Grade 10 Amharic Textbook PDF

Document Details

DeadOnHeliotrope3862

Uploaded by DeadOnHeliotrope3862

Ethiopian Civil Service University

2014

Anaanya Dersso Adugna, Destawu Andarge Ashemafi, Getahun Siyum Belechaw, Mesfin Defresu W/Medhin, Daniel Asrat Mengiste, Fasil Bezuneh Bekele, T'nbit Girma Haylu, Frehiwot Assefa Kebbede, Getachew Tal

Tags

amharic language ethiopian education grade 10 textbook

Summary

This Amharic textbook for grade 10 covers a range of topics related to language, society, and culture in Ethiopia. The book includes chapters on communication, writing, and social interaction.

Full Transcript

Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ቋንቋ የተማሪ መጽሐፍ አስረኛ ክፍል ፲ኛ ክፍል Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ቋንቋ የተማሪ መጽሐፍ ፲ኛ ክፍል የአዲስ አበ...

Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ቋንቋ የተማሪ መጽሐፍ አስረኛ ክፍል ፲ኛ ክፍል Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ቋንቋ የተማሪ መጽሐፍ ፲ኛ ክፍል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአዘጋጆች አናንያ ደርሶ አዱኛ ደስታው አንዳርጌ አሸናፊ ጌታሁን ስዩም በላቸው ገምጋሚዎችና አርታኢዎች መስፍን ደፈረሱ ወ/መድኅን ዳንኤል አስራት መንግስቴ ፋሲል ብዙነህ በቀለ ትንቢት ግርማ ሃይሉ ጥራት ተቆጣጣሪና ገምጋሚ ፍሬህይወት አሰፋ ከበደ አስተባባሪ ጌታቸው ታለማ አቀማመጥ እና ስዕል እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ (TMS) Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website ©የመጽሐፉ ሀጋዊ ቅጂ ባለቤት 2014 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ነው፡፡ ምስጋና ይህን የትምህርት መጽሐፍ ከዝግጅት ጀምሮ በከተማችን በሚያስተምሩ መምህራን እንዲዘጋጅ በማድረግ፣አስፈላጊውን በጀት በማስፈቀድ እንዲሁም በጥብቅ ዲስፕሊን እንዲመራ ላደረጉት ከፍተኛ ሙያዊና አስተዳደራዊ ድጋፍ ላደረጉት ለትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ፣እንዲሁም የዝግጅቱ ስራ ቁልፍ ስራ መሆኑን ተረድተው ትኩረት በመስጠት በሚያጋጥሙ ችግሮች መፍትሄ በመስጠት፣ የአፈጻጸም ሂደቱን በመከታተል፣በመገምገም ሁሌም ከጎናችን ለነበሩ የትምህርት ቢሮ የማኔጅመንት አባላት የስርዓተ ትምህርት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ ፣ የትምህርት ቴክኖሎጂ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኛው ገብሩ፣ የመምህራን ልማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ ለትምህርት ቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ ፣ ለትምህርት ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ ፣ለቴክኒክ አማካሪ አቶ ደስታ መርሻ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡ በመጨረሻም መጽሐፉ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን ለአዘጋጅ መምህራን ከዚህ በላይ ስራ የለም በማለት ፍቃድ በመስጠትና የሞራል ድጋፍ ስላደረጋችሁ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website ማውጫ ይዘት ገፅ መግቢያ_________________________________________________iv ምዕራፍ አንድ (፩) ቋንቋና ማህበረሰብ____________________________1 ምዕራፍ ሁለት (፪) ባህላዊ ጋብቻ_____________________________14 ምዕራፍ ሶስት (፫) ሴቶች እና እድገት__________________________31 ምዕራፍ አራት (፬) በልዩነት ውስጥ ያለ አንድነት___________________48 ምዕራፍ አምስት (፭) የቋንቋ ለዛ_______________________________66 ምዕራፍ ስድስት (፮) የታላላቆች ሚና___________________________85 ምዕራፍ ሰባት (፯) ረጅም ልቦለድ_____________________ ______101 ምዕራፍ ስምንት (፰) ማህበራዊ መገናኛ ብዙኀን__________________118 ምዕራፍ ዘጠኝ (፱) ሥራ ፈጠራ_____________________________137 አባሪዎች_______________________________________________152 ዋቢ ጽሑፎች___________________________________________152 ሙዳዬቃላት____________________________________________154 ፈሊጣዊ አነጋገር_________________________________________155 የኢትዮጵያ ቁጥሮች ______________________________________157 የአማርኛ የፊደል ገበታ_____________________________________157 Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website መግቢያ የቋንቋ ትምህርት ዋነኛ ዓላማ የተማሪዎችን የማዳመጥ፣ የመናገር፣ የማንበብ እና የመጻፍ ክሂልን ማዳበር፣ እንዲሁም የዕውቀት ዘርፍ የሆኑትን የስነ ጽሁፍ እና የስነልሳን ዕውቀትን ማዳበር ነው፡፡ እነዚህን ዓላማዎች ለማሳካት በመርሀ ትምህርቱ ላይ የማዳመጥ፣ የመናገር፣ የማንበብ እና የመጻፍ ክሂልን ለማዳበር፣ እንዲሁም የቃላት እና የሰዋስው ዕውቀትን ለማጎልበት የሚያስችሉ ይዘቶች ተካተዋል፡፡ የቋንቋን ትምህርት ዋነኛ ዓላማዎች ለማሳካት ከሚያስችሉ የማስተማሪያ መሳሪያዎች ውስጥ አንዱ የተማሪው መማሪያ መጽሐፍ ነው፡፡ የተማሪው መማሪያ መጽሐፍ እንዲለወጥ ወይም በአዲስ መልክ እንዲዘጋጅ የሚያስችሉ በርካታ ነገሮች አሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ አንዱ የመርሀ ትምህርት ማሻሻል ወይም ለውጥ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ይህ አዲስ የመማሪያ መጽሐፍ እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡ ይህ የአስረኛ ክፍል መማሪያ መጽሐፍ በመርሀ ትምህርቱ ላይ ትኩረት የተሰጣቸውን ነገሮች ሙሉ በሙሉ እንዲያካትት ተደርጓል፡፡ ምንባቦቹና ማብራሪያዎቹ ግልጽና ሳቢ በሆነ መልኩ እንዲካተቱ ተደርገው የተዘጋጁ ናቸው፡፡ በመጨረሻም ለመጽሐፉ ዝግጅት ጽሁፎችን በመስጠት የተባበሩትን እያመሰገንን ስለመጽሀፉ ከመምህራን፣ ከተማሪዎች እና ከሌሎች አካላት የሚቀርበውን አስተያየት ለመቀበል ዝግጁ መሆናችንን እንገልጻለን፡፡ iv Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል አማርኛ ፲ኛ ክፍል ምዕራፍ አንድ (፩) ቋንቋና ማህበረሰብ የምዕራፉ አጠቃላይ ዓላማዎች፡- ተማሪዎች ይህንን ትምህርት ካጠናቀቃችሁ በኋላ፡- መረጃዎችን በማዳመጥ ትወያያላችሁ፡፡ ውይይት በማድረግ የተገኘውን ውጤት በቃል ታንፀባርቃላችሁ፡፡ ሰፊ ርዕሰ-ጉዳይን የያዘ ጽሁፍ በማንበብ ተደራሲያንን ትለያላችሁ፡፡ በጽሁፋችሁ ውስጥ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን ትጠቀማላችሁ፡፡ ድርሰት ትጽፋላችሁ፡፡ ጥምር ቃላት በመመስረት በዓረፍተነገር ውስጥ ትጠቀማላችሁ፡፡ 1 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፩ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል ክፍል አንድ ማዳመጥ ቋንቋ እና ጽሕፈት የቅድመ ማዳመጥ ጥያቄዎች ፩. ቀጥሎ ከቀረቡት ዓረፍተ ነገሮች ውስጥ ለተሰመረባቸው ቃላትና ሀረጋት ዓውዳዊ ፍቻቸውን ስጡ፡፡ ሀ. ቋንቋ ድምጻዊና አንደበታዊ የሰው ልጅ መግባቢያ ነው፡፡ ለ. ስለቋንቋ አጀማመር ሊቃውንት የተለያዩ መላምቶችን ሲሰነዝሩ ኖረዋል፡፡ ሐ. የስነ-ሰብ ተመራማሪዎች የቋንቋ ጥንተ አመጣጥን ጠቅለል አድርገው በሁለት ይከፍሉታል፡፡ መ. ቀለማዊ ሥርዓተ-ጽሕፈት የሳባ ፊደላትን ይጠቀማል፡፡ ፪. ቋንቋና ጽሕፈት ስላላቸው ግንኙነት ግምታችሁን ለክፍል ጓደኞቻችሁ አስረዱ፡፡ የማዳመጥ ሂደት ጥያቄዎች ፩. መምህራችሁ ‹‹ቋንቋ እና ጽሕፈት›› በሚል ርዕስ አንድ ጽሑፍ ያነቡላችኋል፡፡ ምንባቡ ሲነበብ በጥሞና እያዳመጣችሁ ቀጥሎ በቀረቡት ጥያቄዎች ውስጥ የሚገኙ ባዶ ቦታዎችን