጥነት ለመቀየር የሚደረግ ማንኛውም ተጽዕኖ ነው፡፡ ድምጽ በነገሮች እርግብግብት የሚፈጠር እና በጠጣር ፣ በፈሳሽ እና በጋዝ ነገሮች ውስጥ የሚተላለፍ ነው፡፡ 19 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ 2.1.ሥርዓተ ልመት የንዑስ ርዕሱ አጥጋቢ የመማር ብቃት ተማሪዎች ይህን ክፍለ ትምህርት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡- ዋና ዋና የሥርዐተ ልመት አካላትንና ተግባራት ትገልጻላችሁ፡፡ የሥርዓተ ልመት አካላት ጠቀሜታ ትገልጻላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት ስርዓተ-ልመት ሬክተም ሬብ የምግብ መተላለፉያ ቱቦ ተማሪዎች ስለ አልሚ ምግቦች በአራተኛ ክፍል የአካባቢ ሳይንስ ትምህርታችሁ ተምራችኋል፤ በዚህ ክፍል ትምህርታችሁ ደግሞ ስለ ሥርዓተ ልመት ትማራላችሁ፡፡ የቡድን ውይይት 2.1 ዓላማ - ስለ ምግብ ልመት ምንነት መግለፅ፡ መመሪያ - በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ በቡድን ተከፋፍላችሁ በመወያየት መልሶቻችሁን ለመምህራችሁ አቅርቡ። የመወያያ ጥያቄዎች 1. የምንመገበው ምግብ በሰውነታችን ውስጥ እንዴት የሚፈጭ ይመስላችኋል? 2. በሥርዓተ-ልመት ውስጥ የጥርስ፣ የምላስ፣ የጉሮሮና የጨጓራን ተግባር ዘርዝሩ፡፡ 20 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ 2.1.1. ስርዓተ ልመት በሰውነታችን ውስጥ ስርዓተ ልመት (digestive system) ማለት ምግብ ጥቃቅን ወደ ሆኑና በቀላሉ ወደ ደም ውስጥ ሊሰርጉ ወደሚችሉበት ደረጃ የመቀየር ሂደት ነው፡፡ የምግብ መፈጨት ዋና አሰፈላጊነቱ የሰውነት ሕዋሶች ምግብን አግኝተው ሥራቸውን በሚገባ እንዲያከናውኑ ለማድረግ ነው፡፡ የምግብ መፈጨት በተለያዩ የምግብ መፍጫ አካላትና በእነዚህ አካላት ውስጥ በሚገኙ ፈሳሾችና ኢንዛይሞች አማካይነት የሚከናወን ነው፡፡ በስርዓተ ልመት ምግብ የሚተላለፍባቸውና የሚፈጭባቸው የሰውነት ክፍሎች የምግብ መተላለፊያ ቱቦዎች ይባላሉ፡፡ የምግብ መተላለፊያ ቱቦ የሚባሉት:- አፍ፣ ጉሮሮ፣ ጨጓራ፣ ትንሹ አንጀት፣ ትልቁ አንጀት፣ ሬብና ፊንጢጣ ናቸው፡፡ ከእነዚህ አካላት ውስጥ ምግብ የሚፈጭባቸው አፍ፣ ጨጓራና ትንሹ አንጀት ናቸው፡፡ ሀ. አፍ በስርዓተ ልመት የመጀመሪያው ተግባር ምግብን ወደ አፍ ማስገባት ነው፡፡ አፍ ምግብ መፈጨት የሚጀምርበት የሥርዓተ ልመት አካል ነው፡፡ በመጀመሪያ ምግብ በጥርስ አማካይነት ይሰባበራል፤ ከዚያም በምራቅ ይለወስና በምላስ አማካይነት ተመቻችቶ ወደ ጉሮሮ ይገፋል፡፡ ለ. ጉሮሮ ጉሮሮ አፍንና ጨጓራን የሚያገናኝ የምግብ መተላለፊያ ቱቦ ነው። ከአፍ ወደ ጉሮሮ የደረሰው ምግብ በሚፈጠረው አካላዊ እንቅስቃሴ አማካይነት በፍጥነት ወደ ጨጓራ ይደርሳል፡፡ ሐ. ጨጓራ (ሆድ) ከአፍ በጉሮሮ ተውጦ ያለፈው ምግብ ጨጓራ ውስጥ ገብቶ የመፈጨት ሂደቱ ይቀጥላል። ጨጓራ ምግብ በጊዜያዊነት የሚከማችበትና ምግብ የሚፈጭበት ሥፍራ ነው፡፡ ጨጓራ ውስጥ ዝልግልግ ፈሳሽ፣ ሃይድሮ ክሎሪክ አሲድና ኢንዛይሞች ይገኛሉ። ኢንዛይሞች የምግብ ልመት እንዲፋጠን ያደርጋሉ፡፡ 21 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ በጨጓራ ውስጥ የሚገኘው ንፍጥ መሳይ ወፍራም ዝልግልግ ፈሳሽ የጨጓራ ግድግዳ በኢንዛይሞች እንዳይፈጭና በሃይድሮ ክሎሪክ አሲድ እንዳይጎዳ ይከላከላል፡፡ ሃይድሮ ክሎሪክ አሲድ ሃይለኛ አሲድ ስለሆነ ከምግብ ጋር አብሮ ወደ ጨጓራችን የሚገቡ ጀርሞችን ለመግደል ያገለግላል፡፡ ሥዕል 2.1 ጨጓራ ተግባር 2.1 የቡድን ሥራ ዓላማ፡- የጨጓራን ቅርፅ መረዳት መመሪያ፡-የጨጓራ ሞዴል በቡድን ሆናችሁ ስሩ፡፡ ይህን ተግባር ለማከናወን በቅድሚያ ክርታስና ማጣበቂያ ነገር አዘጋጁ። ቀጥሎ በስዕል እንደሚታየው አይነት አድርጋችሁ ሞዴሉን አዘጋጁ። መ. ትንሹ አንጀት በጨጓራ ውስጥ በከፊል ተብላልቶ የነበረው ምግብ ቀስ በቀስ ወደ ትንሹ አንጀት ይተላለፋል፡፡ በትንሹ አንጀት ውስጥ ምግብ ወደ መጨረሻ ልምት /የምግብ ንጥረ ነገሮች/ ይለወጣል፡፡ ስለዚህ ትንሹ አንጀት የምግብ ልመት የሚጠናቀቅበት የስርዓተ ልመት የአካል ክፍል ነው፡፡ ልመቱ የተጠናቀቀው ምግብ በትንሹ አንጀት ግድግዳ ላይ በሚገኙት ትንንሽ ቧንቧዎች አማካይነት ወደ ደም ስሮች ይገባል፤ ይህ ሂደት ስርገት ይባላል፡፡ የሰረገውም ምግብ ወደ ተለያዩ አካል ክፍሎች በደም ሥሮች አማካይንት ይጓጓዛል፡፡ የላመ ምግብ በቀላሉ መስረግ እንዲችል የትንሹ አንጀት ግድግዳ ትናንሽ ጣት መሰል ነገሮች አሉት፡፡ እነዚህም ቪላይ ተብለው ይጠራሉ፡፡ 22 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ሠ. ትልቁ አንጀት ትልቁ አንጀት ያልተፈጨ ምግብን በፊንጢጣ በኩል በሰገራ መልክ ወደ ውጭ ለማስወገድ ያገለግላል፡፡ በትልቁ አንጀት ውስጥ፡- ምግብ አይፈጭም፡፡ ውሃ ይመጠጥና ወደ ሰውነት ይሠርጋል፡፡ ያልተፈጨ ምግብ ሁሉ ለተወሰነ ጊዜ በሬክተም (ሬብ) ከተጠራቀመ በኋላ በተገቢው ጊዜና ሰዓት ከሰውነታችን በሰገራ መልክ በፊንጢጣ በኩል ይወገዳል፡፡ ረ. ፊንጢጣ ይህ ክፍል ጠቃሚ ያልሆኑና ወደ ደም ሰርገው ያልገቡ ቆሻሻዎች በትልቁ አንጀት በኩል አልፈው ሲመጡ በሰገራ መልክ የሚወገዱበት ቀዳዳ ነው። ሥዕል 2.2 የምግብ መተላለፊያ ቱቦ 23 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ተግባር 2.2 የሰው የምግብ መፍጫ አካላትን የሚያሳይ ስዕል በጠንካራ ነገር (ካርቶን፣የስዕል ወረቀት፣ጣውላ) ላይ ከሠራችሁ በኋላ እያንዳንዱን የምግብ መፍጫ አካል በቀስት አመልክቱ፤ በመቀጠልም በቡድን በመሆን የእያንደንዱን የምግብ መፍጫ አካል ጥቅም ተወያይታችሁ ለክፍል ጓደኞቻችሁ አስረዱ። ሙከራ 2.1 ከምግብ ቧንቧዎች ውሰጥ አፍ የሚያመነጨውን ምራቅ በመጠቀም የልመትሂደትን መሞከር የሚያስፈልጉ ነገሮች- - ዳቦ - ሁለት ብርጭቆዎች - ምራቅ - ውሃ የአሠራር ቅደም ተከተል -ሁለቱን ብርጭቆዎች ጎን ለጎን በጠረጴዛ ላይ አስቀምጡ፡፡ - እኩል የሆነ የዳቦ ቁራሽ በእያንዳንዱብርጭቆ ውስጥ ጨምሩ በአንደኛው ብርጭቆ ውስጥ ምራቅ በሌላኛው ብርጭቆ ውስጥ ደግሞ ውሃ ጨምሩበት የጨመራችሁት የምራቅ እና የውሃ መጠን እኩል መሆን አለበት፡፡ የተወሰነ ደቂቃ መጠበቅ ጥያቄ፡- 1. በየትኛው ብርጭቆ ውስጥ ለውጥ አያችሁ? 2. ምን አይነት ለውጥ አያችሁ? ለምን ? 24 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ መልመጃ 2.1 ሥዕል2.3 የሥርዓተ ልመት አካል ክፍሎች ከላይ በሥዕል2.3 የተመለከቱትን የሥርዓተ ልመት አካላት ቀጥሎ ከተሰጠው ጥቅማቸው ጋር በማዛምድ የተሰየመበትን ፊደል ጻፉ፡፡ 1 ምግብ የሚታኘክበት ቦታ 2 የመጀመሪያውን የምግብ ቱቦ ከጨጓራ ጋር ያገናኛል 3 ውሃ ይመጠጥበታል 4 የምግብ ንጥረ-ነገሮች ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች የሚሰርጉበት 5 ምግብ በጊዜያዊነት የሚጠራቀምበት 2.2 ቁስ አካል(Matter) የንዑስ ርዕሱ አጥጋቢ የመማር ብቃት ተማሪዎች ይህን ክፍለ ትምህርት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡- ¾ የቁስ አካልን ምንነት ትገልጻላችሁ፡፡ ¾ ድብልቅ ያልሆኑ ልዩ ቁሶችን ምንነት ትገልጻላችሁ፡፡ ¾ ድብልቅ ያልሆኑ ልዩ ቁሶችን ምሳሌዎች ትዘረዝራላችሁ፡፡ ¾ የውህድን ምንነት ትገልጻላችሁ፡፡ ¾ የኦክሳይዶችን፣ አሲዶችን፣ ቤዞችን እና ጨዎችን ምንነት ትገልጻላችሁ፡፡ ¾ የተለመዱ ኦክሳይዶችን፣ አሲዶችን፣ ቤዞችን እና ጨዎችን ምሳሌዎች ትጠቅሳላችሁ፡፡ 25 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ቁልፍ ቃላት -ቁስ አካል -ውህድ -አሲድ -ንጥረ ነገር -ልዩ ቁስ -ኦክሳይድ -ቤዝ -ጨው የማነቃቂያ ጥያቄ 1. ቁስ አካል ምንድን ነው? 2. የቁስ አካል አይነቶችን ዘርዝሩ:: ማንኛውም ቦታ የሚይዝና መጠነ-ቁስ(mass) ያለው ነገር ሁሉ ቁስ አካል በመባል ይታወቃል፡፡ ለምሳሌ ውሃ፣ ድንጋይ፣ ብረት፣ እንጨት፣ የቤት ቁሳቁሶችና የመሳሰሉት ቁስ አካላት ናቸው፡፡ ቁስ አካል ድብልቅ ያልሆኑ ልዩ ቁሶችና ድብልቅ ልዩ ቁሶች በመባል በሁለት ይመደባል:: ልዩ ቁስ (substance) ማለት አንድ ዓይነት ወይም ድብልቅ ምንዝሮች የያዘ ነገር ማለት ነው፡፡ ንጥረ ነገሮች (elements)፣ ውህዶች (Compounds)፣ ድብልቆች (mixtures) ልዩ ቁሶች ናቸው:: ድብልቅ ያልሆኑ ልዩ ቁሶች(pure substances) የማነቃቂያ ጥያቄ 1. ድብልቅ ያልሆኑ ልዩ ቁሶች ምንድን ናቸው? 2. ድብልቅ ያልሆኑ ልዩ ቁሶችን ምሳሌዎች ዘርዝሩ:: 3. ንጥረ ነገሮች ምንድን ናቸው? 4. ውህድ ምንድን ነው? ድብልቅ ያልሆኑ ልዩ ቁሶች ከአንድ አይነት ንጥረ ነገር ብቻ ወይም ሁለትና ከሁለት በላይ የሆኑ ንጥረ ነገሮች በሚያካሂዱት ኬሚካዊ ለውጥ የሚፈጠሩ ልዩ ቁሶች ናቸው:: ወርቅ፣ ብረት፣ ውሃ፣ የገበታ ጨው፣ መዳብ፣ ካርቦን፣ ናይትሮጂን፣ ሶድየም ሃይድሮክሳይድና የመሳሰሉት ድብልቅ ያልሆኑ ልዩ ቁሶች ምሳሌዎች ናቸው:: 26 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ንጥረ ነገር ከአንድ አይነት አቶም የተሰራ ልዩ ቁስ ሲሆን ወደ አነስተኛ ልዩ ቁሶች ሊከፋፈል አይችልም፡፡ ውህድ ሁለትና ከሁለት በላይ ከሆኑ ንጥረ ነገሮች በኬሚካዊ መስተጋብር የሚፈጠር ልዩ ቁስ ነው፡፡ ወርቅ፣ መዳብ፣ ብር፣ ኦክስጅን፣ ናይትሮጅንና የመሣሠሉት የንጥረ ነገሮች ምሳሌዎች ሲሆኑ ካርቦን ዳይኦክሳይድ፣ ያልተደባለቀ ውሃና የገበታ ጨው ደግሞ የውህድ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ የውህድ አይነቶች የማነቃቂያ ጥያቄ 1. የውህድ አይነቶችን ዘርዝሩ:: 2. የኦክሳይዶችን፣ አሲዶችን፣ ቤዞችን እና ጨዎችን ምንነት ግለጹ:: 3. የተለመዱ ኦክሳይዶችን፣ አሲዶችን፣ ቤዞችን እና ጨዎችን ምሳሌዎች ዘርዝሩ፡፡ ኦክሳይዶች(Oxides)፣ አሲዶች(Acids)፣ ቤዞች(Bases) እና ጨዎች(Salts) የውህድ አይነቶች ናቸው:: ኦክሳይዶች(Oxides) ኦክሳይዶች በውስጣቸው ኦክስጅንና አንድ ሌላ ንጥረ ነገር ብቻ የያዙ ውህዶች ናቸው:: ውሃ፣ ካርቦን ዳይኦክሳይድ፣ ሰልፈር ዳይኦክሳይድ፣ ማግኒዚየም ኦክሳይ፣ ሶድየም ኦክሳይድና የመሳሰሉት የተለመዱ የኦክሳይዶች ምሳሌዎች ናቸው:: አሲዶች(Acids) አሲድ “አሲደስ” ከሚለው የላቲን ቃል የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙም ኮምጣጣ ማለት ነው:: ሃይድሮክሎሪክ አሲድ፣ ናይትሪክ አሲድ፣ ሰልፈሪክ አሲድ፣ሲትሪክ አሲድ፣ላክቲክ አሲድና የመሳሰሉት አሲዶች ናቸው:: 27 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ቤዞች(Bases) ቤዞች አብዛኞቹ ብረት አስተኔያማ ኦክሳይዶች ወይም አሞኒያ ጋዝ ከውሃ ጋር ሲፀገበሩ የሚፈጠሩ ኬሚካዊ ውህዶች ናቸው:: ለምሳሌ ማግኒዚየም ሃይድሮክሳይድ፣ አሞኒየም ሃይድሮክሳይድ፣ ሶድየም ሃይድሮክሳይድ፣ ካልሲየም ሃይድሮክሳይድ የተለመዱ ቤዞች ናቸው:: ጨዎች(Salts) ጨዎች አሲዶችና ቤዞች ሲፀገበሩ የሚፈጠሩ ውህዶች ናቸው፡፡ ይህ ሂደት አግልሎት(Neutralization) ተብሎ ይጠራል፡፡ ሶድየም ክሎራይድ (የገበታ ጨው)፣ አሞኒየም ናይትሬት፣ ሶዲየም ካርቦኔት፣ ኮፐር (II) ሰልፌት፣ ካልሲየም ካርቦኔትና የመሳሰሉት ጨዎች ናቸው:: መልመጃ 2.2 I. ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡ 1. ከሚከተሉት ውስጥ ቁስ አካል ያልሆነው የቱ ነው? ሀ. ድንዳይ ሐ. ጨው ለ. ውሃ መ. ብርሃን 2. ከሚከተሉት ውስጥ ድብልቅ ያልሆኑ ልዩ ቁሶች የትኞቹ ናቸው? ሀ. መዳብ ሐ. ሃይድሮክሎሪክ አሲድ ለ. ካርቦን ዳይኦክሳይድ መ. ሁሉም 3. ከሚከተሉት ውስጥ “ጨው “ የሆነው የቱ ነው? ሀ. ካልሲየም ሃይድሮክሳይድ ሐ. ናይትሪክ አሲድ ለ. ሶድየም ክሎራይድ መ. ሰልፈር ዳይኦክሳይድ II. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ጻፉ 1. የውህድን ምንነት አብራርታችሁ ጻፉ:: 2. የተለመዱ ኦክሳይዶችን፣ አሲዶችን፣ ቤዞችን እና ጨዎችን ምሳሌዎች ዘርዝሩ:: 3. በአካባቢያችሁ የሚገኙ አራት የቁስ አካል ምሳሌዎችን ጥቀሱ:: 28 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ 2.3 ልኬት የንዑስ ርዕሱ አጥጋቢ የመማር ብቃት፡- ተማሪዎች ይህን ክፍለ ትምህርት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡- ¾ መጠነ-ቁስ፣ ርዝመት፣ ይዘት፣ ጊዜን እና የመሳሰሉትን ትለካላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት መጠነ -ቁስ አሐድ ልኬት፡- የአንድን ነገር መጠን፣ ብዛት፣ ርዝመት፣ ይዘት እና የመሳሰሉትን ነው፡ ፡ በውስጡ የሚለካበት አሐድ እና መጠኑን የያዘ ነው፡፡ ልኬትን በሁለት ዘዴ በመጠቀም መለካት ይቻላል። 1. ባህላዊ የመለኪያ ዘዴ በሀገራችን ውስጥ በድሮ ጊዜ ሰዎች ባህላዊ የአለካክ ዘዴን ይጠቀሙ ነበር፡፡ ለምሳሌ ጊዜን የፀሐይን መውጣትና መግባት እያዩ ንጋት ወይም ምሽት ብለው ይጠሩ ነበር፡ ፡ ርዝመት ለመለካት ደግሞ ስንዝርን፣ ክንድን፣ እርምጃንና የመሳሰሉትን ይጠቀሙ ነበር፡፡ ነገር ግን እነዚህ መስፈሪያዎች ሙሉ በሙሉ ትክክለኛ ናቸው ማለት አይቻልም፡ ፡ ምክንያቱም በተለያዩ ቦታ እና ሰዎች ሲለካ የተለያዩ ውጤቶችን እናገኛለን፡፡ እርምጃ ሥዕል፡- 2.5 የተለያዩ የባህላዊ መለኪያ መሳሪያዎች (ክንድ፣ ጫማ) 2.ዘመናዊ የመለኪያ ዘዴ የዘመናዊ የመለኪያ ዘዴዎች ዓለም አቀፍ መለኪያ አሐድ እና ትክክለኛ የመለኪያ ዘዴ አላቸው፡፡ 29 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ሥዕል፡- 2.6 የተለያዩ የዘመናዊ መስፈሪያ መሳሪያዎች( መለኪያ ሜትር፣ ማስመሪያ) 2.3.1 መጠነ-ቁስን መለካት ተግባር 2.3 ተግባራዊ ክንውን ዓላማ ፡- መጠነ ቁስን መለካት አራት የተለያዩ መጠን ያላቸውን ነገሮችን ውሰዱና ሚዛን በመጠቀም ለክታችሁ ውጤቱን በደብተራችሁ ጻፉ፡፡ የለካችሁት መጠን ምን ይባላል? የመጠነ ቁስ እና የክብደት ልዩነት ምንድነው? መጠነ ቁስ ማለት አንድ አካል በውስጡ የያዘው የቁስ መጠን ነው፡፡ ዓለም አቀፍ የመጠነ ቁስ መለኪያ ኪሎ ግራም ነው፡፡ በተጨማሪ ግራም ፣ ሚሊግራም፡ ቶን እና የመሳሰሉት ሌሎች የመጠነ ቁስ አሐዶች ናቸው፡፡ የመጠነ-ቁስ መለኪያ መሳሪያ ሚዛን ይባላል፡፡ ሚዛን በሁሉም ቦታ ተመሳሳይና ትክክለኛ የመጠነ ቁስ መለኪያ መሳሪያ ነው፡፡ ሥዕል:- 2.7 የመጠነ ቁስ መለኪያ (ሚዛን) 30 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ክብደትና መጠነ ቁስ የተለያዩ ናቸው፡፡ መጠነ ቁስ ማለት አንድ አካል በውስጡ የያዘው የቁስ መጠን ሲሆን ክብደት ማለት ደግሞ አንድ አካል በመሬት ስበት ምክንያት የሚኖረው ኃይል ነው፡፡ ሰንጠረዥ 2.1 የመጠነ ቁስ መለኪያ አሐዶች ዝምድናቸው 1ኪ.ግ 1000 ግ 1ግ 1000 ሚ.ግ 1ቶን 1000ኪ.ግ 1ኩንታል 100ኪ.ግ ክብደትና መጠነ ቁስ የተለያዩ ናቸው፡፡ መጠነ ቁስ ማለት አንድ አካል በውስጡ የያዘው የቁስ መጠን ሲሆን ክብደት ማለት ደግሞ መሬት አንድን አካል ወደራሷ የምትስብበት ኃይል ማለት ነው፡፡ ምሳሌ 1. 2ኪ.ግ ወደ ግራም ቀይሩ፡፡ መፍትሔ 1ኪ.ግ = 1000ግ 1ኪ.ግ = ? 1ኪ.ግ x ? = 2 ኪ.ግ x 1000 ግ 2ኪ.ግ x 1000ግ = 2000ግ 1 ኪ.ግ = 2000ግ ሁለት ኪሎ ግራም 2000 ይሆናል። 2. 1000ኪ.ግ ስንት ኩንታል ነው? 1ኩንታል= 100 ኪ.ግ ? = 1000 ኪ.ግ 1 ኩንታል X 1000 ኪ.ግ = 100 ኪ.ግ x ? 100 ኪ.ግ 100 ኪ.ግ x=10 ኩንታል 10 ኩንታል 1000 ኪ.ግ ይሆናል 31 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ መልመጃ 2.3 1. የአበበ ክብደት 30ኪ.ግ ከሆነ ፣ በግራም ስንት ይሆናል? 2. ከዚህ በታች የተቀመጡትን ስዕሎች በመመልከት ካነበባችሁ በኋላ መጠኑን ጻፉ፡፡ ----------ግ ----------ግ ---------ግ 3. ሀ. 10ግ =----------ሚ.ግ ለ. 2ኪ.ግ= -----------ሚ.ግ 2.3.2 ርዝመትን መለካት ተግባር 2.4 በቡድን የሚከናወን ተግባር ዓላማ፡- የተለያዩ አሐዶች የሚገልፁ ልኬቶችን መለየት፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቁሶች ርዝመታቸውን ለክታችሁ በደብተራችሁ ላይ መዝግቡ ቁስ ልኬት በ(ሴ.ሜ) በ(ሜ) የክፍላችሁ ርዝመት የአካባቢ ሳይንስ መጽሐፋችሁ ርዝመት የቁመታችሁ ርዝመት ርዝመት በሁለት ቦታ መካከል ያለውን ርቀት ነው፡፡ ዓለም አቀፍ የርዝመት መለኪያ አሐድ ሜትር ነው፡፡ ሌሎችም ሴንቲሜትር፣ ኪሎሜትር፣ ሚሊሜትር የመሳሰሉት የርዝመት አሐዶች አሉ፡፡ 32 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ሰንጠረዥ 2.2 የተለያዩ የርዝመት መለኪያ አሐዶች ዝምድናቸው 1ኪ.ሜ 1000ሜ 1ሜ 100 ሳ.ሜ 1ሜ 1000ሚ.ሜ 1ሜ 10 ዴ.ሜ 1 ዴ.ሜ 10 ሳ.ሜ 1ዴ.ሜ 100 ሚ.ሜ 1ሴ.ሜ 10 ሚ.ሜ ምሳሌ 1. 1000ሜ ስንት ኪ.ሜ ይሆናል መፍትሔ 1ኪ.ሜ =1000ሜ ? = 1000ሜ 1ኪ.ሜX1000ሜ = 1ኪ.ሜ 1000ሜ 2. 2ሜ ወደ ሴ.ሜ ቀይሩ መፍትሔ 1ሜ = 100ሴ.ሜ 2ሜ = ? 2ሜX100ሴ.ሜ = 200 ሴ.ሜ 1ሜ መልመጃ 2.4 1. በሁለት ቤቶች መካከል ያለው ርቀት 200 ሜትር ነው፡፡ ይሕ ርቀት ወደ ሴ.ሜ እና ሚሊሜትር ሲቀየር፤ ሀ. ----------ሴ.ሜ ለ. ------------ሚ.ሚ 2. ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ወደ ሚሊ ሜትር ቀይሩ ሀ. 0.002ኪ.ሜ ለ. 0.01ሜ 3. ሀ. 20ሜ + 100ሴ.ሜ = ------------ ሜ ለ. 2000ሜ +1,000,000ሚ.ሜ=----------ኪ.ሜ 33 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ስፋት የአንድ ገጽ ስፋት ማለት በተወሰኑ መስመሮች የተከበበ ቦታ ነው፡፡ የስፋት መለኪያ ዓለም አቀፋዊ አሐድ ካሬሜትር(ሜ2) ሲሆን ሌሎች አሐዶች ደግሞ ካሬ ኪሎሜትር፣ ካሬ ሴንትሜትር፣ ካሬ ሚሊ ሜትር እና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡ ስፋት = ርዝመት X ወርድ 2.3.3 ይዘትን መለካት የማነቃቂያ ጥያቄ ይዘት ምንድነው? የይዘት መለኪያ አሐዶች ዘርዝሩ፡፡ ይዘት በአንድ ቁስ አካል የተያዘ ቦታ ነው፡፡ የተለያዩ ቁስ አካሎች የተለያየ ቦታን ይይዛሉ፡፡ የይዘት ዓለምዓቀፋዊ አሐድ ኪዩቢክ ሜትር (ሜ3) ነው፡፡ ሌሎች የይዘት መለኪያዎች ኪዩቢክ ዴሲ ሜትር፣ ኪዩቢክ ሴንት ሜትር፣ ኪዩቢክ ሚሊ ሜትር እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ከዚህ በታች የተገለፀውን ሰንጠረዥ የይዘት አሐድ ዝምድና በመጠቀም አንዱን የይዘት አሀድ ወደ ሌለኛው የይዘት አሐድ መቀየር ይቻላል፡፡ ሰንጠረዥ 2.3 የይዘት የተማከሉና ያልተማከሉ አሐዶች ዝምድና 1 ሜ3 1,000,000 ሴ.ሜ3 1 ዴ.ሜ3 1,000 ሴ.ሜ3 1 ሴ.ሜ3 1,000 ሚ.ሜ3 ምሳሌ 1. 0.05 ኪዩቢክ ሜትር ውስጥ ስንት ኪዩቢክ ሴንቲ ሜትር ይገኛል? የተሰጠ ተፈላጊ ይዘት = 0.05ሜ3 ይዘት በሳ.ሜ3 = ? መፍትሔ 1ሜ3 = 1,000,000ሳ.ሜ3 0.05 ሜ3 = ? ይዘት በሳ.ሜ = 0.05ሜ X 1,000,000ሳ.ሜ 3 3 1ሳሜ3 ይዘት = 50,000ሳ.ሜ3 34 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ቁስ አካል በጠጣር፣ በፈሳሽ እና በጋዝ ሁኔታ ሊገኝ ይችላል፡፡ ጥጥር ቁሶች ደንባዊ ወይም ኢ-ደንባዊ ቅርጽ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ጠጣር የራሱ የሆነ ቅርጽ ሲኖረው ፈሳሽ እና ጋዝ ግን የራሳቸው የሆነ ቅርጽ የላቸውም፡፡ ፈሳሽ የመያዣውን እቃ ቅርጽ ይይዛል፡፡ ስለዚህ የጠጣር፣ የፈሳሽ እና የጋዝ ይዘትን ለመለካት የተለያዩ ዘዴዎችን እንጠቀማለን፡፡ ደንባዊ ቅርጽ ያላቸውን ጠጣሮች ይዘት መለካት ጠጣር የራሳቸው ቅርጽ እና ይዘት አላቸው፡፡ የነዚህ ጠጣሮች ቅርጽ ደንባዊና ኢ-ደንባዊ ሊሆን ይችላል፡፡ ሰንጠረዥ 2.4 የደንባዊ ቅርጽ ይዘት መገኛ ቀመሮች ደንባዊ ቅርጽ የይዘት ቀመር ሥዕል ሬክታንጉላር ብሎክ ይዘት= ር X ወ X ቁ ኪዩብ ይዘት = ርXር X ር = ር3 ር (ምክንያቱም የኪዩብ ቁ ር=ወ=ቁ) ወ ር ቁ ር= ርዝመት ወ = ወርድ ቁ = ቁመት 35 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ምሳሌ 1. የአንድ ሳጥን ርዝመት 3ሴ.ሜ፣ ወርዱ 2ሴ.ሜ እና ቁመቱ 5ሴ.ሜ ቢኖረው ይዘቱ ስንት ነው የተሰጠ ተፈላጊ 5ሴ.ሜ ር =3ሴ.ሜ ይዘት=? ወ=2ሴ.ሜ ቁ=5ሴ.ሜ 3ሴ.ሜ 2ሴ.ሜ መፍትሔ ይዘት= ር X ወ X =2ሰ.ሜ X 3ሴ.ሜ X 5ሴ.ሜ = 30 ሴ.ሜ3 መልመጃ 2.4 1. ከዚህ በታች ያለውን ሰንጠረዥ በትክክል ሙሉ ሥዕል ርዝመት ወርድ ቁመት ስፋት ይዘት (ሴ.ሜ) (ሴ.