Grade 5 Environmental Science 3 PDF
Document Details
Uploaded by LustrousSavanna6540
Abiyot Primary School
Tags
Summary
This document is a chapter from a Grade 5 environmental science textbook focusing on Ethiopia's natural environment. It covers topics such as climate types, natural resources, and conservation efforts.
Full Transcript
Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ ምዕራፍ ሦስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ አጥጋቢ የመማር ውጤቶች ተማሪዎች ይህን ምዕራፍ ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡- በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች የሚታየውን ወቅታዊ የሙቀት መጠን ልዩነት ትገልጻላችሁ፡ የሙቀትና የዝናብ መጠንን የመለካትና መረጃን መዝግቦ የመ...
Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ ምዕራፍ ሦስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ አጥጋቢ የመማር ውጤቶች ተማሪዎች ይህን ምዕራፍ ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡- በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች የሚታየውን ወቅታዊ የሙቀት መጠን ልዩነት ትገልጻላችሁ፡ የሙቀትና የዝናብ መጠንን የመለካትና መረጃን መዝግቦ የመያዝ ክህሎት ታዳብራላችሁ፡፡ ኢትዮጵያ በሐሩር ሞቃታማ የአየር ንብረት ክልል ከሚገኙ ሀገራት የተለየ የአየር ንብረት የምታሳይበትን ምክንያቶች ትተነትናላችሁ፡፡ በኢትዮጵያ ዋና ዋና የአየር ንብረትን የሚቆጣጠሩ ነገሮችን ትለያላችሁ፡፡ የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብት ዓይነቶች ትለያላችሁ፡፡ የኢትዮጵያን የአፈር ዓይነቶችና የአፈር መሸርሸርን ትገልጻላችሁ፡፡ በኢትዮጵያ የተለመዱ የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ዘዴዎችን ትለያላችሁ፡፡ በኢትዮጵያ የሚበቅሉ የዕፅዋት ዓይነቶችን ትለያላችሁ፡፡ ውጤታማ የውሃ ሀብት አጠቃቀም ዘዴዎችን ትገልጻላችሁ፡፡ በኢትዮጵያ የውሃ ሀብት ላይ ተጽዕኖ የሚያደርሱ ሁኔታዎችን ትዘረዝራላችሁ፡፡ የኢትዮጵያ ውሃማ አካላትንና የተፋሰስ ሥርዓትን ትመረምራላችሁ፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ማዕድናትንና በአጠቃቀም ምክንያት የሚፈጠሩ አካባቢያዊ ችግሮችን ትተነትናላችሁ፡፡ በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ጉዳዮችን ትገልጻላችሁ፡፡ የኢትዮጵያን ዋና ዋና የጉልበት ምንጮችን ትዘረዝራላችሁ፡፡ የኢትዮጵያን ታዳሽና ታዳሽ ያልሆኑ የጉልበት ምንጮችን ትለያላችሁ፡፡ በኢትዮጵያ በተፈጥሮ አካባቢ ላይ የሚስተዋሉ ዋና ዋና ችግሮችን ትዘረዝራላችሁ፡፡ በኢትዮጵያ ዋና ዋና የአካባቢ ብክለት መንሥኤዎችን ማብራራትና አማራጭ መፍትሔዎችን ትሰጣላችሁ፡፡ 53 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ የምዕራፉ ይዘቶች 3.1 የኢትዮጵያ የአየር ንብረት 3.1.1. የአየር ሁኔታና የአየር ንብረት ልዩነት 3.1.2. የአየር ንብረት ይዘት 3.1.3. የአየር ንብረት ክልሎች 3.1.4.የኢትዮጵያ ዋና ዋና የአየር ንብረት ዓይነቶች 3.1.5. የአየር ንብረት ተቆጣጣሪዎች 3.2 የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቶች 3.2.1. የተፈጥሮ ሀብት ዓይነቶች 3.2.2. የአፈር ዓይነቶች 3.2.3 የዕፅዋት ዓይነቶች 3.2.4 የተፈጥሮ ሀብት አጠባበቅ ዘዴዎች 3.2.5 ውጤታማ የውሃ ሃብት አጠቃቀም 3.2.6. የሐይቅ ዓይነቶችና ባሕርያት 3.2.7 ዋና ዋና የውሃ ተፋሰስ ሥርዓት 3.2.8 የማዕድን ሀብቶች 3.2.9 የዱር ሃብቶች 3.2.10 የጉልበት ምንጭ ዓይነቶች እና ባህርያት 3.2.11 ዋና ዋና ከባቢያዊ ችግሮች 3.2.12 የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምና ጥበቃ 54 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ መግቢያ አካባቢ ሲባል በተወሰነ ቦታ የሚገኙ ህይወት ያላቸውና ህይወት የሌላቸው ነገሮች ጥምር ነው፡፡አካባቢ ሲባል ፊዚካላዊና ስነ-ሕይወታዊ እንዲሁም ማህበራዊና ባህላዊ ሁኔታዎችን ያካትታል፡፡በአራተኛ ክፍል የአካባቢ ሣይንስ ምዕራፍ ሦስት ትምህርታችሁ የከተማችሁን ሕዝቦችና ባህሎች እንዲሁም የከተማችሁን ምጣኔ ሀብታዊ እንቅስቃሴዎችን ተምራችኋል:: በዚህ ክፍል ትምህርታችሁ የኢትዮጵያን የአየር ንብረት ይዘት፣ የአየር ንብረት ከክልሎች፣ የአየር ንብረት ተቆጣጣሪዎች፣ የኢትዮጵያን የአፈር ዓይነቶች፣ የኢትዮጵያን የተለያዩ ታዳሽ እና ታዳሽ ያልሆኑየተፈጥሮ ሀብቶች፣ የኢትዮጵያን ውሃማ አካላት እና የተፋሰስ ስርዓትአጠቃቀም እና የኢትዮጵያን ዋና ዋና የጉልበት ምንጮች ትማራላችሁ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የተፈጥሮ ሃብቶች ለሰው ልጅ ህይወት እጅግ አስፈላጊ በመሆናቸው የሚያደርሱትን ተፅዕኖ እና የመንከባከቢያ ስልቶችንም ጭምር ትማራላችሁ:: 55 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ 3.1 የኢትዮጵያ የአየር ንብረት አጥጋቢ የመማር ብቃቶች ተማሪዎች ይህን ምዕራፍ ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡- ¾ በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች የሚታየውን ወቅታዊ የሙቀት መጠን ልዩነት ትገልጻላችሁ፡: ¾ የሙቀትና የዝናብ መጠንን የመለካትና መረጃን መዝግቦ የመያዝ ክህሎት ታዳብራላችሁ፡፡ ¾ ኢትዮጵያ በሐሩር ሞቃታማ የአየር ንብረት ክልል ከሚገኙ ሀገራት የተለየ የአየር ንብረት የምታሳይበትን ምክንያቶች ትተነትናላችሁ፡፡ ¾ በኢትዮጵያ ዋና ዋና የአየር ንብረትን የሚቆጣጠሩ ነገሮችን ትለያላችሁ የንዑስ ርዕሱ ይዘቶች 3.1.1.የአየር ሁኔታና የአየር ንብረት ልዩነት 3.1.2.የአየር ንብረት ይዘት 3.1.3. የአየር ንብረት ክልሎች 3.1.4.የኢትዮጵያ ዋና ዋና የአየር ንብረት ዓይነቶች 3.1.5. የአየር ንብረት ተቆጣጣሪዎች 56 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ 3.1.1.የአየር ሁኔታና የአየር ንብረት አጥጋቢ የመማር ብቃት ተማሪዎች ይህን ትምህርት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡- በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች የሚታየውን ወቅታዊ የሙቀት መጠን ልዩነት ትገልፃላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት የአየር ንብረት የአየር ሁኔታ የማነቃቂያ ጥያቄ የአየር ሁኔታ እና የአየር ንብረት ልዩነትን ግለፁ፡፡ የአየር ሁኔታ ማለት በአንድ አካባቢ የሚስተዋል የዕለቱ የአየር ሙቀት፣ ቅዝቃዜ፣ የዝናብ እና የነፋስ ሁኔታ ነው፡፡ ለምሳሌ በአንድ አካባቢ በአንድ ዕለት ቅዝቃዜ፣ ሙቀት፣ ደመና ወይም ዝናብ ሊመዘገብ ይችላል፡፡ ይህ በ24 ሰዓታት የሚለዋወጥ የአየር ሁኔታ የአየር ጠባይ ይባላል፡፡ ለምሳሌ- በአንድ አካባቢ ጠዋት ቀዝቃዛ፣ ከሰዓት ሞቃት እና ማታ ዝናብ በመዝነብ የአየር ጠባይን ሊያሳይ ይችላል፡፡ የአየር ንብረት ማለት በአንድ ቦታ የሚስተዋል ለረጅም ዘመናት የሚቆይ (ብያንስ ለ30 ዓመታት) አማካይ የአየር ጠባይ ነው፡፡ ለምሳሌ፦ በኢትዮጵያ ሰኔ፣ ሀምሌ እና ነሀሴ ለረዢም ዘመናት ከሌሎች ወቅቶች የተሻለ ዝናብ የሚመዘገብበት የክረምት ወቅት ነው፡፡ 57 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ ስዕል 3.1 የተለያዩ የአየር ሁኔታዎች ገጽታ የግል ስራ 3.1 ስዕል 3.1ን በመመልከት አጭር መልስ ስጡ፡፡ 1. ከላይ በስዕሉ ከተመላከቱት ውጪ በአካባቢያችሁ የሚስተዋሉ የአየር ጠባዮችን ጥቀሱ፡፡ 2. ነፋስና ደመና ምን ዓይነት ግንኙነት አላቸው? መልሳችሁን በአጭሩ አብራሩ፡፡ 3.1.2 የአየር ንብረት ይዘት አጥጋቢ የመማር ብቃት ተማሪዎች ይህን ትምህርት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡- ¾ የሙቀትና የዝናብ መጠንን የመለካትና መረጃን መዝግቦ የመያዝ ክህሎት ታዳብራላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት ሙቀት የአየር ግፊት 58 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ የማነቃቂያ ጥያቄ የኢትዮጵያ የአየር ንብረት ይዘት የሚባሉትን ዘርዝሯቸው፡፡ የአየር ንብረት ይዘት የሚባሉት በአንድ አካባቢ የሚስተዋሉ የአየር ንብረት የሚገለፅባቸው የተፈጥሮ ክስተቶች ናቸው፡፡እነዚህ ክስተቶች ከሀገር ሀገር ወይም ከአካባቢ አካባቢ ይለያያሉ፡፡ እነርሱም ሙቀት፣ ዝናብ፣ የአየር ግፊት፣ንፋስ እና ደመና ናቸው፡፡እነዚህን የአየር ንብረት ይዘቶች በአካባቢያችሁ በተለያዩ ጊዜያት ስለሚከሰቱ መመልከት እና ማስተዋል ትችላላችሁ፡፡ ሙቀት የአንድ ነገር የመሞቅ ወይም የመቀዝቀዝ መጠን ነው፡፡የሙቀት ምንጩ ከፀሐይ የሚገኘው የፀሐይ ሀይል ነው፡፡ በመሬት ላይ ለሚገኙ ነገሮች ሁሉ የሀይል ምንጩ ፀሐይ ነው፡፡ ዕለታዊ፣ ሳምንታዊ፣ ወርሃዊ እና ዓመታዊ አማካኝ የፀሐይ ሙቀት መጠንን መለካት እና መመዝገብ ይቻላል፡፡ የዕለቱን ከፍተኛ እና ዝቅተኛ የሙቀት መጠን በመለካት የዕለቱን አማካኝ የሙቀት መጠን መመዝገብ ይቻላል፡፡ ዕለታዊ አማካኝ የሙቀት መጠን የሚሰላው የዕለቱን ከፍተኛ እና ዝቅተኛ የሙቀት መጠን በመደመር እና ለሁለት በማካፈል ነው፡፡ ስዕል 3.2 የኢትዮጵያ ከተሞች አማካኝ ዓመታዊ የሙቀት መጠን 59 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ የግል ሥራ 3.2 ስዕል 3.2.