እንዲሟሉ አድርጓቸው፡፡ ሀ. ሰብአዊ የሆነ ፍጡር ሁሉ ሊግባባበት የሚችል መሳሪያ ነው፡፡ ለ. በጽህፈት ስርዓት የመጀመሪያው የአፃፃፍ ዘዴ ነው፡፡ ሐ. በ እና በ መካከል ተፈጥሯዊ የሆነ ዝምድና የለም፡፡ መ. ለመማር ከባድ፣ ለመጠቀም ውስብስብ የሆነ የአፃፃፍ ስርዓት--------ነው፡፡ ሠ. የቋንቋ የት መጣነት መላምቶች እና ናቸው፡፡ 2 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፪ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል የአዳምጦ መረዳት ጥያቄዎች ፩. ቀጥሎ የአዳምጦ መረዳት ጥያቄዎች ቀርበውላችኋል፡፡ በየግላችሁ እያዳመጣችሁ አስፈላጊውን ማስታወሻ በመያዝ፤ በቡድን እየተነጋገራችሁ ለክፍል ጓደኞቻችሁ በቃል መልሱ፡፡ ሀ. ንግግር ምንድን ነው? ለ. የጽህፈት ዓይነቶች የሚባሉት እነማን ናቸው? ሐ. አማርኛ ቋንቋ የሚከተለው የጽህፈት ስርዓት ምንድን ነው? መ. በስዕላዊ የአጻጻፍ ስርዓትና በፊደላዊ የአጻጻፍ ስርዓት መካከል ያለውን ልዩነት አብራሩ፡፡ ሠ. ቁስ አካላውያን ስለ ቋንቋ አጀማመር የሚሰነዝሩትን መላምት ግለፁ፡፡ ፪. የሚከተሉት ዓረፍተ ነገሮች ሰዋስዋዊ ቅደም ተከተላቸው ተዘበራርቆ የቀረበ ነው፡፡ በመሆኑም እንደገና አስተካክላችሁ ጻፉ፡፡ ሀ. ማሰብ የምንችለው ሰብለ ቋንቋ ስላለን ነው አለች፡፡ ለ. ሀገሮች ኢትዮጵያ ብዙ ልሳነ ከሚባሉ ተጠቃሽ ነች፡፡ ሐ. የሚለዋወጥበት ቋንቋ ብቻ የተሰጠ፣ አንዱ ከሌላው ለሰው ልጅ ጋር ሀሳብ ታላቅ የመግባቢያ መሳሪያ ነው፡፡ ፫. የሥርዓተ ጽሕፈት የሽግግር ደረጃዎችን በቅደም ተከተል አስፍሩ፡፡ (ቃላዊ ሥርዓተ ጽሕፈት፣ ስዕላዊ ሥርዓተ ጽህፈት፣ ፊደላዊ ሥርዓተ ጽሕፈት እና ቀለማዊ ሥርዓተ ጽህፈት) ሀ. --------------- ለ. --------------- ሐ.-------------- መ. ----------------- ፬. ‹‹ኮረና›› በሚል ርዕስ ከተለያዩ ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ያዳመጣችኋቸውን መረጃዎች ተጠቅማችሁ አንድ ድርሰት ጻፉ፡፡ ክፍል ሁለት (፪) መናገር ፩. ከሚከተሉት የመወያያ ሃሳቦች ውስጥ አንዱን በመምረጥ ከታች 3 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፫ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል የቀረበውን የውይይት መመሪያ መሰረት በማድረግ የቡድን ውይይት አድርጉ፡፡ ሀ. ሀገር ልትበለፅግ የምትችለው እኛ ዜጎች ምን ስናደርግ ነው ለ. ሀገርበቀል የሆኑ እውቀቶቻችን ምን ምን ናቸው? የውይይት አዘገጃጀትና አቀራረብ መመሪያ ውይይት ምንድን ነው? ውይይት ማለት በማንኛውም አጋጣሚ የተፈጠረን ችግር ለመፍታት ወይም ደግሞ በአንድ አሰራር ላይ የነበረን መርህ ለመቀስቀስ እንዲሁም አዲስ ሃሳብ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ሲባል ጊዜና ቦታ ተዘጋጅቶለት፣ ርዕስ ተነድፎለት ሁለትና ከዚያ በላይ በሆኑ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች መካከል የሚከወን የሃሳብ ልውውጥ ነው፡፡ ውይይትን ከጭውውት እና ክርክር የተለየ የሚያደርገው ችግርን መፍታት ተቀዳሚ ዓላማው በማድረጉ ነው፡፡ አንድ ውይይት ስኬታማ እንዲሆን የሚከተሉትን ቅድመ ዝግጅትና አቀራረብ ሊከተል ይገባል፡፡ የውይይት ዝግጅት የውይይቱ ተሳታፊ የሆኑ ሰዎችን (ዕድሜ፣ የትምህርት ደረጃ፣ ጾታ የህይወት ፍልስፍናቸውን ወዘተ…)ቀድመን መገንዘብ አለብን፡፡ ርዕሰ ጉዳዩን ጠንቅቆ መረዳትና በታዳሚዎች የእድሜና የእውቀት ደረጃ ልክ የርዕሱን ጥልቀት መወሰን መረጃ ማሰባሰብና መለየት (ከባለሙያ፣ ከቤተ-መጽሐፍ፣ ከመገናኛ ብዙኀንዘ የውይይት አቀራረብ ውይይት በምንሳተፍበት ጊዜ ልንከተላቸው የሚገቡ ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፡፡ የሌሎችን ሰዎች ሃሳብ ማክበር ማስታወሻ መያዝ ተራን ጠብቆ ማቅረብ 4 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፬ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል ጊዜን በአግባቡ መጠቀም ሃሳብን በግልፅና በማስረጃ ማቅረብ የእኔ ሃሳብ ብቻ ይሁን አለማለት ወዘተ… የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ቃላዊ ዘገባ የሚለውን አጭር ማስታወሻ ካነበባችሁ በኃላ በአካባቢያችሁ የተከሰቱ ወቅታዊ ነገሮችን በመመልከት (ከመገናኛ ብዙሃን በመከታተል) አጭር ዘገባ በመጻፍ ለክፍል ጓደኞቻችሁ በቃል አቅርቡ፡፡ ቃላዊ ዘገባ ቃላዊ ዘገባ ያየነውን፣ ያነበብነውን እና ያዳመጥነውን ጉዳይ በራሳችን የቃላት አጠቃቀምና የአገላለጽ ችሎታ በንግግር የምናቀርብበት ነው፡፡ ይህን ተግባር በምንከውንበት ጊዜ በቂ የሆነ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ፣ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን (የሰው፣ የቦታ፣ ስሞችን፣ ቀንና ሰዓቶችን፣ ቁጥሮች ወዘተ… ) በማስታወሻ በመያዝ በቃል ማቅረብ፣ አድማጮች ጥያቄ እንዲጠይቁ እድል መስጠት የሚሉት የተለመዱ የቃል ንግግር አቀራረብ መመሪያ ናቸው፡: በድሉ ዋቅጅራ (ዶ/ር) (2007፡95) በሥነ-ጽሑፍ ቋንቋን ማስተማር ክፍል ሶስት (፫) ንባብ ቋንቋና ሰው የቅድመ ንባብ ጥያቄዎች ሀ. ቋንቋ እና ሰው ሲባል ምን ማለት ይመስላችኋል? ለ. ቋንቋና ሰው ምን አይነት መስተጋብር ያላቸው ይመስላችኋል? ሐ. ቋንቋ ባይኖር የሰው ልጅ እጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል ብላችሁ ትገምታላችሁ? መ. በዚህ ርዕስ ምን ምን ጉዳዮች ይነሳሉ ብላችሁ ትገምታላችሁ? ግምታችሁን ለክፍል ጓደኞቻችሁ በቃል አስረዱ፡፡ ሠ. የሚከተሉት ቃላትና ሃረጋት ስለ ቋንቋ እና ሰው የሚያትቱ ናቸው፡፡ ስለፍቻቸው የምታውቁትን ለመምህራችሁ እና ለክፍል ጓደኞቻችሁ 5 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፭ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል በቃል ግለጹላቸው፡፡ ሀ. ቋንቋ ለ. ምርምር ሐ. ሰው መ. ቃል አልባ ተግባቦት ቋንቋ እና ሰው ቋንቋን ከሰው፣ ሰውንም ከቋንቋ፣ አንዱ ከአንዱ ለይቶ ለመናገርም ሆነ ለማሰብ በፍጹም አዳጋች ይሆናል፡፡ ስብእናውን ፣ ማህበራዊ ግንኙነቱን ፣ አመለካከቱንና ባህሉን ወዘተ…. ለመናገርም ሆነ ለመጻፍ ለመከራከርም ሆነ ‹‹ለመስበክ›› የቋንቋው መኖር ግድ ነው፡፡ የቋንቋው መኖር በግዴታ መፈረጁም ለሰው ልጅ ህልውና እጅግ አስፈላጊ በመሆኑም ጭምር ነው:: ‹‹የሰው ልጅ የመግባቢያ ቋንቋ ባይኖረውስ? ያለ ቋንቋ መኖር አይቻለውም?›› ይህ ጥያቄ በዘመናት ውስጥ አከራካሪ መሆን ብቻ ሳይሆን ከትናት እስከ ዛሬ ምርምር እየተደረገበት ያለ ርዕሰ ጉዳይ ነው፡፡ጥያቄው ሁሉንም ሰው በጋራ የሚያግባባ ዓለምአቀፋዊ ምላሽ ያልተገኘለት ‹‹ድፍን እንቁላል›› ይሉት ዓይነት የምርምር አጀንዳ እንደሆነ መቀጠሉም ለዚህ ነው፡፡ የሰው ልጅ ግን በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ‹‹አጉራ ጠናኝ›› ብሎ ሳይረታ ዛሬም ድረስ ምርምሩን በስፋት እያከናወነ ይገኛል፡፡ የሰው ልጅና የቋንቋን ቁርኝት በተመለከተ ሁለት ማሳያ የሆኑ ታሪኮችን እናንሳ፡፡ ተማሪዎች እስኪ ንባባችሁን ገታ አድርጋችሁ ቀጥሎ ለቀረቡት ጥያቄዎች ምላሽ ስጡ፡፡ ሀ. እስካሁን ያነበባችሁትን ምን ያህል ተገንዝባችኋል? ለ. ሁለቱ ታሪኮች ሊያነሱ የሚችሉትን ሃሳብ በማጤን ግምታችሁን ለመምህራችሁ ንገሯቸው? ታሪክ አንድ በምርምር ዘርፍ ከፍተኛ ፍላጎት ያለው የቀድሞው የጀርመን መራሔ መንግስት ንጉሰ ነገስት ዳግማዊ ፍሬዴሪክ (እ.ኤ.አ ፲፩፻፺፷-፲፪፻፶ ) ዓ.