ሜ) (ሴ.ሜ) (ሴ ሜ2) (ሴ.ሜ3) 5 4 2 3 3 3 የፈሳሽን ይዘት መለካት ፈሳሽ ነገሮች የራሳቸው ቅርጽ የላቸውም፡፡ ነገር ግን የመያዣውን ዕቃ ቅርጽ ይይዛሉ፡፡ ይሁን እንጂ የተወሰነ ይዘት አላቸው፡፡ የፈሳሽ ይዘት መስፈሪያ ሲሊንደር ሲሆን የፈሳሽ ዓለምዓቀፋዊ አሐድ ሊትር ይባላል፡፡ በተጨማሪ ሚሊ ሊትር፣ ኪዩቢክ ሜትር፣ ኪዩቢክ ሴንትሜትር እና የመሳሰሉት አሉ፡፡ 1ሜ3 = 1000ሊ 1ሊ = 1000ሚ.ሊ 1ሚ.ሊ = 1ሴ.ሜ3 36 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ መልመጃ 2.6 1. ሀ. 2 ሊትር =____________ሚ.ሊ ለ. 1ሜ3 = ______________ሚ.ሊ ከዚህ በታች ያለውን ሲሊንደር አይታችሁ የፈሳሽ ይዘቱ ልኬት አንብባችሁ ጻፉ፡፡ 1. ---------ሚ.ሊ 2. --------ሚ.ሊ 3. ------ሚ.ሊ 4. ------ሚ.ሊ 3.3.4 ጊዜን መለካት የማነቃቂያ ጥያቄ ሰዓት ከመሰራቱ በፊት ሰዎች ጊዜን እንዴት ይለኩ ነበር? ጊዜን ለመለካት የሚረዱ አሐዶችን ጥቀሱ፡፡ ተግባር 2.5 ዓላማ ፡- ጊዜን መለካት ከትምህርት ቤት እስከ ቤታችሁ ድረስ ምን ያህል ደቂቃ እንደሚወስድ ተናገሩ፡፡ በቀን ውስጥ ለምን ለምን ተግባራት ምን ያህል ጊዜ እንደምትጠቀሙ ተናገሩ፡፡ ጊዜ በአንድ ክስተት መጀመሪያና መጨረሻ መካከል ያለው ቆይታ ሲሆን በአንድ አቅጣጫ የሚጓዝ ያለፈውን፣ የአሁኑንና የወደፊቱን ሁኔታ የሚያሳይ የተፈጥሮ ክስተት ነው፡፡ ጊዜ ዛሬ፣ አሁን፣ በኋላ፣ ነገ፣ ከነገ ወዲያ በማለት የሚገለጽ ነው፡፡ 37 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ዓለም አቀፍ የጊዜ መለኪያ አሐድ ሴኮንድ ነው፡፡ ከሴኮንድ በተጨማሪ ሌሎች የጊዜ መለኪያዎች ደቂቃ፣ ሰዓት፣ ቀን፣ ሳምንት፣ ወር፣ ዓመት እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ሥዕል 2.8 የተለያዩ የጊዜ መስፈሪያ መሳሪያዎች የጊዜ መለኪያዎች ዝምድናቸው፡፡1ደቂቃ = 60 ሴኮንድ 1ሰዓት = 60 ደቂቃ 1ቀን = 24 ሰዓት 1 ሳምንት = 7 ቀናት 1 ወር = 4 ሳምንታት 1 ወር =30 ቀናት 1ዓመት = 12 ወራት/ (ጳጉሜን ጨምሮ 13 ወራት) 1ዓመት = 365 ¼ ቀናት ምሳሌ 1. 2ሰዓት ወደ ደቂቃ ቀይሩ መፍትሔ 1ሰዓት = 60ደቂቃ 2ሰዓት =? 2ሰዓትX60ደቂቃ/1ሰዓት = 120 ደቂቃ 38 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ መልመጃ 2.7 1. በሰንጠረዡ የተቀመጠውን ሰዓት አንብባችሁ ከመዘገባችሁ በኋላ ወደ ደቂቃና ሴኮንድ ቀይራችሁ ጻፉ፡፡ የጊዜ መለኪያ ሰዓት ደቂቃ ሴኮንድ 2. አንድ ዓመት =________ ወራት=________ ሳምንታት=_________ቀናት 2.3.5 መጠነ-ሙቀትን መለካት የማነቃቂያ ጥያቄ ሰዎች መጠነ-ሙቀታቸውን እንዴት ማወቅ ይችላሉ? ሰዎች በአካባቢያችሁ መጠነ ሙቀትን ለመለካት የሚጠቀሙት ዘዴ ምንድ ነው? መጠነ ሙቀትን እንዴት መለካት ይቻላል? 39 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ሙከራ 2.2 የቡድን ሥራ ሦስት የሻይ ኩባያዎችን አዘጋጁ፤ በመጀመሪያ ውስጥ የሞቀ ውሃ፣ በሁለተኛ ውስጥ ለብ ያለ ውሃ እና በሦስተኛ ውስጥ ደግሞ ቀዝቃዛ ውሃ ጨምሩ፡፡ የተግባር ቅደም ተከተል 1. የቀኝ እጅ ጣታቸሁን ሙቅ ውሃ የያዘ ኩባያ ውስጥ ጨምሩ፣ የግራ እጅ ጣታችሁን ደግሞ ቀዝቃዛ ውሃ የያዘ ኩባያ ውስጥ ጨምሩ 2. ጣቶቻችሁን ከሁለቱም ኩባያዎች አውጡ፡፡ 3. በፍጥነት ሁለቱንም ጣቶቻችሁን ለብ ያለ ውሀ ውስጥ ክተቱ፡ በሁለቱም ጣቶቻችሁ ምን እንደተሰማችሁ ተናገሩ፡፡ 4. በመጠነ ሙቀትና በግለት መካካል ያለውን ልዩነት ግለጹ፡፡ መጠነ ሙቀት የነገሮች የሙቀት ወይም ቅዝቃዜ ልኬት ነው ወይም በሞለኪውሎች አማካኝ የእንቅስቃሴ ጉልበት ልኬት ነው፡፡ መጠነ ሙቀትን ለመለካት የምንጠቀመው መሳሪያ ቴርሞሜትር ይባላል፡፡ የመጠነ ሙቀት አለምዓቀፍ መለኪያ አሐድ ኬልቪን በመባል ይታወቃል፡፡ ሌሎች ድግሪ ሴልሽየስ እና ዲግሪ ፋራናይት አሉ፡፡ ግለት ከአንድ አካል ወደ ሌላ አካል በመጠነ ሙቀት ልዩነት ምክንያት የሚተላለፍ የጉልበት ዓይነት ነው፡፡ ይሄውም የግለት ጉልበት ሁለቱም አካላት እኩል መጠነ ሙቀት ላይ እስከሚደርሱ ድረስ ከፍተኛ መጠነ ሙቀት ካለው አካል ወደ ዝቅተኛ መጠነ ሙቀት ያለው የሚተላለፊ ነው፡፡ ሥዕል2. 9 የመጠን ሙቀት መለኪያ መሣሪያ (ቴርሞ ሜትር) 40 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ መልመጃ 2.8 ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ልኬቶች በአጭሩ ገልጻችሁ አለምዓቀፍ መለኪያ አሐዶችንም ጻፉ፡፡ ልኬት ገለጻ አለምዓቀፍ መለኪያ አሐድ መጠነ- ቁስ ጊዜ መጠነ- ሙቀት 2.4 የጉልበት ምንነት የንዑስ ርዕሱ አጥጋቢ የመማር ብቃት፡- ተማሪዎች ይህን ክፍለ ትምህርት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡- ለእንቅስቃሴና ለውጥ ለማምጣት አስፈላጊ የጉልበት ምንጮችን (ምግብ፣ ነዳጅ፣ የፀሐይብርሃን) ትገልጻላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት ጉልበት ምንጭ የማነቃቂያ ጥያቄ ጉልበት ምንድን ነው? ሰዎች