Grade 6 Environmental Science 56 PDF
Document Details
Uploaded by LustrousSavanna6540
Abiyot Primary School
Tags
Summary
This document is a chapter from a grade 6 environmental science textbook covering various topics, including HIV/AIDS, harmful practices such as female genital mutilation and child marriage, and environmental issues like drought. It includes details about the causes, consequences, and methods for combating these issues.
Full Transcript
Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አምስት ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ምዕራፍ አምስት ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ተማሪዎች ይህን ምዕራፍ ይዘት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ ፡- የኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ምንነት ትገልጻላችሁ። በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ልንጋለጥ የምንችልባቸውን መንገዶች ታስረዳላችሁ። ከኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ራሳችንን ለመጠበቅ መደረግ...
Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አምስት ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ምዕራፍ አምስት ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ተማሪዎች ይህን ምዕራፍ ይዘት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ ፡- የኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ምንነት ትገልጻላችሁ። በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ልንጋለጥ የምንችልባቸውን መንገዶች ታስረዳላችሁ። ከኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ራሳችንን ለመጠበቅ መደረግ ስለሚገባው ጥንቃቄ ታብራራላችሁ። አደገኛ ኬሚካሎችና ዕፆችን ትለያላችሁ፡፡ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ትለያላችሁ፡፡ በአካባቢያችሁ የሚገኙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ታወግዛላችሁ፡፡ የድርቅና የረሃብ ፅንሰ ሐሳብን ትናገራላችሁ፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ ለሚታየው ድርቅ መንሥኤውንና ውጤቱን ትለያላችሁ፡፡ የምሥራቅ አፍሪካን የዝናብ መጠንና ለድርቅ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን የሚያሳይ ካርታ በመመልከት ግንኙነታቸውን ትገልጻላችሁ፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ ለድርቅ ተጋላጭ ቦታዎችን ትለያላችሁ፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ ድርቅን ለመቋቋም የሚያስችሉ ሀገር በቀል ዘዴዎችን ትዘረዝራላችሁ፡፡ 149 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አምስት ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች 5.1 ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ በኢትዮጵያ ከንዑስ ርዕሱ የሚጠበቁ አጥጋቢ የመማር ብቃቶች ይህንን ንዑስ ትምህርት ተምራችሁ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፡- የኤች አይ ቪ/ኤድስን ምንነት ትገልጻላችሁ። በኤች አይ ቪ/ኤድስ ልንጋለጥ የምንችልባቸውን መንገዶች ታስረዳላችሁ። ከኤች አይ ቪ/ኤድስ ራሳችንን ለመጠበቅ መደረግ ስለሚገባው ጥንቃቄ ታብራራላችሁ። ቁልፍ ቃላት ኤድስ ቫይረስ ምክር የማነቃቂያ ጥያቄዎች 1. ኤች አይ ቪ/ኤድስ ምንድነው? 