ን በመመልከት የኢትዮጵያ ከተሞች አማካኝ ዓመታዊ የሙቀት መጠናቸው ከ250c በላይ እና በታች በመለየት በዝርዝር ፃፉ፡፡ ዝናብ የማነቃቂያ ጥያቄ ዝናብ እንደት ይፈጠራል? ዝናብ በደመና አማካኝነት የሚፈጠር እና ከሰማይ ላይ ወደ መሬት የሚወርድ እርጥበት ነው፡፡በምድር ላይ ከሚገኙ የውሃ አካላት ላይ እንዲሁም ከእፅዋት ውስጥ ውሃ በሙቀት አማካኝነት ይተናል፡፡ ይህ የተነነ ውሃ በነፋሳት አማካኝነት ከምድር በላይ ባለው ከፍታ ደመና ይፈጥራል፡፡ ደመናው ባለበት ከፍታ ክብደቱ ሲበዛ በትንሽ በትንሹ ወደ መሬት ተመልሶ ይወርዳል፡፡ይህ መሬት የሚደርሰው እርጥበት አዘል ውሃ ዝናብ ተብሎ ይጠራል፡፡ በኢትዮጵያ የዝናብ መጠንም ሆነ ስርጭት ከተለያየ የውሀ ክፍሎች በሚመነጩ ዝናብ አምጭ ነፋሳት ይወሰናል፡፡ ወርሃዊ እና ዓመታዊ አማካኝ የዝናብ መጠንን መለካትም ሆነ መመዝገብ ይቻላል፡፡ ወርሃዊ አማካኝ የዝናብ መጠን የሚሰላው የየዕለቱን የዝናብ መጠን በመደመር እና ለወሩ ቀናት ብዛት በማካፈል ነው፡፡ ሙቀት፣ዝናብ እና ከፍታ ያላቸው ግንኙነት አንድ ሺ ሜትር የከፍተኛ እና ዝቅተኛ ቦታዎች መለያ የከፍታ ልኬት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታዎች አማካይ ከፍታቸው ከባህር ጠለል በላይ አንድ ሺ ሜትር እና ከዚያ በላይ ነው፡፡ ነገር ግን በኢትዮጵያ አማካይ ከፍታቸው ከባህር ጠለል በላይ ከአንድ ሺ ሜትር በታች ከሆነ ዝቅተኛ ቦታዎች ይባላሉ፡፡ የኢትዮጵያን አጠቃላይ የአየር ሁኔታ ስንመለከት ዝቅተኛ ስፍራዎች ከፍተኛ ሙቀት ያላቸው ሲሆኑ ከፍተኛ ቦታዎች ደግሞ ዝቅተኛ ሙቀት ይስተዋልባቸዋል፡፡ ለምሳሌ- የዳሎል (አፋር ክልል) ዓመታዊ አማካኝ የሙቀት መጠኑ 350C እና ዝቅተኛ የዝናብ መጠን ያለው ሲሆን ራስ ደጀን (አማራ ክልል) ከ00C በታች አማካኝ የሙቀት መጠን እና ከፍተኛ የዝናብ መጠን ይመዘገብበታል፡፡ 60 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ 1.የኢትየጵያ ከፍተኛ ቦታዎች፡- - ሰሜን ኢትዮጵያ ለምሳሌ ትግራይ፣ ሸዋ፣ ወሎ፣ ጎጃም፣ ጎንደር - ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ለምሳሌ ወለጋ፣ ኢሉአባቦራ፣ ከፋ፣ ጋሞ ጎፋ - ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ ለምሳሌ አርሲ፣ ባሌ፣ ሐረርጌ 2.የኢትዮጵያ ዝቅተኛ ቦታዎች፡- - ምዕራብ ኢትዮጵያ ለምሳሌ ተኬዘ ሰቲት፣ አባይ ዲንደር፣ ባሮ-አኮቦ - ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ ለምሳሌ ቦረና፣ ኤልከሬ፣ ኦጋዴን - የአዋሽ ሸለቆ እና የአፋር ዝቅተኛ ቦታዎች ናቸው፡፡ ቁልፍ ሥዕል3.3 የኢትዮጵያ ከፍተኛ እና ዝቅተኛ ቦታዎች የአየር ግፊት አየር ክብደት አለው፡፡ ይህ ክብደት ግፊትን ይፈጥራል፡፡ አየር ወደ ታች የሚጫነው ክብደት የአየር ግፊት ተብሎ ይጠራል፡፡ ለምሳሌ- በመሬት ላይ የቆመ ሰርከስ የሚሰራ ሰው ላይ ሌሎች ሦስት ሰርከስ የሚሰሩ ሰዎች አንዱ በአንዱ ላይ በመሆን ቢሰሩ የበለጠ ክብደት የሚሰማው ከስር ያለው ሰው ሲሆን ከሦስቱም ሰዎች ከላይ ባለው ሰው ላይ ምንም ጫና ስለሌለበት ክብደት አይሰማውም፡፡ 61 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ መልመጃ 3.1 ሀ.የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል ካልሆኑ ደግሞ ሀሰት በማለት በተሰጣችሁ ባዶ ቦታ ላይ መልሱን ፃፉ፡፡ 1. ነፋሳት የዝናብ ምንጮች ናቸው፡፡ 2. ኢትዮጵያ በሀሩር ሞቃታማ የአየር ንብረት ክልል ውስጥ የምትገኝ ብቸኛ ሀገር ናት፡፡ 3. ከፍታ እና ዝናብ ግንኙነት የላቸውም፡፡ ለ. ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የኢትዮጵያ ከፍተኛ እና ዝቅተኛ ቦታዎች በሣጥኑ ውስጥ ከተሰጣችሁ መገኛ አቅጣጫዎች ጋር በማዛመድ ፃፉ፡፡ ጎንደር ወለጋ አርሲ ባሮ-አኮቦ ቦረና ተ.ቁ ቦታዎቹ የሚገኙበት አቅጣጫ 1 ሰሜን ኢትዮጵያ 2 ምዕራብ ኢትዮጵያ 3 ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 4 ደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ሐ. ለሚከተሉትን ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ፡፡ 1.የኢትዮጵያን የአየር ንብረት ይዘቶችን ዘርዝሩ፡፡ 2.ዳሎል እና ራስ ዳጀን ከሙቀት ጋር ያላቸው ግንኙነት እንዴት ይገለፃል? 3.1.3. የኢትዮጵያ የአየር ንብረት ክልሎች አጥጋቢ የመማር ብቃት ተማሪዎች ይህን ትምህርት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡- ኢትዮጵያ በሐሩር ሞቃታማ የአየር ንብረት ክልል ከሚገኙ ሀገራት የተለየ የአየር ንብረት የምታሳይበትን ምክንያቶች ትተነትናላችሁ ፡፡ ቁልፍ ቃላት ደጋማ ቆላማ በረሃማ 62 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ የማነቃቂያ ጥያቄ ሙቀት እና ዝናብ ያላቸውን ግንኙነት አብራሩ? የኢትዮጵያ የሙቀት መጠንም ሆነ የዝናብ ስርጭት የሚወሰነው በኢትዮጵያ መገኛ እና በኢትዮጵያ ከፍታ ነው፡፡ 1. የኢትዮጵያ መገኛ ሲባል ኢትዮጵያ በምድር ወገብ አካባቢ የምትገኝ ሀገር መሆኗን ያመላክታል፡፡ 2. የኢትዮጵያ ከፍታ ሲባል የኢትዮጵያ አብዛኛዎቹ አካባቢዎች ከባህር ጠለል ከፍታ በላይ ከፍ ያሉ ቦታዎች ላይ መገኘታቸውን ያመላክታል፡፡ ስለዚህ ከላይ በተዘረዘሩት ሁለቱ ምክንያቶች ኢትዮጵያ በሀሩር ሞቃታማ የአየር ንብረት ክልል ውስጥ ከሚገኙ ሀገራት የተለየ የአየር ንብረት አላት፡፡ በርካታ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ከባህር ጠለል ከፍታ በላይ መገኘታቸው የከፍተኛ አካባቢ የአየር ንብረት እና የኢትዮጵያ በምድር ወገብ አካባቢ መገኘቷ ደግሞ ሞቃታማ የአየር ንብረት እንዲኖራት አድርጓታል፡፡ አማካኝ የሙቀት መጠንን እና ከባህር ጠለል በላይ ያለውን ከፍታ መሰረት በማድረግ የኢትዮጵያ የአየር ንብረት በአምስት ዋና ዋና ክልሎች ይመደባል፡፡ እነርሱም 1.ውርጫማ -ይህ የአየር ንብረት እርጥበታማ እና በጣም ቀዝቃዛ የአየር ንብረት ክልል ሲሆን በኢትዮጵያ ከፍ ያሉ ቦታዎች ላይ ይገኛል፡፡ 2.ደጋማ -ቀዝቃዛ እና እርጥበት አዘል የአየር ንብረት ክልል ነው፡፡ 3.ወይና ደጋማ -መካከለኛ ሙቀት እና መካከለኛ እርጥበት የሚስተዋልበት የአየር ንብረት ክልል ነው፡፡ 4.ቆላማ -ሞቃታማ እና ዝቅተኛ እርጥበት ያለው የአየር ንብረት ክልል ሲሆን በኢትዮጵያ ዝቅተኛ ያሉ ቦታዎች ላይ ይስተዋላል፡፡ 5.በረሀማ -በጣም ሞቃታማ እና ደረቃማ የሆነ የአየር ንብረት ክልል ሲሆን በኢትዮጵያ በጣም ዝቅተኛ ስፍራዎች ይስተዋላል፡፡ 63 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ መፍቻ በረሀ ቆላ ወይና ደጋ ደጋ ውርጭ ሥዕል 3.4 -የኢትዮጵያ የአየር ንብረት ክልሎች እና የኢትዮጵያ ክልሎች የግል ስራ 3.3 መመርያ- ሥዕል 3.4ን በመመልከት የኢትዮጵያን የአየር ንብረት ክልሎች የሚገኙቸባችውን የኢትዮጵያ ክልሎች መግለፅ እና በስዕሉ ላይ ማሳየት ዓላማ - የኢትዮጵያ የአየር ንብረት ክልሎች የሚገኙባቸውን ክልሎች መለየት መልመጃ 3.2 በ ‘ሀ’ ስር የተሰጡትን የአየር ንብረት ክልል ዓይነቶችን በ ‘ለ’ ስር ከተሰጡት የአየር ንብረት ባህርያት ጋር አዛምዱ፡፡ ሀ ለ 1. በረሀማ ሀ. ዝቅተኛ እርጥበት 2. ቆላማ ለ. ደረቅ 3. ወይና ደጋማ ሐ. ቀዝቃዛ 4. ደጋማ መ. መካከለኛ ሙቀት 3.1.4. ዋና ዋና የኢትዮጵያ የአየር ንብረት ዓይነቶች ዋና ዋና የኢትዮጵያ የአየር ንብረት ዓይነቶች የሚባሉት በኢትዮጵያ ውስጥ ለረጅም ግዜያት አንድን አካባቢ ሞቃታማ፣ እርጥበታማ እና ቀዝቃዛማ የሚያደርጉ የአየር ንብረት አካላት ናቸው፡፡ እነዚህ የአየር ንብረት አካላት አማካኝ የሙቀት መጠን እና የዝናብ ስርጭት ናቸው፡፡ አማካኝ የሙቀት መጠንን እና የዝናብ ስርጭትን መሰረት በማድረግ የኢትዮጵያ የአየር ንብረት በሶስት ዋና ዋና ዓይነቶች ይከፈላል፡፡ 64 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ 1.ሞቃታማ የአየር ንብረት - ከፍተኛ አማካኝ የሙቀት መጠን እና የዝናብ ስርጭት አለው፡፡ 2.ሞቃታማ እና እርጥበታማ የአየር ንብረት - አማካኝ የሙቀት መጠንም ሆነ የዝናብ ስርጭቱ መካከለኛ ነው፡፡ 3.ቀዝቃዛማ የአየር ንብረት - ደረቃማ እና ዝቅተኛ አማካኝ የዝናብ መጠን ይስተዋልበታል፡፡ መልመጃ 3.3 ሀ.የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል ከሆነ እውነት ትክክል ካልሆነ ሀሰት በማለት በተሰጣችሁ ባዶ ቦታ ላይ መልሱን ፃፉ፡፡ 1. ኢትዮጵያ የተለያዩ የአየር ንብረት ይዘቶች አሏት፡፡ 2. ቀዝቃዛማ የአየር ንብረት ከፍተኛ የዝናብ መጠን አለው፡፡ ለ. ለሚከተሉትን ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ፡፡ 1. የኢትዮጵያን የአየር ንብረት ዓይነቶች የሚከፈሉት ምንን መሰረት በማድረግ ነው፡፡ 2. የኢትዮጵያ ዋና ዋና የአየር ንብረት ዓይነቶችን በዝርዝር አስቀምጡ፡፡ 3.1.5. የአየር ንብረት ተቆጣጣሪዎች የንዑስ ርዕሱ አጥጋቢ የመማር ብቃት ተማሪዎች ይህን ትምህርት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡- በኢትዮጵያ ዋና ዋና የአየር ንብረትን የሚቆጣጠሩ ነገሮችን ትለያላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት ኬክሮስ ደመና ቀለይ ሞገድ ነፋስ ከፍታ የማነቃቂያ ጥያቄ የኢትዮጵያን ዋና ዋና የአየር ንብረት ዓይነቶችን ለመምህራችሁ ተናገሩ፡፡ 65 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ የአንድ አካባቢ የአየር ንብረት ተቆጣጣሪዎች የሚባሉት የአካባቢውን የአየር ንብረት ይዘት የሚለዋውጡ እና የአየር ንብረት ክልሎችን የሚወስኑ ናቸው፡፡ የአየር ንብረት ተቆጣጣሪዎች የሚባሉት፡- 1. ኬክሮስ 2. ከፍታ 3. ከባህር ያለው ርቀት 4. ቀለይ ሞገድ 5. ነፋስ 6. ደመና ኬክሮስ አንድን ቦታ የሚያሞቀው ወይም የሚያቀዘቅዘው የፀሐይ ጨረር ማዕዘን ነው፡፡ በአንድ ቦታ የፀሐይ ጨረር በቀጥታ የሚያርፍ ከሆነ ጨረሩ የሚያርፍበት ቦታ መጠኑ አነስተኛ ሲሆን የሙቀቱ መጠን ግን ከፍተኛ ይሆናል፡፡ጨረሩ የሚያርፈው በሰያፍ ከሆነ የሚሸፍነው የቦታ መጠን ሰፊ ይሆናል፡፡ ቀትር ላይ ሙቀቱ ከፍተኛ ሆኖ ጠዋትና ምሽት ላይ አነስተኛ ሙቀት የሚሰማን በዚህ ምክንያት ነው፡፡ ቀጥተኛ ጨረር የሚያርፍበት የምድር ወገብ ሞቃት ነው፡፡ ከፍታ ከፍታ ወደ ላይ ሲጨምር ሙቀት ይቀንሳል፡፡ ከፍታ ሲጨምር ሙቀት የሚቀንስበት ምክንያት አንድ አካባቢ የሚሞቀው ቀጥታ ከፀሐይ በሚመጣው ጨረር ሳይሆን ከመሬት ወደ ላይ በሚመለሰው የመሬት ጨረር(ራድየሽን) ነው፡፡ ከመሬት ጨረር ወደ ላይ እየራቅን ስንሄድ የሙቀት መጠንም እየቀነሰ ይሄዳል፡፡ለከፍታ ሙቀት መቀነስ ሌላው ምክንያት ደግሞ የአካባቢ አየር ዝቅተኛው ክፍል አቧራ፣ እርጥበት እና የመሳሰሉት ስላሉት እነዚህ ነገሮች ከመሬት የሚመጣውን ጨረር እንዳያልፍ አፍነው መያዝ ስለሚችሉ ዝቅተኛው ከባቢ አየር ስስ፣ ንጹህና ደረቅ ስለሆነ ሙቀትን መያዝ አይችልም፡፡ ከባህር ያለው ርቀት በአንድ ኬክሮስ ላይ ተመሳሳይ ከፍታ ያላቸው ሁለት የተለያዩ ሥፍራዎች አንደኛው ወደ ባህር ጠረፍ የሚጠጋ ከሆነ እና ሁለተኛው ከባህር ርቆ የሚገኝ ከሆነ በበጋም ሆነ በክረምት የሙቀት ልዩነት አይኖርም፡፡ አንድ ቦታ ከባህር ጠረፍ ከራቀ ክረምት በጣም ሲሞቅ በጋ ላይ ደግሞ ይቀዘቅዛል፡፡ 66 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ ቀለይ ሞገድ የውቅያኖስ ውሃ በፍጥነት ሲሄድ የሚከሰት ነው፡፡ በሞቃት አካባቢ ያለው ውሃ ሞቃት ሲሆን በቀዝቃዛ አካባቢ ያለው ውሃ ደግሞ ይቀዘቅዛል፡፡ ከሞቃት አካባቢ በንፋስ እየተገፋ የሚሄደው ገስጋሽ ውሃ የደረሰበትን አካባቢ ሲያሞቅ በተቃራኒው ከቀዝቃዛ አካባቢ የሚሄደው ገስጋሽ ውሃ የሚደርስበትን አካባቢ ሙቀት ያቀዘቅዛል፡፡ ንፋስ አየር ወደ ጎን ሲንቀሳቀስ የሚፈጠር ነው፡፡ ይህ እንቅስቃሴ የራሱ የሆነ ፍጥነት እና አቅጣጫ አለው፡፡ ንፋስ ባህር አካባቢ የሚገኘውን የሙቀት መጠን እና ስርጭት የሙቀት መጠኑን ተሸክሞ በማጓጓዝ ይቀይራል፡፡በምድራችን ላይ የተለያዩ የነፋሳት ዓይነቶች ሲኖሩ ስማቸው የሚሰየመው የሚነሱበትን አቅጣጫ መሰረት በማደረግ ነው፡ ፡ንፋስ የአንድን አካባቢ የዝናብ መጠን እና ስርጭትን ይቆጣጠራል፡፡ ደመና ደመና ከፀሐይ የሚመነጨውን የፀሐይ ጨረር መጠን እና መሬት ደርሶ ከመሬት ላይ የሚንፀባረቀውን የፀሐይ ጨረር ይቀንሳል፡፡ ነገር ግን ደመና በማይኖርበት ጊዜ ከፀሐይ የሚመነጨው የፀሐይ ጨረር መጠንም ሆነ መሬት ደርሶ ከመሬት ላይ የሚንፀባረቀው የፀሐይ ጨረር ይጨምራል፡፡ የኢትዮጵያን የአየር ንብረት በዋናነት የሚቆጣጠሩት ደመና፣ ኬክሮስ እና ከፍታ ናቸው፡፡ መልመጃ 3.4 ለሚከተሉትን ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ፡፡ 1. የአንድ አካባቢ የአየር ንብረት ተቆጣጣሪዎች ማለት ምን ማለት ነው? 2. የኢትዮጵያን የአየር ንብረት ተቆጣጣሪዎች የሚባሉትን ጥቀሱ ፡፡ 3. ቀለይ ሞገድ ምንድን ነው? 67 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ 3.2 የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቶች አጥጋቢ የመማር ብቃቶች ተማሪዎች እነዚህን የትምህረት ይዘቶች ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡- የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብት ዓይነቶች ትለያላችሁ፡፡ የኢትዮጵያን የአፈር ዓይነቶችና የአፈር መሸርሸርን ትገልፃላችሁ፡፡ በኢትዮጵያ የተለመዱ የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ዘዴዎችን ትለያላችሁ፡፡ በኢትዮጵያ የሚበቅሉ የዕፅዋት ዓይነቶችን ትለያላችሁ፡፡ ውጤታማ የውሃ ሀብት አጠቃቀም ዘዴዎችን ትገልፃላችሁ፡፡ በኢትዮጵያ የውሃ ሀብት ላይ ተጽዕኖ የሚያደርሱ ሁኔታዎችን ትዘረዝራላችሁ:: የኢትዮጵያ ውሃማ አካላትንና የተፋሰስ ሥርዓትን ትመረምራላችሁ፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ማዕድናትንና በአጠቃቀም ምክንያት የሚፈጠሩ አካባቢያዊ ችግሮችን ትተነትናላችሁ፡፡ በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ጉዳዮችን ትገልጻላችሀሁ:: የኢትዮጵያን ዋና ዋና የጉልበት ምንጮችን ትዘረዝራላችሁ፡፡ የኢትዮጵያን ታዳሽና ታዳሽ ያልሆኑ የጉልበት ምንጮችን ትለያላችሁ፡፡ በኢትዮጵያ በተፈጥሮ አካባቢ ላይ የሚስተዋሉ ዋና ዋና ችግሮችን ትዘረዝራላችሁ፡፡ የንዑስ ርዕሱ ይዘቶች 68 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ 3.2.1. የተፈጥሮ ሀብት ዓይነቶች የመማር ውጤት ተማሪዎች ይህን ትምህርት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡- የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብት ዓይነቶችን ትለያላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት የተፈጥሮ ሀብት ታዳሽ ታዳሽ ያልሆኑ የማነቃቂያ ጥያቄ በኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቶች የሚባሉት ምንድን ናቸው? የተፈጥሮ ሀብቶች በአካባቢያችን ውስጥ በተፈጥሮ የሚገኙ ለሰው ልጅ ህልውና አስፈላጊ የሆኑ ወይም ለመሰረታዊ ፍላጎቶች ማሟያ፣ ለመዝናኛ፣ ለኢንዱስትሪ ግብዓት፣ ለንግድ፣ ለጤና፣ ለትምህርት እና ለመሳሰሉት የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ የተፈጥሮ ሀብቶች ልዩ ልዩ ባህርያት አላቸው፡፡ መጠናቸውን፣ ዓይነታቸውን እና ራሳቸውን ለመተካት የሚወስድባቸውን ጊዜ መሰረት በማድረግ የተፈጥሮ ሀብቶች በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ይመደባሉ፡፡ እነርሱም ታዳሽ እና ታዳሽ-ያልሆኑ የተፈጥሮ ሀብቶች ይባላሉ፡፡ ታዳሽ የተፈጥሮ ሀብቶች ታዳሽ የተፈጥሮ ሀብቶች የሚባሉት በየጊዜው በተፈጥሮአዊ መንገድ ሊተኩ የሚችሉ ናቸው፡፡ይህ ማለት አንድ ጊዜ አገልግሎት ላይ ከዋሉ በድጋሚ አገልግሎት ላይ መዋል የሚችሉ ሀብቶች ናቸው፡፡ሆኖም እነዚህ የተፈጥሮ ሀብት መተኪያ ሂደቶች በሰው ሰራሽ መንገዶች ሊቋረጡ ይችላሉ፡፡ የተፈጥሮ ሀብቶችን በአግባቡ በመጠቀም እና በመንከባከብ ታዳሽነታቸውን ማጠናከር እና ቀጣይነት እንዲኖራቸው ማድረግ ይቻላል፡፡ለምሳሌ- አፈር፣ ውሀ፣ አየር፣ ዕፅዋት፣ እንስሳት፣ የፀሐይ ሀይል እና የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ 69 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ የፀሐይ ጨረር አየር ውሀ እፅዋት ሥዕል 3.5 ታዳሽ የተፈጥሮ ሀብቶች ታዳሽ ያልሆኑ የተፈጥሮ ሀብቶች ታዳሽ ያልሆኑ የተፈጥሮ ሀብቶች የሚባሉት በተፈጥሮ በተወሰነ መጠን ብቻ የሚገኙ፤ ሊተኩ የማይችሉ እና አንድ ግዜ አገልግሎት ላይ ከዋሉ በድጋሚ አገልግሎት ላይ መዋል የማይችሉ ናቸው፡፡ እያለቁ የሚሄዱ እና በተፈጥሮ የማይተኩ ናቸው፡፡ ለምሳሌ- የተለያዩ ማዕድናት፣ የድንጋይ ከሰል፣የተፈጥሮ ጋዝን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ሥዕል3.6 -ታዳሽ ያልሆኑ የተፈጥሮ ሀብቶች መልመጃ 3.5 ሀ.