ም የነበረው ከተወለዱ የሳምንት ዕድሜ ያልሞላቸው ህጻናትን ወደ ቤተ-መንግስት 6 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፮ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል በማስገባት ያለምንም ጣልቃ ገብነት በተፈጠሮ ሂደት ብቻ አፋቸውን እንዲፈቱ ሙከራ አድርገው ነበር፡፡ ይህንን ሲያደርጉም ለህጻናቱ ሞግዚቶች ምግብን እና ሌሎችን ማቅረብ እንዳለባቸው ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡ እንዲሁም በቃል አልባ ተግባቦት (Non Verbal Communcation) ዘዴ ከህጻናት ጋር ለመግባባት እንዳይሞክሩ የሚያግድ ትዕዛዝ ሰጥተው ነበር፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኃላ ስለሞቱ ውጤቱ መና መቅረቱ ይፋ ሆነ፡፡ ማንኛውም ህጻን (ሰው) ለመኖር የሚያስፈልጉት መሰረታዊ ነገሮች ቢሟሉለትም ያለ መግባቢያቋንቋ ያለፍቅር ቃል ያለ አፍቃሪ ጠረን ና እሹሩሩ ለብቻው ተዘግቶበት እንዲኖር ቢፈረድበት መኖር አይቻልም ፡፡ ስብእናው ያለመግባቢያ ቋንቋ ወይም ያለ ቃል አልባ ግንኙነት እንዲኖር አይፍቅድለትም፡፡ ታሪክ ሁለት አምስት ሰዎች ሽልማት ለሚያስገኝ የዝምታ ውድድር ተመርጠው ጸጥታ በሰፈነበት ክፍል ውስጥ አብረው እንዲቆዩ ተዘጋባቸው፡፡ በቆይታው ወቅት እርስ በርስም ሆነ አንዱ ከሌላው ጋር በምንም ሁኔታ እንዳይነጋገሩና በየትኛውም ዓይነት የቃል አልባ ግንኙነት እንዳይግባቡ ጥብቅ ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡ አንደኛ የወጣው ሰው በዝምታ እንደጸና ሳይናገር የቆየው ለስምንት ቀናት ብቻ ሲሆን ሦስቱ ያለ ንግግር የቆዩት ለሁለት ቀናት ነበር፡፡ ሌላኛው ሰው የቆየው ለአንድ ሰዓት ያህል ብቻ ነው፡፡ በእነዚህ ሁለት ተጠቃሽ ታሪኮች የምንረዳው ጤናማ ሰው ከብጤው የሰው ልጅ ጋር ወይንም ከፈጣሪው ጋር ፣ አልያም ከየትኛውም ፍጡር ጋር በንግግርም ሆነ በቃል አልባ ግንኙነት ከመግባባት ቢታቀብ ውጤት አልባ ከመሆን እንደማይዘል አስረግጦ ያስታውሰናል፡፡ (ጌታቸው በለጠ የጥበባት ጉባኤ 2004 ፤ 4-7 በመጠኑ ተሻሽሎ የቀረበ) 7 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፯ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች ፩. የሚከተሉትን ጥያቄዎች በምንባቡ መሰረት በቃል መልሱ፡፡ ሀ. የሰው ልጅ ስለ ስብእናው፣ ማህበራዊ ግንኙነቱ፣ አመለካከቱ፣ ባህሉ ወዘተ… ለመናገርም ሆነ ለመጻፍ እንዲሁም ለመከራከር ቋንቋ አስፈላጊ ነው ሲል ምን ማለቱ ነው? ለ. ‹‹የቋንቋው መኖር በግዴታ መፈረጁም ለሰው ልጅ ህልውና እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው::›› በሚለው ሃሳብ ትስማማላችሁ? ወይስ አትስማሙም? በምክንያት አስደግፋችሁ መልሱ፡፡ ሐ. በታሪክ አንድና ሁለት መካከል ያለው የሃሳብ አንድነት እና ልዩነት ምንድን ነው? መ. አንደኛ የወጣው ተወዳዳሪ ዝም ብሎ የቆየው ለምን ያህል ጊዜ ነበር? ህጻናቱ የሞቱት በምን ምክንያት ነበር? ፪. የሚከተሉት ቃላትና ሃረጋት ከምንባቡ የወጡ ናቸው፡፡ ጥንድ ጥንድ በመሆን ዓውዳዊ ፍቻቸውን ከሰጣችሁ በኋላ ዓረፍተነገር ስሩባቸው፡፡ ሀ. ብጤ ለ. ጸና ሐ. አፍቃሪ መ. ቃል አልባ ሠ. ጠረን ረ. እሹሩሩ ሰ. መና ሸ. መስበክ ቀ. ዓለምአቀፍ በ. ስብእና ፫. ከላይ በቀረበው ምንባብ ውስጥ አያያዥ ቃላትና ሀረጋትን እንዲሁም ስርዓተ ነጥቦችን ለይታችሁ አውጡ፡፡ ፬. ለሚከተሉት ቃላት ፍቻቸውን ከመዝገበ ቃል በመፈለግ ጻፉ፡፡ ሀ. ቁርሾ ረ. ዚቀኛ ለ. መረን ሰ. ሀመልማል ሐ. ነቁጥ ሸ. ምንዝር መ. ህቡዕ ቀ. ነጸብራቅ ሠ. ጨረፍታ በ. እንቦቀቅላ ክፍል አራት (፬) ጽሕፈት ፩. ቋንቋ እና ሰው ከሚለው ጽሁፍ የተረዳችሁትን በአንድ አንቀጽ አሳጥራችሁ ጻፉ፡፡ በምትጽፉበት ጊዜ አያያዥ ቃላትን፣ ሥርዓተ ነጥብን እንዲሁም የሃሳብ 8 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፰ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል ፍሰቱን (ቅድም ተከተሉ) የጠበቀ መሆን መቻል እንዳለበት እንዳትዘነጉ፡፡ ፪. የሚከተሉት ዓረፍተ ነገሮች የአንቀጽ ባህርያትን የጠበቁ ናቸው፡፡ ነገር ግን ቅደም ተከተላቸውን ጠብቀው አልተቀመጡም፤ ስለሆነም ቅደም ተከተላቸውን ጠብቃችሁ አንቀጽ ጻፉ፡፡ 1. ንጉስ እንኳን ቢመጣ ምግብ ላይ አንነሳም፡፡ 2. እህሉን በአክብሮትና በፀጥታ እንበላዋለን፡፡ 3. ሲሉ አባቶች ይመክራሉ፡፡ 4. ገበታ ክቡር ነው፡፡ 5. ምግብ እየበላን እያለ ማንም ሰው ቢመጣ እንብላ እንለዋለን እንጂ አንነሳለትም፡፡ 6. ተቀምጠን እያለ ማንም ሰው ቢመጣ በከበሬታ ተነስተን ኖር ብለን አንቀበለውም፡፡ ፫. ገላጭ ቃላትን እና ምሳሌያዊ አነጋገሮችን በመጠቀም የመጣችሁበትን ሰፈር ‹‹ሰፈሬ›› በሚል ርዕስ ገላጭ በሆነ መንገድ ሁለት አንቀጽ ያለው አጭር ድርሰት ጻፉ፡፡ አንቀጻችሁን በምትጽፉበት ጊዜ የሚከተሉትን ምሳሌያዊ ንግግሮች ተጠቀሟቸው፡፡ - ሰው ባገሩ ወይራ ነው፡፡ - ወፍ እንዳሃገሯ ትጮኻለች፡፡ - ውሻ በሰፈሩ ይጮኻል፡፡ ክፍል አምስት (፭) ቃላት የቃላት ሚና ፩. ቀጥሎ የቃላት ሚና የሚል ማስታወሻ ቀርቧል፡፡ በመሆኑም ማስታወሻውን መሰረት በማድረግ አምስት አምስት ገላጭ ቃላትን ከጽሁፍ ወይም ከመገናኛ ብዙኃን በመፈለግ (በማዳመጥ) አምጡ፡፡ የቃላት ሚና ቃላት በቋንቋ ውስጥ ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ቃል የሌለው ቋንቋ አለ ማለት አይቻልም፡፡ ምክንያቱም ቋንቋ ድምጻዊ መግባቢያ ነው፡፡ እነዚህ ድምጾች በስርዓት ተቀናጅተው ቃልን የመመስረት ደረጃ ሲደርሱ 9 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፱ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል ለድርሰት ጽሁፍ ያላቸው ሚና ጉልህ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ገላጭ ቃላትን በመውሰድ ሰፈርን፣ ቁመናን፣ መልክዓ ምድርን ወዘተ ገልጾ ምስል ከሳች በሆነ መልኩ መጻፍ ይቻላል፡፡ ፪. በሚከተለው አጭር ጽሁፍ ውስጥ ሃሳብን የበለጠ ሊገልፁ የሚችሉ ቃላት ተካተዋል፡፡ በመሆኑም ገላጭ ቃላት የምትሏቸውን ለይታችሁ አውጡ፡፡ … ዶ/ር ደስታ ይባላል፡፡ ቀጥ ብሎ የተሰደረ አፍንጫውና ጎላጎላ ያሉ ዓይኖቹ ቀይዳማ ፊቱ ግርማን አላብሰውታል፡፡ ተክለ ሰውነቱ ረዘም ያለ ሆኖ ደልዳላ ነው፡፡ የእጅና የእግር ጡንቻዎቹ በትክክል መስመራቸውን ይዘው የፈረጠሙ ናቸው፡፡ ከደረቱ ወጣ ያለ ሆኖ፤ ሆዱ ከጀርባው ሊጣበቅ ትንሽ ነው የሚቀረው፡፡ (ዳዊት ወንድማገኝ ፣ 209፡1) ክፍል ስድስት (፮) ሰዋስው ጥምር ቃላት ጥምር ቃላት ሁለት ሊጣመሩ የሚችሉ የተለያዩ ቃላት ናቸው፡፡ እነዚህ ቃላት በተናጠል የተለያየ ፍቺ ከሚሰጡት በተጨማሪ ሌላ አዲስ ፍቺ ወይም የነበረውን የተናጠል ፍቺ የበለጠ የሚያጠናክሩ ቃላት ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- ሀ. ቤት + መጽሐፍ = ቤተ-መጽሐፍ ለ. ህግ + መንግስት = ህገ-መንግስት ሐ. ወጥቶ + አደር = ወታደር መ. ወዝ + አደር = ወዛደር ጥምር ቃላት አንዳንድ ጊዜ በንዑስ ጭረት (ንዑስ ሰረዝ) አንዳንዴ ደግሞ ያለ ስርዓተ ነጠብ የሚጣመሩበት ጊዜ አለ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሁለት የተለያዩ ተጣማሪ ቃላት ሲጣመሩ ጥምርነታቸውን ረስተው አንድ ቃል የሚመስሉበት አጋጣሚ አለ፡፡ በምሳሌ ‹‹ሐ›› እና ‹‹መ›› የቀረቡት ለዚህ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ታዲያ እነዚህ ጥምር ቃላት የተለያዩ ዓረፍተ ነገሮችን ለመመስረት ጉልህ 10 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፲ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል ሚና አላቸው፡፡ ለምሳሌ፡- ሀ. ኢትዮጵያ የራሷን ህገ-መንግስት ቀርጻ መተዳደር ከጀመረች በርካታ ዓመታትን አስቆጥራለች፡፡ ለ. ወዛደር ለሀገር ግንባታ የራሱ የሆነ ሚና አለው፡፡ ፩. በሚከተለው ሳጥን ውስጥ ተጣማሪ ሊሆኑ የሚችሉ ቃላት ይገኛሉ፤በመሆኑም ተጣምረው ትክክለኛ ፍቺ ሊያስገኙ የሚችሉ ቃላትን መስርቱ፡፡ ለምሳሌ፡- ዓለም አቀፍ ወፍ አቀፍ ምድር ሥርዓት ዘራሽ ወዶ ማር ዓመት መልካ ግብ ገብ ምህረት ዓለም ሥነ ፪. ከላይ በመሰረታችኋቸው ጥምር ቃላት በአምስቱ ሁለት ሁለት ዓረፍተነገር ስሩባቸው፡፡ ለምሳሌ፡- ዓለምዓቀፍ ሀገራችን ኢትዮጵያ የተለያዩ ዓለምአቀፍ ዲፕሎማሲዎች መቀመጫ ናት፡፡ 11 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፲፩ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል የምዕራፉ ማጠቃለያ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ቋንቋና ሰው ያላቸውን መስተጋብር እንዲሁም የሰው ልጅ ያለ መግባቢያና ቋንቋ የመኖር ህልውናው አደጋ ውስጥ እንደሚገባ አመላካች የሆኑ የተለያዩ ሁለት አስተማሪ ታሪኮችን ተመልክታችኋል፡፡ ቋንቋ የሰው ልጅ ስሜቱን፣ ሃዘኑንና ደስታውን፣ ማህበራዊ ግንኙነቱን፣ ሰዋዊነቱን፣ አስተሳሰቡን፣ ባህሉን ወዘተ…ለመናገርም ሆነ ለመጻፍ ለመከራከርም ሆነ ለማስተማር የቋንቋው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተገንዝባችኋል፡፡ ስለ ቃላት ሚና በተለይም ደግሞ ቃላት በድርሰት ውስጥ ያላቸውን ሚና ተመልክታችኋል፡፡ ገላጭ ቃላት ተጠቅመን መልካዓ ምድርን፣ ቁመናንና ማንኛውንም የሚገለጹ ነገሮች መጻፍ እንደምንችል ተረድታችኋል፡፡ በተጨማሪም ስለጥምር ቃላት አመሰራረትና ሲመሰረቱ ምን እንደሚመስሉ ተገንዝባችኋል፡፡ ጥምር ቃላት በንዑስ ጭረት ወይም ያለ ንዑስ ጨረት ይመሰረታሉ፡፡ በእነዚህም ቃላት ዓረፍተ ነገር እንዴት እንደሚመሰረት ተረድታችኋል፡፡ የክለሳ ጥያቄዎች ፩. ቋንቋ በሰው ልጆች ወይስ የሰው ልጆች በቋንቋ ውስጥ ተካተው ይገኛሉ? የራሳችሁን ግላዊ አመለካከት ለክፍል ጓደኞቻችሁ አስረዱ፡፡ ፪. ቃል አልባ መግባቢያ መንገዶች የሚባሉትን በመዘርዘር ለመምህራችሁ ግለጹ፡፡ ፫. ከሚከተሉት ሁለት የድርሰት መጻፊያ ርዕሶች አንዱን በመምረጥ ገላጭ ቃላትን በመጠቀም ባለ ሁለት አንቀጽ ድርሰት ጻፉ፡፡ ሀ. የኔዋ ሞናሊዛ ለ. ለምለሚቷ ሀገሬ ፬. በሚከተሉት ጥምር ቃላት ፍቻቸውን የሚገልጽ ዓረፍተ ነገር መስርቱ፡፡ ሀ. በትረ መንግስት ለ. አመለቢስ ሐ. ቀዶ ጥገና መ. ሥነ-ዘዴ 12 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፲፪ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል የግንዛቤ ማመሳከሪያ ቅፅ ፩. ከዚህ በታች በምዕራፍ አንድ ትምህርት ምን ያህል እንደ ተረዳችሁ የምታመሳክሩበት ሰንጠረዥ ቀርቧል፡፡ በዚህ መሰረት በእያንዳንዱ የማመሳከሪያ ነጥብ ትይዩ ስለመረዳታችሁ እርግጠኛ ከሆናችሁ የ(√)፣ እርግጠኛ ካልሆናችሁ የ (?) ሙሉ በሙሉ ካልተረዳችሁ ደግሞ (X) ምልክት በማድረግ ሰንጠረዡን አሟሉ፡፡ ተ.