2. ኤች አይ ቪ/ኤድስ እንዴት ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል? 3. ከኤች አይ ቪ/ኤድስ ራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንችላለን? ኤች አይ ቪ/ኤድስ፡ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ በቫይረስ የሚመጣ በሽታ ነው። ይህ በሽታ ነጭ የደም ህዋሳትን በማጥቃት የሰውነታችንን በሽታ የመከላከል አቅም ያዳክማል፡፡ የኤች አይ ቪ (HIV) ስያሜ የተወሰደው ‘’ሂዩማን ኢሚዩኖ ዴፊሽየንሲ ቫይረስ (Human Immune deficiency Virus|) ከተሰኘ የእንግሊዘኛ ስያሜ ሲሆን ይህም፡- - የሰው (Human): - በሽታ የመከላከል አቅምን የሚያዳክም (Immune deficiency): - በሽታ አምጪ ተህዋስ (Virus): ኤድስ (AIDS) የሚለው ደግሞ ‘’አኳየርድ ኢሚዩኖ ዴፊሽየንሲ ሴንድሮም (Acquired Immune Deficiency Syndrome)’’ ይህም፡- - ከሰው ወደ ሰው ተላላፊ Aquired (A)፦ - የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም ማዳከም አጥቂ Immune Deficiency(ID)፦ - የበሽታ ምልክቶች Syndrome (S) የሚል ስያሜ አለው:: 150 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አምስት ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ኤድስ (AIDS) በራሱ በሽታ ሳይሆን የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅምን በማዳከም ለሞት ለሚያበቁ የተለያዩ የበሽታ ዓይነቶች የመጋለጥ ሁኔታ ነው። የኤች አይ ቪ/ኤድስ መተላለፊያ መንገዶች ኤች አይ ቪ/ኤድስ በሚከተሉት መንገዶች ይተላለፋል። እነዚህም፦ y ልቅ የሆነ ግብረ- ስጋ ግንኙነት y በእርግዝና ወቅት ከእናት ወደ ልጅ y ስለታም ነገሮችን በጋራ በመጠቀም y ያልተመረመረ የደም ልገሳ በመውሰድ ምስል 5.1 ኤች.አይ. ቪ የሚተላለፍባቸውና የማይተላለፍባቸው መንገዶች ኤች አይቪ/ ኤድስ በመነካካት፣ አብሮ በመኖርና አብሮ በመብላት አይተላለፍም። የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ዋና ዋና ምልክቶች አንድ በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ የተያዘ ሰው የሚከተሉት ዓበይት ምልክቶች ሊታዩበት ይችላል። በአጭር ጊዜ ውስጥ የሰውነት ክብደት መቀነስ፣ ለብዙ ጊዜ የሚቆይ ተቅማጥ፣ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ትኩሳት፣ የድካም ስሜት መሰማት፣ የረጅም ጊዜ ራስ ምታትና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ 151 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አምስት ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያ መንገዶች ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን በሚከተሉት መንገዶች መከላከል ይቻላል። ሳይመረመሩ ከጋብቻ በፊት የግብረ-ስጋ ግንኙነት አለማድረግ ስለታም ነገሮችን በጋራ አለመጠቀም በእርግዝና ወቅት ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ የህክምና ክትትል ማድረግ ደም በሚለገስበት ጊዜ የተመረመረ እና ከቫይረሱ የጸዳ ደም መውሰድ ናቸው። በተጨማሪም ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከላከል የሚከተሉትን የህይወት ክህሎቶች ማዳበር አስፈላጊ ነው። እነዚህም የህይወት ክህሎቶች፡ y መተሳሰብ y ጭንቀትን መቋቋም y መተባበር y የመግባባት ችሎታን ማዳበር y በራስ መተማመን y በተገቢው ውሳኔ መጽናት y ራስን መግዛት የቡድን ውይይት 5.1 ዓላማ፡ ኤች.