ሥራ ለመሥራት፣ ለመንቀሳቀስ እና ለመሳሰሉት ሥራ ጉልበት ከየት ያገኛሉ? ጉልበት ስራን የመስራት አቅም ወይም ችሎታ ነው፡፡ ያለጉልበት ምንም ነገር መስራት አይቻልም፡፡ ለምሳሌ መመገብ፣ መታጠብ፣ ምግብ ማብሰል፣ ደብተር መሸከም፣ መሮጥ ፣ መነሳት፣ መውጣት፣ መውረድና የመሳሰሉትን ለማከናወን 41 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ጉልበት ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም መኪናዎች፣ አውሮፕላኖች፣ ፋብሪካዎች፣ ማሽኖችና ሌሎች በነዳጅ፣ በኤሌክትሪክ ወይም በሌላ ዘዴ የሚሰሩ ነገሮች በሙሉ ጉልበት ያስፈልጋቸዋል፡፡የጉልበት መለኪያ አሀድ ጁል ይባላል። ጉልበት ሥዕል 2.9 በጉልበት አማካይነት የሚከናወኑ የተለያዩ ተግባራት 2.4.1 የጉልበት ምንጮች የጉልበት ምንጮች ጉልበትን በተለያየ መልኩ በውስጣቸው ይዘው የሚገኙ አካላት ወይም ሥርዓቶች ናቸው፡፡ ጉልበት ከተለያዩ ምንጮች በተለያየ ሁኔታ ይገኛል፡፡ ጉልበት የሚሰጡ ነገሮች የጉልበት ምንጮች ይባላሉ፡፡ የጉልበት ምንጮች የምግብ ጉልበት የነዳጅ ጉልበት የፀሐይ ጉልበት የውሃ ጉልበት የነፋስ ጉልበት የድንጋይ ከሰል እንጨት የከርሰ-ምድር እንፋሎት እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ የምግብ ጉልበት፡- ማንኛውም ሰው ጉልበት የሚያገኘው ከሚመገበው ምግብ ነው:: በምግብ ውስጥ የሚገኘው ጉልበት በካሎሪ ይለካል፡፡ 42 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ የነዳጅ ጉልበት፡- የተፈጥሮ ነዳጅ የሚባሉት የተፈጥሮ ዘይት፣ ቤንዚን፣ ናፍጣ፣ ነጭ ጋዝ፣ የተፈጥሮ ጋዝና የድንጋይ ከሰል ናቸው፡፡ እነዚህ የተፈጥሮ ነዳጆች ለመኪናዎች፣ ለባቡሮች፣ ለአውሮፕላኖች፣ ለመርከቦችና ለፋብሪካዎች ማንቀሳቀሻ የሚያስፈልገውን የሙቀት ጉልበት ያስገኛሉ፡፡ የፀሐይ ብርሃን ጉልበት፡- ፀሐይ ዋና የምድራችን የጉልበት ምንጭ ናት፡፡ የፀሐይ ብርሃን በነፃ የሚገኝ የጉልበት ምንጭ ነው፡፡ ለምሳሌ፦ ልብስን ለማድረቅ፣ ወደ ሙቀት ጉልበት በመቀየር ምግብን ለማብሰል፣ እፅዋቶች ምግባቸውን ለማዘጋጀት ወደ ኤሌክትሪክ ጉልበት በመቀየር ለተለያዩ ነገሮች መጠቀም ይቻላል፡፡ የንፋስ ጉልበት፡- የንፋስ ጉልበት የተለያዩ ጥቅሞችን ይሰጣል፡፡ ለምሳሌ ውሃን ከጉድጓድ ለማውጣትና ከወንዝ ለመሳብ፣ በንፋስ ወፍጮዎች፣ እህል ለመፍጨት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት እና ለመሳሰሉት ጥቅም ይውላል፡፡ የውሃ ጉልበት፡- የውሃ ጉልበት በሀገራችን ለቡዙ ጥቅም ይውላል፡፡ ከነዚህም ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ፣ ለእህል መፍጫ ወፍጮ እና ለመሳሰሉት አገልግሎት ይጠቅማሉ፡፡ ተግባር 2.7 የቡድን ወይይት በቡድን ሆናችሁ የተለያዩ 1. የተለያዩ የጉልበት ምንጮችን በመዘርዘር ጥቅማቸውን ተወያይታችሁ ለመምህራችሁ ተናገሩ፡፡ መልመጃ 2.9 1. ከዚህ በታች የተዘሩትን የጉልበት ምንጮች የሚሰጡት የጉልበት ዓይነቶች በባዶ ቦታ ላይ ጻፉ ሀ. የፀሐይ ጉልበት:- _________________________________ _________________________________ __________________________________ 43 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ለ. ምግብ፡- __________________________________ ___________________________________ ሐ. ነፋስ፡- ___________________________________ ___________________________________ ___________________________________ መ. ነዳጅ፡- ___________________________________ ___________________________________ ___________________________________ ___________________________________ 2.5 ድምፅ የንዑስ ርዕሱ የመማር ውጤቶች፡- ተማሪዎች ይህን ክፍለ ትምህርት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡- ¾ የድምጽ ምንነትን በመግለጽ ድምጽ የሚተላለፍባቸውን ቁሶች ትገልጻላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት ወና (vacuum) ፈሳሽ ድምጽ ጋዝ ጠጣር የማነቃቂያ ጥያቄ 1. ድምፅ ምንድን ነው? 2. ድምፅ እንዴት ይፈጠራል? 