ቁ የማመሳከሪያ ነጥቦች (√) (?) (X) 1. ስለቋንቋ እና ሰው ምንነት በቃል እና በጽሁፍ መግለፅ እችላለሁ፡፡ 2. የውይይት አዘገጃጀትና አቀራረብ መመሪያን መሰረት በማድረግ መወያየት እችላለሁ፡፡ 3. የቃል ዘገባ አቀራረብን መመሪያ ተከትየ ያነበብኩትንና የተወያየሁበትን በቃል ማቅረብ እችላለሁ፡፡ 4. ቋንቋ እና ሰው ያላቸውን መስተጋብር ለጓደኞቼ በቃል መግለጽ እችላለሁ፡፡ 5. ለቃላት ዓውዳዊ እና መዝገበ ቃላዊ ፍች መስጠት እችላለሁ፡፡ 6. የቃላትን ሚና በመረዳት ገላጭ ቃላትን ተጠቅሜ አንድን ነገር መግለጽ እችላለሁ፡፡ 7. ሁለት ሊጣመሩ የሚችሉ ቃላትን በማጣመር ዓረፍተ ነገር መመስረት እችላለሁ፡፡ ፪. ከዚህ በላይ በሰንጠረዥ የ(?) እና የ (X) ምልክት ያደረጋችሁባቸውን ነጥቦች በሚገባ እስክትረዷቸው፣ ድረስ የምዕራፉን ትምህርት ደጋግማችሁ ከልሱ፡፡ 13 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፲፫ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል አማርኛ ፲ኛ ክፍል ምዕራፍ ሁለት (፪) ባህላዊ ጋብቻ የምዕራፉ አጠቃላይ ዓላማዎች ፡- ተማሪዎች ይህን ትምህርት ካጠናቀቃችሁ በኋላ፡- የሌሎችን ንግግር በማዳመጥ ግብረ መልስ ትሰጣላችሁ፡፡ ክርክር ታደርጋላችሁ፡፡ የጽሁፍን ሀሳብ እያገናዘባችሁ ታነባላችሁ፡፡ የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ሀሳባችሁን በፅሁፍ ትገልጻላችሁ፡፡ ትምህርታዊ እና ቴክኒካዊ ቃላትን በጽሁፍ እና በንግግር ውስጥ ትጠቀማላችሁ፡፡ አስረጅ፣ መጠይቃዊ እና ትዕዛዛዊ ዓ.ነገሮችን በጽሁፋችሁ ውስጥ ትጠቀማላችሁ፡፡ 14 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፲፬ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል ክፍል አንድ (፩) ማዳመጥ የተቋረጠው ጋብቻ የቅድመ ማዳመጥ ጥያቄዎች ፩. ቀጥሎ የቀረቡትን ጥያቄዎች በቡድን እየተወያያችሁ የደረሳችሁበትን ሃሳብ ለክፍል ጓደኞቻችሁ በቃል አቅርቡ፡፡ ሀ. ባህላዊ ጋብቻ ማለት ምን ማለት ነው?ጋብቻ ሊቋረጥባቸው የሚችሉ ነጥቦች ምን ምን ናቸው? ለ. የሚከተሉት ቃላትና ሃረጋት ‹‹የተቋረጠው ጋብቻ›› በሚል ርዕስ ከቀረበ ምንባብ ውስጥ የወጡ ናቸው፡፡ ፍቻቸውን ለመምህራችሁ ተናገሩ፡፡ ሀ. ነገረ ፈጅ መ. አምቻነት ለ. ሲቃ ሠ. መልከ ቀና ሐ. አንኮራፉ ረ. ባለጋሻ ሐ. መምህራችሁ ከፍቅር እስከ መቃብር ረጅም ልቦለድ ውስጥ ‹‹የተቋረጠው ጋብቻ›› በሚል የተቀነጨበ አንድ አጭር ጽሁፍ ሁለት ጊዜ ያነቡላችኋል፡፡ እናንተ ደግሞ ጽሁፉን በጥሞና አዳምጣችሁ፤ከታች ያሉትን ጥያቄዎች መልሱ፡፡ በምታዳምጡበት ጊዜ ፍቻቸውን የማታውቋቸው አዳዲስ ቃላት ሲገጥሟችሁ ማስታወሻ መያዝ አትዘንጉ፡፡ የአዳምጦ መረዳት ጥያቄዎች ሀ. የፊታውራሪ አሰጌንና የሰብለ ወንጌልን ጋብቻ ደስ ብሏቸው የተቀበሉትን ሰዎች ዘርዝሩ፡፡ ለ. ጋብቻው የተቋረጠባቸውን ምክንያቶች በቃል ግለጹ፡፡ ሐ. ‹‹የተቋረጠው ጋብቻ›› በሚል ርዕስ የተነበበላችሁን ምንባብ አጠቃላይ መልዕክት በቡድን ከተነጋገራችሁበት በኋላ ለመምህራችሁ በቃል ግለጹላቸው፡፡ መ. ባህላዊ ጋብቻ ማለት ምን ማለት ነው? ከቤተሰቦቻችሁ ወይም በአካባቢያችሁ ከሚያውቁ ሰዎች ጠይቃችሁ በመምጣት ያገኛችሁትን መልስ በክፍል ውስጥ በየተራ ለጓደኞቻችሁ አቅርቡ፡፡ 15 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፲፭ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል ክፍል ሁለት (፪) መናገር ፩. ቀጥሎ የክርክርን ምንነት፣ አዘገጃጀትና አቀራረብ የሚመለከት ማብራሪያ ቀርቦላችኋል፡፡ ስለሆነም ማብራሪያውን በጥሞና ካነበባችሁ በኋላ ከቀረቡላችሁ የመከራከሪያ ርዕሶች መካከል አንዱን ምረጡ፡፡ በመቀጠል መምህራችሁ በሚመሰርቱላችሁ ቡድን መሠረት ክርክር አድርጉ፡፡ ሀ. የባህላዊ ጋብቻ ተጽእኖ ከወንዶችና ከሴቶች በየትኞቹ ላይ ጎልቶ ይታያል? ለ. ባህላዊ ጋብቻ ከጥቅሙና ጉዳቱ የትኛው ይበልጣል? ሐ. አርበኝነት የሚገለጸው በጦርነት በመሳተፍ ወይስ በሌላ ጉዳይ ነው? ክርክር ክርክር በሁለት ቡድኖች ወይም ግለሰቦች መካከል በአንድ ርዕሰ ጉዳይ የተለያየ አቋምን በማራመድ የሚደረግ ሥርዓት ያለው እሰጣ ገባ ወይም የሃሳብ ሙግት ነው፡፡ ክርክር በተለያየ አጋጣሚ ሊከወን ይችላል፡፡ ለአብነት ያክል የሚከተሉት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ዕውቀት ለማግኘት ይከራከራሉ፡፡ ከሳሽና ተከሳሽ ፍትህ ለማግኘት በፍርድ ቤት ይከራከራሉ፡፡ ፖለቲከኞች ለመመረጥና ሃገር ለመምራት በመገናኛ ብዙኀን ይከራከራሉ፡፡ ወዘተ… ተከራካሪዎቹም ለማሸነፍ ዝግጅት ያደርጋሉ፡፡ በመሆኑም በክርክር አዘገጃጀት እና አቀራረብ ጊዜ የሚነሱ ነጥቦችን ቀጥለን እንመለከታለን፡፡ ፩ የክርክር ዝግጅት በርዕሰ ጉዳያችን ዙሪያ መረጃ መሰብሰብ (ከቤተ-መጽሐፍ፣ ከባለሙያ…..) መረጃዎችን በቅደም ተከተል ማደራጀት፣ ክርክሩን ከማቅባችን በፊት ልምምድ ማድረግ፣ ወደክርክር ከመቅረባችን በፊት (አለባበሳችንን እና ንጽህናችንን አስተካለን እንዲሁም 16 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፲፮ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል የአሸናፊነት ሥነ-ልቦናን ይዘን መቅረብ መቻል) አለብን፡፡ ፪. የክርክር አቀራረብ አድማጭን በማመስገን የመከራከሪያ ርዕሳችንን ማስተዋወቅ፣ ሃሳባችንን በግልጽና በተረጋጋ መንፈስ፣ በልበ ሙሉነትና በቅደም ተከተል ማቅረብ፣ ሃሳብን በተገቢው የአካል እንቅስቃሴ እያጀቡ ማቅረብ፣ በሌላ ሃሳብ ላይ ያሉ ተከራካሪዎችን ሃሳብ በጥሞና በማዳመጥ ማስታወሻ መያዝ፣ የምናቀርበው መረጃ የተከራካሪዎችን አቅም /ችሎታ/ ያገናዘበ መሆን ለክርክር የተሰጠን ጊዜ ማክበር እና በአግባቡ መጠቀም፣ ከርዕሳችን እንዳንወጣ መጠንቀቅ፣ በመጨረሻም አመስግነን ሃሳባችንን መቋጨት መቻል አለብን፡፡ ክፍል ሶስት (፫) ንባብ የየም ብሔረሰብ ባህላዊ ጋብቻ የቅድመ ንባብ ጥያቄዎች ፩. ስንት አይነት የጋብቻ አይነት ታውቃላችሁ? ስማቸውን ግለፁ፡፡ ፪. ቀጥሎ የቀረቡት ቃላትና ሐረጋት ‹‹የየም ብሔረሰብ ባህላዊ ጋብቻ›› በሚለው ምንባብ ውስጥ የሚገኙ ናቸው፡፡ ስለፍቻቸው የምታውቁትን በቃል ለክፍል ጓደኞቻችሁ ተናገሩ፡፡ ሀ. ስብጥር ለ. ጥምር ሐ. ዕደ-ጥበብ መ. አጃቢ ፫. ቀጥሎ የየም ብሔረሰብ ባህላዊ ጋብቻ የሚል ምንባብ ቀርቦላችኋል፡፡ በመሆኑም ቡድን ከመሰረታችሁ በኃላ በምንባቡ ውስጥ ምን ምን ጉዳዮች ሊነሱ እንደሚችሉ ግምታችሁን ለመምህራችሁ በቃል ተናገሩ፡፡ 17 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፲፯ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል የየም ብሔረሰብ ባህላዊ ጋብቻ የየም ብሔረሰብ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ውስጥ ከሚገኙ ብሔረሰቦች መካከል አንዱ ነው፡፡ ብሔረሰቡ በዋናነት በልዩ ወረዳው ውስጥ በሚገኙ 1 የገጠርና 2 የከተማ ቀበሌዎች የሚኖር ሲሆን፤ በጉራጌና በሃድያ ዞኖች ውስጥም ከሌሎች ብሄረሰቦች ጋር በስብጥር ይኖራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በርካታ የብሄረሰቡ አባላት በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን ውስጥም ይኖራሉ፡፡ የብሄረሰቡ ዋነኛ የኢኮኖሚ መሰረት ጥምር ግብርና ሲሆን እንሰት፣ ገብስ፣ ስንዴ፣ ጤፍ፣ በቆሎ፣ ባቄላ፣ አተር፣ አደንጓሬ፣ ምስር፣ ኮክ እና ቦይና ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ከእርሻ ስራው ጎን ለጎን የከብት እርባታና የእደጥበብ ስራዎችንም ያከናውናሉ፡፡ የብሄረሰቡ አፍ መፍቻ ቋንቋ ‹‹ የምሳ ›› ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በምስራቅ ኦሟዊ 18 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፲፰ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል የቋንቋ ቤተሰብ የሚመደብ ነው፡፡ በየም ብሄረሰብ በድምቀት ከሚከናወኑ ስርዓቶች አንዱ የጋብቻ ስርዓት ነው፡፡ በብሄረሰቡ አምስት ዓይነት የጋብቻ ዓይነቶች አሉ፡፡እነሱም፡- በቤተሰብ የሚፈጸም ጋብቻ (ዛታግሩ)፣ ድንገተኛ ጋብቻ (ራራግሩ)፣ የጠለፋ ጋብቻ (ቦአገሩ)፣ በደላላ የሚፈጸም ጋብቻ (ዘክኛ) ወይም (ዛካግሩ)እና የፍቅር ወይም በሁለቱ ተጋቢዎች ስምምነት የሚፈጸም ጋብቻ (ሹኖግሩ)በመባል ይታወቃሉ፡፡ ተማሪዎች ማንበባችሁን ገታ አድርጉና እስካሁን በአነበባችሁት ጽሁፍ ያገኛችኋቸውን ዋና ዋና ነጥቦች ለመምህራችሁ ግለጹላቸው፡፡ ቀጥሎ ምንባቡ ምን ምን ጉዳዮችን ያነሳል ብላችሁ ትገምታላችሁ? ግምታችሁን ለመምህራችሁ ተናገሩ፡፡ ‹‹ዛታግሩ›› ሁለቱ ተጋቢዎች ሳይተዋወቁ በወላጆቻቸው መልካም ፍቃድ / ስምምነት/ ብቻ የሚፈጸም የጋብቻ ዓይነት ነው፡፡ ‹‹ራራግሩ›› ደግሞ ሳይታሰብ በድንገት የሚፈጸም ጋብቻ ሲሆን፣ ልጆቹም ሆኑ የልጅቷ ወላጆች ስለጋብቻው አንዳች ዕውቀት ሳይኖራቸው ወይም ሳይሰሙ አግቢው ጎረምሳ ከቤቱ ደግሶ ፈረሱን ጭኖና አጃቢ አስከትሎ ሽማግሌ በመያዝ በድንገት ወደ ልጅቷ ቤት ሄዶ በደጅ በመገኘት የሚፈጸም የጋብቻ ዓይነት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ጋብቻ ተቀባይነት ባያገኝም እንኳን የሚከፈለው የጥሎሽ መጠን ከተለመደው መጠን ከፍ ይላል፡፡ ‹‹ዛካግሩ›› በሶስተኛ ወገን አገናኝነት በሁለት ጥንዶች መካከል የሚፈጸም የጋብቻ ዓይነት ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የማግባባት ተግባር የሚፈጸመው በሴቶች አማካኝነት ሲሆን፤ አግባቢዋም ይህንን የምታደርገው ከአግቢው የገንዘብ ወይም የሌላ ነገር ጥቅም ለማግኘት እንደሆነ ይነገራል፡፡ ጥቅማጥቅሙን ለማግኘት ስትልም ወንዱ ለከጀላት ሴት የተለያዩ የማግባቢያ ስልቶችን ተጠቅማ ጋብቻ እንድትፈጽም ታደርጋለች፡፡ ይህ አይነቱ ጋብቻ ባብዛኛው ተፈጻሚ የሚሆነው በተለያየ ምክንያት ባሎቻቸውን ፈትተው ወይም በሞት ተነጥቀው በተቀመጡት ሴቶች ላይ ሲሆን አልፎ አልፎ ባላገቡ ሴቶች ላይም ተፈጻሚ የሚሆንበት ጊዜ አለ፡፡ 19 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፲፱ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል ‹‹ሹኖ ግሩ›› ደግሞ በሁለቱ ተጋቢዎች ስምምነት የሚፈጸም ጋብቻ ሲሆን ሁለቱ ወጣቶች ከወላጆቻቸው ዕውቅና ውጭ በድብቅ ፍቅር ጀምረው በድንገት ልጅቷ ከጸነሰች ሁለቱ ጥንዶች በአንድ ላይ ለመኖር ሲሉ የሚፈጽሙትጋብቻ ነው፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት የጋብቻ ዓይነቶች መካከል ከተወሰኑት በስተቀር አብዛኞቹ በአሁኑ ወቅት ተግባራዊ ሲደረጉ አይስተዋልም፡፡ በብሄረሰቡ የጋብቻ ዕድሜ ለሴት ልጅ 18 ዓመት ሲሆን፤ ለወንድ ልጅ ደግሞ 20 ዓመት ነው፡፡ ወንዶች ከ15 ዓመት እስከ 20 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገረዙ ሲሆን፣ የሴት ልጅ ግርዛት ግን በብሄረሰቡ ዘንድ የተለመደ አይደለም፡፡ (ዳግማይ ነቅዓጥበብ፣ አዲስ ፲፷፻፸፱፣ 2007::) የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች ፩. ምንባቡን መሰረት በማድረግ የሚከተሉትን ዓረፍተ ነገሮች ትክክል የሆኑትን ‹‹እውነት›› ስህተት የሆኑትን ‹‹ሀሰት›› በማለት ከነምክንያታችሁ በጽሁፍ መልሱ፡፡ ሀ. የየም ብሄረሰብ መሰረታዊ የኢኮኖሚ ምንጩ ግብርና ሲሆን ጎን ለጎን የአደን ስራዎችንም ያከናውናሉ፡፡ ለ. በቤተሰብ የሚፈፀም ጋብቻ በተጋቢዎቹ ስምምነት የሚፈፀም የጋብቻ ዓይነት ነው፡፡ ሐ. አብዛኞቹ የየም የጋብቻ ዓይነቶች አሁን ላይ ተግባራዊ ሲደረጉ ይታያሉ፡፡ መ. በደላላ የሚፈፀም ጋብቻ ብዙውን ጊዜ የማግባባት ተግባሩ የሚቋጨው በሴቶች በኩል ነው፡፡ ሠ. በየም ብሄረሰብ ጋብቻ የሚፈፀመው ለወንድ ልጅ በ18 ዓመት ሲሆን ለሴት ልጅ ደግሞ በ15 ዓመት ነው፡፡ ፪. የሚከተሉት ጥያቄዎች ምንባቡን መነሻ በማድረግ የቀረቡ ናቸው፡፡ ጥያቄዎችን በቡድን እየተወያያችሁ በቃል መልሱ፡፡ ሀ. የየም ብሔረሰብ በወረዳው ውስጥ ከየትኞቹ ብሔረሰቦች ጋር ተሰባጥሮ ይኖራል? ለ. ‹‹ዛካግሩ›› በሶስተኛ ወገን አገናኝነት በሁለት ጥንዶች መካከል የሚፈጸም ጋብቻ ነው ሲባል ምን ማለት ነው? 20 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፳ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል ሐ. የብሔረሰቡ ዋነኛ የኢኮኖሚ መሰረት ጥምር ግብርና ነው ሲባል ምን ለማለት ተፈልጎ ነው? መ. የየም ብሔረሰብ አፍ መፍቻ ቋንቋ ምን ተብሎ ይጠራል? ሠ. ድንገተኛ ጋብቻ በየም ባህል ተቀባይነት የሌለው ለምንድን ነው? ፫. የሚከተሉት ቃላት ከምንባቡ የወጡ ናቸው፡፡ በ ‹‹ሀ›› ክፍል ለቀረቡት ቃላት ተመሳሳይ የሆኑትን በ ‹‹ለ›› ክፍል ከቀረቡት ጋር አዛምዱ፡፡ ሀ ለ 1. ተፈፃሚ ሀ. ዘዴ 2. ጥሎሽ ለ. አገናኝ 3. ስልት ሐ. ፈለገ 4. ከጀለ መ. ተግባራዊ 5. ደላላ ሠ. ስጦታ ረ. መላሽ ክፍል አራት (፬) ጽሕፈት የድርሰት ክፍሎች ድርሰት ሶስት ዋና ዋና ክፍሎችን አካቶ ይይዛል፡፡ እነዚህም መግቢያ፣ ሐተታ እና መደምደሚያ ናቸው፡፡ ሀ. መግቢያ፡- ድርሰት በምንጽፍበት ጊዜ ቀድመን የምንጽፈው ተግባር መግቢያ ነው፡፡ መግቢያ ድርሰታችን ስለምን እንደሚተነትን ለአንባቢ የምንነግርበት የድርሰት ክፍል ነው፡፡ ለ. ሐተታ፡- ድርሰት በምንጽፍበት ጊዜ በመግቢያ ላይ የሰፈሩ ሃሳቦች በዝርዝር የምናቀርብበት ነው፡፡ በዚህ የድርሰት ክፍል የርዕሰ ጉዳያችን ዋና ሃሳብ የሚሰፍርበት ክፍል ነው፡፡ ሐ. መደምደሚያ፡- ከመግቢያው አንስተን እስከ ሐተታ ድረስ ያለውን ሃሳብ ጠቅለል አድርገን የምናሰፍርበት ነው፡፡ (ደበበ ኃይለጊዮርጊስ ፣ 2012፡298) ፩. ቀጥሎ አንድ አንቀጽ ቀርቦላችኋል፡፡ በአንቀጹ ውስጥ ሶስቱ የድርሰት ክፍሎች ይገኛሉ፡፡ እነዚህን ሶስት የድርሰት ክፍሎች ነጣጥላችሁ በደብተራችሁ ጻፉ፡፡ 21 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፳፩ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል የአውራ አምባ ማኅበረሰብ አባላት የጋራ ፍልስፍና፣ የህይወት ዘይቤና የአኗኗር ዘዴ ከአብዛኞቹ የሀገራችን ማኅበረሰቦች አቋም የተለየ ይመስላል፡፡ ማህበረሰቡ ከሌሎች ማህበረሰቦች የሚለይባቸውንም ሆነ የሚመሳሰልባቸውን ልምምዶቹን የሚገልጸው በተግባር ብቻ ሳይሆን የማህበረሰቡ የጋራ መግባቢያ በሆነው የአካባቢ ቋንቋ ፣ ማህበረሰቡ በተለማመደው ዘዬና የቃል አልባ ግንኙነት ጭምር ነው፡፡ በቋንቋው ራሱንና አካባቢውን ይገልጽበታል፤ ልምዱንና ወጉን ያስጠብቅበታል፤ ሀዘን ደስታውንም ይገልጽበታል፡፡ የመግባቢያ ቋንቋው የማህበረሰቡን እውነታ ለመግለጽ ብቃት መኖር ብቻ ሳይሆን የፍልስፍናውንና የእምነቱን ዕሴት ለመሸከምም አቅም አለው፡፡የማህበረሰቡ ሁለንተናዊ ጥንካሬ የተመሰረተው በቋንቋው ላይ ሲሆን መታወቂያና መለያ የሆኑት ባህሎች፣ ልማዶች፣ ወግና ስርዓቱንም ከቋንቋው ውጭ ማስብ የማይቻል ነው፡፡ ፪. ቀጥሎ ከተሰጧችሁ ርዕሶች አንዱን በመምረጥ ሶስቱን የድርሰት ክፍሎች (መግቢያ፣ ሐተታና መደምደሚያ) የያዘ አንድ አንቀጽ ጻፉ፡፡ ሀ. ኮሮና ለ. ትምህርት ቤቴ ሐ. በጎ ስነ-ምግባር ክፍል አምስት (፭) ቃላት የቃላት አጠቃቀም ፩. በፅሑፋችን ውስጥ የምንጠቀምባቸው ቃላት አንባቢያችን ሀሳባችንን እንዲረዳልን ለማድረግ ከፍተኛ ሚና አላቸው፡፡ በመሆኑም በአንድ ቋንቋ ውስጥ ተዘውታሪ /የተለመዱ/፣ ሙያዊ የመሳሰሉትን ቃላት ልንጠቀም እንችላለን፡፡ ተዘውታሪ ቃላት፡- ተዘውታሪ ቃላት የሚባሉት በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ዘንድ በስፋት የሚታወቁና በዕለት ከዕለት የምንገለገልባቸው ቃላት ናቸው፡፡ ምሳሌ፡- የሰላምታ ቃላት፡- ሰላም ሙያዊ ቃላት፡- የሚባሉት በተመሳሳይ ሙያ ላይ የተሰማሩ ሰዎች የሚያውቋቸውና የሚጠቀሙባቸው ሲሆኑ ሌላው የህብረተሰብ ክፍል በግልጽ 22 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፳፪ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል የማያውቃቸው ቃላት ናቸው፡፡ ምሳሌ፡- የህክምና ቃላት ፪. ቃላትን እያዋቀርን ዓረፍተ ነገር በምንመሰርትበት ጊዜ የቃላት ድግግሞሽ፣ ድረታ፣ የተሰለቹ ቃላት፣ የተውሶ ቃላትና አገላለጽ መጠቀም የለብንም፡፡ አላስፈላጊ የቃላት ድግግሞሽ፡- አንድን ቃል ያለ ዓላማ በዓረፍተነገር ውስጥ መደጋገም ቃላትን እንደማባከን ይቆጠራል፤ሃሳብን ያደበዝዛል፤ ውበት ይቀንሳል፤ መልዕክቱ በቀጥታ እንዳይተላለፍ እንቅፋት ይሆናል፡፡ ምሳሌ፡- ‹‹ፍቅርን ያወቅሁት በእርሱ ነው፤ ህይወትን ያጣጣምኩት በእርሱ ነው፤ ተድላና ደስታዬን ያየሁት በእርሱ ነው፡፡›› በሚሉት አረፍተ ነገሮች ውስጥ የተደጋገሙ ቃላት አፅንኦት ለመስጠት ታስቦ ቢሆንም ድግግሞሹ ግን ተገቢ አይደለም፡፡ የቃላት ድረታ፡- አንድ ቃል በራሱ የሚፈልገውን ትርጉም ማስተላለፍ እየተቻለ ሌላ ተጨማሪ ቃል ደርበን የምንጠቀምበት ከሆነ የቃላት ድረታ ይባላል፡፡ ምሳሌ፡- ራሴን አሞኝ ስለነበር ፓራሲታሞል መድሃኒት ውጨ ተኛሁ፡፡ በእስር ቤቱ ውስጥ ጽሁፎችን መጻፍ የሚያስቀጣ ነበር፡፡ በእነዚህ ምሳሌዎች እንደምንረዳው ፓራሲታሞል የሚለው ቃል የእንግሊዘኛ ቃል ቢሆንም …ዲፕሮን ውጬ ተኛሁ (…መድሃኒት ውጬ ተኛሁ፡፡) ማለት እየተቻለ፤ ዓረፍተ ነገሩ ድረታን አስተናግዷል፡፡ እንዲሁም … መጻፍ የሚያስቀጣ ነበር፡፡ ማለት እየተቻለ ጽሁፎችን መጻፍ የሚለው ድረታን ያመላክታል፡፡ የተሰለቹ ቃላት፡- ብዙ ጊዜ በተደጋጋሚ የምንሰማቸው አገላለፆች ናቸው፡፡ እነዚህ ቃላት በአንድ ወቅት ማራኪነትን የተላበሱ አባባሎች የነበሩ፤ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ትኩስነታቸውንና ኃይላቸውን ያጡ ቃላት ወይም ሀረጋት ናቸው፡፡ ምሳሌ፡-ውድ ወንድሜ የሰማይ ርቀቱን፣ የባህር ጥልቀቱን፣ የአሽዋ ብዛቱን፣ የከዋክብት ድምቀቱን ያህል እንደምን አለህ! የቀረበው አገላለጽ በቀደመው ጊዜ ደብዳቤ ሲጻፍ የተለመደና ለዛ ያለው ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ይህ አገላለጽ የተሰለቸ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ 23 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፳፫ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል ፩. በሚከተሉት ዓረፍተ ነገሮች ውስጥ የተደገሙ፣ የተሰለቹና የተደረቱ ቃላት ይገኛሉ፡፡ ስለሆነም በምሳሌው መሰረት ቃላትና ሃረጋቱን በሌሎች ቃላት በመተካት ዓረፍተ ነገርቹን አስተካክላችሁ ጻፉ፡፡ ምሳሌ በእግሩ ተራምዶ ደረሰብኝ፡፡ ሲስተካከል፡- ተራምዶ ደረሰብኝ፡፡ አጉል ሱስን የመተውና እርግፍ አርጎ የመተው እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡ ሲስተካከል፡- ሱስን እርግፍ አድርጎ የመተው እርምጃ ያስፈልጋል፡፡ 1. በርዕሰ ከተማችን በአዲስ አበባ የመኖሪያ ቤት ችግር አለ፡፡ 2. አርአያ መሆን ሲገባቸው አርኣያ አይሆኑም፡፡ 3. በሀቅ ላይ የተመሰረተ እውነተኛ አባባል ነው፡፡ 4. ስቃይ በርትቶብኝ እየተሰቃየሁ ቆየሁና ስቃዬን ልገልጽለት ፈልጌ አጎቴ ቤት በስንት ስቃይ ደረስኩ፡፡ 5. የአባቴ እህት የሆነችው አክስቴ መጣች፡፡ 6. ታላቁ ደራሲ በትናንትናው እለት ተቀብሮ ግብአተ መሬቱ ተፈጸመ፡፡ 7. በአእምሮዬ የማስበውን ያወቀብኝ መስሎኝ ድንግጥ አልኩ፡፡ ፪. በሚከተሉት ዓፍተነገሮች ውስጥ የሚገኙ ሙያዊና ተዘውታሪ ቃላትን ለይታችሁ አውጡ፡፡ ሀ. መሐመድ በቀዶ ጥገና ትናንት ተመረቀ፡፡ ለ. ቤቶች በሚገነቡበት ወቅት የውሃ ልካቸው ተጠብቆ መስራት አለባቸው፡፡ ሐ. ሰላምታ መለዋወጥ ከባህላችን አንዱ ነው፡፡ መ. መልካም ህይወት እንዲገጥማችሁ እመኝላችኋለሁ፡፡ ፫. የሚከተለው አንቀጽ የተሟላ ሃሳብ ማስተላፍ አይችልም፡፡ የተሟላ ሀሳብ ማስተላለፍ የሚችለው ያሉት ክፍት ቦታዎች በተገቢ ቃላት ሲሟሉ ነው፡ ስለዚህ ከቃላቱ መካከል እየመረጣችሁ በክፍት ቦታዎች በማስገባት አንቀጹ የተሟላ ሃሳብ ማስተላለፍ እንዲችል አድርጉ፡፡ (ቃላቱ ለሚገቡበት ቦታ ተስማሚ 24 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፳፬ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል ቅርጽ እንዲይዙ ማድረጋችሁን አትዘንጉ፡፡) 1. ቋጥኝ 3. አበባ 5. ስኩየር 2. ሜዳ፣ ፏፏቴ 4. ሰማይና ምድሩ 6. ምልክት … ጥቂት ቆይቶ ደግሞ ____________ (1) ቅርጽ እንደተዥጎረጎረ ብርድ ልብስ የተሸነሸነ አረንጓዴ ምድር ብቅ አለ፤ በአዝመራ የተንቆጠቶጠ ማሳ ____________ (2) የተሞሸረ ጋራ፣ በጅረት ጥበብ የተሰጣበት ____________ (3) የሚተፋ ቋጥኝ፡፡ የሀገሩ ሰማይ ለመሆኑ ሁሌም ማረጋገጫው ይሄ ነው፤ ከታች ያለውም የሀገሩ ምድር ለመሆኑ ሌላ ____________ (4) አላስፈለገውም የሀገሩ፣ ____________ (5) ከማንም ከሌላ ሀገር ሰማይና ምድር ጋር ተመሳስሎበት አያውቅም፡፡ (ይስመዐከ ወርቁ፣ ዮቶድ፣ 2009፡31) ክፍል ስድስት (፮) ሰዋስው የዓረፍተነገር ስልቶች የዓ.ነገር ስልቶች ከአገልግሎታቸው አንጻር ጥያቄያዊ፣ ሀተታዊ፣ትእዛዛዊና አጋናኝ ዓ.ነገር በመባል ይታወቃሉ፡፡ ሀ. ሐተታዊ ዓ.ነገር፡- ስለ አንድ ድርጊት ወይም ሁነት የሚያትትና መልዕክትን ማስተላለፍ ዓላማው አድርጎ የሚመሰረት ነው፡፡ ሐተታዊ ዓ.ነገር በውስጡ አዎንታዊና አሉታዊ ዓ.ነገሮችን ይይዛል፡፡ አዎንታዊ ዓ.ነገር፡- በአዎንታ የሚነገር የዓረፍተ ነገር ስልት ነው፡፡ ምሳሌ፡- ጓደኛዬ በጣም ጎበዝ ተማሪ ናት፡፡ እውቀት የማይሞት ሃብት ነው፡፡ አሉታዊ ዓ.ነገር፡- በአሉታ ወይም በአፍራሽ የሚነገር የዓረፍተ ነገር ስልት ነው፡፡ በውስጡም አፍራሽ የሆኑ ቅጥያዎችን (አል-ም፣ አይ- ም፣ አን - ም) ወዘተ…ይይዛል፡፡ ምሳሌ፡- ጎበዙ ተማሪ ዛሬ አልመጣም፡፡ ጓደኛዬ የእግር ኳስ መጫወት አይወድም፡፡ ለ. ጥያቄያዊ ዓ.ነገር፡- መጠይቃዊ ቃላትን ወይም የጥያቄ ምልክትን በመጠቀም 25 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፳፭ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል የሚመሰረት ሲሆን ምላሽ ሚያስፈልገው ዓ.ነገር ነው፡፡ ምሳሌ፡- የኮሮና ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው የት ሀገር ነው? ጓደኛሽ ነገ መምጣት ትችላለች? ሐ. ትዕዛዛዊ ዓ.ነገር፡- አንድ ነገር እንዲከናወን ወይም እንዲፈጸም ሲባል በትዕዛዝ መልክ የሚቀርብ የዓ.ነገር ስልት ነው፡፡ ይህ ዓረፍ ተነገር በአራት ነጥብና በትዕምርተ አንክሮ ሊቀርብ ይችላል፡፡ ምሳሌ፡- ነገ ሀገር ተረካቢ እንድትሆኑ በርትታችሁ ተማሩ! መልዕክቱን በነገርኩሽ መሰረት አድርሽ! መ. አጋናኝ ዓ.ነገር፡- ነገሮችን በማጋነን፣ በመገረም፣ በመደነቅ የሚያቀርብ ዓ.ነገር ሲሆን መደሰትን፣ መገረምን፣ መናደድና መሰል ስሜቶችን ያንፀባርቃል፡፡ ምሳሌ፡- ዋው! ዛሬ ቀኑ ደስ ይላል፡፡ እሰይ! እህቴ ነገ ከውጭ ሃገር ትመጣለች፡፡ ፩. የሚከተሉትን ዓረፍተ ነገሮች ከላይ የቀረበውን ማስታወሻ መነሻ በማድረግ ሐተታዊ (አዎንታዊ፣ አሉታዊ)፣ ትእዛዛዊ፣ መጠይቃዊና አጋናኝ እያላችሁ መልሷቸው፡፡ ሀ. እኛ ሳናየው ጠላት ቀድሞ ገብቷል፡፡ ለ. ዘምዘም ህይወቷን ሙሉ ለሃገሯ እየገበረች ነው፡፡ ሐ. ትምህርት ለሃገር እድገት መሰረት ነው፡፡ መ. የክብር እንግዳው ሳይመጣ ቀረ፡፡ ሠ. መምህራችን መጽሐፍ ማምጣት እንዳለብን ነገሩን፡፡ ረ. ከቢሮዬ በፍጥነት ውጣ! ሰ. ኦ! ፈጣሪዬ ከዚህ ፈተና አውጣኝ፡፡ ሸ. ወደ ኢትዮጵያ መቼ ትመለሳለህ? ፪. በሚከተሉት ቃላት ሐተታዊ፣ ትዕዛዛዊ፣ ጥያቄያዊና አጋናኝ ዓ.ነገሮችን መስርቱ፡፡ ሀ. ፈለገ (ሐተታዊ) ሠ. አመረቃ (ሐተታዊ) ለ. ብሩህ (አጋናኝ) ረ. ኩራት (አጋናኝ) 26 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፳፮ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል ሐ. ራእይ (ጥያቄያዊ) ሰ. ቆረጠ (ጥያቄያዊ) መ. መሰረት (ትዕዛዛዊ) ሸ. አረንቋ (ሐተታዊ) አዎንታዊ የሆኑ ሶስት ዓረፍተ ነገሮችን በመመስረት ወደ አሉታዊ ዓረፍተ ነገር ለውጧቸው፡፡ 27 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፳፯ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል የምዕራፉ ማጠቃለያ በዚህ ምዕራፍ ‹‹ባህላዊ ጋብቻ›› በሚል ርዕስ ስለ ክርክር ምንነት፣ ዝግጅትና አቀራረብ ተምራችኋል፡፡ ስለሆነም ክርክር በሁለት ቡድኖች ወይም ግለሰቦች መካከል በአንድ ርዕሰ ጉዳይ የተለያየ አቋምን በማራመድ የሚደረግ የሃሳብ ሙግት ነው፡፡ የክርክር አዘገጃጀት እና አቀራረብ መመሪያ መሰረት አድርጋችሁም ክርክር አቅርባችኋል፡፡ የድርሰት ክፍሎችን ተምራችኋል፡፡ እነዚህም መግቢያ፣ ሀተታና መደምደሚያ ሲሆኑ ክፍሎቹን ባካተተ መልኩ በተሰጣችሁ ርዕስ ድርሰት ጽፋችኋል፡፡ የቃላትን አውዳዊ ፍች በንግግርና በጽሁፍ ውስጥ ሰጥታችኋል፡፡ የቃላት አጠቃቀምን በተመለከተ ዘወትራዊና ሙያዊ ቃላትን በዓረፍተ ነገር ውስጥ በመለየት ጽፋችኋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዓረፍተ ነገር ውስጥ የተሰለቹ፣ የተደረቱና የተደጋገሙ ቃላትን በመለየት አስተካክላችሁ መጻፍ እንዳለባችሁ ተገንዝባችኋል፡፡ አንድን ቃል ያለ ዓላማ በዓረፍተነገር ውስጥ መደጋገም አስፈላጊ እንዳልሆነ፤ አንድ ቃል በራሱ የሚፈልገውን ትርጉም ማስተላለፍ እየተቻለ ሌላ ተጨማሪ ቃል ጨምረን መጠቀም እንደሌለባችሁና ብዙ ጊዜ በተደጋጋሚ የምንሰማቸው አገላለጾች በሌላ ጊዜ ትኩስነታቸውን ስለሚያጡ ይህን ግንዛቤ ውስጥ ማስገባጥ እንዳለባችሁ አይታችኋል፡፡ በመጨረሻም የዓረፍተ ነገር ስልቶችን በመለየት ሐተታዊ፣ ትእዛዛዊ፣ ጥያቄያዊና አጋናኝ ዓረፍተ ነገሮችን መስርታችኋል፡፡ የክለሳ ጥያቄዎች ፩. ክርክር የሚያቀርብ ሰው ከሚተገብራቸው ነጥቦች መካከል አራቱን ጠቅሳችሁ አብራሩ፡፡ ፪. በሚከተሉት የቃላት አጠቃቀሞች በራሳችሁ ሁለት ሁለት አረፍተ ነገሮችን ለእያንዳንዱ መስርቱ፡፡ 28 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፳፰ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል ሀ. ሙያዊ ቃላት ለ. ዘወትራዊ ቃላት ሐ. አላስፈላጊ የቃላት ድግግሞሽ መ. ድረታ ሠ. የተሰለቹ ቃላት ፫. የሚከተሉትን የአረፍተ ነገር ስልቶች ተጠቅማችሁ ሁለት ዓረፍተ ነገሮችን መስርቱ፡፡ ሀ. ጥዕዛዛዊ ዓረፍተ ነገር ለ. ጥያቄያዊ ዓረፍተ ነገር ሐ. ሐተታዊ ዓረፍተ ነገር መ. አጋናኝ ዓረፍተ ነገር ፬. መግቢያ ፣ሀተታና መደምደሚያ ያለው ከአንድ ገጽ ያልበለጠ አጭር ጽሁፋ ጻፉ፡፡ ፭. በሚከተሉ ቃላት ዓረፍተ ነገር ከመሰረታችሁ በኋላ አውዳዊ ፍቻቸውን ጻፉ፡፡ ሀ. ራደ ሐ. አገደ ለ. በላው መ. ሰማ የግንዛቤ ማመሳከሪያ ነጥቦች ተ.