አይ.ቪ በምሥራቅ አፍሪካ ላይ ያለው ተፅእኖ መገንዘብ መመሪያ፡ ተማሪዎች በቡድናችሁ ኤች.አይ.ቪ. እና ኤድስ በምሥራቅ አፍሪካ ላይ የሚያደርሰውን ጫና በተመለከተ መረጃ ፈልጋችሁ በመወያየት ገለጻ አድርጉ፡፡ የምክር አገልግሎት የምክር አገልግሎት ማለት ምክር ሰጪዎች እና በተመካሪዎች መካከል በውይይት የሚካሄድ የሥራ ግንኙነት ነው፡፡ ይህ የምክር አገልግሎት አስጨናቂ ያልሆነ ውሳኔ ወይም ፍርድ አልባ የሆነና በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ የምክር አገልግሎት ዓላማና ተግባር ችግር በሚከሰትበት ጊዜ ድጋፍ መስጠት፡፡ የተዛባ አመለካከትን መለወጥ፡፡ 152 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አምስት ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ልዩ ልዩ ችግሮች ሲያጋጥሙ መወሰድ የሚገባቸውን እርምጃዎች መጠቆም፡፡ ግለሰቦች በጤናና ማህበራዊ ደህንነት አግባብነት ያላቸውን መረጃ እንዲቀበሉና ተፅዕኖዎችን እንዲቋቋሙ መርዳት ነው፡፡ መልመጃ 5.1 የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሱ፡፡ 1. ቫይረስ ምንድን ነው? 2. ኤች አይ ቪ/ኤድስ መተላለፌያ እና መከላከያ መንገዶችን ዘርዝሩ፡፡ 3. የምክር ገልግሎት ምን እንደሆነ አብራሩ:: 4. እናንተ ራሳችሁን ከኤች አይ ቪ ኤድስ እንዴት ትከላከላላችሁ? 5.2 በወረዳችን የሚገኙ ኬሚካሎችና ተገቢነት የሌላቸው የመድኃኒት አጠቃቀም ከንዑስ ርዕሱ የሚጠበቅ አጥጋቢ የመማር ብቃት ይህንን ንዑስ ርዕሱ ተምራችሁ ካጠናቀቃሁ በኋላ፡- አደገኛ ኬሚካሎችና ዕፆችን ትለያላችሁ፡፡ የሰው ልጅ በዕለት ከእለት እንቅስቃሴው የታሸጉ ምግቦችና መጠጦች፣ የፀረ-ነፍሳት ኬሚካሎችንና የተለያዩ መድሐኒቶችን ለተለያየ አገልግሎት በሰፊው በመጠቀም ላይ ይገኛል፡፡ ነገር ግን እነዚህን ምግቦችና መጠጦች፣ ኬሚካሎችና መድሐኒቶችን እንዳይበላሹ ለፀሀይ ብርሀን ተጋላጭ አለማድረግ፣ በደረቅ ቦታ ማስቀመጥ፣ ያገልግሎት ጊዜያቸው ሳያልቅ በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ የተበላሹ ምግቦችና መጠጦች፣ ኬሚካሎችና መድሐኒቶችን በአግባቡ ካልተወገዱ የሰውልጆችን፣ ዕፅዋትን እና እንስሳትን ይጎዳሉ፡፡ በተፈጥሮ የሚገኙና የተቀመሙ እንዲሁም በተለያየ መልክ የተዘጋጁና የሚወሰዱ መድሃኒቶች አሉ። እነዚህ መድሃኒቶች በትክክል ከተወሰዱ ህመምንና በሽታን ሊያስታግሱና ከበሽታም ሊያድኑ ይችላሉ። አብዛኛዎቹ እንደ አስፕሪን፣ ሞርፊን፣ ኮዴየን፣ የእንቅልፍ ክኒንና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል። ነገር ግን መድሃኒቶቹ በተዛባ መልኩ ከተወሰዱ ከጥቅማቸው ጉዳታቸው ያመዝናል። በማዕከላዊ ሥርዓተ-ነርቭ ላይ ተፅዕኖ በማድረስ ወደ ሱስነት የመቀየር፣ ባህሪን በመቀየር፣ ተጠቃሚውን በተፅዕኗቸው ውስጥ የማድረግና ሲከፋም ሞትን የማስከተል ባህሪ አላቸው። 153 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አምስት ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች በአካባቢያችን ሰዎች የተለያዩ አደንዛዥና ሱስ አምጪ እጾችና ኬሚካሎችን ይወስዳሉ። አብዛኛዎቹ፡- ትምባሆ፣ አልኮሆል፣ ሲጋራ፣ ጫት፣ ሀሽሽ፣ ኮኬይንና ማሪዋና ናቸው። ስለሆነም በሰውነታችን ላይ የአጭርና የረጅም ጊዜ ተጽዕኖ ማሳደር የሚችሉ ናቸው። ተግባር 5.2 በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያይታችሁ መልሱ። 