አጭር መልስ በፅሁፍ በመስጠት አጠገባችሁ ካሉ የክፍል ጓደኞቻች ጋር በመልሱ ዙርያ ተነጋገሩ፡፡ 1. የተፈጥሮ ሀብት ማለት ምን ማለት ነው 2. ታዳሽ የተፈጥሮ ሀብት ምንነትን በማብራራት ምሳሌያቸውን ጥቀሱ፡፡ 3. ታዳሽ ያልሆኑ የተፈጥሮ ሀብቶችን ጥቀሱ፡፡ 70 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ ማዕድናት፣ የድንጋይ ከሰል፣ የተፈጥሮ ጋዝ፣ አፈር፣ ውሀ፣ አየር፣ ዕፅዋት፣ እንስሳት፣ የፀሐይ ሀይል ከላይ የተዘረዘሩትን የተፈጥሮ ሀብቶች ታዳሽ እና ታዳሽ ያልሆኑ በማለት በሁለት ምድብ ፃፏቸው፡፡ 3.2.2. የአፈር ዓይነቶች አጥጋቢ የመማር ብቃት ተማሪዎች ይህን ትምህርት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡- የኢትዮጵያን የአፈር ዓይነቶችና የአፈር መሸርሸርን ትገልጻላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት አፈር የአፈር ቅንጣጢት የአፈር መሸርሸር የማነቃቂያ ጥያቄ 1. አፈር ምንድን ነው? 2. በአካባቢያችሁ ያለው አፈር ምን ዓይነት ነው? ለተክሎች ዕድገት ተስማሚ ነው? አፈር ህይወት ያላቸው ነገሮችን፣ ጥቃቅን ነፍሳትን፣ ትላልቅ፣ መካከለኛና ደቃቅ የአፈር ቅንጣቶችን፣ የተለያዩ የተክል ክፍሎችንና የእንስሳት ብስባሽ የያዘ ጠቃሚ የተፈጥሮ ሃብት ነው፡፡ አነዚህም የአፈር ስሪቶች ይባላሉ፡፡ አፈር በውስጡ ጠጠር፣ አሸዋ፣ ሸክላ(ጭቃ)፣ መካከለኛና ትናነሽ የአፈር ቅንጣቲቶችን እነዲሁም የሞቱ ዕፅዋትና እንስሳት ብስባሽን ይይዛል፡፡ የአፈር ቅንጣጢቶች በጣም ደቃቅ የሆኑ የአፈር አካላት ናቸው፡፡ ማስታወሻ ኮሲ የሞቱ ተክሎችና እንስሳት አካል ብስባሽን የያዘ የአፈር ክፍል ነው፡፡ 71 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ ሦስት የአፈር ዓይነተች አሉ። እነርሱም፦ አሸዋማ አፈር፣ የሸክላ አፈርና ለም አፈር ናቸው፡፡ እነዚህ የአፈር ዓይነቶች በቅንጣቲት መጠናቸው፣ ውሃ በውስጣቸው በመያዝ ችሎታቸውና ባላቸው የንጥረ-ነገር ዓይነት ይለያያሉ፡፡ አሸዋማ አፈር፡- ከትላልቅ የአፈር ቅንጣቲቶች የተሰራ ነው፡፡የተሰራበት የቅንጣቲት መጠን ትላልቅ በመሆኑ ውሃ የመቋጠር ችሎታ የለውም፡፡ ውሃ በውስጡ በፍጥነት ስለሚያልፍ ለተክሎች የሚያስፈልጉ ንጥረ ነገሮችን ያጥባችዋል፡፡ ስለዚህ ውሃና ለተክሎች ምግብ መስሪያ የሚሆን ንጥረ-ነገር በውሰጡ ስለማይዝ ለተክሎች ዕድገት ተስማሚ አይደለም፡፡ ሥዕል 3.7 አሽዋማ አፈር የሸክላ አፈር፡- ትናንሽ ከሆኑ የአፈር የቅንጣቲቶች የተሰራ ነው፡፡ ውሃ የመቋጠር ችሎታው ከፍተኛ ነው፡፡ መጠነኛ የሆነ ለተክሎች ምግብ መስሪያ ንጥረ-ነገር አለው፡፡ የሸክላ አፈር የአፈር ቅንጣቲቶቹ የተጠጋጉ በመሆናቸው የተክሎች ስር በቂ አየር ስለማያገኝ ለተክሎች ዕድገት ተስማሚ አይደለም፡፡ ሥዕል 3.8 የሸክላ አፈር ለም አፈር፡- ትናንሽም ትላልቅም ቅንጣቲቶች አሉት፡፡ ከፍተኛ መጠን ያለው ለተክሎች ምግብ መስሪያ የሚሆን ንጥረ-ነገር አለው፡፡ ውሃ ይቋጥራል፤በውስጡ ብዙ ውሃ ማሳለፍ ይችላል፡፡ለም አፈር የአሸዋማና የሸክላ አፈር ድብልቅ ስለሆነ በቂ ውሃ፣ በቂ አየርና ለተክሎች ዕድገት ጠቃሚ ንጥረ-ነገሮችን ስለሚይዝ ለተክሎች ዕድገት ተስማሚ ነው፡፡ 72 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ ሥዕል 3.9 ለም አፈር ተግባራዊ ክንውን 3.4 ርዕስ፡- የአፈር ስሪት ዓላማ፡- የአፈር ስሪትን መለየት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ሰፋ ያለ አፍ ያለው ባለ ክዳን የፕላስቲክ ጠርሙስ ውሃ-ከአትክልት ቦታ የተወሰደ አፈር የአሰራር ቅደም ተከተል፡፡ 1. የፕላስቲክ ውሃ መያዣውን ሩብ ያህል አፈር በፕላስቲክ ጠርሙሱ ውስጥ ጨምሩ፡፡ 2. የፕላስቲክ ውሃ መያዣውን ሦስት አራተኛ በውሃ ሙሉት፡፡ 3. የውሃ መያዣውን በመክደን አፈርና ውሃውን በደንብ በጥብጡት፡፡ 4. የውሃ መያዣውን አስቀምጡና የተበጠበጠው አፈር እስኪረጋ ለተወሰነ ጊዜ ጠብቁት፡፡ምን ተረዳችሁ?የተገነዘባችሁትን በስዕል አሰቀምጡ፡፡ ከሙከራው በኋላ ቀጥሎ የተቀመጠውን ስዕል በመመልከት በፊደላቱ ቦታ ጠጠር፣ አሸዋ፣ ትላልቅ የአፈር ቅንጣጢቶች፣ ትናንሽ የአፈር ቅንጣጢቶችና ኮሲ በማለት ሙሉ፡፡ 73 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ የአፈር መሸርሸር መንስዔዎች የአፈር መሸርሸር ማለት ለም የሆነ አፈር በዝናብ በመታጠብ እና በንፋስ በመነሳት ወደ ሌላ ቦታ መወሰድ ነው፡፡ የቡድን ውይይት 3.1 ዓላማ፡- የአፈር መሸርሸር መንስዔዎችን መረዳት መመሪያ፡- በቡድን በመከፋፈል በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያይታችሁ የደረሳችሁበትን ለክፍል ጓደኞቻችሁ አቅረቡላቸው፡፡ የመወያያ ጥያቄዎች 1. በዕፅዋት ከተሸፈነ መሬትና ካልተሸፈነ መሬት ለጎርፍ ተጋላጭ የሆነው የቱ ነው? 2. በአንድ ቦታ ብዙ ከብቶችን ማሰማራት ምን ሊያስከትል ይችላል? 3. ገበሬዎች የእርሻ መሬትን ሲያርሱ አይታችሁ ታውቃላችሁ?አግድም ወይስ ቁልቁል ያርሳሉ? የትኛው የአስተራርስ ዘዴ የአፈር መሸርሸርን ያስከትላል? የአፈር መሸርሸር ዋና ዋና መንስዔዎች፡- የደን መጨፍጨፍ ተዳፋት መሬትን ቁልቁል ማረስ በትንሽ የግጦሽ መሬት ብዙ ከብቶችን ማሰማራት የአዝርዕቶችን ቅሬት አካል መንቀል፣ማቃጠልና ለግጦሽ ማዋል አንድን የእርሻ መሬት በተደጋጋሚ ማረስ በአንድ የእርሻ ማሳ ላይ አንድ ዓይነት ሰብል መዝራት ኩታ ገጠም የአስተራርስ ዘዴን አለመጠቀም ናቸው። 74 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ መልመጃ 3.6 ለሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ፡፡ 1. ለተክሎች ዕድገት ተስማሚ የሆነው የአፈር ዓይነት የቱ ነው? ሀ. የሸክላ አፈር ለ. አሽዋማ አፈር ሐ. ለም አፈር መ. ቀይ አፈር 2. በቀላሉ ሊሸረሸር የሚችለው የአፈር ዓይነት የቱ ነው? ሀ. ለም አፈር ለ. አሽዋማ አፈር ሐ. የሸክላ አፈር መ. የደለል አፈር 3. ከሚከተሉት ውስጥ የአፈር መሸርሸር መንስዔ ያልሆነው የቱ ነው? ሀ. የደን መጨፍጨፍ ለ. በትንሽ የግጦሽ መሬት ብዙ ከብቶችን ማሰማራት ሐ. አግድም ማረስ መ. የሰብል ቅሬቶችን ማቃጠል 4. ከሚከተሉት ውስጥ በጣም ትናንሽ ከሆኑ የአፈር ቅንጣቲቶች የተሰራው የአፈር ዓይነት የቱ ነው? ሀ. የሸክላ አፈር ለ. አሽዋማ አፈር ሐ. ለም አፈር መ. ኮሲ 5. የሞቱ እንስሳትና ዕፅዋት ብስባሽ የያዘ የአፈር ክፍል ምን ይባላል? ሀ. ጠጠር ለ. ደለል ሐ. ለም አፈር መ. ኮሲ 3.2.3 የዕፅዋት ዓይነቶች አጥጋቢ የመማር ብቃት ተማሪዎች ይህን የትምህርት ተምረው ስታጠናቅቁ፡- ¾ በኢትዮጵያ የሚበቅሉ የዕፅዋት ዓይነቶችን ትለያላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት ዕፅዋት ሀገር በቀል ዕፅዋት ዛፍ ቁጥቋጦ የማነቃቂያ ጥያቄ ዕፅዋት ህይወት አላቸው? ዕፅዋት ምግብ ይመገባሉ? ዕፅዋት የፀሐይ ብርሃንን በመጠቀም የራሳቸውን ምግብ ማዘጋጀት የሚችሉ ህይወት ያላቸው ነገሮች ናቸው፡፡ 75 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ የቡድን ውይይት 3.6 ዓላማ፡- የዕፅዋት ዓይነቶችን መለየት መመሪያ፡- ቡድን በመመስረት በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያይታችሁ የደረሳችሁበትን ለመምህራችሁ ተናገሩ፡፡ 1. በአካባቢያችሁ ምን ምን ዓይነት ዕፅዋቶች ይገኛሉ? በምን በምን ዓይነት ሁኔታዎች ይለያያሉ? 2. በአካባቢያችሁ ስንት የዕፅዋት ዓይነቶች አሉ? 3. በአካባቢያችሁ የምታውቋቸውን የዕፅዋት አይነቶች ዘርዝሩ? ዕፅዋትን የግንድ ጥንካሬያቸውንና ቁመታቸውን መሰረት በማድረግ በሦስት ይከፈላሉ፡ እነርሱም፡- 1. ለስላሳ ግንድ ያላቸው፡- አጫጭር ቁመትና ለስላሳ ግንድ ያላቸው ዕፅዋቶች ናቸው፡፡ ለምሳሌ አዝርቶችና የጓሮ አትክልቶች (ስንዴ፣ ጎመን፣ ቆስጣ በቆሎ፣ ካሮት ወ.ዘ.ተ) ሥዕል 3.10 ለስላሳ ግንድ ያላቸው ዕፅዋት 2. ቁጥቋጦዎች፡- መካከለኛ ቁመትና ጠንካራ ግንድ ያላቸው የዕፅዋት ዓይነቶች ናቸው፡፡ ለምሳሌ ቀጋ፣አጋም ሥዕል 3.11 ቁጥቋጦዎች 76 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ 3. ዛፎች፡- ወፍራም፣ ጠንካራና ረጃጅም ግንድ ያላቸው የዕፅዋት ዓይነቶች ናቸው:: ለምሳሌ ዝግባ፣ ዋንዛ፣ ኮሶ፣ ባህርዛፍ፣ ግራር ሥዕል 3.11 ዛፎች የዕፅዋት ዝርያዎች አበባማና አበባ አልባ ተብለው ይከፈላሉ፡፡ አበባማ ዕፅዋት፡- አበባ ያላቸውና በአበባቸው አማካኝነት የሚራቡ ሲሆኑ ከሌሎች የተክል ዝረያዎች ይልቅ በዓይነታቸውና በቁጥራቸው አጅግ ብዙ ናቸው፡፡ ለቁጥራቸውም ሆነ ለዓይነታቸው መብዛት ምክንያቱ የአበባ መኖር ነው፡፡ምሳሌ ጽጌረዳ፣ በቆሎ፣ ባቄላ፣ ጤፍ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ አበባ አልባ ዕፅዋት፡- አበባ የሌላቸው የዕፅዋት ዓይነቶች ናቸው፡፡ ለምሳሌ ሳረንስቶች፣ ፈርኖችና ቅምብብማ ዕፅዋት ዕፅዋት ሳረንስቶች ፈርኖች ቅምብብማ አበባማ ሥዕል 3.12 አበባማና አበበ አልባ እፅዋት ሳረንስቶች፡- እርጥበትና ጥላ ባለበት ቦታ የሚኖሩ መጠናቸው ትናንሽ የሆኑ፣ ትክክለኛ የሆነ ቅጠል፣ግንድና ስር የሌላቸው የዕፅዋት አይነቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ተክሎች እርጥበት ባለበት ሁኔታ በግድግዳና በድንጋይ ላይ መኖር ይችላሉ፡፡ ፈርኖች፡- ትክክለኛ የሆነ ስር፣ ግንድና ቅጠል አላቸው፡፡እርጥበት ባለበት ቦታ ይኖራሉ:: ፈርኖች በከተሞች አካባቢ፤በቤት ውስጥ ወይም በግቢ ውስጥ ተተክለው እንደ ጌጥ ያገለግላሉ፡፡ 77 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ ቅምብብማ ዕፅዋት፡- የሚባሉት አበባ የሌላቸው ነገር ግን ዘር ያላቸው ትላልቅ የዛፍ ዓይነቶች ናቸው፡፡ ምሳሌ ጥድ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሀገር በቀል ዕፅዋት ሀገር በቀል ዕፅዋት የመጀመሪያ መገኛቸው በአንድ ሀገር የሆኑና ከሌላ ሀገር ያልመጡ ማለት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ሀገር በቀል ዕፅዋቶች ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ ዝግባ፣ ኮሶ፣የአበሻ ጥድ፣ ግራር፣ዋንዛ የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡ የደን መጨፍጨፍ መንሥኤዎች ደን በትላልቅ ዛፎችና ጥቅጥቅ ብለው በበቀሉ ተክሎች የተሸፈነ ቦታ ነው፡፡ የደን ጥቅሞች ደኖች ለአካባቢያችንና ለሰው ልጆች ብዙ ተቀሜታ ይሰጣሉ፡፡ ደን የአፈርን ለምነት ያዳብራል፡፡ የዛፎች ስር አፈርን በአንድ ቦታ ቆንጥጦ በመየዝ የአፈር መሸርሸርን ይከላከላል፡፡ ደን በውስጡ የተለያዩ የዱር እንስሳትና አዕዋፍ ስለሚኖሩ የተፈጥሮን ሚዛን ለመጠበቅ ይረዳል፡፡ ደኖች ብዙ ካርቦን ዳይኦክሳይድ ከአየር አስወግደው ወደ ውስጣቸው በማስገባትና ከውሃ ጋር በማዋሃድ ምግባቸውን ያዘጋጁበታል፡፡ በዚህም የካርቦንዳይ ኦክሳይድ መጠንን በመቀነስ የዓለም የሙቀት መጠን እንዳይጨምር ይረዳሉ፡፡ የቡድን ውይይት 3.2 ዓላማ፡- ስለ ደን ጥቅም መግለፅ የመወያያ ጥያቄዎች 1. ደን ምንድን ነው? 2. በሃገራችን ውሰጥ የሚገኙ ደኖች ለምን ለምን አገልግሎት ይውላሉ?የደን መጨፍጨፍ ማለት ምን ማለት ነው? በኢትዮጵያ ዋነኛ የደን መጨፍጨፍ መንሰዔዎችን ዘርዝሩ፡፡ የደን መጨፍጨፍን ለመከላከል የሚወሰዱ መፍተሄዎችን ዘርዝሩ፡፡ 78 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ ካርቦንዳይኦክሳይድ ከእንስሳት፣ ከኢንዱስተሪዎችና ከተሸከርካሪዎች የሚወጣ ጋዝ ነው፡፡ የዚህ ጋዝ በአየር ውሰጥ ሲጨምር የአለም የሙቀት መጠን ይጨምራል፡፡ የደን መጨፍጨፍ የደን መጨፍጨፍ ማለት ዛፎችን ያለአግባብ መቁረጥ ነው፡፡ አንድ ዛፍ ሲቆረጥ በምትኩ ከአንድ በላይ ዛፍ ሊተከል ይገባል፡፡ ደኖች በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ይጨፈጨፋሉ፡፡ የደን መጨፍጨፍ መንሰዔዎች ከቦታ ቦታ የሚለያዩ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡ መጠለያና የቤት ቁሳቁሶችን ለመስራት ለምግብ ማብሰያ ማገዶነት ለእርሻ የሚሆን መሬት ለማግኘት ሥዕል፡-3.13 የደን ጭፍጨፋ የቡድን ውይይት 3.3 የመወያያ ጥያቄ በአካባቢያችሁ ሰዎች ለጥርስ መፋቂያ ዕፅዋትን በብዛት ይጠቀማሉ?ይህ ሁኔታ የደን መጨፍጨፍን ያሰከትላል? በብዛት የሚጠቀሙት አንድ አይነት ዛፍ ነው? ከሆነ ምን ያስከትላል? መፍትሄው ምን መሆን አለበት? የተወያያችሁበትን ለመምህራችሁ አቅርቡ፡፡ 79 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ የደን መጨፍጨፍ ከሚያስከትላቸው ችግሮች መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡ የአፈር መሸርሸር የዱር እንስሳት መኖሪያ ማጣት(መሰደድ) የአየር ንብረት ለውጥ ማስከተል ለምግብነትና ለመድሃኒትነት የሚሆኑ ተክሎች መጥፋት የመዝናኛና ንጹህ አየር የማግኘት ችግር የደኖች አጠባብቅ የቡድን ውይይት 3.4 ዓላማ፡- ደኖችን እንዴት መንከባከብ እነደሚቻል ማወቅ መመሪያ፡- በቡድን በመሆን በመወያያ ጥያቄው መሰረት ተወያይታችሁ የደረሳችሁበትን ለክፍል ጓደኞቻችሁ አቅርቡላቸው፡፡ የመወያያ ጥያቄ፡- በአካባቢያችሁ የሚገኝ ደን አለ? ካለ ስለሚሰጠው ጥቅምና ስለሚደረግለት እንክብካቤ ተወያዩ፡፡ ደኖችን በሚከተሉት መንገዶች መንከባከብና መጠበቅ ይቻላል፡፡ 1. እሳት በደን አካባቢ እንዳይነሳ መከላከል፡፡ 2. ደኖችን ከልሎ በመጠበቅ ከመጨፍጨፍ መከላከል፡፡ 3. በሚቆረጡ ዛፎች ምትክ ብዙ ችግኞችን መትከል፡፡ 4. በደን አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች በደኑ ላይ ጉዳት ሳያደርሱ ከደኑ ከሚገኘው ጥቅም እንዲጠቀሙ ማድረግ፡፡ 5. በአንድ አካባቢ የሚገኝ ብቸኛ የዛፍ ዝርያ ሲቆረጥ በምትኩ ሌላ ተመሳሰይ የዛፍ ችግኝ መትከል ናቸው ፡፡ 80 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ ሥዕል3.14 የችግኝ ተከላ ችግኝ ተክላችሁ ታውቃላችሁ? ከተከላችኋቸው ችግኞች ምን ያህሉ ጸድቀዋል (አድገዋል)? ለመምህራችሁ ተናገሩ፡፡ ማንኛውም ሰው በየአመቱ በክረምት ወቅት ችግኝ ሊተክልና የተከላቸውን ችግኞች ሊንከባከብ ይገባል፡፡ መልመጃ 3.7 ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ፈደል ምረጡ፡፡ 1. ከሚከተሉት ውስጥ የዛፍ ዓይነት የሆነው የቱ ነው? ሀ. ጎመን ለ. ግራር ሐ. ጽጌ ረዳ መ. በቆሎ 2. ትክከለኛ ሥር፣ ግንድና ቅጠል የሌለው የዕፅዋት ዓይነት የቱ ነው? ሀ. ሳረንስት ለ. ፈርን ሐ. ቅምብብማ ዕፅዋት መ. አበባማ ዕፅዋት 3. ከሚከተሉት ውስጥ የደን መጨፍጨፍ መንስዔ ያልሆነው የቱ ነው? ሀ. የከተሞች መስፋፋት ለ. የእርሻ መሬት እጥረት ሐ. የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መጨመር መ. የጣውላ ሥራ መስፋፋት 4. ከሚከተሉት ውስጥ ሀገር በቀል ዕፅዋት ያልሆነው የቱ ነው? ሀ. ኮሶ ለ. ባህር ዛፍ ሐ. ዝግባ መ. የሐበሻ ጥድ 5. በደን መጨፍጨፍ ምክንያት የማይከሰት የቱ ነው? ሀ. የአየር ንብረት መዛባት ለ. የአፈር መሸርሸር ሐ. የሙቀት መጠን መጨመር መ. የተስተካከለ የተፈጥሮ ሚዛን 81 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ 3.2.4 የተፈጥሮ ሀብት አጠባበቅ ዘዴዎች አጥጋቢ የመማር ብቃት ተማሪዎች ይህን ትምህርት ተምራችሁው ስታጠናቅቁ፡- በኢትዮጵያ የተለመዱ የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ዘዴዎችን ትለያላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት መተካት መቆጠብ መልሶ መጠቀም የማነቃቂያ ጥያቄ በኢትዮጵያ የሚዘወተሩ የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ዘዴዎችን ጥቀሱ፡፡ የተፈጥሮ ሀብቶችን በዘላቂነት እና በቀጣይነት ለመጠቀም በአግባቡ መጠቀም እና በሚገባ መንከባከብ ያስፈልጋል፡፡ የተፈጥሮ ሀብቶች የሰውን ልጅ ማህበራዊም ሆነ ሚጣኔ-ሀብታዊ እንቅስቃሴ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ስለሚወስኑ ከብክነት እና ከብክለት መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡ የተፈጥሮ ሀብቶችን በተለያዩ ዘዴዎች መጠበቅ እና መንከባከብ ይቻላል፡፡በኢትዮጵያ የሚዘወተሩ ዋና ዋና የተፈጥሮ ሀብቶች መንከባከቢያ ዘዴዎች መተካት፣ መልሶ መጠቀም እና መቆጠብ ናቸው፡፡ 1. መተካት- በተለይ የማይታደሱ የተፈጥሮ ሀብቶችን በቀጣይነት ለመጠቀም ታዳሽ የሆኑ የተፈጥሮ ሀብቶችን በመተካት በስፋት መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ለምሳሌ- ለሀይል ምንጭነት የነዳጅ ጋዝ ከመጠቀም ማገዶ መጠቀም፡፡ 2. መልሶ መጠቀም- የተፈጥሮ ሀብቶችን አንዴ ከተገለገልንባቸው በኋላ በቀጥታ ለሌላ አገልግሎት ማዋል ወይም ይዘታቸውን፣ ቅርጻቸውን እና ዓይነታቸውን በመቀየር ለሌላ አገልግሎት ማዋል ማለት ነው፡፡ለምሳሌ-የተለያዩ ብረታብረቶችን፣ የእንጨት ውጤቶችን፣ የፕላስቲክ ውጤቶችን እና ሌሎችን አገልግሎት ሰጥተው ከተወገዱ በኋላ በተለያዩ ሁኔታዎች እንገለገልባቸዋለን፡፡ 3. መቆጠብ- የሰው ልጅ ፍላጎት ገደብ ባይኖረውም የተፈጥሮ ሀብቶች በአቅርቦት ውስን ናቸው፡፡ ስለዚህ ገደብ የሌለውን ፍላጎት ለማሟላት በተፈጥሮ አካባቢያችን 82 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ የሚገኙ ሀብቶችን አሟጠን መጠቀም ሳይሆን ቆጥበን መጠቀም አለብን ፡፡ ለምሳሌ- የማዕድን ሀብቶች የቡድን ውይይት 3.5 ዓላማ- የተለመዱ የተፈጥሮ ሀብቶች እንክብካቤ ዘዴዎችን በምሳሌ ማብራራት መመርያ- ከ2-3 ተማሪዎች በመሆን ቡድን መስርታችሁ ተወያዩ፡፡ የውይይቱን ውጤት ለክፍሉ አቅርቡ፡፡ የመወያያ ቃላት፡- 1. መተካት 2. መልሶ መጠቀም 3. መቆጠብ ሀገር በቀልና የተለመዱ ውጤታማ የአፈር አጠባበቅ ዘዴዎች በኢትዮጵያ አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች የሚጠቀሟቸው የተለያዩ ሀገር በቀልና የተለመዱ ውጤታማ የአፈር አጠባበቅ ዘዴዎች አሉ፡፡ እነዚህ ዘዴዎች ከአካባቢ አካባቢ የሚለዩ ሲሆን ከመሬት አቀማመጥ አንጻርም የሚተገበሩ ናቸው፡፡ እነርሱም፡- አግድም-ማረስ ድነና እና ዳግም ድነና መሬት ማሳደር የተለያዩ ብስባሾችን መጠቀም አፈራርቆ መዝራት እና እርከን መስራት ናቸው፡፡ የቡድን ውይይት 3.6 ዓላማ- የተለመዱ የተፈጥሮ ሀብቶች እንክብካቤ ዘዴዎችን በምሳሌ ማብራራት መመርያ- ከ2-3 ተማሪዎች በመሆን ቡድን መስርታችሁ ተወያዩ፡፡ የውይይቱን ውጤት ለክፍል አቅርቡ፡፡ 83 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ መልመጃ 3.8 ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ፡፡ 1. በኢትዮጵያ የሚዘወተሩ የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ዘዴዎችን ጥቀሱ፡፡ 2. ሀገር በቀልና የተለመዱ ውጤታማ የአፈር አጠባበቅ ዘዴዎችን ዘርዝሩ፡፡ 3.2.5 ውጤታማ የውሃ ሃብት አጠቃቀም አጥጋቢ የመማር ብቃቶች ተማሪዎች ይህን ትምህርት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡- ውጤታማ የውሃ ሀብት አጠቃቀም ዘዴዎችን ትገልጻላችሁ፡፡ በኢትዮጵያ የውሃ ሀብት ላይ ተጽዕኖ የሚያደርሱ ሁኔታዎችን ትዘረዝራላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት የውሃ ሃብት ብክነት የቡድን ውይይት 3.7 ዓላማ የውሃ ሀብት አጠቃቀም ዘዴዎችን እና በኢትዮጵያ የውሃ ሀብት ላይ ተፅእኖ የሚያደርሱ ሁኔታዎችን ማሳወቅ 1. በእናንተ እይታ ዘላቂ የሆነ የኢትዮጵያ የውሃ ሀብት አጠቃቀም ዘዴዎችን ለይታችሁ አስረዱ፡፡ 2. በኢትዮጵያ የውሃ ሀብት ላይ ተፅእኖ የሚያሳድሩ መንስኤዎች ላይ ተወያይታችሁ ሃሳባችሁን ግለፁ፡፡ በምዕራፍ ሁለት ትምህርታችሁ ስለ ውሃ ጠቀሜታ ተምራችኋል በዚህ ምዕራፍ ደግሞ ውሃን እንዴት ውጤታማ በሆነ ዘዴ እንጠቀማለን የሚለውን እናያለን፡፡ ውሃ ታዳሽ የተፈጥሮ ሃብት ነው፡፡ በመሆኑም ውጤታማ በሆነ መንገድ ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ ውጤታማ የውሃ አጠቃቀም ስንል ውሃን በተገቢዉ መጠን በቁጠባ ለፈለግነው አገልግሎት ማዋል ነዉ፡፡ 84 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ ውጤታማ የውሃ ሀብት አጠቃቀም ዘዴዎች ሀ. ንፅህናችንን ስንጠብቅ ፣ምግብ ስናበስል፣ አትክልቶችን ስናጠጣ (ለመስኖ ስንጠቀም) በጥንቃቄና በቁጠባ መጠቀም ለ. የተበላሹና የዛጉ የውሃ ቧንቧዎችን መቀየር ሐ. ኢንዱስትሪዎች ውሃን በማከም እንደገና እንዲጠቀሙ ማድረግ መ. በተለያየ ምክንያት ቧንቧዎች ሲፈነዱ በአስቸኳይ መጠገን ሠ. በዝናብ ወቅት የዝናብ ውሃን መጠቀም እና ማጠራቀም ሰ. ውሃን ከተለያዩ በካይ ነገሮች ጠብቆ መጠቀም የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡ ረ. የውሃ አካላትን መንከባከብ በኢትዮጵያ የውሃ ሀብት ላይ ተፅእኖ የሚያሳድሩ ሁኔታዎች 1. የዝናብ መጠን መቀነስ 2. የውሃ ብክነት 3. የውሃ ብክለት መልመጃ 3.9 ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ፡፡ 1. ዉጤታማ የዉሃ ሃብት አጠቃቀም ዘዴዎችን ዘርዝሩ፡፡ 2. በዉሃ ሃብት ላይ ተፅእኖ የሚያሳድሩ ሁኔታዎችን ዘርዝሩ፡ 3.2.6. የሐይቅ ዓይነቶችና ባሕርያት ሐይቅ- ጥልቀቱ አነስተኛ የሆነ በሁሉም አቅጣጫ በመሬት የተከበበ የውሀ ክፍል ነው፡፡ በኢትዮጵያ በርካታ ሀይቆች የሚገኙ ሲሆን መገኛ ቦታቸውን መሰረት በማድረግ በሁለት ይከፈላሉ፡፡ እነርሱም፡- 1. ከፍታ ቦታዎች ላይ የሚገኙ ሐይቆች ለምሳሌ-ጣና፣ ሐይቅ(ወሎ)፣ ወንጭ እና አሸንጌ ሐይቆች ናቸው። የጣና ሐይቅ በስፋት ትልቁ ሀይቅ ነው፡፡ሻላ ከፍተኛ ጥልቀት ያለው ሐይቅ ሲሆን ዝዋይ ደግሞ በጥልቀት ዝቅተኛ ነው፡፡ 2. ስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኙ ሀይቆች፡- የዝቅተኛ ስፍራ ሐይቆች በመባል ይታወቃሉ፡፡ ለምሳለ አቤ፣ ዝዋይ፣ ላንጋኖ፣ ሻላ፣ አቢጃታ፣ ሐዋሳ፣ ጫሞ፣ አባያ እና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ:: 85 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ የኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ ከሰሜን ምስራቅ ወደ ደቡብ ምዕራብ የተዘረጋ ነው፡ይህ ቦታ ዝቅተኛ ስፍራ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሐይቆች የተለያዩ ባህርያት አሏቸው፡፡ 1. በአንድ ቦታ የተወሰኑ ናቸው፡፡ 2. በፀሐይ ትነት የውሃ መጠናቸው የሚቀንስ ነው-ሀሮማያ እና ላንጋኖ መልመጃ 3.10 አጭር መልስ ስጡ፡፡ 1. በኢትዮጵያ ከፍታ ቦታዎች ላይ የሚገኙ ሐይቆችን ጥቀሱ፡፡ 2. በኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኙ ሐይቆችን ጥቀሱ፡፡ 3.2.7. ዋና ዋና የውሃ ተፋሰስ ሥርዓት የንዑስ ርዕሱ የመማር ብቃት ተማሪዎች ይህን ትምህርት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡- የኢትዮጵያ ውሃማ አካላትንና የተፋሰስ ሥርዓትን ትመረምራላችሁ። ቁልፍ ቃላት ወንዝ ተፋሰስ የውሃ ተፋሰስ ሥርዓት ማለት ወንዞች እና ገባሮዎቻቸው የሚፈሱበት አቅጣጫ እና መዳረሻ ማለት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ሶስት ዋና ዋና የተፋሰስ ስርዓቶች አሏት፡፡ እነርሱም፡- 1. ወደ ሜድትራንያን ባህር የሚፈሱ ወንዞች- እነዚህ ወንዞች ድንበር ተሻጋሪ ሲሆኑ ወደ ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ ይፈሳሉ፡፡ ለምሳሌ- ተከዜ፣ አባይ እና ባሮ 2. ወደ ህንድ ውቅያኖስ የሚፈሱ ወንዞች- እነዚህ ወንዞች ወደ ደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ ይፈሳሉ፡፡ ለምሳሌ- ዋቢ ሸበሌ እና ገናሌ 3. በስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚቀሩ ወንዞች- እነዚህ ወንዞች በመሀል ሀገር የሚቀሩ ናቸው፡፡ ለምሳሌ- ጊቤ እና አዋሽ 86 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ በሥዕል 3.15 ላይ ዋና ዋና የኢትዮጵያ ወንዞች ተፋሰሶች ይታያሉ:: በካርታው ላይ የሚታዩት የወንዝ ተፋሰሶች የሚሸፍኑትን ቦታ በጥንቃቄ ተመልከቱ፡፡ ሥዕል 3.15 የኢትዮጵያ ወንዝ ተፋሰሶች 87 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ ዋና ዋና የወንዝ ዓይነቶችና ባሕርያቸው በኢትዮጵያ የሚገኙ ዋና ዋና ወንዞች በሁለት ይከፈላሉ፡፡ እነርሱም፡- 1. ድንበር ተሸጋሪ፣ለምሳሌ፣ አባይ፣ ተከዜ እና ባሮ ናቸው፡፡ 2. ሀገር ውስጥ የሚቀሩ፣ለምሳሌ፣አዋሽ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ወንዞች የሚከተሉት ባህርያት አላቸው፡፡ 1. አብዛኛኞቹ ወንዞች የሚመነጩት ከከፍተኛ ቦታ ነው፡፡ 2. አብዛኞቹ ወንዞች ፏፏቴ አላቸው፡፡ 3. እንደ ዓለም አቀፍ ድንበር ያገለግላሉ፡፡ መልመጃ 3.11 አጭር መልስ ስጡ፡፡ 1. ወደ ሜድትራንያን ባህር የሚፈሱ የኢትዮጵያ ወንዞችን ዘርዝሩ፡፡ 2. በስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚቀሩ ወንዞች እነ ማን ናቸው? 3. የኢትዮጵያ ወንዞች ባህርያትን ጥቀሱ፡፡ 3.2.8 የማዕድን ሀብቶች አጥጋቢ የመማር ብቃት ተማሪዎች ይህን ትምህርት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡- በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ማዕድናትንና በአጠቃቀም ምክንያት የሚፈጠሩ አካባቢያዊ ችግሮችን ትተነትናላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት ማዕድናት ዘላቂ ጥቅም የማነቃቂያ ጥያቄ በኢትዮጵያ ዉስጥ የሚገኙ ማዕድናትን ዘርዝሩ፡፡ 88 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ ማዕድናት በጠጠር፣ በፈሳሽና በጋዝ መልክ በመሬት ላይና ውስጥ፣ በውሃ ውስጥና ስር ይገኛሉ፡፡በሀገራችን ኢትዮጵያ በርካታ ማዕድናቶች ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም መካከል ወርቅ ፣ብር፣ መዳብ፣ ታንታለም፣ሊድ፣ ኦፓል፣ ብረት፣ የከሰልድንጋይ፣ የነዳጅ ዘይት የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ እነዚህ ማዕድናት ዘላቂና ዘላቂ ባልሆነ መልኩ ለጥቅም ሲውሉ ይስተዋላል፡፡ ሥዕል 3.16 ማዕድናት ዘላቂ የማዕድን አጠቃቀም የቡድን ውይይት 3.8 ዓላማ ዘላቂ የማዕድን አጠቃቀም ዘዴዎችን ማሳወቅ 1. በኢትዮጵያ ዘላቂ የማዕድን ሀብት አጠቃቀም ላይ ተወያይታችሁ ለክፍል ተማሪዎች አስረዱ፡፡ ዘላቂ የማዕድን አጠቃቀም ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ጥናት ተደርጎ አካባቢዉን በማይጎዳ ሁኔታ ማዕድናት የማምረት ዘዴ ነው፡፡ ዘላቂ የማዕድን አጠቃቀም ዘዴዎች ከሰው ጉልበት ይልቅ ዘመናዊ መሣሪያዎችን ይጠቀማሉ፡፤ በሳይንሳዊ ጥናት ላይ የተመሠረቱ ናቸው፡፡ ማዕድናቶች እንዳይባክኑ እና በተሻለ ጥራት እንዲመረቱ ያስችላሉ፡፡ አካባቢን በማይጎዳ እና በማይበክል መልኩ ይከናወናሉ፡፡ ዘላቂ ያልሆነ የማዕድናት አጠቃቀም ያለ ሳይንሳዊ ጥናት ሰዎች በልምድ እና በግምት ቁፈራ ማዕድን የሚያወጡበት ስልት ነዉ፡፡ ዘላቂ ያልሆነ የማዕድን አጠቃቀም ዘዴዎች የሰው ጉልበት ይጠቀማሉ፡፡ በልምድ እና በግምት ቁፈራ ላይ የተመሠረቱ ናቸው፡፡ 89 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ ማዕድናቶቹ ላይ ብክነት እና የጥራት ጉድለት ይስተዋላል ፡፡ አካባቢ ላይ የተለያዩ ችግሮችን ያስከትላሉ፡፡ ዘላቂ ያልሆነ የማዕድናት አጠቃቀም የሚያስከትላቸዉ አካባቢያዊ ችግሮች የመሬት ገፅታ መጎሳቆል፣ የውሃ ማቆር፣ የአየር ብክለት፣ የአፈር መሸርሸር፣ የውሃ ብክለት፣ የሰው ህይወት መጥፋት ሊያስከትል ይችላል፡፡ የሰው ህይወት መጥፋት፡-በቁፈራ ወቅት የመሬት መደርመስ ሊያጋጥም ይችላል:: በዚህ ወቅት የሰው ህይወት ሊጠፋ ይችላል፡፡ የውሃ ማቆር፡- ማዕድናት ሲመረቱ መሬቱ በጥልቀት ስለሚቆፈር ጉድጓድ ይፈጠራል፡፡ዝናብ በሚዘንብበት ወቅት ጉድጓዱ ውሃ ያቁራል፡፡ የአፈር መሸርሸር፡- በቁፈራ ወቅት አፈሩ አንድ ቦታ ላይ ይከማችና ዝናብ ሲዘንብ በጎርፍ ይጠረጋል፡፡ መልመጃ 3.12 ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ፡፡ 1. በኢትዮጵያ የሚገኙ ማዕድናትን ዘርዝሩ፡፡ 2. በማዕድናት አጠቃቀም ዙሪያ የሚፈጠሩ አካባቢያዊ ችግሮችን ግለፁ፡ 3.2.9 የዱር ሀብቶች አጥጋቢ የመማር ብቃት ተማሪዎች ይህን የትምህርት ይዘት ተምረው ሲያጠናቅቁ፡- በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ጉዳዮችን ይገልጻሉ፡፡ ቁልፍ ቃላት ብርቅዬ እንስሳት የዱር እንስሳት የማነቃቂያ ጥያቄ የዱር ሀብት ምንድን ነው? 90 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ በኢትዮጵያ የተለያዩ ከፍታና የተለያየ የአየር ንብረት ያላቸው ስፍራዎች አሉ፡፡በእነዚህ የተለያዩ አካባቢዎች የተለያዩ እንስሳትና ተክሎች ይኖራሉ፡፡እነዚህም የዱር ሀብቶች ይባላሉ፡፡ ለምሳሌ፦ በኢትዮጵያ በርካታ የዱር እንስሳት ይገኛሉ፡፡በዱር የሚኖሩና በሰው ለማዳ እንዲሆኑ ያልተደረጉ የተለያዩ ወፎች፣አጥቢዎች፣ተራማጅና ተሳቢ እንስሳት ሁሉ የዱር እንስሳት በመባል ይታወቃሉ፡፡ ለምሳሌ ቀይ ቀበሮ፣ አንበሳ፣ ጅብ፣ ሚዳቋ፣ ቀጭኔ፣ ቁራ፣ ንስር አሞራ፣ርግብ፣የሌሊትወፍ፣ የመስቀል ወፍ፣ አዞና ጉማሬ የመሳሰሉት የዱር እንስሳት ናቸው፡፡ ብርቅዬ የዱር እንስሳት (የደጋ አጋዘን) ሥዕል 3.17በኢትዮጵያ የሚገኙ ብርቅዬ የዱር እንስሳት 91 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ ብርቅዬ እንስሳት በኢትዮጵያ ብቻ ተገድቦ የሚኖር የእንስሳት ዝርያ ማለትነው፡፡ ብርቅዬ እንስሳትና መገኛቸው ሠንጠረዥ3.1 በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኙ የዱር እንስሳት ስምና መገኛ ተ.