ቁ የማመሳከሪያ ነጥቦች (√) (?) (X) ፩ ስለ ባህላዊ ጋብቻ የማውቃቸውን ለጓደኞቼ መናገር እችላለሁ፡፡ 2 ንግግሮችን በማዳመጥ ግብረ መልስ መስጠት እችላለሁ፡፡ 3 የክርክር አዘገጃጀትና አቀራረብ መመሪያን መሰረት በማድረግ በማንኛውም ርዕስ መከራከር እችላለሁ፡፡ 29 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፳፱ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል 4. ለቃላት ዓውዳዊ እና መዝገበ ቃላዊ ፍች መስጠት እችላለሁ፡፡ 5 የጽሁፍን ሀሳብ አገናዝቤ አነባለሁ፡፡ 6 የድርሰት ክፍሎችን መለየት እችላለሁ፡፡ 7. የደርሰት ክፍሎች መሰረት አድርጌ በተሰጠኝ ርዕስ ድርሰት መጻፍ እችላለሁ፡፡ 8 በጽሁፍ ውስጥ ሙያዊና ዘወትራዊ ቃላትን መለየት እችላለሁ፡፡ 9. የተሰለቹ ቃላት፣ የቃላት ድግግሞሽና ድረታ ለይቼ ማስተካከል እችላለሁ፡፡ ፲. ዓረፍተ ነገር ስልቶችን በመለየት በተሰጡት ቃላት ዓረፍተ ነገር መመስረት እችላለሁ፡ ፪. ከዚህ በላይ በሰንጠረዥ የ(?) እና የ (X) ምልክት ያደረጋችሁባቸውን ነጥቦች በሚገባ እስክትረዷቸው፣ ድረስ የምዕራፉን ትምህርት ደጋግማችሁ ከልሱ፡፡ 30 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፴ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል አማርኛ ፲ኛ ክፍል ምዕራፍ ሶስት (፫) ሴቶች እና እድገት የምዕራፉ አጠቃላይ ዓላማዎቸ፡-ተማሪዎች ይህን ምዕራፍ ከተማራችሁበኋላ፡- ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን በሴቶች እና እድገት ዙሪያ የቀረቡ ሀሳቦችን አዳምጣችሁ የተናጋሪውን ሀሳብ ትገመግማላችሁ፡፡ አንድን ምንባበ አንብባቸሁ ተፈላጊውን ሀሳብ ታወጣላችሁ፡፡ በሴቶችና እድገት ዙሪያ ቃለ መጠይቅ በማድረግ ያገኛችሁትን ሀሳብ በቃል ታንጸባርቃላችሁ፡፡ ለተሰጣችሁ ጽሁፍ በአንድ አንቀጽ ማጠቃለያ ትጽፋላችሁ፡፡ ከውስብስብ ዓርፍተ ነገሮችን ነጠላ አርፍተ ነገረሮችን በማውጣት ትጠቀማላችሁ፡፡ 31 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፴፩ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል ክፍል አንድ (፩) ማዳመጥ ተመጣጣኝ ወግ ያላየው ወጋየሁ ንጋቱ የቅድመ ማዳመጥ ጥያቄዎች ፩. በሀገራችን ከምታውቋቸው ታዋቂ የጥበብ ሰዎች መካከል የተወሰኑትን ጥቀሱ፡፡ ፪. ቀጥሎ መምህራችሁ ‹‹ተመጣጣኝ ወግ ያላየው ወጋየሁ ንጋቱ›› የሚል አንድ አጭር ጽሁፍ ሁለት ጊዜ ያነቡላችኋል፡፡ ማዳመጥ ከመጀመራችሁ በፊት ሀ. ከዚህ ርዕስ ምን ምን ነጥቦች ይነሳሉ ብላችሁ ትገምታላችሁ? ግምታችሁን በየግላችሁ ለመምህራችሁ ተናገሩ፡፡ ለ. ወጋየሁ ንጋቱ የተባለውን ታላቅ ሰው በየትኛው ስራው ታስታውሱታላችሁ? ፫. መምህራችሁ ምንባቡን ሲያነቡላችሁ ማስታወሻ እየያዛችሁ ካዳመጣችሁ በኋላ የአዳምጦ መረዳት ጥያቄዎችን በየግላችሁ ሰርታችሁ በቡድን ተወያዩባቸው፡፡ መልሳችሁን ለመምህራችሁ በቃል አቅርቡ፡፡ የአዳምጦ መረዳት ጥያቄዎች ሀ. ወጋየሁ ንጋቱ ልጆች የሚከቡትና ዓይኖች የሚከተሉት ተወዳጅና ተፈቃሪ ልጅ የነበረው በምን ምክንያት ነበር? ለ. ወጋየሁ ለመጀመሪያ ጊዜ የተወነው ትያትር ምን የሚል ነበር? ሐ. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን ወጋየሁን በሙያው እንዲገፋበት ያበረታቱት የነበረው በምን ምክንያት ነው? መ. ከወጋየሁ ታሪክ ምን እንደተማራችሁ በየግላችሁ አስረዱ፡፡ ሠ. ሴቶች በሀገር እድገት ላይ ስላበረከቷቸው የተለያዩ ተግባራት በመገናኛ ብዙሃን የሚተላፉ መርሀግብሮችን በቤታችሁ ወይም ምቹ ሁኔታን በሚፈጥርላችሁ ቦታ ሆናችሁ አዳምጡ፡፡ ካዳመጣችሁ በኋላ 32 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፴፪ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል በቀጣዩ ክፍለ ጊዜ የተናጋሪዎቹን ሀሳብና አመለካከት በመገምገም በክፍል ውስጥ ለተማሪዎች በቃል አቅርቡ፡፡ ክፍል ሁለት (፪) መናገር ፩.አጀንዳቸውን በሴቶች እድገት ላይ ያደረጉ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃንን (ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ ወ.ዘ.ተ) አዳምጡ፡፡ ስታዳምጡ የተናጋሪዎቹን መልዕክት፣ አመለካከትና ዝንባሌ በአግባቡ ከመረመራችሁ በኋላ የተረዳችሁትን በክፍል ውስጥ ለጓደኞቻችሁ በቃል አቅርቡ፡፡ ፪. በአካባቢያችሁ ወደሚገኙ የህዝብ መገልገያ ተቋማት ቢሮ ኃላፊዎች በመሄድ ከታች የቀረበውን የቃለ መጠይቅ መመሪያ መሰረት አድርጋችሁ ቃለ መጠይቅ አድርጉ፡፡ መረጃ ለመሰብሰብ እንድትችሉ የሚከተሉትን ነጥቦች ተግባር ላይ አውሉ፡፡ ሀ. አምስት አባላት ያለው ቡድን በመመስረት መረጃ ሊገኙባቸው የሚችሉ መሰረታዊ ጥያቄዎችን አዘጋጁ (ጥያቄዎቻችሁ ስለመረጣችሁት ተቋም ጥሩ መረጃ የሚሰጡ መሆናቸውን አረጋግጡ፡፡) ለ. ስለተቋሙ መረጃ የሚሰጧችሁን ሶስት ሰዎች ምረጡ፡፡ ሐ. በጥያቄዎቻችሁ መሰረት የሰበሰባችኋቸውን መረጃዎች በጽሁፍ አዘጋጅታችሁ በቡድን መሪያችሁ አማካኝነት ለመምህራችሁና ለጓደኞቻችሁ በቃል አቅርቡ፡፡ ቃለ-መጠይቅ ቃለ መጠይቅ ጠያቂው ከተጠያቂው ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ መረጃ የሚሰበሰብበት ሒደት ነው፡፡ ቃለ መጠይቅ የተዋቀረ ወይም ያልተዋቀረ ሊሆን ይችላል፡፡ በተዋቀረ የቃለመጠይቅ አቀራረብ ጊዜ የምንተገብራቸው ነጥቦች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡ የቃለ መጠይቅ አቀራረብ ◆ ለቃለ መጠይቁ ዝግጁ በመሆናቸው ተጠያቂዎችን በቅድሚያ ማመስገንና ዓላማውን በአጭሩ ማስተዋወቅ፣ ◆ የወዳጅነትና የመግባባት ስሜት መፍጠር፣ 33 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፴፫ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል ◆ ጥያቄዎችን በልበ ሙሉነት በቅደም ተከተል ማቅረብ፣ ◆ ትህትና ያልተለየው አቀራረብ ማሳየት (ግትርና ተሟጋች አለመሆን) ◆ አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነትን ማስወገድ፣ ◆ ዋና ዋና ሀሳቦችን እያዳመጡ ማስታዎሻ መያዝ፣ ◆ በተጠያቂው ዘንድ ግልጽና ታማኝ ሆኖ መገኘት (የመዘገቡትን መረጃ ለተጠያቂው መልሶ ማሳየት) ◆ ሁኔታዎችን እዳስፈላጊነቱ ለመቀያየር ዝግጁነት ማሳየት ◆ ቃለ መጠይቁ ሲጠናቀቅ ተጠያቂውን ማመስገን የሚሉት በቃለ መጠይቅ፣ አቅርቦት ወቅት የሚከናወኑ ተግባራት ናቸው፡፡ ፫. ‹‹በአካባቢያችሁ በሚገኙ ማንኛውም ማህበራዊ መስተጋብሮች ላይ ሴቶችን ማሳተፍ ስላለው ጠቀሜታ ቃለ ምልልስ አድርጉ፡፡ ቃል ምልልሱን በክፍል ውስጥ ከማቅረባችሁ በፊት መለማመዳችሁንና ጠቃሚ ነጥቦችን ማንሳታችሁን አትዘንጉ፡፡ ክፍል ሶስት (፫) ንባብ እቴጌ ጣይቱ ብጡል የቅድመ ንባብ ጥያቄዎች ሀ. የኢትዮጵያ ሴቶች ተሳትፎ በሀገር እድገት ላይ የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ ጥቀሱ፡፡ ለ. በማንኛውም የሙያ መስክ ላይ ተሰማርተው አንቱታን ያተረፉ የሀገራችንን ሴቶች ተናገሩ፡፡ ሐ. ቀጥሎ ‹‹እቴጌ ጣይቱ ብጡል›› በሚል የቀረበው ንባብ የሚያነሳቸው ነጥቦች ምን ምን ሊሆኑ ይችላሉ ብላችሁ ትገምታላችሁ? ንባብችሁን ስታነቡ እንግዳ የሆኑ ቃላት ካጋጠሟችሁ መዝግባችሁ በመያዝ ከንባብ በኋላ ተነጋገሩባቸው፡፡ 34 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፴፬ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል እቴጌ ጣይቱ ብጡል እቴጌ ጣይቱ ነሐሴ ፲፪ ቀን ፲፰፻፴፪ ዓ.