1) ተገቢነት የሌለው የመድሃኒት አጠቃቀም ስንል ምን ማለታችን ነው? 2) የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድሃኒቶች ማለት ምን ማለት ነው? አልኮል አልኮል ኢታኖል የተባለ ውህድ በውስጡ ያለውና የነርቭ ሥርዓትን የሚያደነዝዝ ሱስ አምጪ ኬሚካል ነው። በአጠቃላይ አልኮሆል የማዕከላዊ ሥርዓተ-ነርቭን በማደንዘዝ የማስታወስና የማሰብ ችሎታ በመቀነስ፣ በማኮላተፍ፣ በማንገዳገድ፣ ግንፍል ግንፍል ማለትን ያስከትላል። በተጨማሪም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ከማስከተሉም በላይ ጉበትና ጨጓራን በመጉዳት ለሞት ሊዳርገን ይችላል። ሲጋራ ሲጋራ ከትንባሆ ቅጠል የሚዘጋጅ በውስጡ ኒኮቲን የሚባል ኬሚካል ያለው እፅ ነው:: ይህ ኬሚካል የልብ ምትን ያፋጥናል፣ የደም ግፊትን ይጨምራል፣ የመተንፈሻ አካላት ተግባርን ያዛባል እንዲሁም ለካንሰር በሽታ ያጋልጣል፡፡ ጫት ጫት እፅ ሲሆን ቅጠሉን እና ቀንበጡን ለማነቃቂያነት ሰዎች ያኝኩታል፡፡ ይህ እፅ በሀገራችን ውስጥ በአስፈሪ ሁኔታ እየተዛመተ ይገኛል፡፡ ጫት ውስጥ ካቴኒን የተባለ ውህድ ኬሚካል አለ፡፡ ጫት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ከማስከተሉም በላይ የሆድ ድርቀትን፣ የምግብ ፍላጎትን መቀነስ፣ የጥርስ መበላሸትን፣ የአዕምሮ ችግርንና ቅዠት ያስከትላል፡፡ ተግባር፡ 5.3 በቡድናችሁ ሁናችሁ አንድ ሰው ወደ አደንዛዥ እፅ ተጠቃሚነት እንዴት ሊገፋፋ እንደሚችል ተወያዩ፡፡ 154 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አምስት ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች መልመጃ 5.2 የሚከተሉትን ጥያቄዎች በአጭሩ መልሱ፡፡ 1. የተዛባ መድሀኒት አጠቃቀም በቤተሰብ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ፃፉ፡፡ 2. በአካባቢያችሁ የተለመዱ አደንዛዥ እፆችንና ጉዳታቸውን ዘርዝሩ፡፡ 3. አደንዛዥ እፅ ምንድን ነው? 4. አልኮል መጠጦች በአንጎል ላይ ምን ዓይነት ተፅዕኖ አላቸው? 5. ጫት እና ሲጋራ በጤንነት ላይ ምን ዓይነት ጉዳት ያስከትላሉ? 6. የታሸጉ ምግቦችን፣ መጠጦችንና የተለያዩ መድሐኒቶችን ከመጠቀማችን በፊት መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች ምን ምን ናቸው? 5.3 በከተማችን የሚገኙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ከንዑስ ርዕሱ የሚጠበቅ አጥጋቢ የመማር ብቃቶች ተማሪዎች ይህን ንዑስ የትምህርት ክፍል ተምራችሁ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፦ በከተማችሁ የሚስተዋሉትን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ታወግዛላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት ግርዛት ግግ ማስወጣት ጠለፋ ያለእድሜ ጋብቻ አስገድዶ መድፈር የማነቃቂያ ጥያቄዎች 1) ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ምንድን ነው? 2) በአካባቢያችሁ የሚተገበሩ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ምን ምን ናቸው፡፡ 3) ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ሊያስከትለው የሚችለውን ጉዳት አብራሩ። ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ማለት ከግንዛቤ እጥረት ወይም እየታወቀ በማህበረሰቡ የሚደረግ ድርጊት ነው። እነዚህ በማህበረሰባችን ዘንድ የተለመዱ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እንደ የወተት ጥርስ(ግግ) ማስወጣት፣ የሴት ልጅ ግርዛት፣ ያለእድሜ ጋብቻ፣ ጠለፋና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል። አብዛኛዎቹ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የሚፈጸሙት በሴቶች 155 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አምስት ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ላይ ነው። ለምሳሌ፡ የሴት ልጅ ግርዛት፣ ያለእድሜ ጋብቻና ጠለፋ። 1. የሴት ልጅ ግርዛት የማነቃቂያ ጥያቄ የሴት ልጅ ግርዛት ምን ጉዳት ያደርሳል? የሴት ልጅ ግርዛት ማለት የሴትን ልጅ ብልት ውጫዊ ክፍል በከፊል ወይም በሙሉ ቆርጦ ማንሳት ማለት ነው። የሴት ልጅ ግርዛት በግርዛቱ ጊዜ ከፍተኛ ህመም፣ ከፍተኛ ደም መፍሰስ፣ በብልት ላይ ጠባሳ መፍጠር፣ የወሲብ ስሜት ማጣት(መቀነስ)፣ በወሊድ ጊዜ ምጥ እንዲጠና ማድረግ፣ የስነ-ልቦና ችግር እና የመሳሰሉት ያስከትላል። 2. የወተት ጥርስ (ግግ) ማስወጣት፡- ገና በተወለደ ህጻን ላይ ድድን በመቁረጥ ወይም በመጠቅጠቅ የሚፈጸም ጎጂ ልማዳዊ ደርጊት ነው፡፡ ደርጊቱ የሚፈፀመው ህፃናት እንዲታመሙ ያደርጋል ከሚል ከተሳሳተ አመለካከት ነው፡፡ 3. ያለእድሜ ጋብቻ ይህ ደግሞ በዕድሜ ያልጠነከሩ ሴት ልጆችን መዳርውድ(ማጋባት) ማለት ነው። ይህም በሴት ልጆች ላይ ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ፣ ያለእድሜያቸው ሀላፊነት እንዲቀበሉ፣ በእርግዝና ወቅት ለውስብስብ ችግሮች እና ለሞት ሊዳርጋቸው ይችላል። 4. ጠለፋ አንድ ሴት ልጅ ካለፍላጎቷ በግዳጅ በማታውቀው ወይም በምታውቀው ወንድ ለጋብቻ መወሰድ ጠለፋ ይባላል። በምትጠለፍበት ጊዜም ለአካል ጉዳት፣ ለተላላፊ በሽታዎች እና ላልተፈለገ እርግዝና ልትዳረግ ትችላለች። ተግባር 5.3 ሀ) በአራት ቡድን ሆናችሁ ከላይ ከተጠቀሱት ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች አንዳንድ በመውሰድ በሥነ ጥበባዊ መንገድ (በድራማ፣ በስነ-ጽሁፍ፣ በመዝሙር፣ በዘፈንና በመሳሰሉት) አውግዙ፡፡ ለ) ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ለኤች አይ ቪ/ኤድስ መተላለፊያ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉን? በዝርዘር ተወያዩ፡፡ 156 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አምስት ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች 5.4 ድርቅና ረሃብ ከንዑስ ርዕሱ የሚጠበቁ አጥጋቢ የመማር ብቃቶች ተማሪዎች ይህንን ንዑስ ርዕስ ተምራችሁ ካጠናቀቃችሁ ብኋላ ፡- የድርቅና የረሃብ ፅንሰ-ሐሳብን ትናገራላችሁ፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ ለሚታየው ድርቅ መንሥኤውንና ውጤቱን ትለያላችሁ፡፡ የምሥራቅ አፍሪካን የዝናብ መጠንና ለድርቅ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን የሚያሳይ ካርታ በመመልከት ግንኙነታቸውን ትገልጻላችሁ፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ ለድርቅ ተጋላጭ ቦታዎችን ትለያላችሁ፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ ድርቅን ለመቋቋም የሚያስችሉ ሀገር-በቀል ዘዴዎችን ትዘረዝራላችሁ፡፡ ቁልፍ ቃላት ድርቅ ረሃብ ተጋላጭ ስለ ድርቅና ረሃብ ምንነት የሰዎች ግንዛቤ የማነቃቂያ ጥያቄዎች 1. ድርቅ ምንድን ነው? 2. ረሃብ እንዴት ይከሰታል? ድርቅ ማለት ባልተለመደ ሁኔታ የዝናብ እጥረት ሲያጋጥም ወይም ለረዥም ጊዜ ሳይዘንብ ሲቀር የሚከሰት ችግር ነው፡፡ ይህ ችግር ለረጅም ጊዜ ሲቆይ ለረሃብ ያጋልጣል:: በአንድ በተወሰነ አካባቢ ባሉ ህዝቦች ዘንድ የሚበላ ምግብ ሲጠፋ ወይም የተመጣጠነ ምግብ ሳይሟላ ሲቀር ረሃብ ይባላል፡፡ በምስራቅ አፍሪካ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦች ለረሃብ ተጋልጠዋል፡፡ በተለይ ብዙ ቀጥር ያላቸው ህፃናት የተመጣጠነ ምግብ አያገኙም፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ ዋና ዋና የረሃብ መንስኤዎች የሚባሉት፡- የእርስ በርስ ግጭት፣ የአየር ሁኔታ መቀያየር፣ ወረርሽኝ (የኮሮና ቫይረስ፣ ኮሌራ፣ ወባ) የመሳሰሉት መከሰት እና ሌሎች ምክንያቶች ናቸው፡፡ ድርቅ በምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና እየጨመረ ያለ ችግር ነው፡፡ 157 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አምስት ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች የድርቅ ምክንያትና ውጤት በምሥራቅ አፍሪካ የቡድን ውይይት 5.4 ሀ ዓላማ፡ ስለ ድርቅ ምክንያትና ውጤት ግንዛቤ መፍጠር መመሪያ፡ በቡድናችሁ በመሆን የሚከተለውን ሥሩ፡፡ በድርቅ ምክንያትና ውጤት ላይ ተወያይታችሁ መልሳችሁን ለመምህራችሁ አብራሩ፡፡ በምስራቅ አፍሪካ ዋና ዋና የድርቅ ምክንያቶች የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው፡፡ እነዚህም፡- የደን መጨፍጨፍ፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ከብቶችን አንድ ቦታ ለብዙ ጊዜ ማሰማራት፣አንድን ቦታ ለብዙ ጊዜ ለእርሻ መጠቀም፣ የህዝብ ቁጥር መጨመር እና የእርሻ ቦታ መስፋፋት፣ የአካባቢ መራቆት እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ በተጨማሪም የኢንዱስትሪዎች መስፋፋት የሙቀት መጠን ከዕለት ወደ ዕለት እንዲጨምር አድርጎታል፡፡ ኢንዱስትሪ ሲስፋፋ የሙቀት መጠን ስለሚጨምር በአፈር ውስጥ ያለውን እርጥበት እንዲተን በማድረግ ምንም አይነት ሰብል እንዳይበቅል ያደርጋል፡፡ በተለያየ መንገድ ይሄው ችግር እየተባባሰ አሁን እስካለንብት ወቅት ድረስ የምግብ ችግር አስከትሏል፡፡ ይህ ድርቅ ረሃብን አስከትሎ የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል። ይህ ችግር አሁንም በቀጠናው በጣም አነስተኛ የዝናብ መጠንና ከፍተኛ የሙቀት መጠን በመኖሩ ምክንያት ሰዎችን ለምግብ እጥረት፣ ለጤና ችግር፣ የሞት መጠን መጨመር፣ የኢኮኖሚ ማሽቆልቆል፣ የብዝሀ-ህይወት መመናመን፣ የምግብ ዋጋ መጨመር፣ የከብቶችና የሰብል ውጤታማነት መቀነስ፣ የውሃ እጥረት (ለመጠጥና ለመስኖ) እና ለመሳሰሉት ተዳርገዋል፡፡ በነዚህም ምክንያቶች የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ህዝቦች ተረጋግተው ህይወታቸውን ለመምራት በመቸገራው ለስደት ተዳርገዋል፡፡ 158 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አምስት ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ለድርቅ ተጋላጭ የሆኑ የምሥራቅ አፍሪካ አካባቢዎች የቡድን ውይይት 5.4 ለ ዓላማ፡ ለድርቅ ተጋላጭ የሆኑ የምሥራቅ አካባቢዎችን መለየት መመሪያ፡ የምሥራቅ አፍሪካን የዝናብ መጠንን የሚያሳይ ካርታ በመመልከት አንዳንድ ቦታዎች ለምን ለድርቅ ተጋላጭ እንደሆኑ ተወያይታችሁ ለመምህራችሁ በፅሁፍ አቅርቡ፡፡ ምስል 5.2 ለድርቅ ተጋላጭ የሆኑ የምሥራቅ አፍሪካ አካባቢዎች ለድርቅ ተጋላጭ የሆኑ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት የሚከተሉት ናቸው፡፡ y ኢትዮጵያ y ኬንያ y ሶማሊያ y ጅቡቲ y ዩጋንዳ በምሥራቅ አፍሪካ ድርቅን ለመቋቋም የሚያስችሉ ሀገር- በቀል ዘዴዎች የማነቃቂያ ጥያቄ በምሥራቅ አፍሪካ ድርቅን ለመቋቋም የሚያስችሉ ዘዴዎችን ዘርዝሩ፡፡ 159 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አምስት ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ምሥራቅ አፍሪካ ካለበት ወቅታዊ የድርቅና ረሃብ ችግር ለመውጣት የሚያስችሉ ሀገር በቀል ዘዴዎች ፡- እህልን በጎተራ መርጎ ማስቀመጥ፣ በቤት ጣሪያ ጭስ ላይ ለምሳሌ ፡- በቆሎ፣ ማሽላ፣ ዘንጋዳ የመሳሰሉትን ማስቀመጥ፣ ድርቅን መቋቋም የሚችሉ ዕፅዋትንና እንስሳትን ትኩረት ሰጥቶ መንከባከብ፣ በአጭር ጊዜ የሚደርሱ የሰብል ዓይነቶችን መዝራት ለምሳሌ በአርባ ቀን የሚደርስ ጤፍ (ቡርቄ ጤፍ)፣ በተጨማሪም፡-ችግኝ መትከል፣ በመስኖ የመጠቀም ልምድን ማዳበር፣ አፈራርቆ ማረስ፣ እርከን መስራት፣ የቤተሰብ መጠንን ከገቢ አንጻር መወሰን፣ የምስራቅ አፍሪካን ቀጣናዊ፣ ሰላማዊ እና ልማታዊ ትስስር ማጠናከር፣ ድርቅን መቋቋም የሚችሉ ምርጥ ዘሮችን መጠቀም፣ ውሃን ማቆር፣ ዘመናዊ የአስተራረስ ዘዴ መጠቀምና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ምስል 5.3 መስኖ ውሃ ማቆር፣ ድርቅን የሚቋቋሙ ሰብል ዘሮች 160 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አምስት ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች መልመጃ 5.4 የሚከተሉትን ጥያቄዎች በአጭሩ መልሱ 1. የድርቅና የረሃብ ልዩነትን ግለፁ፡፡ 2. ድርቅና ረሃብን እንዴት መከላከል ይቻላል? የምዕራፉ ማጠቃለያ ¾ ኤች አይ ቪ /ኤድስ የሰውነትን ነጭ የደም ህዋስ የሚያጠቃ ቫይረስ ነው፡፡ ¾ ኤድስ በኤች አይ ቪ ቫይረስ የተነሳ የሚመጣ በሽታ ነው፡፡ ¾ ኤች አይ ቪ የሚተላለፈው በደም ንክኪ፣ ልቅ በሆነ ግብረ-ሥጋ ግኑኝነት፣ በስለታም ነገሮች እና በእርግዝና ወቅት ከእናት ወደ ልጅ ነው፡፡ ¾ ኤች አይ ቪ/ ኤድስ የማይተላልፍባቸው መንገዶች፡- አብሮ በመኖር፣ በመብላት፣ በመጫወት፣ በመጠጣት፣ በመጨባበጥ እና በመሳሰሉት፡፡ ¾ ስለ ኤች አይ ቪ/ኤድስ በቂ ግንዛቤ ካለ በሽታውን መከላከል ይቻላል፡፡ ¾ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ማለት ከግንዛቤ እጥረት ወይም እየታወቀ ማህበረሰቡን የሚጎዳ ድርጊት ማለት ነው። ¾ እነዚህ በማህበረሰባችን ዘንድ የተለመዱ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እንደ የወተት ጥርስ(ግግ) ማስወጣት፣ የሴት ልጅ ግርዛት፣ ያለእድሜ ጋብቻ፣ ጠለፋና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል። ¾ ድርቅ ማለት ባልተለመደ ሁኔታ የዝናብ እጥረት ሲከሰት ወይም ለረዥም ጊዜ ሳይዘንብ ሲቀር የሚከሰት ችግር ነው፡፡ ይህ ችግር ለረጅም ጊዜ ሲቆይ ለረሃብ ያጋልጣል፡፡ ¾ የሚበላ ምግብ ሲጠፋ ወይም የተመጣጠነ ምግብ ሳይሟላ ሲቀር ረሃብ ይባላል፡፡ ¾ ዋና ዋና የድርቅ ምክንያቶች የሚባሉት፡- የደን መጨፍጨፍ፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ በከብቶችን በአንድ ቦታ ለብዙ ጊዜ ማሰማራት፣አንድን ቦታ ለብዙ ጊዜ ለእርሻ መጠቀም፣ የህዝብ ቁጥር መጨመር እና የእርሻ ቦታ መስፋፋት፣ የአካባቢ መራቆት እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ¾ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት አሁን ካሉበት ወቅታዊ የድርቅና ረሃብ ችግር ለመውጣት አዋጭ እና የተለያዩ አማራጮችን መጠቀም አለባቸው፡፡ 161 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አምስት ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች የምዕራፉ ማጠቃለያ ጥያቄዎች ሀ. በ “ሀ” ስር የቀረቡትን ገለፃዎች በ “ለ” ስር ከቀረቡት ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ጋር አዛምዱ፡፡ ሀ ለ 1. የሴትን ልጅ ውጫዊ ብልት ክፍል መቁረጥ ሀ) ጠለፋ 2. የህፃን ልጅ ድድ መጠቅጠቅ ለ) የወንድ ልጅ ግርዛት 3. በዕድሜ ያልጠነከሩ ልጆችን መዳር ሐ) ያለ ዕድሜ ጋብቻ 4. አንድን ሴት ልጅ ካለፍላጎቷ ለጋብቻመወሰድ መ) የሴት ልጅ ግርዛት ሠ) ግግ ማስወጣት ለ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክከለኛውን መልስ የያዘውን ሆሄ በመምረጥ መልሱ 1. ከሚከተሉት ውስጥ የኤች አይ ቪ/ኤድስ መተላለፊያ መንገድ የሆነው የቱ ነው? ሀ) መጨባበጥ ለ) መጎራረስ ለ) አብሮ መጫወት መ) በጋራ መርፌ መጠቀም 2. ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ የሚያጠቃው የደም ህዋስ የቱ ነው? ሀ) ቀይ የደም ህዋስ ለ) ነጭ የደም ህዋስ ሐ) ፕላትሌቶች መ) ሁሉም 3. የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያ መንገድ የቱ ነው? ሀ) መታቀብ ለ) በቫይረሱ የተጠቃ ደም መለገስ ሐ) መታጠብ መ) በእርግዝና ጊዜ ከእናት ወደ ልጅ 4. ከሚከተሉት ውስጥ የህይወት ክህሎት ያልሆነው የቱ ነው? ሀ) መተባበር ለ) ራስን መግዛት ሐ) መተሳሰብ መ) በራስ አለመተማመን 162 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አምስት ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች 5. በሲጋራ ውስጥ የሚገኝ ኬሚካል ምን ይባላል? ሀ) ኒኮቲን ለ) ካቴኒን ሐ) ሞርፊን መ) ኢታኖል ሐ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች በአጭሩ መልሱ፡፡ 1. ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ምንድን ነው? 2. በጫት ሱስ ምክንያት የሚመጡ ችግሮች ምን ምን ናቸው? 3. የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ዋና ዋና ምልክቶችን ዘርዝሩ፡፡ 4. በሰፈራችሁ የሚታዩትን አደገኛ ኬሚካሎችንና እፆችን ዘርዝሩ፡፡ 5. ምሥራቅ አፍሪካን ካለበት ወቅታዊ የድርቅና ረሃብ ችግር ለመውጣት የሚረዱ ሀገር- በቀል ዘዴዎችን ዘርዝሩ፡፡ 6. የድርቅና ረሃብ መንስኤዎችንና ውጤቶችን ጥቀሱ፡፡ 7. ለድርቅ ተጋላጭ ከሆኑ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል ቢያንስ ሦስቱን ጥቀሱ፡፡ 163 Fetena.net : Ethiopian No#1 Educational Resource ምዕራፍ አምስት ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ፍተሻ ልታከናውኗቸው የምትችሏቸውን ተግባራት የ() ምልክት በሣጥኖች ውስጥ በማኖር አመልክቱ፡፡ 1. አደገኛ ኬሚካሎችና ዕፆችን እለያለሁ፡፡ 2. ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን እለያለሁ፡፡ 3. የኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ምንነት እገልጻለሁ። 4. በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ልንጋለጥ የምንችልበትን መንገዶች አስረዳለሁ። 5. ከኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ራሳችንን ለመጠበቅ መደረግ ስለሚገባው ጥንቃቄ አብራራለሁ። 6. የኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ምንነት እገልጻላሁ፡፡ 7. በአካባቢያቸው የሚገኙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን አወግዛሉ፡፡ 8. የድርቅና የረሃብ ፅንሰ ሐሳብን እናገራለሁ፡፡ 9. በምሥራቅ አፍሪካ ለሚታየው ድርቅ መንሥኤውንና ውጤቱን እለየለሁ፡፡ 10.የምሥራቅ አፍሪካን የዝናብ መጠንና ለድርቅ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን የሚያሳይ ካርታ በመመልከት ግንኙነታቸውን እገልፃለሁ፡፡ 11. በምሥራቅ አፍሪካ ለድርቅ ተጋላጭ ቦታዎችን እለያለሁ፡፡ 12. በምሥራቅ አፍሪካ ድርቅን ለመቋቋም የሚያስችሉ ሀገር በቀል ዘዴዎችን እዘረዝራለሁ፡፡ 164