ቁ የዱር እንሰሳው ስም የሚገኝበት ብሔራዊ/ ጥብቅ ክልል 1. ዋልያ አይቤክስ በስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ 2. የደጋ አጋዘን (ኒያላ) በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ 3. ጭላዳ ዝንጀሮ በስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ 4. የምኒልክ ድኩላ በስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክና በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ 5. ቆርኬ በነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ በሰንቀሌ ጥብቅ ክልል 6. ቀይ ቀበሮ በስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክና በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ 7. የዱር አህያ በያንጉዲ ራሳ ብሔራዊ ፓርክ (አፋር) በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ አዕዋፋት፡-ነጭ ፔሊካን፣ፍላሚንጎ፣ዝይና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ነጭ ፔሊካን ፍላሚንጎ ዝይ ሥዕል 3.17 ብርቅዬ አዕዋፋት 92 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ የዱር እንስሳትን መመናመን የሚያባብሱ መንሥኤዎች የማነቃቂያ ጥያቄ በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ላይ ተጽዕኖ የሚያደርሱ መንስኤዎችን ጥቀሱ፡፡ የኢትዮጵ የዱር እንስሳት ሃብት በቁጥርም ሆነ በአይነቱ እጅግ ከፍተኛ በሆነ ፍጥነት እየቀነሰ ነው፡፡ እንዲያውም ጥቂት የእንስሳት ዝርያዎች ጨርሰው ሊጠፉ ተቃርበዋል:: ለምሳሌ፦ ብርቅዬ እና ብቸኛ እንስሳት እንደ ዋልያ፣ የሰሜን ቀበሮ፣ ኒያላ የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ ስለመጣው የዱር እንስሳት መጥፋት የሚከተሉት ምክንያቶች በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ 1. በእርሻ መሬቶች መስፋፋት እንዲሁም በከተሞችና በኢንዲስቱሪዎች ፈጣን እድገት የተነሳ በደን መመንጠር የዱር እንስሳት መካነ ህይወት ይወድማል 2. የእንስሳቱን ስጋ፣ ቆዳ፣ ፀጉር፣ቀንድና ጥርስ ለማግኘት ሲባል የሚፈፀም ህገ-ወጥ አደን የእንስሳቱ ቁጥር እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ 3. የግጦሽ መሬትችን የማስፋፋት ተግባር የዱር እንስሳትን መካነ-ህይወት እያጣበበ ይመጣል፡፡ 4. በየጊዜው የሚከሰት ሰደድ እሳት እንስሳቱ እንዲሰደዱ ያደርጋል፡፡ 5. የድርቅ በየጊዜው መደጋገም፣ በውሃና ምግብ ላይ እጥረት ቦታ መፈጠር፣ ከቤት እንስሳት ጋር መዳቀል (ለምሳሌ-ቀይ ቀበሮ ከውሻ ጋር) በምክንያት ይጠቀሳሉ፡፡ ዋና ዋና ተጋላጭ ብርቅዬ እንስሳት የሰሜን ቀበሮ፣ ዋልያ አይቤክስ፣እና የደጋ አጋዘን ናቸው:: 93 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ መልመጃ 3.13 1. የሚከተለውን ሠንጠረዥ በደብተራችሁ ሠርታችሁ የተዘረዘሩትን የዱር እንስሳት ብርቅዬ የሆኑና ብርቅዬ ያልሆኑትን በመለየት ይህን ምልክት() በማስቀመጥ መልሶቻችሁን ለመምህራችሁ አሳዩ፡፡ የዱር እንስሳት ብርቅዬ የሆኑ ብርቅዬ ያልሆኑ ቀይ ቀበሮ ጉማሬ አንበሳ የምኒሊክ ድኩላ ንስር አሳ ወጊ ጅብ አዞ ኒያላ ዝይ የሌሊት ወፍ 2. በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኙ የዱር እንስሳት ስምና መገኛ ግለጹ፡፡ 3.በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ላይ ተጽዕኖ የሚያደርሱ መንስኤዎችን ዘርዝሩ፡፡ 3.2.10 የጉልበት ምንጭ ዓይነቶች አጥጋቢ የመማር ብቃት ተማሪዎች ይህን ትምህርት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡- የኢትዮጵያን ዋና ዋና የጉልበት ምንጮችን ትዘረዝራላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት ታዳሽ ታዳሽ ያልሆኑ የማነቃቂያ ጥያቄ በአካባቢያችሁ ምን ዓይነት የጉልበት ምንጮች አሉ? 94 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ ጉልበት ከተለያዩ ምንጮችና በተለያየ ሁኔታ እንደሚገኝ በምዕራፍ ሁለት ተምራችኋል፡፡ በዚህ ንዑስ ርዕስ ስር ደግሞ በኢትዮጵያ ታዳሽና ታዳሽ ያለሆኑ የጉልበት ምንጮችን ትማራላችሁ፡፡ በሀገራችን ብዙ ዓይነት የጉልበት ምንጮች አሉ፡፡ እነዚህም ውሃ፣ ነዳጅ፣ የፀሐይ ብርሃን፣ ነፋስ፣ ምግብ፣ የድንጋይ ከሰል እና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡ ለምሳሌ፡-የምንመገበው ምግብ የሙቀት፣ ለመንቀሳቀስ ወይም ዕቃ ለማንሳት የሚያስችለንን ጉልበት ይሰጠናል፡፡ የፀሐይ ብርሃን የሙቀት፣ የኤሌክትሪክና የመሳሰሉትን ጉልበት ይሰጠናል፡፡ ከባትሪ ድንጋይ ደግሞ የብርሃን ወይም የድምፅ ጉልበትን እናገኛለን፡፡ የጉልበት ምንጭ ዓይነቶች ታዳሽና ታዳሽ ያልሆኑ ተብለው በሁለት ይመደባሉ፡፡ ታዳሽና ታዳሽ ያልሆኑ የጉልበት ምንጮች ባህርያት አጥጋቢ የመማር ብቃት ተማሪዎች ይህን ትምህርት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡- የኢትዮጵያን ታዳሽና ታዳሽ ያልሆኑ የጉልበት ምንጮችን ትለያላችሁ ታዳሽ የጉልበት ምንጮች ታዳሽ የጉልበት ምንጮች የሚባሉት በየጊዜው ራሳቸውን በተፈጥሯዊ መንገድ ሊተኩ የሚችሉ ሀብቶች ናቸው፡፡ እነዚህን የጉልበት ምንጮች በስርዓትና በአግባቡ መጠቀም አለብን፡፡ ታዳሽ የጉልበት ምንጮች የፀሐይ ብርሃን፣ ውሃ፣ አየር፣ የከርሰ ምድር እንፋሎት እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ሥዕል 3.18 ታዳሽ የሆኑ የጉልበት ምንጮች 95 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ ታዳሽ ያልሆኑ የጉልበት ምንጮች ታዳሻ ያልሆኑ የጉልበት ምንጮች በተፈጥሮ በተወሰነ መጠን ብቻ የሚገኙና ራሳቸውን ሊተኩ የማይችሉ ሀብቶች ናቸው፡፡ እነዚህ የጉልበት ምንጮች በአግባቡ ካልተጠቀምንባቸው ተሟጠው ያልቃሉ፡፡ስለዚህ በስርዓት እና በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ ታዳሽ ያልሆኑ የጉልበት ምንጮች ፦ነዳጅ ድፍድፍ ዘይት፣ የከሰል ድንጋይ፣ የተፈጥሮ ጋዝ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ሥዕል 3.19 ታዳሽ ያልሆኑ የጉልበት ምንጮች መልመጃ 3.14 በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የጉልበት ምንጮች ታዳሽና ታዳሽ ያልሆነ ብላችሁ ይህን ምልክት () በመጠቀም አመልክቱ ተ/ቁ የጉልበት ምንጭ ታዳሽ ታዳሽ ያልሆነ 1 አየር 2 ምግብ 3 የተፈጥሮ ዘይት 4 የድንጋይ ከሰል 5 የከርሰ ምድር እንፋሎት 6 እንጨት 96 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ 3.2.11 ዋና ዋና ከባቢያዊ ችግሮች አጥጋቢ የመማር ውጤት ተማሪዎች ይህን ትምህርት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡- በኢትዮጵያ በተፈጥሮ አካባቢ ላይ የሚስተዋሉ ዋና ዋና ችግሮችን ትዘረዝራላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት ድርቅ በረሃማነት በአካባቢያችን ውስጥ የተለያዩ ሰው ስራሽ እና የተፈጥሮ ችግሮች ይከሰታሉ፡፡ ከባቢያዊ ችግሮች የሚባሉት በድንበር ያልተወሰኑ እና በአካባቢ ያልተገደቡ ዓለም ዓቀፍ ባህርይ ያላቸው ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮ ክስተቶች ናቸው፡፡ በኢትየጵያ ዋና ዋና ከባቢያዊ ችግሮች የሚባሉት፡- 1. የአየር ንብረት ለውጥ 2. የበረሀማነት መስፋፋት 3. የብዝሀ-ህይወት መቀነስ 3.2.12 የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምና ጥበቃ የንዑስ ርዕሱ አጥጋቢ የመማር ውጤት ተማሪዎች ይህን ትምህርት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡- በኢትዮጵያ ዋና ዋና የአካባቢ ብክለት መንሥኤዎችን በማብራራት አማራጭ መፍትሄዎችን ትሰጣላችሁ፡፡ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ማለት በተፈጥሮ ያለው ሀብት በብዛትም ሆነ በጥራት እንዳይበዘበዝ መንከባከብ እና በአግባቡ መጠቀም ማለት ነው፡፡ የተፈጥሮ ሀብት ተፈጥሮውን ተጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ መተላለፍ ይኖርበታል፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለው ሁሉም የተፈጥሮ ሀብቶች- ውሀ፣ አፈር፣ አየር፣ ደኖች፣ እጽዋት፣ የዱር እንስሳትና ማዕድናት የተፈጥሮ ባህርያቸው ጠብቀን ስንገለገልባቸው ነው፡፡ 97 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ የአካባቢ ብክለት ብክለት የተፈጥሮንና ሰው ሰራሽ ሀብቶችን የተፈጥሮ ይዘታቸውን ማጥፋት ወይም ወደ ሌላ ይዘት መቀየር ነው፡፡ ዋና ዋና የብክለት ዓይነቶች የአየር፣ የአፈር እና የውሃ ናቸው፡፡ የቡድን ውይይት 3.9 መመሪያ፡- በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ አምስት አምስት ሁናችሁ ተወያይታችሁ በተወካዮቻችሁ አማካኝነት ለክፍል ጓደኞቻችሁ አቅርቡ፡፡ አቅርቡ፡፡ መልመጃ 3.15 ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ፡፡ 1. በኢትዮጵያ ውስጥ የአየር፣ የአፈር፣ የውሃና የድምፅ ብክለት መንሰዔዎች ምንድን ናቸው? 2. የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የሚያስችሉ መፍትሄዎችን ዘርዝሩ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ዋና ዋና የብክለት መንስኤዎች የከተሞች እና የኢንዱስትሪ መስፈፋት ሰፋፊ የግብርና እንቅስቃሴዎች ነዳጅን በስፋት መጠቀም(ለባለሞተር ተሽከርካሪዎች፣ለማብሰያ፣ እና ለቀላል ማሽኖች) ከፋብርካዎች ወደ አካባቢ የሚለቀቁ የተበከሉ ጋዞች እና ኬሚካሎች የተለያዩ የፕላስቲክ ምርቶች እና ተረፈ ምርቶች(ፌስታሎች እና የውሃ ማሸጊያዎች) የአካባቢ ብክለት ውጤቶች የአካባቢ ብክለት በጤና፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃዎች ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡ በኢትዮጵያ የአካባቢ ብክለት ከሚያስከትላቸው ውጤቶች ዋና ዋና የሚከተሉት ናቸው፡፡ የጤና መታወክ(የልብ ድካም፣ ጉንፋን፣አስም፣ የአተነፋፈስ ችግር፣ የአይን ፣ የአፍንጫ እና ጉሮሮ መቆጣት) ድርቅ እና ረሀብ ናቸው፡፡ 98 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የሚወሰዱ መፍትሄዎች የተፈጥሮ ሀብትን በአግባቡ መጠቀም እና መንከባከብ መልሶ መጠቀም ፕላስቲኮችን እና ተረፈ ምርቶችን በአግባቡ መጠቀም እና በአግባቡ ማስወገድ ዛፎችን መትከል እና መንከባከብ ናቸው፡፡ መልመጃ 3.16 ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ፡፡ 1. ዋና ዋና ከባቢያዊ ችግሮች የሚባሉትን ዘርዝሩ፡፡ 2. የተፈጠሮ ሀብት ጥበቃ ማለት ምን ማለት ነው? 3. የአካባቢ ብክለት መንስዔዎችን ጥቀሱ፡፡ 4. የአካባቢ ብክለት እንዳይከሰት ሊወሰዱ የሚችሉ መፈትሔዎችን ዘርዝሩ፡፡ የቁልፍ ቃላት ፍቺ ድነና-ደን ባልነበረበት ሥፍራ ላይ ዛፎችን በመትከል በደን ማልበስ መልሶ ድነና- ደን ተመንጥሮ በወደመበት ሥፍራ ዛፎችን በመትከል ዳግመኛ በደን ማልበስ፡፡ በረሀማነት- ቀደም ሲል ለም የነበሩ ሥፍራዎች ሰው ሰራሽ በሆኑ መንገዶች ወደ ምድረበዳነት የመለወጥ ሂደት ነው፡፡ ደን- በትላልቅ ዛፎች የተሸፈነ መሬት ቅምብብማ ዕፅዋት- ዘራቸው በኮን የተሸፈነ አበባ የሌላቸው ዕፅዋት ቁጥቋጦ- መካከለኛ ቁመትና ጠንካራ ግንድ ያላቸው ዕፅዋት ኩታ ገጠም- ፊት ለፊት ብርቅዬ- በአንድ አካባቢ ብቻ የሚገኝ እንስሳትና ዕፅዋት 99 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ የምዕራፉ ማጠቃለያ በአንድ አካባቢ የሚስተዋል የዕለቱ የአየር ሁኔታ የአየር ጠባይ ይባላል፡፡ የአየር ንብረት ማለት በአንድ ቦታ የሚስተዋል ለረጅም ዘመናት የሚቆይ አማካይ የአየር ጠባይ ነው፡፡ የአየር ንብረት ተቆጣጣሪዎች የሚባሉት፡-ኬክሮስ፣ ከፍታ፣ ከባህር ያለው ርቀት፣ ቀለይ ሞገድ፣ ነፋስ እና ደመና ናቸው፡፡ የአፈር አይነቶች ሦስት ሲሆኑ፤እነርሱም አሸዋማ አፈር፣የሸክላ አፈርና ለም አፈር ናቸው፡፡ ዕፅዋት የፀሐይ ብርሃንን በመጠቀም የራሳቸውን ምግብ ማዘጋጀት የሚችሉ ህይወት ያላቸው ነገሮች ናቸው፡፡ የደን መጨፍጨፍ የአፈር መሸርሸር፣የዱር እንስሳት መሰደድ እና የአየር ንብረት መዛባትን ያስከትላል፡፡ በኢትዮጵያ የውሃ ሃብት ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ሁኔታዎች የዝናብ መቀነስ፡ የውሃ ብክነት እና የውሃ ብክለት ናቸዉ፡፡ በሃገራችን ኢትዮጵያ እንደ ወርቅ፣ ብር፣ ነሃስ፣ መዳብ፣ ታንታለም፣ ኦፓል የመሳሰሉት ማዕድናት ይገኛሉ፡፡ዘላቂ ያልሆነ የማዕድናት አጠቃቀም በአካባቢ ላይ የተለያየ ችግር ያስከትላል፡፡ በአንድ ሀገር ብቻ የሚኖሩ የዱር እንስሳት ብርቅዬ የዱር እንስሳት ይባላሉ፡፡ ዋና ዋና ከባቢያዊ ችግሮች የሚባለሉት የአየር ንብረት ለውጥ፣ የድርቅ መከሰት፣ የበረሀማነት መስፋፋት፣ የብዝሀ-ህይዎት መቀነስ፣ አሲዳማ ዝናብ መዝነብ፣ የዓለም ሙቀት መጨመር፣ የበረዶ መቅለጥ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ 100 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ የምዕራፉ ማጠቃለያ መልመጃ I. የሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል ካለሆኑ ሐሰት በማለት መልሶቻችሁን በደብተራችሀ ላይ ፃፉ፡፡ 1. የአየር ንብረት ማለት የአየር ጠባይ ማለት ነው፡፡ 2. ከፍታ ሲጨምር የአየር ሙቀት ይቀንሳል፡፡ 3. ሊተኩ የማይችሉ የተፈጥሮ ሀብቶች ታዳሽ የሆኑ የተፈጥሮ ሀብቶች ናቸው፡፡ 4. ዕፅዋት የራሳቸውን ምግብ ያዘጋጃሉ፡፡ 5. ቅምብብማ ዕፅዋት ከአበባማ ተክሎች ይመደባሉ፡፡ 6. ሳረንስቶች በጾታዊ የአረባብ ዘዴ ይራባሉ፡፡ 7. የደን መጨፍጨፍ ለአፈር መሸርሸር መንስዔ ነው፡፡ 8. የአፈር ዓይነቶች በቅንጣቲት መጠናቸው ይለያያሉ፡፡ II. በ ሀ ስር የተዘረዘሩትን ዋና ዋና የውሃ ተፋሰሶች በ ለ ስር ካሉት ወንዞች ጋር በማዛመድ መልሶቻችሁን በተሰጠው ቦታ ላይ ፃፉ፡፡ ሀ ለ 1. ሜድተራንያን ባህር ሀ. አዋሽ 2. ህንድ ውቅያኖስ ለ. ተከዜ 3. ስምጥ ሸለቆ ሐ. ገናሌ III. የሚከተሉትን ጥያቄዎች በደብተራችሁ ከጻፋችህ በኋላ ከተሰጡት አማራጮች ውሰጥ ትክክልኛውን መልስ የያዘውን ሆሄ ምረጡ፡፡ 1. ከሚከተሉት ማዕድናት ውስጥ በኢትዮጵያ የሚገኘው የቱ ነው? ሀ. ወርቅ ለ. መዳብ ሐ. ኦፓል መ. ሁሉም 2. ለተክሎች ዕድገት ተስማሚ የሆነው የአፈር ዓይነት የቱ ነው? ሀ. አሸዋማ አፈር ለ. ለም አፈር ሐ. የሸክላ አፈር መ. ሁሉም 3. ከሚከተሉት ውስጥ የአየር ንብረት ይዘት ያልሆነው የቱ ነው ? ሀ. ሙቀት ለ. ዝናብ ሐ. ደመና መ. ኬክሮስ 4. በኢትዮጵያ የከፍታ ቦታዎች ሀይቅ የሆነው የቱ ነው? ሀ. ሐዋሳ ለ. ላንጋኖ ሐ. ጣና መ. አባያ 5. ከሚከተሉት ውስጥ የአየር ንብረት ተቆጣጣሪ የሆነው የቱ ነው? ሀ. ቀለይ ሞገድ ለ. ንፋስ ሐ. ደመና መ.ሁሉም 101 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ 6. ከሚከተሉት ዕፅዋቶች ውስጥ በኢተዮጵያ ሀገር በቀል ያልሆነው የቱ ነው? ሀ. ኮሶ ለ. ዝግባ ሐ. ባህር ዛፍ መ. ግራር 7. መካከለኛ ቁመትና ጠንካራ ግንድ ያላቸው የዕፅዋት ዓይነቶች የትኞቹ ናቸው? ሀ.ቁጥቋጦዎች ለ.ዛፎች ሐ. አዝዕርቶች መ.የጓሮ አትክልቶች 8. ከሚከተሉት ውስጥ የአፈር መሸርሸር መንስዔ ያልሆነው የቱ ነው? ሀ. የደን መጨፍጨፍ ሐ. የግጦሽ መሬትን ከመጠን በላይ ማስጋጥ ለ. ቁልቁል ማረስ መ. አግድም ማረስ 9. ከፀሐይ ምን ዓይነት ጉልበት ሊገኝ ይችላል? ሀ. የሙቀት ለ. የብርሀን ሐ. የኤሌክትሪክ መ. ሁሉም 10.ዘር ያላቸው ነገር ግን አበባ የሌላቸው የዕፅዋት ዓይነቶች የትኞቹ ናቸው? ሀ. ሳረንሰቶች ሐ. ፈረኖች ለ. ቅምብብማ ዕፅዋት መ. አበባማ ዕፅዋት 11.ከሚከተሉት ውስጥ ታደሽ የተፈጥሮ ሀብት የቱ ነው? ሀ. የድንጋይ ከሰል ለ. ነፋስ ሐ. ማዕድን መ. ነዳጅ 12.ከሚከተሉት የዱር እንስሳት ውሰጥ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኝ እንስሳት የቱ ነው? ሀ. ቀጭኔ ለ. ጉማሮ ሐ. ኒያላ መ. ዝሆን VI. የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሱ፡፡ 1. በኢትዮጵያ የውሃ ሀብት ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ሁኔታዎችን ዘርዝሩ፡፡ 2. በኢትዮጵያ ውሰጥ ብቻ የሚገኙ የዱር እንስሳት ስምና መገኛ ግለፁ፡፡ 3. ውጤታማ የውሃ ሀብት አጠቃቀም ዘዴዎች ለምን ያገለግላሉ፡፡ 4. ዘላቂ ያልሆነ የማዕድናት አጠቃቀም የሚያስከትላቸውን አካባቢያዊ ችግሮች ዘርዝሩ፡፡ 5. በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ላይ ተፅዕኖ የሚያደርሱ መንስኤዎችን ዘርዘሩ፡፡ 102 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ ሶስት ተፈጥሮአዊ አካባቢ ፍተሻ ልታከናውናቸው የምትችሏቸውን ተግባራት ለመግለፅ ይህን ()ምልክት በሳጥኖቹ ውስጥ በማኖር አመልክቱ፡፡ በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች የሚታየውን ወቅታዊ የሙቀት መጠን ልዩነት እገልጻለሁ፡፡ የሙቀትና የዝናብ መጠንን የመለካትና መረጃን መዝግቦ የመያዝ ክህሎት አዳብራለሁ፡፡ ኢትዮጵያ በሐሩር ሞቃታማ የአየር ንብረት ክልል ከሚገኙ ሀገራት የተለየ የአየር ንብረት የምታሳይበትን ምክንያቶች እተነትናለሁ፡፡ በኢትዮጵያ ዋና ዋና የአየር ንብረትን የሚቆጣጠሩ ነገሮችን እለያለሁ፡፡ የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብት ዓይነቶች እለያለሁ፡፡ የኢትዮጵያን የአፈር ዓይነቶችና የአፈር መሸርሸርን እገልጻለሁ፡፡ በኢትዮጵያ የተለመዱ የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ዘዴዎችን እለያለሁ፡፡ በኢትዮጵያ የሚበቅሉ የዕፅዋት ዓይነቶችን እለያለሁ፡፡ ውጤታማ የውሃ ሀብት አጠቃቀ?