ም. ከአባታቸው ከደጃዝማች ብጡል ኃ/ ማሪያም እና ከእናታቸው ከወ/ሮ የውብዳር ደብረ ታቦር ከተማ ውስጥ ተወለዱ፡ አባታቸው የጎንደርና የወሎ፣ እናታቸው ደግሞ የጎጃም ተወላጅ ናቸው፡፡ ጣይቱ ለቤተሰባቸው ሶስተኛ ልጅ ናቸው፡፡ አባታቸው በጦርነት በመሞታቸው በ፲፫ ዓመታቸው ደብረ ታቦርን ለቀው ወደ እናታቸው ትውልድ ቦታ ወደ ጎጃም ሄዱ፡፡ ጎንደር እያሉ በማህደረ ማሪያም የጀመሩትን ትምህርታቸውን በጎጃም ደብረማዊ ደብር ቀጠሉበት፡፡ በዚህ ገዳም ውስጥ ንባብንና ጽሕፈትን፣ የግዕዝና የአማርኛ ቅኔ፣ በገና ድርደራንና የሰንጠረዥ ጨዋታን ተማሩ፡፡ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ በጥበብና በህይወት ፍልስፍና የላቀ ችሎታ እንዳላቸው እየታወቀ መጣ፡፡ ጣይቱ ደብረማዊ ገዳም እያሉ ወንድማቸው ራስ አሉላ በመሞታቸው ወደ ሸዋ መጡ፡፡ አፄ ምኒልክ በ፲፰፻፹፱ ዓ.ም. የፋሲካን በዓል በባህር ዳር አቅራቢያ ሄደው 35 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፴፭ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል በጣይቱ ብጡል እናት በወ/ሮ የውብዳር ቤት ውስጥ ሲያከብሩ በአጋጣሚ ከጣይቱ ጋር ተጫጭተው ሚያዚያ ፳፭/፲፰፻፸፭ ዓ.ም. በአንኮበር መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ተጋቡ፡፡ ጥቅምት ፳፯ ቀን ፲፰፻፹፪ ዓ.ም ጣይቱ ብጡል ‹‹እቴጌ›› ተብለው ተሰየሙ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ስማቸው በመላው ሀገሪቱ ነገሠ፡፡ ከዚህ በኋላ እቴጌ ጣይቱ በፖለቲካዊ፣ በወታደራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና አጠቃላይ በሀገር ግንባታ ታላቅ ስራ የሰሩ የቆራጥነትና የአስተዋይነት ታሪክ ካላቸው ምርጥ ሴቶች መካከል አንዷ መሆን ቻሉ፡፡ አፄ ምኒልክ አዳዲስ ስልጣኔዎችንና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ከውጪ ለማስገባት ቁርጠኛ አቋም ይዘው ሲሰሩ፣ ዋና አማካሪያቸውና አጋራቸው እቴጌ ጣይቱ ነበሩ፡፡ አፄ ምኒልክ ወደ ዘመቻ ሲንቀሳቀሱ የመንግስት አይንና ጆሮ ሆነው አገልግለዋል፡፡ ጣሊያናዊው ጋዜጠኛ ኮራዶ ዞሊ ‹‹የዛሬይቱ ኢትዮጵያ›› በሚለው መጽሐፋቸው ስለ ጣይቱ ሲጽፉ ‹‹ጣይቱ ቆንጆ ብቻ ሳይሆኑ ደስ የሚሉ ደማም እጅግ ብልህና ጀግና ናቸው፡፡››ብለው በአድናቆት ጽፏል፡፡ እቴጌ ጣይቱ‹‹ብርሀን ዘ ኢትዮጵያ›› በሚል ቅጽል ስም መጠራት የጀመሩትም ከዚህ በኋላ ነው፡፡ ተማሪዎች! አሁን ደግሞ ንባባችሁን ገታ አድርጉና ከላይ ካነበባችኋቸው አንቀጾች ምን እንደተረዳችሁ ለመምህራችሁ ንገሯቸው፡፡ ቀጥሎ የቀረቡት አንቀጾችስ ምን ላይ ያተኩራሉ ብላችሁ ትገምታላችሁ፡፡ እቴጌ ጣይቱ በፖለቲካው መስክ በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ግንባር ቀደም በመሆን ውሳኔ በመስጠትና የአፄ ምኒልክ አማካሪ በመሆን ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡ አፄ ምኒልክ ጣይቱን ሳያማክሩ የሚወስኑት ምንም አይነት ውሳኔ አልነበረም፡፡ የፖለቲካ ህይወታቸው ይበልጥ ገኖ የወጣውም ሚያዚያ/፳፭ ቀን ፲፰፻፹፩ ዓ.ም. በአንቶኖሊና በምኒልክ መካከል በተፈጠረው የውጫሌው ስምምነት ላይ ነበር፡፡ስምምነቱ እንዳይፈረምና አገሪቱ አደጋ ውስጥ እንዳትገባ ብዙ ታግለዋል፡፡ ይህንን አስመልክቶ ለሕዝባ ቸው ሲናገሩ ‹‹እኔ ሴት ነኝ ጦርነት አልወድም፤ሆኖም ይህን ኢትዮጵያን የኢጣሊያ ጥገኛ የሚያደርገውን ውል ከመቀበል ጦርነትን 36 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፴፮ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል እመርጣለሁ›› ብለው በምሬት ተናግረው ነበር፡፡ በዚሁ መሰረት በራሳቸው የሚመራ ፴፻ እግረኛ ጦርና ፷፻ ፈረሰኛ አስከትለው ከባለቤታቸው ጎን በመሰለፍ የካቲት/፳፫ ቀን ፲፰፻፹፰ ዓ.ም አድዋ ላይ ጠላትን ድል አደረጉ፡፡ ከአድዋ ጦርነት በፊትም የኢጣሊያን ጋዜጠኞች እኚህን ጀግናና ሀይለኛ ሴት በተመለከተ በዕትማቸው ያቀርቡ ነበር፡፡ ጣይቱ በአድዋ ጦርነት ጊዜም ብዙ ጀብድ ፈጽመዋል፡፡ ‹‹በባህር ከልሎ የሰጠንን አገራችንን የሚቀማ ጠላት መጥቶ እንዴት ዝም እንላለን›› በሚለው ወኔ ቀስቃሽ ንግግራቸው በሰራዊታቸው ተደግፈው እየተፎከረላቸውና እየተሞገሱ ወደ አድዋ ዘመቱ፡፡ ጦርነቱ ከመካሄዱ በፊትም በመቀሌና አካባቢው ሸምቆ የነበረውን የጠላት ሰራዊት ይጠቀምበት የነበረውን የውሃ ገንዳ በ፸፭ኪ.ሜ. ርቀት ላይ አስከብበው የጠላት ሰራዊት በውሃ ጥም እንዲሞትና በመጨረሻም ከምሽጉ ፈርጥጦ እንዲሸሽ ያደረጉትም እኝሁ ብልህ ሴት ናቸው፡፡ እንደተዋጊና የጦር መሪ ብቻ ሳይሆኑ የቆሰሉትን በማከም፣ የተራቡትን በመመገብ፣ የተጠሙትን በማጠጣትና የደከሙትን በማበረታታት ጦሩ በወኔ እንዲዋጋ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡ ከጦርነቱ መልስም አባትና እናት የሌላቸውን ህጻናት በመንከባከብ፣ በማሳደግና በማስተማር ተግባር ላይ ተሰማርተው ነበር፡፡ ጣይቱ በመንፈሳዊ ህይወታቸውም በጣም ጠንካራና ለሌሎች አርዓያ የነበሩ ሴት ናቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በስማቸው የመጀመሪያውን ሆቴል ጣይቱ ሆቴልን አሰርተዋል፡፡ ለአሁኗ አዲስ አበባ መቆርቆርና ስያሜ መሰረት ጥለውም አልፈዋል፡፡ እቴጌ ጣይቱ የካቲት ፬/፲፱፻፲ ዓ.ም በ፹፰ ዓመታቸው በማረፋቸው በመንበረ ፀሐይ እንጦጦ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ስርአተቀብራቸው ተፈፀመ፡፡ ከሞቱከ፶ ዓመት በኋላም ‹‹ታላቋ ንግስት››በሚል የኢትዮጵያ ፖስታ ድርጅት በስማቸው ቴምብር አተመላቸው፡፡ (ብርሃኑ ለማ፣‹‹የታዋቂ የኢትዮጵያ ሴቶች የፖለቲካና የፍቅር ታሪክ›› ከሚል 37 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፴፯ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል መጽሐፍ ለማስተማሪያነት እንዲያመች ተደርጎ የተወሰደ፣ከገጽ114-130) የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች ፩. የሚከተሉትን ጥያቄዎች በምንባቡ መሰረት በጥንቃቄ በማንበብ ትክክል ከሆኑ ‹‹እውነት›› ስህተት ከሆኑ ደግሞ ‹‹ሀሰት›› በማለት በቃል መልሱ፡፡ ሀ. አፄ ምኒልክ ጣይቱን ሳያማክሩ የሚወስኑት ምንም አይነት ውሳኔ አልነበረም፡፡ ለ. እቴጌ ጣይቱ ንባብንና ጽሕፈትን እንዲሁም ቅኔን የተማሩት በደብረማዊ ገዳም ነው፡፡ ሐ. እቴጌ ጣይቱ በሀገር ግንባታ ላይ ታላቅ ስራ በመስራት የቆራጥነትና የአስተዋይነት ተምሳሌት መሆን የቻሉት አጼ ምኒልክን ከማግባታቸው በፊት ጀምሮ ነው፡፡ መ. የኢጣሊያ ጋዜጠኞች እቴጌ ጣይቱን በተመለከተ የተለያዩ ፅሑፎችን በዕትማቸው ያቀርቡ ነበር፡፡ ሠ. ጣይቱ ከአድዋ ጦርነት በኋላ አባትና እናት የሌላቸውን ህጻናት ይንከባከቡ ነበር፡፡ ፪. ቀጥሎ የቀረቡትን ጥያቄዎች በጥሞና ካነበባችሁ በኋላ ምንባቡን መሰረት በማድረግ በጽሁፍ መልስ ስጡ፡፡ ሀ. ጣይቱ ወይዘሮ የውብዳር ወዳሉበት ጎጃም ደብረማዊ ወደምትባል ገዳም የሄዱት በምን ምክንያት ነበር? ለ. የፖለቲካ ህይወታቸው ይበልጥ ገኖ የወጣው በምን ምክንያት ነው? አብራሩ፡፡ ሐ. በአድዋ ጦርነት ወቅት የኢጣሊያ ጦር ከምሽጉ ፈርጥጦ የሸሸው በምን ምክንያት ነው? መ. እቴጌ ጣይቱ ‹‹ብርሀን ዘ ኢትዮጵያ›› በሚል ቅጽል ስም መጠራት የጀመሩት ከመቼ ጀምሮ ነው? ለምን? ሠ. እቴጌ ጣይቱ ደብረ ታቦርን ለቀው ወደ እናታቸው ትውልድ ቦታ ወደ ጎጃም የሄዱት በምን ምክንያት ነው? ረ. እቴጌ ጣይቱ ለሀገራቸው ካከናወኗቸው ጉልህ ተግባራት መካከል ሶስቱን ጥቀሱ፡፡ 38 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፴፰ Ethiofetena.com Ethiopian No 1 Educational Website አማርኛ ፲ኛ ክፍል ፫· ቀጥሎ የቀረቡት ቃላት ከምንባቡ የወጡ ናቸው፤ ስለሆነም በምንባቡ መሰረት ፍቻቸውን ጻፉ፡፡ ሀ. ወግ ረ. ጀብድ ለ. ተጫጩ ሰ. ሸምቆ ሐ. ባጋጣሚ ሸ. ተሰማርተው መ. ደማም ቀ. አርዓያ ሠ. ውል በ. አረፉ ፬. መረጃዎችን ለማግኘት የምንጠቀምባቸውን የተለያዩ የንባብ ስልቶች በመዘርዘር ተወያዩባቸው፡፡ የንባብ ስልቶች አንድ አንባቢ ጽሑፍ ሲያነብ ካለው ዓላማ ተነስቶ የሚከተሉት ስልቶች ሊጠቀም ይችላል፡፡ የአሰሳ ንባብ ይህ የንባብ ስልት ከአንድ ጽሁፍ ውስጥ የምንፈልገውን አንኳር ሃሳብ በፍጥነት አንብቦ ለማግኘት ይጠቅማል፡፡ በአሰሳ ስናነብ መስመር በመስመር ማንበብ አይጠበቅብንም፡፡ ምክንያቱም ከአንድ ጽሁፍ ውስጥ አንድ ተፈላጊ መረጃ ነጥሎ ለማውጣትና ለይቶ ለመረዳት በፍጥነት የሚከናወን የንባብ ስልት ስለሆነ ነው፡፡ የገረፍታ ንባብ የገረፍታ ንባብ ከቀረበ አሃድ ውስጥ በአንድ ጊዜ በርከት ያሉ ቃላትን በአይናችን በመቃኘት ጠቅለል ያለ መረጃን ለማግኘት፣ የአንባቢውን በራስ የመተማመን ብቃት ለመገንባትና ለፈተና ዝግጅት የተደረገ ንባብን ለማስታወስ ወዘተ የምንጠቀምበት የንባብ አይነት ነው፡፡ ጥልቅ ንባብ በጽሁፍ ከቀረበ አሃድ ውስጥ እያንዳንዱን ዝርዝር ነገር በጥልቅ በመፈተሽ 39 ፲ኛ ክፍል አማርኛ የተማሪ መጽሐፍ ፴፱

Use Quizgecko on...
Browser
Browser