2.5.1 የድምፅ ምንነት ድምፅ በነገሮች እርግብግቢት ምክንያት የሚፈጠር ሞገድ ነው፡፡ የማንኛውም የድምፅ ምንጭ የነገሮች መርገብገብ ነው፡፡ አንድ ነገር በሚርገበገብበት ጊዜ የሚፈጠረው እርግብግቢት ወደ ጆሮ ሲተላለፍ ድምፅ ሆኖ ይሰማል፡፡ ለድምጽ መኖር አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ሦስት ናቸው፡፡ እነርሱም የድምጽ ምንጭ፣ ድምጽ አስተላላፊ እና ድምጽ ተቀባይ ናቸው፡፡ 44 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ሥዕል 2.10 የድምጽ አፈጣጠር የድምፅ አይነቶች በአካባቢያችን የተለያየ ድምጽ የሚሰጡ ነገሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ የክራር ድምጽ፣ የከበሮ ድምጽ፣ የማሲንቆ ድምጽ፣ የሰው ድምጽ፣ በተለያዩ እንስሳት የሚፈጠር ድምጽ እና የመሳሰሉት የድምጽ ዓይነቶች ናቸው፡፡ የድምጽ መተላለፍ ድምፅ ከምንጩ ተነስቶ ተቀባይ ዘንድ እስኪደርስ ድረስ ለመተላለፍ የተለያዩ ቁሳቁሶች ያስፈልጉታል፡፡ ድምፅ በጠጣር፣ በፈሳሽና በአየር ውስጥ ይተላለፋል፡፡ ድምፅ በወና (vacuum) ውስጥ አይተላለፍም ምክንያቱም ድምጽ ከአንድ ቦታ ወደ ወደ ሌላ ቦታ ለመተላለፍ መተላለፊያ ቁስ ያስፈልገዋል፡፡ ወና (vacuum) ማለት ደግሞ ምንም አይነት ቁስ ወይም አየር የሌለው ስለሆነ ድምጽ በውስጡ መተላለፍ አይችልም፡፡ ነገሮች የተሰሩት ከትናንሽ ቅንጣቶች ስለሆኑ በጠጣር ውስጥ ያሉ ቅንጣቶች እጅግ በጣም የተጠጋጉ ስለሆኑ ድምጽን በከፍተኛ ፍጥነት በውስጡ የማስተላለፍ አቅም አላቸው፡፡ በፈሳሽ ውስጥ ያሉ ቅንጣቶች ግን በመጠኑ የተራራቁ በመሆናቸው ድምጽን የማስተላለፍ አቅማቸው ከጠጣር ነገሮች ያነሰ ነው፡፡ በጋዝ ውስጥ የሚገኙ ቅንጣቶች ግን በጣም የተራራቁ ስለሆኑ ድምጽ የማስተላለፍ አቅማቸው ከጠጣር እና ከፈሳሽ በጣም አነስተኛ ነው፡፡ በተጨማሪ በነገሮች ውስጥ የሚገኙ የቅንጣቶችን አቀማመጥ ከዚህ በታች ካለው ሥዕል ተመልከቱ፡፡ 45 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ሥዕል2.11 በጠጣር ፣ በፈሳሽ እና በጋዝ ውስጥ ያሉ የቅንጣቶች አቀማመጥ ሙከራ 2.3 ዓላማ፡- ድምፅ በጠጣር ነገሮች ውስጥ እንደሚተላለፍ ማረጋገጥ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች፡- ረጅም ክር፣ የክብሪት ቀፎ የአሰራር ቅደም ተከተል፡- 1. ረጅመም ክር አዘጋጁ 2. የክሩን ሁለቱ ጫፎች በክብሪት መያዣ በስታችሁ አሰገቡ፡፡ 3. ሁለት ተማሪዎች ክሩ እስከሚችልበት ርቀት ድረስ በመወጠር ይያዙት:: 4. አንዱ ተማሪ የክብሪቱ መያዣ በጆሮው ላይ ያድርግ፣ ሁለተኛው ተማሪ ደግሞ አንዱን ጫፍ በአፉ ላይ አድርጎ ይናገር፡፡ 5. ከሙከራ የተገነዘባችሁትን ለመምህራችሁ ተናገሩ፡፡ በተጨማሪ ሥዕል 2.12 ተመልከቱ 46 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ድምጽ በጠጣር ውስጥ ሲተላለፍ ድምጽ በአየር ውስጥ ሲተላለፍ ድምጽ በፈሳሽ ውስጥ ሲተላለፍ ሥዕል፡- 2.12 ድምፅ በጠጣር፣ በፈሳሽና በአየር ውስጥ ሲተላለፍ መልመጃ 2.10 ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ምረጡ፡፡ 1. ከሚከተሉት ውስጥ ድምጽን በከፍተኛ ፍጥነት ማስተላለፍ የሚችለው የትኛው ቁስ ነው? ሀ. ውሃ ለ. ብረት ሐ. አየር መ. ወና 2. ድምጽ የሚፈጠረው በነገሮች እርግብግቢት ብቻ ነው፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሐሰት ለሚከተሉት ጥያቄ አጭር መልስ ስጡ፡፡ 1. ከአንድ በውሃ ውስጥ ከምትንቀሳቀስ መርከብ በእኩል ርቀት ላይ አንዱ በውሃ ውስጥ ሌላኛው በየብስ ላይ ለሚገኙ ሰዎች የመርከቧ ድምጽ ቀድሞ የሚሳማው ለየትኛው ነው? ለምን? 2. ለድምጽ መኖር አስፈላጊ ነገሮችን ጥቀሱ፡፡ 47 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ የምዕራፉ ማጠቃለያ ስርዓተ ልመት ማለት ምግብን በምግብ መተላለፊያ ቱቦ አማካኝነት የሚፈጭበት(የሚልምበት) ሂደት ነው፡፡ አፍ፣ጉሮሮ፣ጨጓራ፣.ትንሹ አንጀት፣ ትልቁ አንጀት፣ ሬብና ፊንጢጣ በስርዐተ ልመት ውስጥ ዋና ዋና የምግብ መተላለፊያ ቱቦ በመባል ይታወቃሉ፡፡ አልሚ ምግቦች በምግብ የመፈጨት ሂደት ከላሙ በኋላ በደም ስሮች አማካኝነት ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍል ይሰራጫሉ፡፡ ማንኛውም ቦታ የሚይዝና መጠነ-ቁስ(mass) ያለው ነገር ሁሉ ቁስ አካል በመባል ይታወቃል፡፡ ልዩ ቁስ (substance) ማለት አንድ ዓይነት ወይም ድብልቅ ምንዝሮች የያዘ ነገር ማለት ነው፡፡ ድብልቅ ያልሆኑ ልዩ ቁሶች ከአንድ አይነት ንጥረ ነገር ብቻ ወይም ሁለትና ከሁለት በላይ የሆኑ ንጥረ ነገሮች በሚያካሂዱት ኬሚካዊ ለውጥ የሚፈጠሩ ልዩ ቁሶች ናቸው:: ውህድ ሁለትና ከሁለት በላይ ከሆኑ ንጥረ ነገሮች በኬሚካዊ መስተጋብር የሚፈጠር ልዩ ቁስ ነው፡፡ መጠነ ቁስ ማለት አንድ አካል በውስጡ የያዘው የቁስ መጠን ማለት ነው፡፡ ርዝመት በሁለት ቦታ መካከል ያለውን ርቀት ያመለክታል፡፡ ይዘት ባንድ ቁስ አካል የተያዘ ቦታ ነው፡፡ ጊዜ በአንድ ክስተት መጀመሪያና መጨረሻ መካከል ያለው ቆይታ ነው፡፡ የጉልበት ምንጮች ጉልበትን በተለያየ መልኩ በውስጣቸው ይዘው የሚገኙ አካላት ወይም ሥርዓቶች ናቸው፡፡ ድምፅ ማለት በአየር፣ በፈሳሽና በጠጣር ነገር ውስጥ የሚጓዝ የአየር ጫና ማለት ነው፡፡ 48 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ የምዕራፉ ማጠቃለያ ጥያቄዎች I. የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል የሆነውን እውነት ትክክል ያልሆነውን ደግሞ ሐሰት በማለት መልሱ፡፡ 1. ሙቀት የጉልበት ዓይነት ነው፡፡ 2. ውህድ ሁለትና ከሁለት በላይ ከሆኑ ንጥረ ነገሮች በፊዚካዊ ለውጥ የሚፈጠር ልዩ ቁስ ነው፡፡ 3. ጨዎች አሲዶችና ቤዞች ሲፀገበሩ የሚፈጠሩ ውህዶች ናቸው፡፡ 4. ድምፅ ከፈሳሽና ከጠጣር በአየር ውስጥ በፍጥነት ያልፋል፡፡ 5. የገበታ ጨውና ሶድየም ሃይድሮክሳይድ ንጥረ ነገሮች ናቸው፡፡ 6. ዓለምአቀፋዊ አሐዶች ከባህላዊ አሐዶች ይለያሉ፡፡ 7. ውሃ ለኃይል ምንጭነት አያገለግልም፡፡ 8. የእለት ተለት ተግባራችንን ለመስራት ግዴታ ጉልበት ያስፈልጋል፡፡ II. በ “ሀ” ስር የተዘረዘሩትን የምግብ መተላለፊያ ቱቦዎች በ”ለ” ስር ከተሰጡት ተግባሮቻቸው ጋር አዛምዱ፡፡ “ሀ” “ለ” 1. ትንሹ አንጀት ሀ. ያልተፈጨ ምግብ ይጠራቀምበታል 2. አፍ ለ. የስርዐተ ልመት የማይካሄድበት ቦታ 3. ሬብ ሐ. የምግብ ልመት ሂደት የሚጠናቀቅበት ቦታ 4. ትልቁ አንጀት መ. ጀርሞችን ለመግደል የሚያስችል አሲድ ይዟል 5. ጨጓራ ሠ. የመጀመሪያው የምግብ መተላለፊያ ቱቦ አካል ነው III. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ከተሰጡት አማራጮች መካከል ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ሆሄ በመምረጥ በተሰጠው ክፍት ቦታ ጻፉ፡፡ 1. ከሚከተሉት መለኪያዎች ውሰጥ ከ4 ሜ ጋር እኩል የሆነው የቱ ነው? ሀ. 4,000 ሴ.ሜ ለ. 0.004 ከ.ሜ ሐ. 40 ኪ.ሜ መ. 0.4ኪ.ሜ 2. ከሚከተሉት የምግብ ቱቦዎች ውስጥ የውሃ ስርገት የሚካሄደው በየትኛው ነው? ሀ. ጨጓራ ለ. ትልቁ አንጀት ሐ. ትንሹ አንጀት መ. ሬብ 49 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ 3. ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ውስጥ ዓለም አቀፍ የጊዜ መለኪያ የቱ ነው? ሀ. ሰዓት ለ. ደቂቃ ሐ. ሴኮንድ መ. ቀን 4. መጠነ ቁስን ለመለካት የሚያስፈልገው የቱ ነው? ሀ. ሰዓት ለ. ሚዛን ሐ. ሜትር መ. ሴኮንድ 5. ከሚከተሉት ወስጥ በጨጓራ ውስጥ የሚገኘው አሲድ የቱ ነው ? ሀ. ሳልፈሪክ አሲድ ሐ. ናይትሪክ አሲድ ለ. ሃይድሮክሎሪክ አሲድ መ. ካርቦንክ አሲድ 6. 2 ሰዓት ከ30 ደቂቃ እኩል ይሆናል --------- ሀ. 9,000 ሴኮንድ ሐ. 90,000 ሴኮንድ ለ.4,500 ሴኮንድ መ. 7,200 ሴኮንድ 7. ከሚከተሉት አንዱ የጉልበት ምንጭ አይደለም፡፡ ሀ. ውሃ ለ. ምግብ ሐ. ነዳጅ መ. ኤሌክትሪክ 8. ከሚከተሉት ቁሶች ውስጥ ድምፅ በፍጥነት የሚያልፈው በየትኛው ነው? ሀ. በጠጣር ለ. በፈሳሽ ሐ. በጋዝ መ. በሁሉም IV. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን ቃል ወይም ሐረግ በመሙላት በተሰጡት ክፍት ቦታዎች ውስጥ መልሱ፡፡ 1. የላመ የምግብ ንጥረ ነገር በደም ስሮች አማካኝነት የመመጠጥ ሂደት ------------------------- ይባላል፡፡ 2. ማንኛውም ቦታ የሚይዝና መጠነ-ቁስ(mass) ያለው ነገር ሁሉ________ ይባላል፡፡ 3. ምግብ በምግብ መፍጫ አካላት አማካኝነት ወደ ትናንሽ የምግብ ንጥረ ነገሮች የመቀየር ሂደት ---------------------------ይባላል፡፡ 50 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ V. ለሚከተሉትን ጥያቄዎች ተገቢውን መልስ ስጡ፡፡ 1. የትንሹን አንጀትና የትልቁን አንጀት ተግባር ግለጹ፡፡ 2. የጉልበት ምንጮችን ዘርዝሩ፡፡ ሀ.___________________________ ለ.___________________________ ሐ.__________________________ መ.__________________________ 3. የተለመዱ አሲዶችን ምሳሌዎች ጥቀሱ፡፡ ሀ. __________________________ ለ. __________________________ ሐ. _________________________ መ. _________________________ ከዚህ በታች የተሰጡትን የሥርዓተ ልመት አካላት በተሰጠው ክፍት ቦታ ስማቸውን ጻፉ፡፡ 51 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሁለት ሳይንስን መገንዘብ ፍተሻ ልታከናውኗቸው የምትችሏቸውን ተግባራት ለመግለጽ ይህን () ምልክት በሳጥኖቹ ውስጥ በማኖር አመልክቱ፡፡ 1. ዋና ዋና የሥርዐተ ልመት አካላትንና ተግባራት እገልጻለሁ፡፡ 2. የሥርዓተ ልመት አካላት ጠቀሜታ እገልጻለሁ፡፡ 3. የቁስ አካልን ምንነት እገልጻለሁ፡፡ 4. ድብልቅ ያልሆኑ ልዩ ቁሶችን ምንነት እገልጻለሁ፡፡ 5. ድብልቅ ያልሆኑ ልዩ ቁሶችን ምሳሌዎች እዘረዝራለሁ፡፡ 6. የውህድን ምንነት እገልጻለሁ፡፡ 7. የኦክሳይዶችን፣ አሲዶችን፣ ቤዞችን እና ጨዎችን ምንነት እገልጻለሁ፡፡ 8. የተለመዱ ኦክሳይዶችን፣ አሲዶችን፣ ቤዞችን እና ጨዎችን ምሳሌዎች እጠቅሳለሁ፡፡ 9. መጠነ ቁስን፣ ርዝመትን፣ ይዘትን ጊዜን እና የመሳሰሉትን እለካለሁ፡፡ 10. ለእንቅስቃሴና ለውጥ ለማምጣት አስፈላጊ የጉልበት ምንጮችን (ምግብ፣ ነዳጅ፣ የፀሐይ ብርሃን) እገልጻለሁ፡፡ 11. የድምጽን ምንነት በመግለጽ ድምጽ የሚተላለፍባቸውን ቁሶች እገልጻለሁ:: የቃላት ፍቺ ልመት-----መድቀቅ እርግብግቢት-------እንቅጥቃጤ ሬክተም-------- ያልተፈጩ የምግብ ስብስቦች ይዘት------በአንድ ነገር የተያዘ ቦታ አሐድ----- መለኪያ ውህድ----- አንድ መሆን አፀግብሮት----ኬሚካዊ ለውጥ ስርገት------- መመጠጥ 52